en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 133
Subscribers
+224 hours
+4237 days
+1 19130 days
Posts Archive
አንድነታችን የሚያስፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል!! ጎንደር ብቻዉን ጦርነቱን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ጫፍ ላይ ግን ሊደርስ አይችልም። * ጎጃም ብቻዉን ዉጊያዉን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ማ
አንድነታችን የሚያስፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል!! ጎንደር ብቻዉን ጦርነቱን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ጫፍ ላይ ግን ሊደርስ አይችልም። * ጎጃም ብቻዉን ዉጊያዉን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ማማ ላይ ግን ሊወጣ አይችልም። * ሸዋ ብቻዉን ጦርነቱን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ጫፍ ግን ሊደርስ አይችልም። * ወሎ ብቻዉን ዉጊያዉን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ማማ ላይ ግን ሊወጣ አይችልም። እያንዳንዳችን በተናጠል የምናደርገዉ ትግል በጦርነት ወይም በዉጊያ አሸናፊ ቢያደርገንም በዘላቂነት ከድሉ ማማ ላይ ወይም ጫፍ ላይ ግን በፍፁም ሊያደርሰንም ሊያወጣንም አይችልም። ከድሉ ጫፍ ላይ የምንደርሰዉና የህዝባችንን ህልዉና በዘላቂነት ማስከበር የምንችለዉ አንድነትታችንን እዉን አድርገን ለጋራ ዓላማ በጋራ መቆና በአንድነት መታገል ስንችል ብቻ ነዉ። አንድነታችን የሚያስፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል!!

121. Mr. Asamenew Tadese 122. Mr. Marew Sileshi 123. Mr. Fasil Getachew 124. Mr. Mesele Cheru 125. Mr. Shegaw Muhabaw 126. Mr. Tadese Melese 127. Mr. G/micheal Abaye 128. Mr. Mekuanent Tesfu 129. Mr. Amanuel Belete 130. Mr. Endale Gize 131. Mr. Henok Wale 132. Mr. Muluken Tesfa 133. Mr. Kenaw Tsegaye 134. Mr. Endesew Getu 135. Mr. Yenalem Mekonen 136. Mr. Temesgen Tachebele 137. Mr. Wondwosen Assefa 138. Mr. Dinknew Mekuanenet 139. Mr. Temesgen Zena 140. Mr. Melkamu Tinfe 141. Mr. Eyasu Gelagel 142. Mr. Daniel Gulema 143. Mr. T/brehan Zewdu 144. Mr. Abreham Abeje 145. Mr. Chane Demeke 146. Mr. Cherent Eshetu 147. Mr. Setegn Beyeno 148. Mr. Tesema Melese 149. Mr. Asemamaw Melak 150. Mr. Dachew Getu 151. Mr. Bekure Mulate 152. Mr. Desalegn Jenbere 153. Mr. Nigusu Tilahun 154. Mr. Adisu Derebew 155. Mr. Mola Bazezew 156. Mr. Belay Sisay 157. Mr. Yonatan Girma 158. Mr. Yimer Mohamed 159. Mr. Niguse Yilekal 160. Mr. Habtamu Dagnew 161. Mr. Tadele Melkamu 162. Mr. Samuel Mengistu. 163. Mrs. Hiwot Alemayehu  እና ሌሎችም... ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ! የህሊና እስረኞችን መደገፍ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ማገዝ ብሎም ''ወገናችን ከጎናችን ነው'' ብለው በፅናት የሚታገሉ ጀግኖችን መፍጠር ጭምር ነው! መልዕክቱን #ሼር በማድረግ ለብዙሃኑ ተደራሽ ያድርጉ!

