ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
📈 Analytical overview of Telegram channel ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
Channel ስፑትኒክ ኢትዮጵያ (@sputnik_ethiopia) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 51 990 subscribers, ranking 5 059 in the News & Media category and 644 in the Ethiopia region.
📊 Audience metrics and dynamics
Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 51 990 subscribers.
According to the latest data from 08 September, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 1 783 over the last 30 days and by 24 over the last 24 hours, overall reach remains high.
- Verification status: Not verified
- Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 4.32%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 3.67% reactions from the total number of subscribers.
- Post reach: On average, each post receives 2 247 views. Within the first day, a publication typically gains 1 906 views.
- Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 6.
📝 Description and content policy
The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“ያልተነገረውን እንነግርዎታለን
ስለ አፍሪካ በእንግሊዘኛ ቋንቋ፤ @sputnik_africa”
Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 09 September, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the News & Media category.
Data loading in progress...
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 09 September | +7 | |||
| 08 September | +71 | |||
| 07 September | +66 | |||
| 06 September | +34 | |||
| 05 September | +97 | |||
| 04 September | +117 | |||
| 03 September | +187 | |||
| 02 September | +71 | |||
| 01 September | +126 |
| 2 | የአዲስ ዓመት በዓል በመብራት እጦት እንዳይደበዝዝ ዝግጅት አድርጊያለሁ ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለፀ
📹 ተቋሙ የበዓሉ ድባብ እና እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል ምን ሠርቷል? 👇
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 654 |
| 3 | በ2018 ዓ.ም ያጣናቸው የኢትዮጵያ አንጸባራቂ ከዋክብት
በሥራቸው አሻራቸውን ለዘላለም ያሳረፉትን ከዋክብት እናስታውስዎ።
በ2018 ዓ.ም ያጣናቸው እና ልናስታውሳቸው የሚገቡ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች እነማን ናቸው? በአስተያየትዎ ያስታውሷቸው 👇
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 622 |
| 4 | ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታዎቹን በጁባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከሱዳን እንዲሁም ከሴኔጋል ጋር በባሕር ዳር ስታዲየም ያደርጋል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 579 |
| 5 | የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመመከት የሰው ኃይል፣ ጊዜና ሌሎች ሀብቶቻችንን እያበረከትን እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል - የአየር ንብረት ፍትሕ ባለሙያ
ባደጉት ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የሚደረጉ የገንዘብ ወጪዎች አፍሪካ ላይ እዳ ማባባስ የለበትም ሲሉ በፓን አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትሕ ትብብር የአኅጉራዊ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የሥነ-ምግባርና የእርቅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግሬሰ አምፖማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለማስወገድ ያገኘነውን ድጋፍ መልሰን እንድንከፍል የሚገፋፋ ሁኔታ ውስጥ መገባት የለብንም።”
