ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 133
Suscriptores
+224 horas
+4237 días
+1 19130 días
Archivo de publicaciones
አንድነታችን የሚያስፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል!!
ጎንደር ብቻዉን ጦርነቱን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ጫፍ ላይ ግን ሊደርስ አይችልም።
*
ጎጃም ብቻዉን ዉጊያዉን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ማማ ላይ ግን ሊወጣ አይችልም።
*
ሸዋ ብቻዉን ጦርነቱን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ጫፍ ግን ሊደርስ አይችልም።
*
ወሎ ብቻዉን ዉጊያዉን ሊያሸንፍ ይችላል፤ ከድሉ ማማ ላይ ግን ሊወጣ አይችልም።
እያንዳንዳችን በተናጠል የምናደርገዉ ትግል በጦርነት ወይም በዉጊያ አሸናፊ ቢያደርገንም በዘላቂነት ከድሉ ማማ ላይ ወይም ጫፍ ላይ ግን በፍፁም ሊያደርሰንም ሊያወጣንም አይችልም።
ከድሉ ጫፍ ላይ የምንደርሰዉና የህዝባችንን ህልዉና በዘላቂነት ማስከበር የምንችለዉ አንድነትታችንን እዉን አድርገን ለጋራ ዓላማ በጋራ መቆና በአንድነት መታገል ስንችል ብቻ ነዉ።
አንድነታችን የሚያስፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል!!
121. Mr. Asamenew Tadese
122. Mr. Marew Sileshi
123. Mr. Fasil Getachew
124. Mr. Mesele Cheru
125. Mr. Shegaw Muhabaw
126. Mr. Tadese Melese
127. Mr. G/micheal Abaye
128. Mr. Mekuanent Tesfu
129. Mr. Amanuel Belete
130. Mr. Endale Gize
131. Mr. Henok Wale
132. Mr. Muluken Tesfa
133. Mr. Kenaw Tsegaye
134. Mr. Endesew Getu
135. Mr. Yenalem Mekonen
136. Mr. Temesgen Tachebele
137. Mr. Wondwosen Assefa
138. Mr. Dinknew Mekuanenet
139. Mr. Temesgen Zena
140. Mr. Melkamu Tinfe
141. Mr. Eyasu Gelagel
142. Mr. Daniel Gulema
143. Mr. T/brehan Zewdu
144. Mr. Abreham Abeje
145. Mr. Chane Demeke
146. Mr. Cherent Eshetu
147. Mr. Setegn Beyeno
148. Mr. Tesema Melese
149. Mr. Asemamaw Melak
150. Mr. Dachew Getu
151. Mr. Bekure Mulate
152. Mr. Desalegn Jenbere
153. Mr. Nigusu Tilahun
154. Mr. Adisu Derebew
155. Mr. Mola Bazezew
156. Mr. Belay Sisay
157. Mr. Yonatan Girma
158. Mr. Yimer Mohamed
159. Mr. Niguse Yilekal
160. Mr. Habtamu Dagnew
161. Mr. Tadele Melkamu
162. Mr. Samuel Mengistu.
163. Mrs. Hiwot Alemayehu እና ሌሎችም...
ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ! የህሊና እስረኞችን መደገፍ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ማገዝ ብሎም ''ወገናችን ከጎናችን ነው'' ብለው በፅናት የሚታገሉ ጀግኖችን መፍጠር ጭምር ነው!
መልዕክቱን #ሼር በማድረግ ለብዙሃኑ ተደራሽ ያድርጉ!
መጪውን የገና በዓል ተመርኩዘን - የህሊና እስረኞችንና ቤተሰቦቻቸውን እናስታውሳቸው!
