en
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
3 721
Subscribers
+4524 hours
+1767 days
+1 15530 days
Posts Archive
የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር 💪💪
የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር 💪💪

ያልተነገረለት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዲሽቃ ተኳሹ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው እሸቱ በቀለ አርበኛ "እሸቱ በቀለ በሸዋ ደቡብ አማራ ኤፍራታ አማራ ፋኖ ውስጥ በጀግንነቱና በልዩ የዲሽቃ ተኩስ ብቃቱ  በተለይም በቅርብ ጊዜያት በነበሩት ውጊያዎች ላይ ያሳየው ፅናትና የጦር ሜዳ ብቃት በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፎለታል። ​አርበኛ እሸቱ በቀለ የጀግንነቱ መገለጫ አርበኛው ተራ ተዋጊ ብቻ ሳይሆን፣ የከባድ መሳሪያ (ዲሽቃ) አጠቃቀም ላይ ልዩ ጥበብ ያለው አርበኛ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ዲሽቃን እንደ ቀላል መሳሪያ ተሸክሞ፣ ጠላትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ይታወቃል። የእሱ ልዩ የሚያደርገው  ​የልብ ትርታ በከባድ ጥይት ዝናብ ውስጥ ሳይበገር መቆሙ። ​ትክክለኛ ኢላማ የዲሽቃ ጥይትን በቁጥብነትና በትክክለኛ ኢላማ ላይ የማሳረፍ ችሎታው ነው። ​ ለጓደኞቹ ያለውን የውጊያ ወኔ የመቀስቀስ አቅሙ እና የውጊያ ውሎ የሽዋ ተራራማና ገደላማ ስፍራዎች በከባድ መሳሪያ ታጅቦ ከሚወዳቸው ፋኖዎች ጋር ሆኖ የጠላትን እንቅስቃሴ አልሞ የመምታት እይታው አጅጉን ማራኪም ነው። አርበኛ እሸቱ በቀለ በአንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ አደላድሎ ይይዛል። የጠላት ጦር መስመር ሰብሮ ለመግባት ሲሞክር፣ እሸቱ "ቁጭ ብሎ" ሳይሆን በቆራጥነት መሳሪያውን በማንቀሳቀስ ተኩስ ይከፍታል። የዲሽቃው ድምፅ ብቻ የጠላትን ስነ-ልቦና ይሰብራል። አርበኛ እሸቱ የዲሽቃ ጥይት የሚተኩሰው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ የጠላትን አሰላለፍ እየመረጠ በመምታት ግስጋሴያቸውን እንዲገታ ያደርጋል። ​መስዋዕትነትና ፅናት ብዙ ጊዜ በቪዲዮዎች ላይ እንደሚታየው፣ ዙሪያውን ጥይት እየዘነበ እሱ ግን በእርጋታና በፈገግታ የታጀበ የጀግንነት ተግባር ሲፈፅም ይታያል። ይህ ለደጋፊዎቹ "የማይበገሩት ጀግኖች" ተምሳሌት አድርጎታል ተምሳሌታዊነቱ ​እሸቱ በቀለ ዛሬ ላይ ለአማራ ፋኖ ትግል የፅናት ምልክት ሆኗል።ጀግንነቱ  የጥንካሬው መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል። የጀግናው ውሎ በየጊዜው በሚለቀቁ የመረጃ አውታሮች ላይ የሚዘገብ ሲሆን፣ የእሱ ተጋድሎ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ የአማራን ህዝብ የመኖር ህልውና ለማስከበር ትልቅ ተጋድሎ እያደርገ ይገኛል።

~ ቁስለኛ #በሄሊኮፕተር ተነሳ !!! በዛሬዉ እለት በቀን 04/06/2018 ዓ.ም ጃዊ ላይ የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ገረድ ሰራዊት ቁስለኛ አመራሮች በሂሊኮፕተር ተለቅመዋል። ለ8 ተከታታይ ቀናት በጀግኖች የአማራ ፋኖ ብርቱ ክንድ የተወቃዉ የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት አመራሮች ለጊዜዉ ከሞት የተረፉት ቁስለኞች መዉጫ አጥተዉ ዛሬ በሂሊኮፕተር ተነስተዋል። አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

