ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 712
المشتركون
+2624 ساعات
+3797 أيام
+1 10930 أيام
أرشيف المشاركات
#በአፋጣኝ_ይዳረስ
መረጃ ሸዋ‼️
አሁንም ተጉለት ቀጠና!
1,ከአንኮበር እስከ ሳሲት
2,ከመሃል አምባ እስከ አይዞሽ አሞራ!
3,ከመጥቆሪያ-ግፍት-ጭምብሬ መስመር ልዩ ጥንቃቄ አድርጉ!
ወደ ሳሲት ለመግባት ጻድቃኔ ማርያም አካባቢ መከላከያ ተሰብስቦ ዝግጅቱን ጨርሷል እንቅስቃሴ ሊጀምር ነዉ!
በቋራ ግንባር የአገዛዙ ኃይል አይነኬ በሚል ሲተማመንበት የነበረው የኮንክሪት ምሽግ ተሰብሮ በርካታ ወታደሮች ተገደሉ!
በተጋድሎው አንድ የሬጅመንት አዛዥን ጨምሮ ከ23 በላይ የብልፅግና ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ በርካታ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችና ሌሎች ወታደራዊ ንብረቶች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
አገዛዙ ከጎንደር በሻሁራ በኩል እና በቋራ በደለጎ በኩል በሁለት አቅጣጫ በርካታ ተሽከርካሪ ሙሉ ሰራዊት አስገብቶ ያሰለፈ ቢሆንም፡ የፋኖ አባላቱ የጠላት ኃይልን እርስ በእርሱ እንዲዋጋ በማድረግ ጭምር በወሰዱት የቆረጣና የከበባ ማጥቃት ታላቅ ድል ማስመዝገባቸውን የፍኖተ አማራ ሚዲያ የጦር ግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
+2
ሰበር ዜና
ቀን 04 /06/2018ዓ,ም
#ባህርደር_ዙሪያውን_ውጥረት_ነግሷል‼️
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር #ጭስ_አባይን ተቆጣጥሯል !!
102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
አሁን በዚህ ስዓት ባህርዳር እና ደብር ታቦር ዙሪያ ከፍተኛ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው መረጃዎችን ከግንባር ሁነን እየተከታተለን ለመላው ህዝባችንን ልናበርስራችሁ ነው የቴሌግራም ገፃችን ለመላው እንዲደርስ ሸርንና ጆይን በማድረግ ይወዳጁን!!
ቡም ቡም ቡም ቴዎድሮስ ዕዝ ባህርዳር ዙሪያ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን ጎልጉሎ በማውጣት ግንባር ቀደም ሆናለች። ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንካችን ጆይን በማለት ይወዳጁን!! አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የእነኢንጅነር ማንችሎት
የእነፋኖ ጌታቸው አጥናፍ
የእነቸርነት ሙሉቀን
የእነዮሐንስ እሱባለው
የወንዶቹ ቀዬ ጭስ አባይ
✊✊✊
በማለዳው የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር ከባህርዳር ከተማ በቅርብ ዕርቀት ምትገኘዉን ጭስ- አባይ ከተማ በእጁ ገቤ አድርጓል
ባህር ዳር ያደፈጥክ ካድሬ ጉድህ ፈላ 😁😁😁
የመከራው ማዕበልና የአሳምነው ልጆች ጽናት
የአብይ አህመድ ብልፅግናው ስርዓት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ፣ የአማራን ሕዝብ ህልውና ከምድር ገፅ ለማጥፋት አሰና ለማዳከም ካለው ስውር ፍላጎት በመነሳት፣ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም ከደቡብና ከኦሮሚያ ያለ የሌለ ኃይሉን በማሰባሰብ በሕዝባችን ላይ ዘግናኝ ግፍና መከራ እየፈፀመ ይገኛል።
ይሁን እንጂ፣ የዚህን ሥርዓት እኩይ ዓላማና ክፉ ተንኮል አስቀድመው የተረዱ የጀግናው የአሳምነው ልጆች "መከሩ፣ ዘከሩ"። በግፍና በትዕቢት ተሞልቶ የመጣውንና "የማይበገሬ" የተባለውን የአየር ወለድ ኮማንዶ፣ በሰማይም ሆነ በምድር ሊያቆማቸው አልቻለም። ይልቁንም፣ የጀግንነት ጥበብንና የጽናት ወታደራዊ ስልትን በመጠቀም፣ ወራሪውን ኃይል በገባበት ተራራና ሸለቆ ሁሉ እንደ አመጣጡ እዚያው እንዲቀር አድርገውታል።
የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ ለነፃነታቸውና ለክብራቸው ሲሉ የከፈሉት መስዋዕትነት የጠላትን ግስጋሴ ገትሮ የክብር ታሪክ እየጻፈ ይገኛል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና የኮርና የዕዝ አመራሮች የአብይን አረመኔያዊ ኃይል እንደ አመጣጡ እየመከቱት ይገኛል!