እኚህ የታሰሩት ቲክቶከሮች ቢሆኑ ኖሮ ከሚዲያው መነጋገሪያ አጀንዳነት ለአፍታም አይዘነጉም ፣ ቤተሰቦቻቸውና ልጆቻቸውን ለመደገፍ የሚረባረቡትን ድርጅቶችና ግለሰቦች በቁጥር መግለፅ ይቸግር ነበር ፥ ጠዋት ማታ እንዲፈቱ የሚደረገው ዘመቻ እንኳንስ የሀገር ውስጡን ፣ የውጪውን አለም ሚዲያ ቀልብ ይስብ ነበር።
ግና እኚህ ወንድም እህቶቻችን ቲክታከሮች አይደሉም። ይልቁንም '' አድርባይ ምሁር የሀገርና የህዝብ ነቀ''ርሳ ነው'' ብለው አድርባይነትን የተፀየፉ ፣ አስመስሎ በድሎት ከመኖር ይልቅ ስለህዝባቸው መገፋትና መበደል ፊት ለፊት ታግለውና ተሟግተው ሞትንም ቢሆን በፀጋ ለመቀበል የቆረጡ ፣ የሞቀ ቤታቸውን ዘግተው ስለህዝባቸው በድቅድቁ የግዞት ጨለማ መሪር መስዋዕትነት መክፈልን የመረጡ ፣ የአማራ ህዝብ በመከራው ውስጥ አምጦ የወለዳቸው የቁርጥ ቀን ልጆቹ ናቸው!
በቃሊቲና በቂሊንጦ ወህኒ ቤቶች ብቻ ከስር የተዘረዘሩትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ምሁራን ፣ ጋዜጠኞች ፣ ፖለቲከኞች ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ፣ በግፍ ታስረው ይገኛሉ!
እነዚህ ወንድም እህቶቻችንን በቡድንም በተናጠልም እየሆንን ቤተሰቦቻቸውንና ልጆቻቸውን በበዓሉ በቀጥታ በማግኘት ''አለንላችሁ'' ማለት ከእኛ ይጠበቃል። የምንችል ደግሞ የህሊና እስረኞቹን እስር ቤት ድረስ ሂደን የሞራልና የመንፈስ ስንቅ ልናቀብላቸው ይገባናል። ይህ ከእኛ የሚጠበቅ ትንሹ ኃላፊነት ነው!
በቃሊቲና በቂሊንጦ እስር ቤቶች ብቻ ከሚገኙት ወንድም እህቶቻችን መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው ፦
1. Hon. Mr. Yohanes Boyalew
2. Hon. Mr. Christian Tadele
3. Hon. Dr. Kassa Teshager
4. Dr. Wondewosen Asefa
5. Dr. Tewodros H/mariam
6. Dr. Meseret Kelemework
7. Dr. Sisay Awgichew
8. Dr. Mearegu Biyabeyen
9. Dr. Chane Kebede
10. Dr. Zerihun Baheriw
11. Dr. Gibreab Alemu
12. Mr. Alelegn Mihretu
13. Mrs. Meskerem Abera (Journalist)
14. Mr. Gobeze Sisay (Journalist)
15. Mr. Dawit Begashaw (Journalist)
16. Miss. Genet Asemamaw (Journalist)
17. Mr. Abay Zewdu (Journalist)
18. Mr. Tesfay Mekuriaw
19. Mr. Tadesse Wodaynew
20. Artist. Yordanos Aleme
21. Mr. Menber Alemu
22. Mr. Sisay Melkamu
23. Mr. Biset Terefe
24. Mr. Dawit Ebabu
25. Mr. Masresha Eneyew
26. Mr. Tewodros Teshome
27. Mr. Andebet Teshager
28. Mr. Abreham Getnet
29. Mr. Molalegn Sisay
30. Mr. Habtamu Dagne
31. Mr. Chane Zeyede
32. Mr. Samuel Beze
33. Miss. Halima Mohamed
34. Mr. Ashagre Melese
35. Mr. Dagne Abebe
36. Mr. Tilaye Yitayew
37. Er. Firdu Tafere
38. Er. Tizazu Yitbarek
39. Saj. Gorefe Wotate
40. Mr. Belay Adamu
41. Mr. Mulugeta Agzew
42. Mr. Kefale Esubalew
43. Mr. Amare Melese
44. Mr. Tewodros Nibret
45. Mr. Tadele Asefa
46. Mr. Wotetu Desalegn
47. Mr. Desalegn Ejigu