የጥንቃቄና ጥብቅ መረጃ! የብልጽግና አመራሮችና ጀሌ ሰራዊታቸው በፋኖ ጠንካራ ጡንቻ ቀምሰው የተለያዩ ከተሞችን ለቀው ሲፈረጥጡ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ እና መሰል የሕዝብ ተቋማትን በማቃጠል ፋኖ እ
የጥንቃቄና ጥብቅ መረጃ! የብልጽግና አመራሮችና ጀሌ ሰራዊታቸው በፋኖ ጠንካራ ጡንቻ ቀምሰው የተለያዩ ከተሞችን ለቀው ሲፈረጥጡ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ እና መሰል የሕዝብ ተቋማትን በማቃጠል ፋኖ እንዳቃጠለው አድርገው ፕሮፓጋንዳ ለመስራት እየተንቀሳቀሱ ነው፣ አሁንም እያደረጉት ነው። ስለሆነም የሕዝብ ልጅ የሆነው ፋኖም ሆነ ጋሻ መከታ የሆነው ሕዝባችን ተቋማትን እንዲጠብቅ ማሳሰብና ማስታወስ እንፈልጋለን። አፋብን ዮሃንስ ሙጨ

የምሽት ዜና! የአዋባል ወረዳ ስልጠናና ክህሎት ም/ኃላፊ አዲሱ አለምነህ በተገደለበት ውሎ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ማምሻውን ድል ተቀናጅቷል። የካቲት 4/2018ዓ.ም =================================== በሉማሜ ከተማ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት በተፈፀመ ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት የአዋባል ወረዳ ስልጠናና ክህሎት ምክት ኃላፊ የነበረው አዲሱ አለምነህ በ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በተወሰደበት እርምጃ በመኖሪያ ቤቱ ተገድሏል። ድንገተኝነትን በማሳካ በጨላማ ካድሪውን በቦምብ ያጋዩት 34ኛ ክ/ጦር ከቀኑ 9:00 እስከ 12:00 ሰዓት በጃማ ከተማ በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአረመኔውን ሰራዊት ደባቅ በመምታት 12 ከባድ ቁስለኛ ከ25 በላይ አስክሬን ለጠላት አሸክመውታል። ከደብረ ማርቆስ ደጀን ባለው አውራ ጎዳና መሐል በምትገኘው ስትራቴጂካዊ ከተማ በሆነችው ሉማሜ ከተማ በሌሊት አስደናቂ ኦፕሬሽን የፈፀሙት የ34ኛ ክ/ጦር ነበልባሎች በድጋሚ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በሉማሜ ከተማ በመሸገው ጠላት ላይ በከፈቱት አውደ ውጊያ እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ተፋልመው ጠላትን አነባብረው ወጠዋል። በሉማሜ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ በተደረገው ውጊያ በርካታ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን የአረመኔው ሰራዊት የከተማዋን ወጣቶች እያፈሰ ይገኛል። በዛሬው እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ድል የተቀናጀ ሲሆን የኮሩ አሀዶች በጃዊ መተከል በተደረገ ትንቅንቅም እየተፋለሙ ይገኛሉ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ጀምበር የጠለቀችበትና ጣዕረ ሞት ላይ ያለው ብልፅግና የመጨረሻ ያለውን እርምጃ እየወሰደ ንፁሃንን እየጨፈጨፈ ንብረትም እያወደመ ነው‼️ ሽንፈቱን በተግባር የተረዳው ተረኛ ስብስብ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ነውና የቻልኩትንና ያገኘሁትን የአማራ እና አማራ አጥፍቸ ነው በማለት ሲጠፋ አመታቶች አስቆጥሯል።ዛሬ ግብዓተ መሬቱ ሲቃረብ ደግሞ በክፋትላይ ክፋት በጭካኔ ላይ አረመኔዊነቱን በንፁሀን ላይ እያሳየን ይገኛል።በዛሬው እለት ደቡብ ወሎ ወረኢሉ ወረዳ ላይ የሶስት አርሶ አደሮች ቤት ከነሙሉ ንብረቱ ቤንዚን አርከፍክፎ ያቃጠለ ሲሆን ቤት ንብረታቸው የተቃጠለባቸው አርሶደሮች ፦ 1. አቶ አያሌው አህመድ ሁለት ቆርቆሮ ቤት 2. አቶ አሊ ይማም ሶስት ቆርቆሮ ቤት 3. አቶ ከበደ ማህሙድ ሁለት ቆርቆሮ ቤት የሶስቱም አርሶደሮች ከነሙሉ ንብረቱ በሀገር አፍራሹ የብልፅግና ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሰየመ የአብይና ሽመልስ አማራን የማጥፋት፣የማቆርቆዝና የማዳከም ልዩ ተልኮ የተሰጠው ተላላኪ ቡድን አማራ መቸም የማይረሳውና ይቅር የማይለው ነውር እየፈፀመ ይገኛል። በመጨረሻም ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጋር ሆናችሁ ወገናችሁ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀማችሁና ቤት ንብረት እያወደማች ያላችሁ ሃይሎች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡና ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦር 04/ዐ6/2018 ዓ.ም