መጪውን የገና በዓል ተመርኩዘን - የህሊና እስረኞችንና ቤተሰቦቻቸውን እናስታውሳቸው! እኚህ የታሰሩት ቲክቶከሮች ቢሆኑ ኖሮ ከሚዲያው መነጋገሪያ አጀንዳነት ለአፍታም አይዘነጉም ፣ ቤተሰቦቻቸውና ልጆቻቸውን ለመደገፍ የሚረባረቡትን ድርጅቶችና ግለሰቦች በቁጥር መግለፅ ይቸግር ነበር ፥ ጠዋት ማታ እንዲፈቱ  የሚደረገው ዘመቻ እንኳንስ የሀገር ውስጡን ፣ የውጪውን አለም ሚዲያ ቀልብ ይስብ ነበር። ግና እኚህ ወንድም እህቶቻችን ቲክታከሮች አይደሉም። ይልቁንም '' አድርባይ ምሁር የሀገርና የህዝብ ነቀ''ርሳ ነው'' ብለው አድርባይነትን የተፀየፉ  ፣ አስመስሎ በድሎት ከመኖር ይልቅ ስለህዝባቸው መገፋትና መበደል ፊት ለፊት ታግለውና ተሟግተው ሞትንም ቢሆን በፀጋ ለመቀበል የቆረጡ ፣ የሞቀ ቤታቸውን ዘግተው ስለህዝባቸው በድቅድቁ የግዞት ጨለማ መሪር መስዋዕትነት መክፈልን የመረጡ ፣ የአማራ ህዝብ በመከራው ውስጥ አምጦ የወለዳቸው የቁርጥ ቀን ልጆቹ ናቸው! በቃሊቲና በቂሊንጦ ወህኒ ቤቶች ብቻ ከስር የተዘረዘሩትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ምሁራን ፣ ጋዜጠኞች ፣ ፖለቲከኞች ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ፣  በግፍ ታስረው ይገኛሉ! እነዚህ ወንድም እህቶቻችንን በቡድንም በተናጠልም እየሆንን ቤተሰቦቻቸውንና ልጆቻቸውን በበዓሉ በቀጥታ በማግኘት ''አለንላችሁ'' ማለት ከእኛ ይጠበቃል። የምንችል ደግሞ የህሊና እስረኞቹን እስር ቤት ድረስ ሂደን የሞራልና የመንፈስ ስንቅ ልናቀብላቸው ይገባናል። ይህ ከእኛ የሚጠበቅ ትንሹ ኃላፊነት ነው! በቃሊቲና በቂሊንጦ እስር ቤቶች ብቻ  ከሚገኙት ወንድም እህቶቻችን መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው ፦ 1. Hon. Mr. Yohanes Boyalew 2. Hon. Mr. Christian Tadele 3. Hon. Dr. Kassa Teshager 4. Dr. Wondewosen Asefa 5. Dr. Tewodros H/mariam 6. Dr. Meseret Kelemework 7. Dr. Sisay Awgichew 8. Dr. Mearegu Biyabeyen 9. Dr. Chane Kebede 10. Dr. Zerihun Baheriw 11. Dr. Gibreab Alemu 12. Mr. Alelegn Mihretu 13. Mrs. Meskerem Abera (Journalist) 14. Mr. Gobeze Sisay (Journalist) 15. Mr. Dawit Begashaw (Journalist) 16. Miss. Genet Asemamaw (Journalist) 17. Mr. Abay Zewdu (Journalist) 18. Mr. Tesfay Mekuriaw 19. Mr. Tadesse Wodaynew 20. Artist. Yordanos Aleme 21. Mr. Menber Alemu 22. Mr. Sisay Melkamu 23. Mr. Biset Terefe 24. Mr. Dawit Ebabu 25. Mr. Masresha Eneyew 26. Mr. Tewodros Teshome 27. Mr. Andebet Teshager 28. Mr. Abreham Getnet 29. Mr. Molalegn Sisay 30. Mr. Habtamu Dagne 31. Mr. Chane Zeyede 32. Mr. Samuel Beze 33. Miss. Halima Mohamed 34. Mr. Ashagre Melese 35. Mr. Dagne Abebe 36. Mr. Tilaye Yitayew 37. Er. Firdu Tafere 38. Er. Tizazu Yitbarek 39. Saj. Gorefe Wotate 40. Mr. Belay Adamu 41. Mr. Mulugeta Agzew 42. Mr. Kefale Esubalew 43. Mr. Amare Melese 44. Mr. Tewodros Nibret 45. Mr. Tadele Asefa 46. Mr. Wotetu Desalegn 47. Mr. Desalegn Ejigu 48. Mr. Admasu Alemu 49. Mr. Shibeshi Mekonnen 