48. Mr. Admasu Alemu
49. Mr. Shibeshi Mekonnen
50. Mr. Tewodros Tamiran
51. Mr. Birehanu Tewelegn
52. Mr. Tariku Tadesse
53. Mr. Desale Alemu
54. Mr. Habtamu Fekadu
55. Mr. Eyob Tamiru
56. Mr. Fetalew Ademasu
57. Mr. Mekonnen Desalegn
58. Mr. Getenet Amare
59. Mr. Dejen G/tsadik
60. Mr. Gizachew Tamiru
61. Mr. Fentahun Fikadu
62. Mr. Wondemu Berehe
63. Mr. Abdurehman Ahmedin
64. E/r. Yeshiwas Aletaseb
65. Saj. Altasb Dinku
66. Mr. Samson Mamo
67. Mr. Desalegn Wubu
68. Mr. Habtamu Teshager
69. Mr. Meleku Tesfe
70. Mr. Asemamaw Arega
71. Mr. Misganaw Abatneh
72. Mr. Hussien Seid
73. Mr. Micheal Melak (Human Right Defender & Journalist)
74. Mr. Brehanu Sileshi
75. Mr. Eskender Shiferaw
76. Miss. Hiwot Alemayehu
77. Mr. Aron Tirefe
78. Mr. Haile Tadesse
79. Mr. Bisrat Kassaye
80. Mr. Solomon Fikadu
81. Mr. Amanuel Yalew
82. Mr. Samuel Yalew
83. Mr. Brehanu Manave
84. Mr. Habtamu Andarege
85. Mr. Bantayehu Ayalew
86. Mr. Tesfaye Birku
87. Mr. Ashenafi Yihune
88. Mr. G/mariam Setegn
89. Mr. Meseret Worku
90. Mr. Melake Misale
91. Mr. Aweke Sineshaw
92. Mr. Gete Amenu
93. E/r. Dawit Yifru
94. Mr. Alembulutena H/micheal
95. Mr. Fekadu Mengiste
96. Mr. Manaye Ayele
97. Mr. Yilem Bezabih
98. Mr. Abreham Ayana
99. Mr. Zena Hailu
100. Mr. Andualem Ashagre
101. Mr. Wubet Akale
102. Mr. Ermiyas Mekuria
103. Mr. Zenebe Shita
104. Mr. Amanuel Haile
105. Mr. Hassen Mohamed
106. Mr. Abdulkader Mohammed
107. Mr. Wogene Sirak
108. Mr. Endashaw Mandefro
109. Mr. Muluneh Ayetenfesu
110. Mr. Melayekt Amare
111. Mr. Chernet. Zemene
112. Mr. Yilake Gedamu
113. Mr. Tamirat Misganaw
114. Mr. Abebaw Fekadu
115. Mr. Chilot Yismaw
116. Mr. Lakew Mose
117. Mr. Habtamu Fentaw
118. Mr.Tseghan H/mariam
119. Dr. Daniel Teshe
120. Mr. Sintayehu Nigatu
"የአገዛዙ ቅጥረኛ ባንዳ እና የውስጥ ተላላኪ ባንዳ ለህዝብ ደራሹ ደም መላሹ #የአማራ_ፋኖ መድኃኒት ነው"
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ_ክፍለ_ጦር_1ኛ_ሬጅመንት የፋኖ አባላት
"ትግላችን እስከ ቀራኒዎ ነው"
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
+1
"ሥልጣንና ሀብት፣ ማዕረግ ከሞት አያስቀርም"
ለቅሶ እየደረሳችሁ ወገን ፋኖ በየአቅጣጫው ከኮሎኔል እስከ መቶ አለቃ ድረስ መምታቱን ሰሞኑን ኮር አመራሩን እንደፋሽን ቆጥሮ እየሸኘው ነው።
አማራ ጋር የተጣላ መጨረሻው ሞት ነው!!!
ሰበር ዜና!