አንድነት በተግባር የተገለጠበት የዓምሐራ ፋኖ በደብረ ታቦር ከተማ    [የካቲት 04/2018ዓ.ም] 01 👉👉👉 13:00 ሠዓታትን የፈጀ አውደ ውጊያ በደብረ ታቦር ከተማ                                       የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትን ለማምበርከክ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር  ለየካቲት 04/2018ዓ.ም የተጠና ዕቅድ ሲያዘጋጅ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክ/ጦር ገ/መሥቀል ብርጌድ አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጋራ የውጊያው ዋዜማ  ከ04:00 ጀምሮ ሌሊቱን የደብረ ታቦር ከተማ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥረው  ያለ ተኩሥ የአገዛዙ ወታደሮችን ሲያፈራርሥ አድሯል። ውጊያውንም ከማለዳ  እሥከ ጠዋቱ 3:20  ደብረ ታቦር የከተመውን የአገዛዙ ታጣቂ በአባታቸው ውባንታዊ ሰይፍ ሲያናፍጡት አርፍደዋል። ከጠዋቱ 03:20 በኋላ የበላይ ዕዙ ግዙፍ ጉና ክፍለ ጦር እና የጠቅላይ ግዛቱ ክፍለ ጦሮች በመናበብና የውጊያ ቀጠናዎችን በመከፋፈል ጠላትን ሲያምበረክኩ ውለዋል። ከቀኑ 6:30 ገደማ ጀምሮ የ5ኛ ኮር ሰራዊት በአርበኛ ሻምበል ሙሉሰውና አርበኛ ግዛቸው አሌ የውጊያው አካል ሆኗል። በውጊያው ተሳታፊ የሆኑ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ እና ጎንደር/ጠ/ግ/ዕዝ ክፍለ ጦሮች፦ 👊ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር 👊ግዙፉ ጉና ክፍለ ጦር 05ቱም ብርጌዶች 👊የዕቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የጀነራል ፋንታ በላይ ክፍለጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የተራራው ራሥ ጉና ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የአፄ ኢያሱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት 👊የዞዝ አምባ ንጉሱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት እና 👊የጋፋት ክ/ጦር 01 ሻለቃ 👊ታሪኳን በወርቅ የደም ቀለም የጻፈችው የነበልባሉ ፎገራ ክ/ጦር አካል የሆነችው ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ እና ከነበልባሉ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አካላት ከወረታ እሥከ ዓለም ሣጋ የሸፈኑ የጠላት አሰላለፍ የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ቅጥረኞች ከ13 ወረዳ የነበረው  የአድማ ብተና፣ ሚሊሻ፣ ፖሊሥና ከሁሉም ወረዳ የተሰባሰበው ከሃዲ ወዶ ገብ ነው። ከቀኑ 5:30 ጀምሮ ደግሞ ✅በመጀመሪያው ዙር ከባሕር ዳር የመጣ 250+ መከላከያ፣ 200+ አድማ ብተና እና 60+ ወዶ ገብ ከሐዲ የጸዳሉ አጃቢዎች ከ02 ዙ-23፣ 02 ዲሽቃ፣ 120 ሞርታር ይዞ የመጣውን ✅ በመቀጠል ከባሕር ዳር የመጣው 54 ተሽከርካሪ መከላከያ 03 መድፍ፣ 02 ታንክ፣ ከ17  ዲሽቃዎች ✅3ኛ ዙር ከአርኖ ጋርኖ በ10 ተሺከርካሪ የመጣውን መከላከያ ✅4ኛ ዙር ከአዲሥ ዘመን የመጣውን አድማ ብተና አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ እና ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ  በጋራ በሥፋት የመጣውን የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መደበኛ ውጊያ ገጥመውት ውለዋል። አገዛዙ የሰራቸው የኮንክሪት ምሽጎች ተሰባብረዋል። ተሥፋ የቆረጠው የአቢይ አሕመድ ፋሽሥት አገዛዝ ለደብረ ታቦር ከተማ 07 ድሮኖችን መድቦ ውሏል። 14 የድሮን ጥቃቶችን በደብረ ታቦር ከተማና ታቦር ዙሪያ ቦታዎች ጥሏል። ሞርታር ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ ላይ ብቻ 23 ጊዜ ጥሏል፤ ነገር ግን የሲቪል መኖሪያ ቤቶችንና የመንግሥት ትምሕርት ቤቶች ነው ያወደመው።   ነገር ግን በዚህ የድሮን ጥቃት በጅምላ የተመቱት አገር አማን ብለው የተቀመጡ የማሕበረሰቡ አካላት ናቸው። ማሰቢያውን የተቀማው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከወጂ እሥከ ደብረ ታቦር ከተማ ድረሥ  02 ዙ-23፣ ቁጥሩ ያልታወቀ ሞርታር፣ ከ17 በላይ ዲሽቃ፣ 03 መድፍ፣ 02  ታንክ እና መሰል የቡድን መሳሪያዎችን ቢይዝም ጥበበኛው የአማራ ፋኖ በክንዱ ሲያደቅቀው ውሏል። ከ11:30 በኋላ የፀዳሉ ደሴን ወደ ዓለም በር መምጣት መረጃው የደረሳቸው የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር  በፍጥነት ወደ ቦታው አምርተው ከበባ ፈጽመዋል። ፀዳሉ ደሴን መከላከያው ወደ ባሕርዳር እንዲያመልጥ ሲያደርጉ ራሳቸው ዋጋ ከፍለዋል። ምሽት 01:00 ፀዳሉ ደሴ ከመማረክ ያመለጠበት መዳኛ ሠዓቱ ሆኖ ተመዝግቧል። ሙሉ ቀናትን በተደረገው አውደ ውጊያ ከሁሉም ሰራዊት የተማረከውን ቅጥረኛ፣ መሣሪያ፣ ተተኳሽና ቁሥ  በነገው ዕለት በቪዲዮ እና በማሥረጃ የምናቀርብ ይሆናል። 02.👉👉👉ደራ ሐሙሲት ከአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በትናንትናው ዕለት 01 ዲሽቃ፣ ከ115+ ክላሽና አንድ ኦባማ ሙሉ የክላሽና የዲሽቃ ተተኳሽ መማረካቸው ይታወሳል። በተመሣሣይ ከትናንት የተረፈውን 01 ክላሽ በጠዋቱ ሐሙሲት ከተማ ላይ ማርከውታል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊 አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው

ታላቅ ትንቅንቅ የተደረገበት የደብረ- ታቦሩ ውጊያ አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሁለቱ ኮሮች( 206ኛ እና 204ኛ) እና አፋብን በላይ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ ኮር ጋር ጥምረት በመፍጠር  በደብረ ታቦር ታላቅም ተጋድሎ ሲደረግ ውሏል ። ዛሬ የካቲት 04/2018 ዓ.ም   ከደብረ -ታቦር ሙያና ቴክኒክና እስከ ፋርጣ ወረዳ ዙርያ  የነበረን ምሽግ በቅንጅት ተሰባብሮ  የአገዛዙን ምርኮና ሎጅስቲክስ የማረከው  የፋኖ ቅንጅት ፣ ከተማው አደባባይ  እስከ አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ በመዝለቅ ከፍተኛ ትንቅንቅ በማድረግ የጠላትን አንገትን አስደፍቶ  ደቁሶታል። የሁሉም ኮሮች ቅንጅት የተሞላበት  ይህ ውጊያ  ከወይብላ ምሽግ  እስከ  እየሱስ   ድባቅ ሲመታ ማረሚያ ቤትን እንደመማፀኛ የነፍስ አውጭኝ የሞት ሽረት  ትግል ሲያደርግ ውሏል። ጠላት  በድሮን የታገዘ ውጊያ በማድረግ በንጹሀን ቤትና ንብረት  ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል። በዚህ አውደ ውጊያ ከፍተኛ የሰው ሀይል ምርኮ ፣ሙትና ቁስለኛው የሆነበት ጠላት ለቁጥር የሚያስቸግር  የትጥቅና የተተኳሽ  አይነት ገቢ ሆኗል። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት !!! የካቲት 04 / 2018 ዓ.ም