+1
ከትናት የቀጠለው የጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦርየድል ጉዞ የካቲት 02/06/2018 ከአንበሳሜ ከተማ ሲወጣ ተቆርጦ የተደባየው የጠላት ሀይል ሐሙሲት ከተማ ከአለው ጠላት ከተቀላቀለ በኋሏ የካቲት03/06/2018 ከሐሙሲት ከተማ 2ኪ/ሜ ወጣ ብሎ ቡራት ወይም ንፋስ ስልክ ከተባ ቦታ ላይ ምሽግ ሲቆፍር የወላው የጠላት ሀይል ክንዱ የማይዝለው የገብርየ የቀኝ እጅ የሆነው ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ከቀኑ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:30 በጨረሸ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ምሽጉ ሲሰበር ጠላት እንትናቱ አስክሬኑን እና ፖሮሎቹን እያጠባጠበ ወደ ሀሙሲት ከተማ ቢገባም ፋኖ እንደ አራስ ነበር እየተከተ ብርቱ ክንዱን ሳሳርፍበት አምሽታል።
በአውደው ጊያው የተገኘ ምርኮ
1ኛ=ድሽቃ 1
2ኛ=ክላሽ 115
3ኛ=የድሽቃ ተተኳሽ አንድ አይሱዙ መኪና
4ኛ=ፖትሮል=1
5ኛ=ኦባማ አይሱዙ 1
ምርኮኛ አድማ ብትን =8
ሙት እና ቁስለኛ ያልተለየ ሲሆን ጠላት ከባድ ኪሳራ ስለደረሰበት ወደ ባህር ዳር ጓዙን ጠቅልሎ ሂዳል
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ህ/ግ ፋኖ ፍቅሩ ባየ
#ማሳሰቢያ ከጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ!!
ለእስቴ ወረዳ መ/ኢየሱስ ከተማ ነዋሪወች በሙሉ ።፦
በጀግናው ፋኖ የህዝብ ልጅ ከብልፅግና የጅብ መንጋ በመላቀቃቹ እንኳን ደስ አላቹ እያለ ከተማውን ለማረጋጋትና መሰራት የሚገባቸውን ተግባራት አስቀምጧል፦
1ኛ፡ የህዝብ አ/ት ሰጪ ተቋማት ከነገ የካቲት4/2018ጀምሮ ስራ እንዲጀምር ይደረጋል
2ኛ፡ ከተፈቀደለት ሰው ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል
3ኛ፡ ከምሽቱ 2፡00ሰአት በኋላ ከተፈቀደለት አስከባሪ ውጭ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ አይችልም
4ኛ፡ በሀዘንም ሆነ በደስታ ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው
5ኛ፡ ማንኛውም ሰው ቤቱ ውስጥ የብልፅግና ባንዳ አከራይቶ(ደብቆ) የተገኘ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ካለም ፈጥኖ ለፋኖ አጋልጦ ይስጥ
6ኛ፡ ማንኛውም ተሽከርካሪ እና የንግድ ድርጅት የተለመደውን ስራቸውን ይስሩ!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ በለይ ዘለቀ እዝ ሜ/ጄኔራል ውባንተ ኮር ጉ/ክ/ጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ፋኖ
የካቲት3/2018 ዓ/ም
+2
ብአዴን ከሰመ ብሎ ከበሮ የደለቀበት የቀጠናው ፋኖ ጋይንት ንፋስ መውጫን ተረክቦ እየተገማሸረበት ነው!!
በቅርቡ ወደ ጠላት ምህረት የገቡና የደለሉት ግን በነፋስ መውጫ አልተገኙም።አለሁ ብለው የታበዩ በቦታው አልተገኙም።ስሁታን ያስመስላሉ እንጅ መቼ ታምነው ይፀናሉ።ከፋኖ ፊት የሚቆም ሞራል ከልቦናቸው አልተዘራም።አልበቀለም የሚበቅል ዘርም የላቸውም።ብአዴን ዘሩ ፍርሃትና ሎሌነት አይደል በሁሉም ቦታ አልተገኙም ። ዛሬ የተገኙትም ነገ አይገኙም ጤዛ ሁነው ረግፈዋል።በፋኖ ክንድ!!
በጭንቁ መድረክ የተገኙት አናብስት ጀግኖች ብቻ ናቸው እሳት ለብልቧቸው እሳትን በውኃ ያጠፉና የበቀሉ ቡቃያዎች!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
+1
በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር መዳረሻ ድሎች እሥከ ቀኑ 12:30 ቀጥለዋል❗
[የካቲት 03/2018ዓ.ም]
የነጻ ነኝ ዐምሐራዊው ትግል ከደራ እሥከ ፎገራ ቀጥሎ አሁን ላይ የዓቢይ ወምበር ጠባቂ ታጣቂዎችና የዓቢይ አማሮች ከባሕር ዳር በቅርብ ርቀት ''ሐሙሲት'' ከተማ ከታጣቂ እሥከ ዓቢይ ካድሬ በሚገባው ቋንቋ እየተነገረው ነው ቀን 12:30። ቀሚሥ ለባሽ ከሐዲ የብአዴን ፈረሶች በቅዱሱ ጣና ሐይቅ እያራከሱ ለማምለጥ እየሞከሩ ነው።
ከዓምሐራ ሠማይ ሥር ዘራፍ ያለው ማን ነው?
ያ ውብ-አንተ አባተ የዓሣ-ምነዉ ልጅ ነው።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊
፩ ዓምሐራ🔑✊
የትግል መለያ ሊትመሳችን ምልዑው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ነው❗
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ዘረ ውባንተ አባተ ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው ዘ ብሔረ ዓ-ም-ሐ-ራ
ቋሚ ምሥል፦ አርበኛ ኃብቴ ወልዴ መንግሥቴ እና ግዙፉ ጣና ገላውዲዎሥ ክፍለ ጦር ሠራዊት በከፊል
አስቸኳይ
ደ/ታቦር እየሱስ ተራራ ላይ እጅ የሰጡ የፋኖ አባላትና አድማ ብተና አባላት የቡድን መሳሪያ ጠምደዉ ፋኖን በመጠበቅ ላይ ሲሆን በማህደረ ማርያም በወይብላ ማርያም በየፀጉር መድሎ በኪዳነምህረትና በቀበሮ ሜዳ መዉጫዎች ምሽግ በመያዝ የሚጠብቅ ኃይል ተሰማርቷል
ለፋኖ አድርሱልኝ
ከሱዳን አዋሳኝ አርማጭሆ አብርሃጅራ እስከ
ባህርዳር አዋሳኝ ሀሙሲት በዛሬው ዕለት በሰራዊታችን እየተዳበሱ ይገኛል!!
አብርሃጅራ ቁርስ... ምሳ ሀሙሲት...ቀጣይ ባህርዳር ራት ጋብዛለች!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
እያመመው_መጣ!!
የአገዛዙ ኃይል ( የአብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት) እንዲሁሜ ሜካናይዝድ ሀይል ሙሉ በሙሉ ወደ አማራ ምድር እየገባ ነው።ወለጋ ቀጠናን ሙሉ በሙሉ ለኦሮሚያ ልዩሀይል አስረክቦ ከ120 በላይ መኪና በወለጋ ጎጃም እያስገባ ነው። በአዲስ አበባ ጎጃም ኃይል እየተንቀሳቀሰ ሲሆን 30 ታታ መኪና ኃይል ደጀን ደርሷል!!
ወይ ንቅንቅ ፋኖ💪
03/ዐ6/2018 ዓ.ም
ሦስት ወሳኝ ውጊያዎች❗️
የአማራ ፋኖ ትግል ወደ አንድ መዋቅር ተሰብስቦ አፋብን ከተመሠረተ ማግስት በቋራ፣ደቡብ ወሎ አካባቢዎች የተደረጉ የመከላከል ውጊያዊች የተደረጉ ቢሆንም፤ ጂኦፖለቲካዊ፣ፓለቲካዊ እና ወታደራዊ ግቦችን ያሳኩ ሌሎች ሦስት ውጊያዎች ተከናውነዋል። እነዚህም:-
1: በደቡብ ጎንደር ዞን የተደረገው ውጊያ ከፖለቲካዊ ፍላጎት አኳያ የብልፅግና ሥርዓት አደግዳጊ የነበረው የዞኑን መዋቅር ሽባ ያደረገ የተዋጣለት ወታደራዊ ኦፕሬሽን ተፈፅሟል። ይሄ የማጥቃት ውጊያ የመረጃ አጠቃቀም፤ ፍጥነት እና ቅንጅት እንዲሁም የብልፅግናን የፖለቲካ ክንፍ ያሽመደመደ ወሳኝ ፖለቲካዊ ተኩስ የተፈፀመበት ነበር። የአማራ ፖለቲካ የአንድነት ቅርፅ ጠንካራ ደረጃ የደረሰበት እና ወደ ሦስተኛ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