ምኒልክ ዕዝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዙ23 በአር ፒ ጂ ያቃጠለበትንና ያወደመበትን ድል ተጎናፀፈ::
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ በሆነው ወልድያ ከተማ ዙሪያ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙ23 ልዩ ስሙ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ በአር ፒ ጂ በማቃጠልና በማውደም ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::
ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር እና የዞብል አምባ ክፍለ ጦር ቃኝ ወልድያ ዙሪያ ከጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ እና ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ቀጠና ላይ በመዝጋት ባጠቃላይ የተጠቀሱት አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ከባድ ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ባጠቃላይ አሳምነው ክፍለጦር የዞብል አምባ ክፍለጦር ቃኝን ጨምሮ ጥቁር ውሃ እስከ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ድረስ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር የማረኩበትን በርካታ ድሎች ሲያስመዘግቡ ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር ድልብና ሰከላ ላይ በመዝጋትና ተጨማሪ የጠላት ሃይል እገዛ እንዳያደርግ በማድረግ የጠላትን ግንኙነት በማቋረጥ ለተገኘው ድል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል::
ማስታወሻ፦ የተማረከ ጠላት እና ንብረት በዝርዝርና በማስረጃ ይዘን እንመጣለን::
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም
አድዋ ክፍለጦር በአለፋ ሰማይ ስር
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አካል የሆነው አድዋ ክፍለጦር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሰፊው በአለፋ ወረዳ ቀበሌዎች እስከ ቋራ እና ጣቁሳ ጣናን አልፎም ጎጃም ሰሜን አቸፈር ወረዳዎች #አዋስኖ የሚንቀሳቀስ ግዙፍ ክፍለጦር ነው።
አድዋ ክፍለጦር በበላይ ዘለቀ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ወታደራዊ ኢንዶክትርኔሽን ባለሙያው በኮማንዶ ሳሙኤል ባለዕድል እና በትሁቱ ትንታግ አርበኛ መምህር አስተውል አምሳሉ በእነ አርበኛ ጌታቸው አማረ በእነ አርበኛ ባበይ በእነ አርበኛ አዳሙ ሌሎችም ተጠቅሰው የማያልቁ በርካታ አርበኞች እና ነባር ልምደኛ ኩማንዶዎች ተሞርዶ በቅቶ የዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ የወታደራዊ እና የፖለቲካዊ ስልጠና ሂደትን አልፎ ዲስፕሊንድ ሁኖ የተገነባ ጥንቅቅ ያለ ክፍለጦር መሆኑ የታወቀ ሀቅ ነው።
አድዋ ክፍለጦር የአማራ የህልውና ትግል ከተጀመረ ጀምሮ እንደ ክፍለጦር #ለ10ኛ ዙር የኩማንዶ እና የእግረኛ ሰራዊት ከተለያየ ቦታ ከአዋሳኝ ወረዳዎች ሆነ ከተለያየ የአማራ ቀጠናዎች ለስልጠና እየመጡ ጭምር የሚቀላቀሉትን አዘምኖ አሰልጥኖ አስመርቋል በርካታ ሰራዊት አደራጅቷል በዚህም ለጎንደር ትግል አይደለም ለሌሎች ቀጠናዎች ለዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ አርያ የሚሆን ሞዴል ክፍለጦር ነው።
