Eth-cryptopia
Open in Telegram
✔️Future millionaire Welcome to Eth-Cryptopia🔥 በዚ ቻናል የተለያዩ Airdrops ከብዙ እውቀት ጋር አብረን የምንሰራበት ቤት ነው። ለማንኛውን ጥያቄ ወይም ውይይት ግሩፓችንን መቀላቀል ትችላላቹ @EthCryptopia_Group Buy ads: https://telega.io/c/EthCryptopia
Show more4 893
Subscribers
-624 hours
-247 days
-2630 days
Posts Archive
4 893
BlackRock 2050 $BTC ወደ Coinbase ከ 8 ሰአት በፊት ልኳል በ አጠቃላይ ወደ $189M Worth የሚያደርግ $BTC በ $92.3K price የሸጡ ይመስላል
1,581 $ETH ደግሞ ገዝተዋል ወደ $5.2M worth የሚያደርግ ከ አንድ ሰአት በፊት
4 893
Repost from Event Addis Media
📌አሻም ቴሌቪዥን ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ
አሻም ቴሌቪዥን ስራውን ለመቀጠል አቅም ስለሌላው ሙሉ በሙሉ ስርጭቱን እንዳቋረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ጣቢያው በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭቱን ማቆሙን ገልጿል።
አሻም ቴሌቪዥን ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉ ለሁሉም የግልና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ጭምር በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።
አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ሲያሰራጭ ቆይቷል።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4 893
Repost from Event Addis Media
ቲክቶከሮቹ በአፈንጋጮች አለባበሳቸው ታሰሩ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አባሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በሀገራችን አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች:-
1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣
2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣
3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣
4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና
5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።
©️ የፌዴራል ፖሊስ
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4 893
Repost from Watcher Guru
+1
BREAKING: Michael Saylor's 'Strategy' buys 10,624 Bitcoin worth $962 million.
@WatcherGuru
4 893
+2
በዚ ሳምንት ብቻ እግር ኳስ እብደት እንደሆነ ያየንብቸው ጨዋታዎች😅
ከነዚ ውጪ Leeds Vs Chelsea + Newcastle Vs Tottenham 🔥
4 893
ትሬደር ከሆናችሁ ወይም ለመሆን ካሰባችሁ፣ 90 በመቶው የትሬዲንግ ስራ በ Psychology ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ታውቃላችሁ💡
ዋናው ቁምነገር የሚወሰነው በምትወስናቸው ውሳኔዎች እና ከራሳችሁ አእምሮ ጋር በምታደርጉት ትግል ነው🧠፤ በኢትዮጵያ ይህንን ወሳኝ ክህሎት በትክክል የሚያስተምር ኮርስ ወይም ግልሰብ እስካሁን አልነበረም📚
አሁን ግን አንጋፋው የክሪፕቶ OG ናቲ እና ላይቭ ትሬደር 'Trade Insight' ያዘጋጁት አዲስ የ30 ቀናት የሳይኮሎጂ ስልጠና መጥቷል🚀
በዚህ ሊንክ ገብታችሁ መቀላቀል ትችላለህ!
🔗 https://t.me/ICE_Ethiopia
ጥሩ እውቀት ይዛችሁ እንደምትወጡ አልጠራጠርም 🙌🏼@EthCryptopia
4 893
❗️የ ጥንቃቄ መልዕክት
✔️በተለምዶ ሿሿ ብለን የምጠራው ሙሉ ታክሲ ሰው ይዞ አንድ ሰው የጎደለው በማስመሰል አንድ ሰውን ብቻ ጭነው ያደርጉት የነበረው ስርቆት አሁን መልኩን ቀይሮ መጥቷል!ይሄንን ዘዴ አብዛኛው ሰው እያወቀ ስለመጣ አሁን ደግሞ ዘዴ ቀይረው አለን ብለዋል (በ ቴክኖሎጂው ዘርፍ System Update በሉት 😁)። አሁን ላይ እንደመጀመርያው 1 ሰው የጎደለው ታክሲ ሳይሆን የሚያጋጥማቹ ከ 5 እስከ 6 ከፍ ሲልም ባዶ ታክሲ ሁላ ሊሆን ይችላል ከዛ ታርጌት ያደረጉትን ሰው እንዳስገቡ ሌሎች ግብረ አበሮች ደግሞ እናንተን ተከትለው ይገባሉ በዚ መሃል ምንም የማያውቅ ሁለት ወይንም 3 ሰው ሊገባ ይችላል እነዛ ሰዎች ተጠቂ ይሆናሉ ማለት ነው። አሁን ላይ ከምታስቡት በላይ በጣም የተስፋፋ ነገር ነው ተመሳሳይ መኪና የተለያዩ ቦታዎች የዚ አይነት ተግባሮችን ሲያደርግ ቆይቶ አመሻሹ ላይ አጋጣሚ ተይዘውም እይየው ነበር ከምን ግዜም በላይ Alert ሆናቹ ራሳቹን ጠብቁ እንደዚ አይነት ሁኔታ ውስጥ ስትሆኑ አካባቢያቹ ላይ ያሉትንም ሰዎች ለማየት ሞክሩ 🙌🏾
✔️ሁለተኛው ሿሿ የሚሰራው እንደዚ በ transport ዘርፉ ላይ ሲሆን እቺ ለየት የሚያደርጋት ህግ አስከባሪ በሚባሉ አካላት መሰራቱ ነው😅
🔑ይሄኛው ደግሞ አንድ ሹፌር አጋጣሚ ሆኖ በሚያሽከረክርበት ሰአት የ ህግ ጥሰት አድርሶ ይያዛል በመቀጠል ህግ አስከባሪውም አካል በዚ በዚ ምክንያት እከስካለው ይላል ክሱን የሚከፈለው ነገሮችን ለማቅለል በሚል በ ቴሌብር ከሆነ ሰነባብቷል።አክፋፈሉም ህግ እስከባሪው System ላይ ስልክ ቁጥር ያስገባና የቅጣቱን መጠን ፅፎ Send ሲል ቀጥታ ወደሚቀጣው ሰው ስልክ Confirmation Box ይመጣል ያ ግለሰብ Code እስገብቶ Confirm ሲያደርግ በቀጥታ ወደ System ይገባና ሰውየው በዚ መልክ ቅጣቱን ይከፍላል ማለት ነው።ነገር ግን ህግ አስከባሪው ይሄንን Process ላለማንዛዛት በሚል መንጃ ፍቃዳቹን Photo ያነሳውና Confirmation box ሲመጣላቹ Cofirm ታደርጋላቹ አሁን ሂዱ ይላል ነገር ግን እናንተ ቀጥታ መንገድ Transport ሄዳቹ እስካልጠየቃቹ ድረስ ምንም አይነት የቅጣት Payment ስልካቹ ላይ Confirm እንድታደርጉ አይመጣላቹም።ይሄ ደግሞ ጉዳቱ ቅጣቱን ያልከፈላቹበት ቀን በረዘመ ቁጥር የሚወልድ የብር መጠን ስላለ ነው እብዛኛው ሰው በመዘናጋት ወይም ባለማወቅ ከ 3 እስከ 5 እጥፍ ድረስ ወልዶ እየጠበቀው ነው ፈሚገኘው ስለዚ ጥንቃቄ አድርጉ።😊ይሄንን ነገር ከምን አንፃር ትመለከቱታላቹ የ System ችግር ወይንስ ገንዘብ መሰብሰብያ መንገድ?
🦋#Share🦋
👩💻 @ethio_techs 👨💻 @ethio_techs 👩💻