50. Mr. Tewodros Tamiran 51. Mr. Birehanu Tewelegn 52. Mr. Tariku Tadesse 53. Mr. Desale Alemu 54. Mr. Habtamu Fekadu 55. Mr. Eyob Tamiru 56. Mr. Fetalew Ademasu 57. Mr. Mekonnen Desalegn 58. Mr. Getenet Amare 59. Mr. Dejen G/tsadik 60. Mr. Gizachew Tamiru 61. Mr. Fentahun Fikadu 62. Mr. Wondemu Berehe 63. Mr. Abdurehman Ahmedin 64. E/r. Yeshiwas Aletaseb 65. Saj. Altasb Dinku 66. Mr. Samson Mamo 67. Mr. Desalegn Wubu 68. Mr. Habtamu Teshager 69. Mr. Meleku Tesfe 70. Mr. Asemamaw Arega 71. Mr. Misganaw Abatneh 72. Mr. Hussien Seid 73. Mr. Micheal Melak (Human Right Defender & Journalist) 74. Mr. Brehanu Sileshi 75. Mr. Eskender Shiferaw 76. Miss. Hiwot Alemayehu 77. Mr. Aron Tirefe 78. Mr. Haile Tadesse 79. Mr. Bisrat Kassaye 80. Mr. Solomon Fikadu 81. Mr. Amanuel Yalew 82. Mr. Samuel Yalew 83. Mr. Brehanu Manave 84. Mr. Habtamu Andarege 85. Mr. Bantayehu Ayalew 86. Mr. Tesfaye Birku 87. Mr. Ashenafi Yihune 88. Mr. G/mariam Setegn 89. Mr. Meseret Worku 90. Mr. Melake Misale 91. Mr. Aweke Sineshaw 92. Mr. Gete Amenu 93. E/r. Dawit Yifru 94. Mr. Alembulutena H/micheal 95. Mr. Fekadu Mengiste 96. Mr. Manaye Ayele 97. Mr. Yilem Bezabih 98. Mr. Abreham Ayana 99. Mr. Zena Hailu 100. Mr. Andualem Ashagre 101. Mr. Wubet Akale 102. Mr. Ermiyas Mekuria 103. Mr. Zenebe Shita 104. Mr. Amanuel Haile 105. Mr. Hassen Mohamed 106. Mr. Abdulkader Mohammed 107. Mr. Wogene Sirak 108. Mr. Endashaw Mandefro 109. Mr. Muluneh Ayetenfesu 110. Mr. Melayekt Amare 111. Mr. Chernet. Zemene 112. Mr. Yilake Gedamu 113. Mr. Tamirat Misganaw 114. Mr. Abebaw Fekadu 115. Mr. Chilot Yismaw 116. Mr. Lakew Mose 117. Mr. Habtamu Fentaw 118. Mr.Tseghan H/mariam 119. Dr. Daniel Teshe 120. Mr. Sintayehu Nigatu

"የአገዛዙ ቅጥረኛ ባንዳ እና የውስጥ ተላላኪ ባንዳ ለህዝብ ደራሹ  ደም መላሹ #የአማራ_ፋኖ መድኃኒት ነው" አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ_ክፍለ_ጦር_1ኛ_ሬጅመንት የፋኖ አባላት     "ትግላችን እስከ ቀራኒዎ ነው" አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

"ሥልጣንና ሀብት፣ ማዕረግ ከሞት አያስቀርም" ለቅሶ እየደረሳችሁ ወገን ፋኖ በየአቅጣጫው ከኮሎኔል እስከ መቶ አለቃ ድረስ መምታቱን ሰሞኑን ኮር አመራሩን እንደፋሽን ቆጥሮ እየሸኘው ነው። አማራ ጋር
+1
"ሥልጣንና ሀብት፣ ማዕረግ ከሞት አያስቀርም" ለቅሶ እየደረሳችሁ ወገን ፋኖ በየአቅጣጫው ከኮሎኔል እስከ መቶ አለቃ ድረስ መምታቱን ሰሞኑን ኮር አመራሩን እንደፋሽን ቆጥሮ እየሸኘው ነው።     አማራ ጋር የተጣላ መጨረሻው ሞት ነው!!!