ቀደም ሲል የክፍለጦሩ የፖለቲካ ዘርፍ አላፊ አርበኛ አዳሙ በሺዎች የሚቆጠር የአባት አርበኞች ጦር እያደራጁ ሳለ ባደረገው ኔግግር ስለአድዋ ክፍለጦር ቁመና ሲናገር አድዋ ክፍለጦር ከአባት አርበኛ ጦር ውጭ የተጠረነፈ ከ10,500በላይ እስከአፍንጫው የታጠቀ ሰራዊት እንዳለው እና በቀጠናው ያለውን ጠላት ሲያካፍለው 1ጠላት ተረባርቦ ለመ*ግደል ለ50ፋኖዎች እንደሚደርስባቸው ሁሉ ሲገልጽ ሰምቻለሁ።
በአንድ ወቅትም የበላይ ዘለቀ ዕዝ ሌሎች የክፍለጦር አባሎች ለተልዕኮ ወደ አድዋ ክፍለጦር ቀጠና ሂደው ያዩትን ሲያጫዎቱኝ እነሱን ተቀብለዋቸው አብረው መጥጥ ሲጠጡ አርበኛ ሳሚ ድንገት ድርስ ሲል የአድዋ ክፍለጦር አባሎች ሹልክ ሹልክ ብለው ሩጠው እንዳመለጡ ነገሩኝ ለካስ ተደብቀው ነበር ሲጠጡ የነበር ከዛ ሌሎች እንግዶችም ያልተለመደ ነገር ሁኖባቸው ሳለ አርበኛ ሳሚ በእኛ ቀጠና አልኮል መጠጣት አይፈቀድም ለዛሬው አልፊአቹህ ሁለተኛ እንዳይደገማቹህ አለን ብለው አወሩኝ ጭራሽም ለግዳጅ የተመደበ ሰራዊቱ ከውጊያ መልስ ማን ስንት ጠይት ተኮሰ እና ኢላማውን መታ ማን ጥይት አባከነ ተብሎ ሁሉ እንደሚገመገም ጭምር አጫውቶኛል።
ታዲያ ከሰሞኑ የጠላት የሚዲያ ሰራዊት አድዋ ክፍለጦርን አልፎም መይሳው ካሳ ኮርን ቀጥሎም በበላይ ዕዝ መካከል ልዩነት የተፈጠረ በማስመሰል ልዩነት ለመፍጠር እና ለመከፋፈል ብዙ የውሸት ድርሰት ሲያራግብ የሰነበተበት ጉዳይ የክፍለጦሩ አካል የሆነችው የንጋት ጮራ ብርጌድ ባለ ሻለቃ የተፈጠረ የአፈንጋጭነት እና የህግ የማስከበር ስራ ጉዳይ ሲሆን ውሰን በሆኑ የአፈንጋጮች አለቃፐ ጌጤ በሚባል ፋኖ ለበላይ ዘለቀ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ አላፊ ደውሎ የተናገረወው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው ።
ከፋፋይ የአገዛዙ የሚዲያ ሰራዊቶች እና የፋኖ ደጋፊ የሚመስሉ ግን ያልሆኑ የአገዛዙ ስትራቴጅካል አጋር አጃቢዎቻቸው ጭምር ኮማንዶ ሳሚ ተያዝ አርበኛ ማንደፍሮ ተያዘ አርበኛ ዮሐንስ ተከቧል 😁😁 (እግዞ ከመያዝ የተረፈ አመራር አልነበረም እኮ 😂)
አይነት ቀደዳዎችን እያራገቡ ስንመለከትም ስንስቅም ነበር ተከትሎም የሚደናገር የአማራ ታጋይ እና የትግሉ ደጋፊ ይኖራል ብለን አናምንም እና መልስም የሰጠ የለም እነዚህን ቀጣፊ ውልደ ብአዲኖችን እሽ ጉዳዩ የት ደረሰ ብላቹህ ብትጠይቋቸው እንኳን ሊመልሱላቹህ ሌላ አጀንዳ ፈጠራ ወከባ ፈጠራ ውጋ በፍለጋ ላይ ተጠምደው ትናንት ያሉትን ጉዳዩን አይደለም ብዙ ማለታቸውን ራሱ ረስተውታል ሌላ የዛው አባዜ አለም ላይ እንደተንሳፈፉ ናቸው እረ እባካቹህ መሬት ላይ ውረዱ እና እርገጡ😂😂
✍️ያም ሆነ እሂ የድርጅትን መምሪያ ያላከበረ የእዝ የኮር የክፍለጦር የብርጌድን የተዋረድ መምሪያ ያልተቀበለ እንዲሁም አመራሮችን ያላከበረ አንጀኝነትን ቡድንተኝነትን ጎጠኝነትን ለመፍጠር የሚሞክርን በቁጥር ከ100 የማይበልጥ አፈንጋጭ ካለ የእርምት እርምጃ መውሰድ እና ተቋሙን መጠበቅ የድርጅቱ አላፊነት እና መብት መሆኑን መታወቅም አለበት እሂ ህግ እና መምሪያ አንጀኝነትን ቡድንተኝነትን አፈንጋጭነትን አለመጠርነፍን እና የፋኖን ትግል የሚያጠለሹ ወንጀል መስራትን የሚከላከል ለየትኛውም ድርጅት ለየትኛውም የፋኖ ዕዝ ይሰራል እየሰራም እየተተገበረም ይገኛል መሆንም አለበት።
ድል ለአማራ ፋኖ
ህልውናችን በተባበረ ከረንዳችን!!!