2: በመተከል ቀጠና የተደረገው ሌላኛው ጂኦ-ፖለቲካዊ ትርጉም ያለው አንዱ ወሳኝ ውጊያ ነበር። በዚህ ውጊያ የአፋብን ሊቀመንበር #አርበኛ_ዘመነ_ካሴ እና የአፋብን ም/ወታደራዊ አዛዥ #ሻለቃ_ዝናቡ_ልንገረው በቀጥታ የመሩት ስኬታማ የማጥቃት ኦፕሬሽን ነበር። የመተከል ቀጠና ሰፊ ቀጠናዊ እና ዓለም-አቀፋዊ ትኩረት የሚደረግበት ስስ ቀጠና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዚህ አካባቢ የሚደረጉ ውጊያዎች ጅኦ-ፖለቲካዊ ትርጉማቸው ከፍ ያለ እና ትኩረት ሳቢ ያደርገዋል።
3: በሸዋ ቀጠና ያለውን የአፋብን መዋቅር በመበተን ቀጠናውን ተቆጣጥሬ ወደ ሰሜን እገሰግሳለሁ፤ በዚያውም የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች #አርበኛ_መከታውን_ማሞን እና #ብርጋዴር_ጀነራል_ተፈራ_ማሞን እደመስሳለሁ ብሎ ያለ የሌለ elite force እና በርካታ ሠራዊት ያሰማራበትን የኮማንዶ ውጊያ ወሳኝ የመከላከል ውጊያ በማድረግ እቅዱን አክሽፎ ቅስም የሰበረበት ውጊያ ነበር። ሸዋን የመከላከል buffer zone በማስፋት በወሎ ቀጠና ላይ ጫና ለማድረግ ያቀደው ዕቅድ ከንቱ ሁኖ ቀርቷል። ለቀጣይ ወሳኝ የማጥቃት ቀጠና የሆነውን የሸዋ አካባቢ በመከላከል የተደረገው ተግባር በወታደራዊ ጠቀሜታ አንፃር ስኬታማ ነበር።
እነዚህ ኦፕሬሽኖች ወደ ታሪክ ቀያሪው ድል መዳረሻ ስኬታማ ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው።
©በዛብህ በላቸው
የአፋብን አሃዶች በጎንደር ንፋስ መውጫ ድል እያስመዘገቡ ቀጥለዋል!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር ቃኝ ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ጋር በጋይንት ንፋስ መውጫ የጥላትን ሰራዊ ምሽግ በመስበር ታላቅ ጀብድን ፈፅመዋል።
የአንሻ ክፍለ ጦር ቃኝ የሆነችው ከመቄት ተወርውራ የብርሀኑ ጁላንና የአረጋ ከበደን የግል ሰራዊት ከአሃዶቹ ጋር ውጤታማ ኦብሬሽን ስትፈፅም፤በዚህ ኦፕሬሽን አንድ ብሬን፣አንድ ጅምስሪና አስር ክላሽ ተማርኳል።
የካቲት 2/2018 ዓ/ም በጋይንት ንፋስ መውጫ በአፋብን አሃዶች ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝና ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አንሻ ክፍለ ጦር ቀጠናዊ ትስስርን በአማራዊ አንድ መንፈስ በታላቅና አመርቂ ውጤት አመርቂ ኦፕሬሽን ሲፈፀም! ተመሳሳይ ኦፕሬሽን ይቀጥላል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ መምሪያ
የኪቲት 3/2018 ዓ.ም
+1
የአስታጥቄ_ገፀ_በረከት‼️
በመደራጀት ላይ ያለው ራስ አንችም ክፍለ ጦር "በዘመቻ ማንደፍሮ" 2ኛ ቀን በመቄት ወረዳ እና ጋይንት አዋሳኝ ቦታዎች በርካታውን ደመስው ቀሪውን በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
የአማራ ፋኖ ብራሔዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር በመደራጀት ላይ ያለው ራስ-አንችም ክፍለ ጦር የክፍለጦሩ ዘመቻ በነበረው "ማንደፍሮ ሙላቴ" ስም በተሰየመ 2ኛ ቀን ዘመቻ ከደቡብ ጎንደር ጋይንት ንፋስ መውጫ ከተማ ፈርሶ ሲፈረጠጥ በነበረ የጠላት ዘብ ላይ ከፍተኛ ድል ያሰመዘገበ ሲሆን በሰብዓዊ ምርኮም ይሆን በመሳሪያ ምርኮ ተንበሺብሿል።
ክፍለ ጦሩ በዋና አዛዡ አርበኛ ሙቀት ሞላ እየተመራ በሰብዓዊ ምርኮ ደግሞ 17 ሚሊሻ ፣ 2 ፖሊሲ እና 1 አድማ ብተና እንዲሁም
👉01 ብሬን
👉 27 ክላሺንኮፍ
👉1500 የክላሺና 970 የብሬን ተተኳሽ
👉55 የክላሺ ካዝና
👉22 የወገብ ትጥቅ ምርኮ ተገኝቷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የክፍለ ጦሩ ቃል አቀባይ አርበኛ 50 አለቃ መንግስቱ መረጃውን አድርሷል!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
03/ዐ6/2018 ዓ.ም