ሰበር ዜና! ምኒልክ ዕዝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዙ23 በአር ፒ ጂ ያቃጠለበትንና ያወደመበትን ድል ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነው ወልድያ ከተማ ዙሪያ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙ23 ልዩ ስሙ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ በአር ፒ ጂ በማቃጠልና በማውደም ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:: ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር እና የዞብል አምባ ክፍለ ጦር ቃኝ ወልድያ ዙሪያ ከጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ እና ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ቀጠና ላይ በመዝጋት ባጠቃላይ የተጠቀሱት አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: ባጠቃላይ አሳምነው ክፍለጦር የዞብል አምባ ክፍለጦር ቃኝን ጨምሮ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ድረስ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር የማረኩበትን በርካታ ድሎች ሲያስመዘግቡ ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ላይ በመዝጋትና ተጨማሪ የጠላት ሃይል እገዛ እንዳያደርግ በማድረግ የጠላትን ግንኙነት በማቋረጥ ለተገኘው ድል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል:: ማስታወሻ፦ የተማረከ ጠላት እና ንብረት በዝርዝርና በማስረጃ ይዘን እንመጣለን:: ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም

አድዋ ክፍለጦር በአለፋ ሰማይ ስር የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አካል የሆነው አድዋ ክፍለጦር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሰፊው በአለፋ ወረዳ ቀበሌዎች እስከ ቋራ እና ጣቁሳ ጣናን አልፎም ጎጃም ሰሜን አቸፈር ወረዳዎች #አዋስኖ የሚንቀሳቀስ ግዙፍ ክፍለጦር ነው። አድዋ ክፍለጦር በበላይ ዘለቀ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ወታደራዊ ኢንዶክትርኔሽን ባለሙያው በኮማንዶ ሳሙኤል ባለዕድል እና በትሁቱ ትንታግ አርበኛ መምህር አስተውል አምሳሉ በእነ አርበኛ ጌታቸው አማረ በእነ አርበኛ ባበይ በእነ አርበኛ አዳሙ ሌሎችም ተጠቅሰው የማያልቁ በርካታ አርበኞች እና ነባር ልምደኛ ኩማንዶዎች ተሞርዶ በቅቶ የዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ የወታደራዊ እና የፖለቲካዊ ስልጠና ሂደትን አልፎ ዲስፕሊንድ ሁኖ የተገነባ ጥንቅቅ ያለ ክፍለጦር መሆኑ የታወቀ ሀቅ ነው። አድዋ ክፍለጦር የአማራ የህልውና ትግል ከተጀመረ ጀምሮ እንደ ክፍለጦር #ለ10ኛ ዙር የኩማንዶ እና የእግረኛ ሰራዊት ከተለያየ ቦታ ከአዋሳኝ ወረዳዎች ሆነ ከተለያየ የአማራ ቀጠናዎች ለስልጠና እየመጡ ጭምር የሚቀላቀሉትን አዘምኖ አሰልጥኖ አስመርቋል በርካታ ሰራዊት አደራጅቷል በዚህም ለጎንደር ትግል አይደለም ለሌሎች ቀጠናዎች ለዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ አርያ የሚሆን ሞዴል ክፍለጦር ነው። ቀደም ሲል የክፍለጦሩ የፖለቲካ ዘርፍ አላፊ አርበኛ አዳሙ በሺዎች የሚቆጠር የአባት አርበኞች ጦር እያደራጁ ሳለ ባደረገው ኔግግር ስለአድዋ ክፍለጦር ቁመና ሲናገር አድዋ ክፍለጦር ከአባት አርበኛ ጦር ውጭ የተጠረነፈ ከ10,500በላይ እስከአፍንጫው የታጠቀ ሰራዊት እንዳለው እና በቀጠናው ያለውን ጠላት ሲያካፍለው 1ጠላት ተረባርቦ ለመ*ግደል ለ50ፋኖዎች እንደሚደርስባቸው ሁሉ ሲገልጽ ሰምቻለሁ። በአንድ ወቅትም የበላይ ዘለቀ ዕዝ ሌሎች የክፍለጦር አባሎች ለተልዕኮ ወደ አድዋ ክፍለጦር ቀጠና ሂደው ያዩትን ሲያጫዎቱኝ እነሱን ተቀብለዋቸው አብረው መጥጥ ሲጠጡ አርበኛ ሳሚ ድንገት ድርስ ሲል የአድዋ ክፍለጦር አባሎች ሹልክ ሹልክ ብለው ሩጠው እንዳመለጡ ነገሩኝ ለካስ ተደብቀው ነበር ሲጠጡ የነበር ከዛ ሌሎች እንግዶችም ያልተለመደ ነገር ሁኖባቸው ሳለ አርበኛ ሳሚ በእኛ ቀጠና አልኮል መጠጣት አይፈቀድም ለዛሬው አልፊአቹህ ሁለተኛ እንዳይደገማቹህ አለን ብለው አወሩኝ ጭራሽም ለግዳጅ የተመደበ ሰራዊቱ ከውጊያ መልስ ማን ስንት ጠይት ተኮሰ እና ኢላማውን መታ ማን ጥይት አባከነ ተብሎ ሁሉ እንደሚገመገም ጭምር አጫውቶኛል። ታዲያ ከሰሞኑ የጠላት የሚዲያ ሰራዊት አድዋ ክፍለጦርን አልፎም መይሳው ካሳ ኮርን ቀጥሎም በበላይ ዕዝ መካከል ልዩነት የተፈጠረ በማስመሰል ልዩነት ለመፍጠር እና ለመከፋፈል ብዙ የውሸት ድርሰት ሲያራግብ የሰነበተበት ጉዳይ የክፍለጦሩ አካል የሆነችው የንጋት ጮራ ብርጌድ ባለ ሻለቃ የተፈጠረ የአፈንጋጭነት እና የህግ የማስከበር ስራ ጉዳይ ሲሆን ውሰን በሆኑ የአፈንጋጮች አለቃፐ ጌጤ በሚባል ፋኖ ለበላይ ዘለቀ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ አላፊ ደውሎ የተናገረወው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው ። ከፋፋይ የአገዛዙ የሚዲያ ሰራዊቶች እና የፋኖ ደጋፊ የሚመስሉ ግን ያልሆኑ የአገዛዙ ስትራቴጅካል አጋር አጃቢዎቻቸው ጭምር ኮማንዶ ሳሚ ተያዝ አርበኛ ማንደፍሮ ተያዘ አርበኛ ዮሐንስ ተከቧል 😁😁 (እግዞ ከመያዝ የተረፈ አመራር አልነበረም እኮ 😂) አይነት ቀደዳዎችን እያራገቡ ስንመለከትም ስንስቅም ነበር ተከትሎም የሚደናገር የአማራ ታጋይ እና የትግሉ ደጋፊ ይኖራል ብለን አናምንም እና መልስም የሰጠ የለም እነዚህን ቀጣፊ ውልደ ብአዲኖችን እሽ ጉዳዩ የት ደረሰ ብላቹህ ብትጠይቋቸው እንኳን ሊመልሱላቹህ ሌላ አጀንዳ ፈጠራ ወከባ ፈጠራ ውጋ በፍለጋ ላይ ተጠምደው ትናንት ያሉትን ጉዳዩን አይደለም ብዙ ማለታቸውን ራሱ ረስተውታል ሌላ የዛው አባዜ አለም ላይ እንደተንሳፈፉ ናቸው እረ እባካቹህ መሬት ላይ ውረዱ እና እርገጡ😂😂 ✍️ያም ሆነ እሂ የድርጅትን መምሪያ ያላከበረ የእዝ የኮር የክፍለጦር የብርጌድን የተዋረድ መምሪያ ያልተቀበለ እንዲሁም አመራሮችን ያላከበረ አንጀኝነትን ቡድንተኝነትን ጎጠኝነትን ለመፍጠር የሚሞክርን በቁጥር ከ100 የማይበልጥ አፈንጋጭ ካለ የእርምት እርምጃ መውሰድ እና ተቋሙን መጠበቅ የድርጅቱ አላፊነት እና መብት መሆኑን መታወቅም አለበት እሂ ህግ እና መምሪያ አንጀኝነትን ቡድንተኝነትን አፈንጋጭነትን አለመጠርነፍን እና የፋኖን ትግል የሚያጠለሹ ወንጀል መስራትን የሚከላከል ለየትኛውም ድርጅት ለየትኛውም የፋኖ ዕዝ ይሰራል እየሰራም እየተተገበረም ይገኛል መሆንም አለበት። ድል ለአማራ ፋኖ ህልውናችን በተባበረ ከረንዳችን!!! ልባሙ ፋኖ

በላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በተወሰደበት የማያዳግም እርምጃ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣በእሸት ክፍለ ጦርና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በላስታና ቡግና ሰንሰለታማ ተራሮች ሲቀጠቀጥ የዋለው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጦር በደረሰበት ሽንፈት ምላሽ ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ። መነሻውን ከአይና ቡግና አድርጎ 05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ) ላይ ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም ንጋት አጥቢያ 12:00 ሰዓት እስከ ቀትር 8:00 ሰዓት ውጊያ የከፈተው የአገዛዙ ሰራዊት በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድና ሦስተኛና አራተኛ ሻለቃዎች በአይቆፍር ጨረሆና ሆዛ ሜዳ አቅጣጫ የመጣውን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል፤በአውደ ውጊያው 35 የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኛውን በአምቡላንስና ፓትሮል እየለቀመ ተመልሷል እንዲሁም ሰባት አባላቱ የአማራን ህዝብ አንወጋም በማለት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል። በዚህም የተበሳጨው የጁላ ሰራዊት ቡግና ወረዳ የ08 ቀበሌ ንብ ዋርካና የ05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ)ን ህዝብ በመድፍ፣በአየር መቃወሚያ(ዙ-23) እና በሞርታር-120 ሲጨፈጭፍ ውሏል፤በዚህ ጭፍጨፋ ሦስት ንፁሃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ አራት የአርሶ አደር ቤቶች በዙ-23 ሲቃጠሉ ተጨማሪ ዘጠኝ ንፁሃን በከባድ ሁኔታ ቆስለው ህይወታቸው በህክምና እየተጠበቀ ይገኛል። በጭፍጨፋው በከባድ መሳሪያ አንዲት የ60 ዓመት መነኩሴና የ15 ዓመት ልጃገረድ ለገና በዓልና ለንጉስ ላልይበላ ልደት ክብረ በዓል ወደ ላስታ ላሊበላ ይጓዙ የነበሩ እና ቅዱስ ሐርቤ ሚኒቃባ መንደር ከእናቷ ማዘል ላይ የነበረች እታቱ ሞላ ወዳይ የተባለች ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ የህፃኗ እናትም ለህይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ:- 1ኛ. ደስታ ዋጋዬ የ28 ዓመት እናትና ልጆቿ መሰረት አበባው የ7 ዓመት ህፃን እንዲሁም ትዕግስት አበባው የ4 ዓመት ህፃን 2ኛ. ሐይማኖት ደማሙ የተባለች የ22 ዓመት ልጃገረድ 3ኛ. ወጋየሁ ባዬ የተባለች የ38 ዓመት እናት 4ኛ. እማሆይ አይቼሽ መልኬ የተባሉ የ75 ዓመት አዛውንት 5ኛ. መንበር አበባው የተባለ የ8 ዓመት ህፃን 6ኛ. ባየች ባዬ የተባለች የ28 ዓመት ወይዘሮ 7ኛ. ቄስ ካሳ ነጋሽ የተባሉ የ78 ዓመት የሐይማኖት አባት ቤተ-ክርስቲያን አገልግለው ሲወጡ እንዲሁም ህዝቡና አገልጋዩ በቅዱስ ሐርቤ ደብር ነዓኩቶልአብ ቤተ-ክርስቲያን እሁድ ሰንበትን እያከበረ በሚገኝበት በቤተ-ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንዳሉ በከባድ መሳሪያ ቆስለዋል ቤተ-ክርስቲያኑም ጉዳት አስተናግዷል። በተያያዘም እሸት ክፍለ ጦርና ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ከላሊበላ ድብኮ ቀጠና በወሰዱበት የማያዳግም እርምጃ የአገዛዙ ሰራዊት በአፀፋው ንፁሃን ላይ መድፍ በመተኮስ ድብኮ ቀጠና ሁለት የአርሶ አደር ቤቶችን ያቃጠለ ሲሆን ስድስት ከብቶችም ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር  ህዝብ  ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 26/ 2018 ዓ.ም

#ትኩረት_የሚሻ_አሳዛኛ_መረጃ እንደሚታወቀው በትናንትናው እለት በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ሽፋን ተሰጦት የነበረው የጣና ገዳማት ጉዳይ በጀግኖቹ ሻለቃ አቢ እና ሻለቃ ዳንኤል ሀብታሙ እየተመራ ሁለት የአገ
+2