ልባሙ ፋኖ
በላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በተወሰደበት የማያዳግም እርምጃ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣በእሸት ክፍለ ጦርና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በላስታና ቡግና ሰንሰለታማ ተራሮች ሲቀጠቀጥ የዋለው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጦር በደረሰበት ሽንፈት ምላሽ ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ።
መነሻውን ከአይና ቡግና አድርጎ 05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ) ላይ ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም ንጋት አጥቢያ 12:00 ሰዓት እስከ ቀትር 8:00 ሰዓት ውጊያ የከፈተው የአገዛዙ ሰራዊት በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድና ሦስተኛና አራተኛ ሻለቃዎች በአይቆፍር ጨረሆና ሆዛ ሜዳ አቅጣጫ የመጣውን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል፤በአውደ ውጊያው 35 የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኛውን በአምቡላንስና ፓትሮል እየለቀመ ተመልሷል እንዲሁም ሰባት አባላቱ የአማራን ህዝብ አንወጋም በማለት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል።
በዚህም የተበሳጨው የጁላ ሰራዊት ቡግና ወረዳ የ08 ቀበሌ ንብ ዋርካና የ05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ)ን ህዝብ በመድፍ፣በአየር መቃወሚያ(ዙ-23) እና በሞርታር-120 ሲጨፈጭፍ ውሏል፤በዚህ ጭፍጨፋ ሦስት ንፁሃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ አራት የአርሶ አደር ቤቶች በዙ-23 ሲቃጠሉ ተጨማሪ ዘጠኝ ንፁሃን በከባድ ሁኔታ ቆስለው ህይወታቸው በህክምና እየተጠበቀ ይገኛል።
በጭፍጨፋው በከባድ መሳሪያ አንዲት የ60 ዓመት መነኩሴና የ15 ዓመት ልጃገረድ ለገና በዓልና ለንጉስ ላልይበላ ልደት ክብረ በዓል ወደ ላስታ ላሊበላ ይጓዙ የነበሩ እና ቅዱስ ሐርቤ ሚኒቃባ መንደር ከእናቷ ማዘል ላይ የነበረች እታቱ ሞላ ወዳይ የተባለች ህፃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ የህፃኗ እናትም ለህይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ:-
1ኛ. ደስታ ዋጋዬ የ28 ዓመት እናትና ልጆቿ መሰረት አበባው የ7 ዓመት ህፃን እንዲሁም ትዕግስት አበባው የ4 ዓመት ህፃን
2ኛ. ሐይማኖት ደማሙ የተባለች የ22 ዓመት ልጃገረድ
3ኛ. ወጋየሁ ባዬ የተባለች የ38 ዓመት እናት
4ኛ. እማሆይ አይቼሽ መልኬ የተባሉ የ75 ዓመት አዛውንት
5ኛ. መንበር አበባው የተባለ የ8 ዓመት ህፃን
6ኛ. ባየች ባዬ የተባለች የ28 ዓመት ወይዘሮ
7ኛ. ቄስ ካሳ ነጋሽ የተባሉ የ78 ዓመት የሐይማኖት አባት ቤተ-ክርስቲያን አገልግለው ሲወጡ እንዲሁም ህዝቡና አገልጋዩ በቅዱስ ሐርቤ ደብር ነዓኩቶልአብ ቤተ-ክርስቲያን እሁድ ሰንበትን እያከበረ በሚገኝበት በቤተ-ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንዳሉ በከባድ መሳሪያ ቆስለዋል ቤተ-ክርስቲያኑም ጉዳት አስተናግዷል።
በተያያዘም እሸት ክፍለ ጦርና ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ከላሊበላ ድብኮ ቀጠና በወሰዱበት የማያዳግም እርምጃ የአገዛዙ ሰራዊት በአፀፋው ንፁሃን ላይ መድፍ በመተኮስ ድብኮ ቀጠና ሁለት የአርሶ አደር ቤቶችን ያቃጠለ ሲሆን ስድስት ከብቶችም ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 26/ 2018 ዓ.ም
+2
#ትኩረት_የሚሻ_አሳዛኛ_መረጃ