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 582 |
| 6 | No text... | 539 |
| 7 | የጥቁር ባሕር የእህል ስምምነት የምዕራባውያን ኮርፖሬሽኖችን ለማበልፀግ ብቻ ያገለገለ ነበር - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
የተቸገሩ ሀገራትን የመርዳት ሽፋን በማድረግ ለምዕራባውያን ጥቅም ብቻ ይሠራ ወደነበረው ስምምነት ሩሲያ እንደማትመለስ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል።
"እነሱ [ምዕራባውያን] ርካሽ የግብርና ምርቶችን ከኪየቭ በመግዛት፤ ለራሳቸው የማቀናበሪያ ኢንዱስትሪዎች በጥሬ ዕቃነት ካዋሉ በኋላ፤ እናስብላቸዋለን ለሚሏቸው ችግረኛ አፍሪካውያን ጭምር በውድ ዋጋ መልሰው ሸጠውላቸዋል" ሲሉ አክለዋል።
🇷🇺 ሞስኮ በጥቁር ባሕር የእህል ስምምነት ስር ያሉባትን ግዴታዎች በጥብቅና በብቃት እንደተወጣች ዛካሮቫ አስምረዋል።
ℹ️ ሩሲያ፤ ድንጋጌዎች አልተፈጸሙም እንዲሁም ምዕራባውያን ሀገራት ገብተውት የነበረውን ቃል አልጠበቁም ማለቷን ተከትሎ ስምምነቱ እ.አ.አ ሐምሌ 2023 ተቋርጧል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 523 |
| 8 | በዓለም መድረክ የኢትዮጵያን ስም ያስጠራችዉ ሩት ይርጋለም ተመለሰች
ሩት፤ በቪየትናም በተካሄደው 73ኛው የሚስ ወርልድ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን አስተዋውቃለች።
📹 ቀሪውን ከስፑትኒክ ኢትዮጵያ ቪዲዮ ይከታተሉ 👆
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 729 |
| 9 | አፍሪካን በትክክለኛ ስፋቷ፣ ጥንካሬዋ እና አቅሟ ለማየት ጊዜው አሁን ነው - የአፍሪካ ኅበረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
🌍 መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፤ የአፍሪካ ኅብረት ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት አፍሪካውያን እና አፍሪካውያን ዳያስፖራዎች ለፓን-አፍሪካኒዝም፣ ለአንድነት እና ለአጋርነት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያድሱ ጥሪ አቅርበዋል።
🔙 እ.አ.አ መስከረም 9 የሚከበረው የአፍሪካ ኅብረት ቀን፤ የአፍሪካ መሪዎች አኅጉራዊ ውህደትን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፋዊ ድምፅ ለማጠናከር ኅብረቱን ለመመስረት ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበትን የ1999 የሰርጥ መግለጫ ለማስታወስ የሚከበር ነው።
🎉 ቀኑ ዘንድሮ የሚከበረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን ትክክለኛ ስፋት በትክክል የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ ጅምር ካጸደቀ በኋላ ነው።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 750 |
| 10 | ሩሲያ በኤል አላሜይን ዓለም አቀፍ የአየር ትዕይንት ላይ የአየር መከላከያ ሥርዓቷን አስተዋወቀች - ዘጋቢ
🇷🇺 የሩሲያው ቲኬቢ-1167 "ባይሰን" ሥርዓት ድሮኖችን ለመመከት እና ወሳኝ ተቋማትን እንዲሁም መሠረተ ልማቶችን ከአየር ላይ ከሚሰነዘሩ አደጋዎች ለመጠበቅ የተነደፈ ነው።
ሥርዓቱ የሚከተሉትን ይጠቀማል፦
▪️ በ360° አግድም እና እስከ 50° የከፍታ ማዕዘን መሸፈን የሚችል ራዳር፣
▪️ የቴሌቪዥን እና የሙቀት ምስል መስመሮች ያሉት ኦፕትሮኒክ ሥርዓት፣
▪️ አውቶማቲክ የዒላማ መከታተያ፣
▪️ የሌዘር ርቀት መለኪያ።
በተጨማሪም እያንዳንዱ መጫኛ አራት የፒኬ/ፒኬኤም 7.62 ሚሜ መትረየሶች የተገጠሙለት ሲሆን ለአንድ መትረየስ እስከ 2,400 የጥይት ማርከሻዎች አሉት። ሥርዓቱ በአብዛኛው አውቶማቲክ ሲሆን ኦፕሬተሩ በዋናነት የመተኮስ ውሳኔ የመስጠት እና ትዕዛዝ የማስተላለፍ ሥራ ብቻ ይሠራል። በፍጥነት ለመሰማራት እና ቦታ ለመቀያየር በተሽከርካሪዎች ላይ ሊጫን ይችላል።
ዒላማ የመለየት እና የመምታት አቅም፦
⚡️ ቋሚ ክንፍ ያላቸው ድሮኖች፦ ከ250 እስከ 3,500 ሜትር ርቀት መለየት፤ እስከ 400 ሜትር ርቀት ላይ መምታት፣
⚡️ ብዙ ክንፍ ያላቸው ድሮኖች፦ ከ250 እስከ 800 ሜትር ርቀት መለየት፣ እስከ 250 ሜትር ርቀት ላይ መምታት።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 725 |
| 11 | #viral | 🚴 ወርቃማውን የመንገድ ሕግ አይዘንጉ!
አቅጣጫ ከመቀየርዎ በፊት ሁልጊዜ ግራ፣ ቀኝና ኋላዎን መመልክት ባለመዘንጋት፤ እራሶን ከተመሳሳይ አደጋ ይጠብቁ፡፡
ከማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምሥል
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 663 |
| 12 | አፍሪካ የተፈጥሮ ሃብቶቿን መቆጣጠር መጀመር አለባት - የአየር ንብረት ባለሙያ
ለአየር ንብረት ለውጥ ሽግግር የሚሆኑ ማዕድናት በአኅጉሪቱ በሰፊው ቢገኙም፤ አፍሪካውያን ቁጥጥር ማድረግና እሴት መጨመር ላይ በቂ ሥራ እየሠሩ አይደለም ሲሉ የፓን አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትሕ ትብብር ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሚቲካ ምዌንዳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“ሀብቶቻችንን በሚገባ መቆጣጠር እንዳለብን በአዲስ አበባና በናይሮቢ ስምምነቶች ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ምክንያቱም ይህንን ሽግግር እየመራን ያለነው እኛ ነን፤ ወደ የቀደመው ዘመን መመለስ አንፈልግም” ብለዋል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 769 |
| 13 | ለኪየቭ አገዛዝ ድጋፍ የሚሰጡ አካላት በሩሲያ የአየር ትራፊክ ላይ በሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች ቀጥተኛ ተባባሪዎች ናቸው - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
የማሪያ ዛካሮቫ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
▪️ የኪየቭ የአየር ማስፈራሪያ የጦር ሜዳን ሽንፈት ለማካካስ እንዲሁም በሩሲያ የኢኮኖሚ እና የትራንስፖርት እክል ለመጣል የሚደረግ ሙከራ ቢሆንም ሩሲያን ሊሰብራት አይችልም፣
▪️ በዜና ማሰራጫዎች በሰፊው እየተነገረ ያለው የእህል ስምምነትን እንደገና የመጀመር ሀሳብን ጨምሮ ሩሲያ ከምዕራባውያን ጋር በሚደረጉ ማናቸውም ስምምነቶች ላይ እምነት የላትም፣
▪️ ሩሲያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በአርክቲክ ቀጣና የሚከሰቱ ስጋቶችን ለማቃለል እና ለማስወገድ ሙሉ ወታደራዊ-ቴክኒካዊ አማራጮችን ለመጠቀም ዝግጁ ናት፣
▪️ ሩሲያ ስለ ቡቻ የሀሰት ድራማ ላቀረበቻቸው ጥያቄዎች ከአሁኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊም ሆነ ከቀጣዩ ኃላፊ ግልጽ ምላሽ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ትቀጥላለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 792 |
| 14 | No text... | 811 |
| 15 | የአዲስ አበባ ታክሲ ሰልፍ ምሬት የወለደው መፍትሄ
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ በፀሐይ ብርሃን ብቻ እየተንሸራሸረች ሕዝቡን ጉድ ያስባለችውን “ዝናሽ አሰፋ”።
📹ተጨማሪውን ከስፑትኒክ ኢትዮጵያ ቪዲዮ ያገኛሉ 👆
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 1 033 |
| 16 | ከዩክሬን የሰላም ስምምነት ጋር ተያይዞ እስካሁን የተቀመጠ ፍኖተ ካርታ የለም፤ ነገር ግን ውይይቱን ለመቀጠል የሚያስችል ፖለቲካዊ ፍላጎት አለ - ክሬምሊን
የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት የሚያስችል ይፋዊ የሰላም ፍኖተ ካርታ እስካሁን እንዳልተዘጋጀ፤ ነገር ግን የሦስትዮሽ ድርድሩን እንደገና ለመጀመር የሚያስችል መሠረታዊ ፖለቲካዊ ፍላጎት እንዳለ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገልጸዋል።
አክለውም ክሬምሊን በዩክሬን ጉዳይ ዙሪያ የሚደረገው የሦስትዮሽ ውይይት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደገና ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠብቅ ተናግረዋል።
ሌሎች መግለጫዎች
🔶 በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚደረገው የጦር እስረኞች ልውውጥ ሥራ ቀጥሏል፣
🔶 የሩሲያ እና አሜሪካ የእስረኞች ልውውጥ ውይይት በከፍተኛ አመራር ደረጃ ጭምር በሂደት ላይ ይገኛል፣
🔶 የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ለቬትናም አቻቸው ቶ ላም የሊኦ ቶልስቶይ ዓለም አቀፍ የሰላም ሽልማት በክሬምሊን ያበረክቱላቸዋል፣