#ትኩረት_የሚሻ_አሳዛኛ_መረጃ እንደሚታወቀው በትናንትናው እለት በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ሽፋን ተሰጦት የነበረው የጣና ገዳማት ጉዳይ  በጀግኖቹ ሻለቃ አቢ እና ሻለቃ ዳንኤል ሀብታሙ እየተመራ ሁለት የአገዛዙን የባህር ኃይል ኮማዶ ተብየ የጫኑ ተዋጊ ጀልባዎች ማስመጥ የቻሉ ሲሆን ገዳማቱንና ማህበረሰቡን ለመታደግ ሲባል የወገን ኃይል ከቀጠናው መውጣቱን የገለጽን ቢሆንም በዛሬ እለት ደግሞ የወገን ኃይል በሌለበት ሁኔታ በጣና ገዳማት ላይ ኃይለኛ የሆነ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተፈጽሟል። ድብደባው የተፈጸመባቸው ገዳማት            1.ዳጋ እስጢፋኖስ            2.ወባ ኪዳነ-ምህረት            3.ደቅ አርሴማ            4.ኮታ ማርያም            5.ናርጋ ስላሴ በተጨማሪ የደቅ ማህበረሰብ  ጠላት "አንይህ" በማለት ወደ ተለያዩ አጎራባች ገዳማትና ቀበሌዎች በጀልባ የሸሸ ቢሆንም በእድሜ አጋፋ የሆኑና በአልጋ ቁራኛ በጽኑ በህመም ላይ የሚገኙትን እያሰቃየ ይገኛል። የተዘጉ ቤቶችን እያፈራረሰ ሙሉ የቤ እቃ ዱቄትና ሊጥ ሳይቀር ጀልባ አስጠግቶ እየጫነ ስለሆነ ድምፅ ትሆኑ ዘንድ አማራዊ መልዕክታችን ነው። የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከትና የባህርዳር ሀገረ ስብከት በገዳማቱ ፣ በመነኮሳቱ ፣ በደቅ ደሴት ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ባለማውገዛችሁ በአባትነታችሁ አፍረናል። ድል ለአማራ ፋኖ አዲስ ትውልድ ፣ አድስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ ፋኖ ዳዊት ሽፈራው

ሰበር ዜና! ጎንደር ሪፈራር ሆስቲታል ህክምና ላይ የነበሩ 37 የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ሀይሎች መሞታቸው ተረጋገጠ ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሰሞኑን በአጅሬ ጃኖራ ፣ በሚጦ ፣ ጦሃ ቀበሌ እና በሌሎች ቦታዎች በተደረጉ አውደ ውጊያዎች የአገዛዙ ብልፅግና ሆድ አደሮች በርካቶች በሞት ሲሸኙ የተቀሩት ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ቁስለኛ ሁነው በቀጠናው ያሉ ሆስፒታሎችን እያጨናነቁ ይገኛል ።በቀጠናው ከሚገኙት ሆስፒታሎች መካከል አንዱ በሆነው ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና ከገቡት ቁስለኞች መካከል ዛሬ ጣት የሞቱትን ሶስት የሚኒሻ አባላትን ጨምሮ ከ37 በላይ የሚሆን የአገዛዙ ጡት ቆራጭ ሀይል አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እስትንፋሳቸው መቋረጡ ተረጋግጧል። አንድ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የሆስፒታሉ ዶክተር ብዙ ጊዜ ለህክምና ከሚመጡት ቁስለኞች አብዛኛዎቹ ይሞታሉ ምክንያቱ ደግሞ ቁስለኞች ከአውደ ውጊያ ግንባሮች ሆስፒታል ሳይደርሱ ብዙ ደም ስለሚፈሳቸው እና በእነሱ የህክምና ሙያተኞች የሚሰጧቸው የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በቂ አለመሆኑ ተዳምሮ ለሞት ያበቃቸዋል ይላሉ ። አሁንም ጎንደር ሪፈራል ሆስቲታል በቁስለኞች በመሞላቱ ዛሬ ተህሳስ 26/2018 ዓ/ም 29 ቁስለኞ ወደ አይራ ሆስፒታል ተልከዋል ከ10 በላይ የሚሆኑት ቁስለኞች ደግሞ አሁንም ማንቂያ ክፍል እንደሚገኙ ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ስጋታቸውን ጠቁመዋል ። ዶክተሩ የጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ሙያተኞች ቁስለኞቹ እንደሚመሞቱ እያወቁ በመከላከያ ሰራዊቱ ጫና የተነሳ በርካታ መዳህኒቶችን ለሟቾች እየባከኑ በመሆኑ ሌሎች በህይዎት የሚድኑ መደበኛ ታካሚዎችን በመዳህኒት እጥረት እና በስራ ጫና የተነሳ ማዳን አልቻልነም ይላሉ ። በመጨረሻም ዶክተሩ የአገዛዙ ሀይሎች የህክምና ጉዳይ በሆስፒታሉ አስተዳደሮች ውሳኔ ካልተሰጠበት