እንደሚታወቀው በትናንትናው እለት በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ሽፋን ተሰጦት የነበረው የጣና ገዳማት ጉዳይ በጀግኖቹ ሻለቃ አቢ እና ሻለቃ ዳንኤል ሀብታሙ እየተመራ ሁለት የአገዛዙን የባህር ኃይል ኮማዶ ተብየ የጫኑ ተዋጊ ጀልባዎች ማስመጥ የቻሉ ሲሆን ገዳማቱንና ማህበረሰቡን ለመታደግ ሲባል የወገን ኃይል ከቀጠናው መውጣቱን የገለጽን ቢሆንም በዛሬ እለት ደግሞ የወገን ኃይል በሌለበት ሁኔታ በጣና ገዳማት ላይ ኃይለኛ የሆነ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተፈጽሟል።
ድብደባው የተፈጸመባቸው ገዳማት
1.ዳጋ እስጢፋኖስ
2.ወባ ኪዳነ-ምህረት
3.ደቅ አርሴማ
4.ኮታ ማርያም
5.ናርጋ ስላሴ
በተጨማሪ የደቅ ማህበረሰብ ጠላት "አንይህ" በማለት ወደ ተለያዩ አጎራባች ገዳማትና ቀበሌዎች በጀልባ የሸሸ ቢሆንም በእድሜ አጋፋ የሆኑና በአልጋ ቁራኛ በጽኑ በህመም ላይ የሚገኙትን እያሰቃየ ይገኛል።
የተዘጉ ቤቶችን እያፈራረሰ ሙሉ የቤ እቃ ዱቄትና ሊጥ ሳይቀር ጀልባ አስጠግቶ እየጫነ ስለሆነ ድምፅ ትሆኑ ዘንድ አማራዊ መልዕክታችን ነው።
የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከትና የባህርዳር ሀገረ ስብከት በገዳማቱ ፣ በመነኮሳቱ ፣ በደቅ ደሴት ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ባለማውገዛችሁ በአባትነታችሁ አፍረናል።
ድል ለአማራ ፋኖ
አዲስ ትውልድ ፣ አድስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ
ፋኖ ዳዊት ሽፈራው
ሰበር ዜና!
ጎንደር ሪፈራር ሆስቲታል ህክምና ላይ የነበሩ 37 የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ሀይሎች መሞታቸው ተረጋገጠ ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሰሞኑን በአጅሬ ጃኖራ ፣ በሚጦ ፣ ጦሃ ቀበሌ እና በሌሎች ቦታዎች በተደረጉ አውደ ውጊያዎች የአገዛዙ ብልፅግና ሆድ አደሮች በርካቶች በሞት ሲሸኙ የተቀሩት ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ቁስለኛ ሁነው በቀጠናው ያሉ ሆስፒታሎችን እያጨናነቁ ይገኛል ።በቀጠናው ከሚገኙት ሆስፒታሎች መካከል አንዱ በሆነው ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና ከገቡት ቁስለኞች መካከል ዛሬ ጣት የሞቱትን ሶስት የሚኒሻ አባላትን ጨምሮ ከ37 በላይ የሚሆን የአገዛዙ ጡት ቆራጭ ሀይል አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እስትንፋሳቸው መቋረጡ ተረጋግጧል።
አንድ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የሆስፒታሉ ዶክተር ብዙ ጊዜ ለህክምና ከሚመጡት ቁስለኞች አብዛኛዎቹ ይሞታሉ ምክንያቱ ደግሞ ቁስለኞች ከአውደ ውጊያ ግንባሮች ሆስፒታል ሳይደርሱ ብዙ ደም ስለሚፈሳቸው እና በእነሱ የህክምና ሙያተኞች የሚሰጧቸው የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በቂ አለመሆኑ ተዳምሮ ለሞት ያበቃቸዋል ይላሉ ። አሁንም ጎንደር ሪፈራል ሆስቲታል በቁስለኞች በመሞላቱ ዛሬ ተህሳስ 26/2018 ዓ/ም 29 ቁስለኞ ወደ አይራ ሆስፒታል ተልከዋል ከ10 በላይ የሚሆኑት ቁስለኞች ደግሞ አሁንም ማንቂያ ክፍል እንደሚገኙ ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ስጋታቸውን ጠቁመዋል ።
ዶክተሩ የጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ሙያተኞች ቁስለኞቹ እንደሚመሞቱ እያወቁ በመከላከያ ሰራዊቱ ጫና የተነሳ በርካታ መዳህኒቶችን ለሟቾች እየባከኑ በመሆኑ ሌሎች በህይዎት የሚድኑ መደበኛ ታካሚዎችን በመዳህኒት እጥረት እና በስራ ጫና የተነሳ ማዳን አልቻልነም ይላሉ ።