🔶 ሩሲያ ከሃንጋሪ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ዝግጁ ስትሆን፤ በሁለትዮሽ ትብብር የተገኘውን ጠቃሚ ልምድ ለመሸርሸር አትሻም።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 1 052 |
| 17 | ዚምቧቤ የንግድ ሥራ ሂደትን ለማቃለል ያለሙ 291 ማሻሻያዎችን ተግባራዊ አደረገች - የሀገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን
🚫 የሀገሪቱ መንግሥት የንግድ ከብቶች ዝውውር ፈቃድ ክፍያዎችን፣ የነዳጅ ማከማቻ ምዝገባ ሰርተፊኬቶችን፣ የከብት ግብሮችን እና የዓሣ ነጋዴዎች ፈቃድን ማስቀረትን ጨምሮ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።
🇿🇼 የተሻሻሉ የባንክ አገልግሎት ክፍያዎች እና የፋይናንስ ዘርፍ ተመኖችም እየተተገበሩ የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ማሻሻያዎች ሀገሪቱ ከዓለም ባንክ "ተጋላጭ ሀገራት" ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን የመረጃ ሚኒስቴሩ ዠሙ ሶዳ አስታውቀዋል።
ከሚያስፈልጋቸው ጥሬ ዕቃ ቢያንስ 40 በመቶ ያህሉን ከሀገር ውስጥ ለሚያቀርቡ ኩባንያዎች የበቆሎ ማስመጫ ታሪፍ ወደ 15 ዶላር በቶን ዝቅ የተደረገ ሲሆን ይህንን መመዘኛ ለማያሟሉ ኩባንያዎች ደግሞ በቶን 25 ዶላር እንዲከፍሉ መደረጉን የግብርና ግብይት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሊስ ማፕፊዛ ገልጸዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 979 |
| 18 | ኢትዮጵያ ከፊት ለፊቷ የተደቀነውን የኤል ኒኖ አደጋ ለመቋቋም የአየር ንብረት ትንበያዎችን መሠረት ያደረገ ጠንካራ የጤና ስርዓት መገንባት ይገባታል ተባለ
የአየር ጠባይ ለውጥ ከጤና ጋር የጠበቀ ቁርኝት አለው ያሉት የኢትዮጵያ ሜትዮሮሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈጠነ ተሾመ፤ “የአየር ጠባይ መለዋወጥ በውሀ ወለድና በሌሎች በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ስርጭት እንዲሁም በግብርና ምርቶች ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ያሳድራል” ብለዋል።
📌 ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት ትኩረቱን የአየር ጠባይ ትንበያዎችን ወደ እውነተኛ የጤና እና ሥርዓተ-ምግብ እርምጃዎች መቀየር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ አድርጎ፤ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተካሄደ ዐውደ ጥናት ላይ እንደሆነ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግቧል።
🔊 የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በበኩላቸው፤ የኢንስቲትዩቱ የምርምር ቡድኖች በአየር ንብረት፣ በአየር ጥራት እና በፖሊሲ ውጤቶች ላይ የሚታዩ ውስብስብ ሁኔታዎችን እየገመገሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ኢኒስቲትዩቱ መረጃዎቹን ወደ ፖሊሲና ተግባራዊ እርምጃዎች ለመቀየር የሚያስችል "የአየር ንብረት እና ጤና አስተዳደር የእውቀት ማዕከል" ማቋቋሙንም ዶ/ር መሳይ አስታውቀዋል።
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 979 |
| 19 | የሩሲያ እና የቬትናም ንግድ በእጥፍ አድጓል - ፑቲን
🇷🇺🇻🇳 ፑቲን፤ የሩሲያ እና የቬትናም ትብብር በባሕል፣ በትምህርት እና በደህንነት ዘርፎች ላይ የተዘረጋ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሚፈረሙ አዳዲስ ሰነዶች “ለልዩ ስትራቴጂያዊ ግንኙነታችን ትልቅ መሠረት” የሚጥሉ ናቸው ብለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X | 916 |
| 20 | የስፑትኒክ ኢትዮጵያ መተግበሪያን አሁን በአንድሮይድ ማውረድ ይችላሉ።
ለአጠቃቀም በጣም ቀላል በሆነው መተግበሪያ የሚከተሉትን ያገኛሉ፦
🟠ቀላል አሰሳ
🟠ትኩስ የኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች
🟠ልዩ ቃለመጠይቆች
🟠ምስላዊ መረጃዎች እና ቪዲዮዎች
🟠የወደዱትን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ማጋራት
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡-
👉 APK ፋይል ሊንክ
👉 Galaxy Store
👉 GetApps
👉 AppGallery
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
#social | 901 |