የአገዛዙ ሰራዊት እየከዳ ወደ ፋኖ እየገባ ነው። ዛሬየአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለጦርን የተቀላቀለ የአገዛዙ የኮማንዶ አባል አንድ ብሬን ከነ
የአገዛዙ ሰራዊት እየከዳ ወደ ፋኖ እየገባ ነው። ዛሬየአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለጦርን የተቀላቀለ የአገዛዙ የኮማንዶ አባል አንድ ብሬን ከነሙሉ ሸንሸሉ እና አንድ ጥቁር ክላሽ 30 ጥይትጋ ይህን ይዞ የገባው አንድ 1 የአገዛዙ የኮማንዶ አባል ብቻውን ነው። የአገዛዙ ሰራዊት ስትከዱ እንደዚህ ጥሩ ነገር ይዛችሁ ኑ መልክታችን ነው።

አኹን ምሽት 1:00 ላይ ብቻ የተማረከ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ✅ፀዳለች ደሴ ወደ ባሕር ዳር በፓትሮል ተሰቃይታ አመለጠች ✅10 መከላከያ የተማረከ ✅03 ጥቁር ጥርጥር ክላሽ ከመከላከያ ✅10  ክላሽ ከመከላከያ ✅የሞርተር ኦሳ እግር ✅የብሬን ጥይት ከነሸንሸሉ ✅03 የመከላከያ ፓትሮል መኪኖች ምሽት 1:00 በውባንተ አብራኮች የተማረከ፤ ውጊያው ቀጥሎ የአቢይ ሸኔ ተቀጣሪ እየተወቀጠ ነው። ክብር ለውብዬ  ልጆች👏 መጽናት ብቻ  ይላል ዘረ ውባንተ አባተ ኃቅ-ዓለው ፀጋ

"የሰላም አማራጭን መርጠው እጅ የሰጡ" እያሉ ሲያሽሞኖሙኗቸው የነበሩትን ኮረዶች፣ አሁን ከፋኖ ጋር ለመዋጋት ፊት ተሰለፉ ብለው ወደ ጦርነት አስገብተዋቸዋል። በአጭር አገላለፅ ትናንት "የሰላም አማራጭን መረጡ" የተባሉት ኮረዳዎች፣ ዛሬ "ለጦርነት እንዲዘጋጁ" መመሪያ ተሰጧቸዋል። በነገራችን ላይ በእነ ፀዳሉና ማስረሻ አማካኝነት አባብለው ወደ አገዛዙ ከገቡ ወጣቶች ውስጥ አብዛኛው በአገዛዙ ሰዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል። ለቀጣይ ፕሮፖጋንዳ እነ ማስረሻን ያሳያሉ እንጅ መረጃዎች የሚጠቁሙት ግን አብዛኛው እንደተወገደ ነው።

የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር በጠላት ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ *********// በዛሬው ዕለት ጥር 04/2018 ዓ. ም ከምዕ/ጎጃሟ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ቁጭ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ ዘራፊና ጨፍጫፊ ሠራዊት ወደ ወምበርማዋ ወረዳ ወይንማ ቀበሌ የተለመደ አርሶ አደሩ ላይ የዘረፋ ተግባሩን ለመፈፀም ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ተንቀሳቅሷል። ነገር ግን የጠላት መቅጫ አይበገሬው አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር በፈርጣማ ክንዱ አቅምሶ እና ደቁሶ እያሯሯጠ መልሶ ከቀበሮ ጉድጓዱ ከቶት ተመልሷል። ወይንማ እና ጭራር በእጅበጅ ተኩስ 1ኛ እና 2ኛ ሻለቃ ጠላትን ሲቆሉት ሽንዲ ከተማ ደግሞ 4ኛ ሻለቃ ከተማ ሰርጎ በመግባትና ተኩስ በመክፈት የጠላትን ትስስር እንዳይፈጥር በማድረግ የጠላትን አከርካሪ መምታት ተችሏል። #በተያያዘ ጥር 03/2018 የክ/ጦሯ ኮማንዶ ዩኒቷ 5ኛ ሻለቃ ሽንዲ ከተማ የመሸገውን ጠላት ከእኩለ ቀን በኋላ ካምፕ ላይ እያለ ተስባ በመጠጋትና ጥቃት በመክፈት ሙትና ቁስለኛ አድርጋ ተመልሳለች። በ2ቱ ቀን ግዳጅ ጠላት በርካታ ሠባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከማስተናገዱ ባሻገር በቀጠናችን የኃይል ሚዛኑን ብልጫ ያረጋገጥንበትም እንደነበር የ88ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት መረጃውን አድርሶናል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት የካቲት 4/2018ዓ.ም

ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት ፋኖን ተቀላቀሉ ‼️ በሸበል በረንታ እና አካባቢው የሚገኘው የአብይ ሰራዊት ፋኖን በመቀላቀል ላይ ነው ➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧ 1ኛ. ዛኪር ንጋቱ ...602ኮር 75ኛክ/ጦር 2ኛገረመው ለሙ..602 ኮር 75ኛ ክ/ጦር 3ኛ ወርቅነህ አባተ....ከ25 ክ/ጦር በመውጣት 64ኛ እና54ኛ ክ/ጦርን የወገብ ትጥቅ እና በርካታ ተተኳሾችን በመያዝ ስርዓቱ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በመቃወም ፋኖን ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! የካቲት 04/2018ዓ.ም አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት

ባልታጠቁ ወገኖቻችን ላይ የሚፈፀሙ የጦር ወንጀሎችን ማጋለጥ የሁላችንም ኃላፊነት ነው! #በደብረታቦር ከተማ አገዛዙ በሚወስደው ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ የዘፈቀደ የድሮን ጥቃት ፣ በርካታ ወገኖቻችን እየሞቱና ሀብት ንብረታቸው እየወደመ ይገኛል! የደቡብ ጎንደር መናገሻ በሆነችው #ደብረታቦር ከተማና ሌሎች አካባቢዎች እንደተለመደው ሁሉ አገዛዙ በዘፈቀደ በሚሰነዝረው የድሮን ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ነዋሪዎች እየተገደሉና ቤቶች እየወደሙ መሆኑን ከስፍራው ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል! አገዛዙ ላለፉት ቀናት በሰሜን ሸዋ ፣ በደቡብ ወሎና በደቡብ ጎንደር ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የወሰደው አሰቃቂ የሆነ እርምጃ እጅግ ከፍተኛ መሆኑም እየተነገረ ነው። ይህን ላለፉት ወደሶስት የሚጠጉ አመታት ጠዋት ማታ ያለእረፍት የሚፈፀም የጦር ወንጀል በመረጃና በማስረጃ አስደግፎ ለአለም ማህበረሰብና ተቋማት ማሳወቅ ያስፈልጋል! በአለምአቀፍ ገለልተኛ አካላት እንዲጠናና ምርመራ እንዲጀመር ግፊት ማድረግ ከእኛ ይጠበቃል! በየትኛውም አካባቢ ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ የጦር ወንጀሎችን ( ግድያ ፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ፣ አስገድዶ መድፈር ፣ ማሰቃየት ፣ የጅምላ እስር ፣ ..ወዘተ) በቦታ ፣ በቀን ፣ በምስልና በሌሎች አስረጂ መረጃዎች አጠናቅሮ መያዝና ለሚመለከታቸው አካላት ተደራሽ ማድረግ ትልቅ ህዝባዊ አበርክቶት ነው! መረጃዎችን አድርሱን!