በመጨረሻም ዶክተሩ የአገዛዙ ሀይሎች የህክምና ጉዳይ በሆስፒታሉ አስተዳደሮች ውሳኔ ካልተሰጠበት በቅርቡ ሆስፒታሉ በመዳህኒት እጥረት ሙሉ በሙሉ መደበኛ ስራው ሊቋረጥ እንደሚችል ጠቁመው ይህ ድርጊት ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ጥሩ ግንኙነት ሊያሻክረው እንደሚችል ስጋታቸውን ጠቁመዋል።
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለጤናው ዘርፍ የምትሰጡት እርዳታ እና ድጋፍ የት እየደረሰ ለምን አገልግሎት እየዋለ እንደሆነ በአግባቡ እንድትመረምሩ እና ለህብረተሰቡ ጤና እንድትጨነቁ ስንል ማሳሰብ እንወዳለን ።
በተያያዘ ዜና ለስብሰባ የመጣው የአገዛዙ አመራር ስብሰባውን አቋርጦ ፈረጠጠ።
የጎንደር ከተማ አንድ አካል በሆነችው ጠዳ ከተማ እግዚአራብ ቤተክርስቲያን ላይ የነበሩ ምዕመናንን ፋኖን ምረሽ እንድታስገቡ ብሎ ለማስፈራራት እና ለማሰር ዛሬ ተህሳስ 26/2018 ዓ/ም የመጣው የአገዛዙ ዘራፊ አመራር በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቃኘው ብርጌድ አባላት በተከፈተበት ተኩስ ስብሰባውን አቋርጦ እስኪያልበው ድረስ ፈርጥጦ መገጭ ግድብ ገብቷል።
የቃኘው ብርጌድ አባላት ለምዕመናን ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርገዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!
አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም
ከጎንደር ሰማይ ስር
አማራዎች ነን የዘሜ ልጆች!! እሳት በሚያዘንበው የጎጃም ምድር 25ኛ ክ/ጦር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሳለች።
206ኛ ኮር ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም
===================================
የአረመኔው ሰራዊት በጠና መልኩ የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25ኛ/32ኛ/57ኛ ክፍለጦሮችን በማሰማራት ወደጮቄ ተራራ ለመውጣት ባደረገው እንቅስቃሴ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ታህሳስ 24እና 25 ባደረገው ትንቅንቅ የአረመኔው ሰራዊት 25ኛ ክፍለ/ጦር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሳለች።
የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን ለማደናቀፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን በመጨረሻም በእነ ሞት አይፈሬዎች ምድር ጎጃም ድባቅ ተመቷል።
ለሶስት ቀናት በወሰደው ምርኮኛ እና ትጥቅ የመልቀም ሒደቱ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን 206ኛ ኮር
3 ዲሽቃ
2 ሞርተር
8 ብሬን
5 ስናይፐር
230 ክላሽ
2 መቶ አለቃዎችን ጨምሮ 61የአረመኔው ሰራዊት ሲማረኩ ፣2 ሻለቃ አዛዦች ፣5(አምስት) መቶ አለቃዎች እና 420 የአረመኔው ሰራዊት ተደምስሰው ከ137 በላይ የጠላት ኃይል ቁስለኛ ሁነዋል።
32ኛ/57ኛ እና 25ኛ ክ/ጦርን አቀናጅቶ ማጥቃት ለማድረግ አቅዶ የነበረው የጀነራል ሶፊያ ማህመድ 602ኛ ኮር በቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ተደቅድቆ በየ ጫካው ሲለቀም ውሏል። የደረሰበትን ምት መቋቋም አቅቶት ብትንትኑ የወጣው የአረመኔው ሰራዊት 4ኛውን ዲሽቃ በ109ኛ ኮር የተማረከ ሲሆን ማህበረሰቡ ለሶስት ቀናት የጠላትን አስክሬን እየሰበሰበ እየቀበረ ይገኛል።
አንድም አስክሬን ሳያነሳ ብትንትኑ ወጦ በየ ጫካው ወድቆ እየተገኘ የሚገኘው የመጄር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን 25ኛ ክ/ጦር እስከ አሁን በአለው ተጨባጭ ሁኔታ 618 የሰው ኃይሉ ከጥቅም ውጭ ሁኗል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