በቅርቡ ሆስፒታሉ በመዳህኒት እጥረት ሙሉ በሙሉ መደበኛ ስራው ሊቋረጥ እንደሚችል ጠቁመው ይህ ድርጊት ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ጥሩ ግንኙነት ሊያሻክረው እንደሚችል ስጋታቸውን ጠቁመዋል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለጤናው ዘርፍ የምትሰጡት እርዳታ እና ድጋፍ የት እየደረሰ ለምን አገልግሎት እየዋለ እንደሆነ በአግባቡ እንድትመረምሩ እና ለህብረተሰቡ ጤና እንድትጨነቁ ስንል ማሳሰብ እንወዳለን ። በተያያዘ ዜና ለስብሰባ የመጣው የአገዛዙ አመራር ስብሰባውን አቋርጦ ፈረጠጠ። የጎንደር ከተማ አንድ አካል በሆነችው ጠዳ ከተማ እግዚአራብ ቤተክርስቲያን ላይ የነበሩ ምዕመናንን ፋኖን ምረሽ እንድታስገቡ ብሎ ለማስፈራራት እና ለማሰር ዛሬ ተህሳስ 26/2018 ዓ/ም የመጣው የአገዛዙ ዘራፊ አመራር በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቃኘው ብርጌድ አባላት በተከፈተበት ተኩስ ስብሰባውን አቋርጦ እስኪያልበው ድረስ ፈርጥጦ መገጭ ግድብ ገብቷል። የቃኘው ብርጌድ አባላት ለምዕመናን ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርገዋል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም ከጎንደር ሰማይ ስር

አማራዎች ነን የዘሜ ልጆች!! እሳት በሚያዘንበው የጎጃም ምድር 25ኛ ክ/ጦር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሳለች። 206ኛ ኮር ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም =================================== የአረመኔው ሰራዊት በጠና መልኩ የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25ኛ/32ኛ/57ኛ ክፍለጦሮችን በማሰማራት ወደጮቄ ተራራ ለመውጣት ባደረገው እንቅስቃሴ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ታህሳስ 24እና 25 ባደረገው ትንቅንቅ የአረመኔው ሰራዊት 25ኛ ክፍለ/ጦር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሳለች። የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን ለማደናቀፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን በመጨረሻም በእነ ሞት አይፈሬዎች ምድር ጎጃም ድባቅ ተመቷል። ለሶስት ቀናት በወሰደው ምርኮኛ እና ትጥቅ የመልቀም ሒደቱ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን 206ኛ ኮር 3 ዲሽቃ 2 ሞርተር 8 ብሬን 5 ስናይፐር 230 ክላሽ 2 መቶ አለቃዎችን ጨምሮ 61የአረመኔው ሰራዊት ሲማረኩ ፣2 ሻለቃ አዛዦች ፣5(አምስት) መቶ አለቃዎች እና 420 የአረመኔው ሰራዊት ተደምስሰው ከ137 በላይ የጠላት ኃይል ቁስለኛ ሁነዋል። 32ኛ/57ኛ እና 25ኛ ክ/ጦርን አቀናጅቶ ማጥቃት ለማድረግ አቅዶ የነበረው የጀነራል ሶፊያ ማህመድ 602ኛ ኮር በቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ተደቅድቆ በየ ጫካው ሲለቀም ውሏል። የደረሰበትን ምት መቋቋም አቅቶት ብትንትኑ የወጣው የአረመኔው ሰራዊት 4ኛውን ዲሽቃ በ109ኛ ኮር የተማረከ ሲሆን ማህበረሰቡ ለሶስት ቀናት የጠላትን አስክሬን እየሰበሰበ እየቀበረ ይገኛል። አንድም አስክሬን ሳያነሳ ብትንትኑ ወጦ በየ ጫካው ወድቆ እየተገኘ የሚገኘው የመጄር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን 25ኛ ክ/ጦር እስከ አሁን በአለው ተጨባጭ ሁኔታ 618 የሰው ኃይሉ ከጥቅም ውጭ ሁኗል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት