cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Group of unity

You can use this for indulgence. If you use this for education , you will enhance your knowledge&skill.

Show more
Ethiopia12 832The language is not specifiedEducation109 197
Advertising posts
214
Subscribers
+124 hours
No data7 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from ATC NEWS
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አመራረጥ አዲስ መመሪያ በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሃብት ብክነት እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደገለፁት፤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በመላክ ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉባቸውን ችግሮች መጠናቱን ገልፀዋል፡፡ "ዩኒቨርሲቲዎች የብዙ ደሃ ሕዝብ ሃብት የሚፈስባቸው ቦታዎች ናቸው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ስለዚህ ተቋማቱ በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨመላለቀ አስተዳደር ሊኖራቸው አይገባም ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በዋናነት የተማረ የሰው ኃይል ከማምረት ይልቅ፣ ህንጻ ማምረት ላይ የተሰማሩ ተቋማት እንደነበሩ ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ "ዩኒቨርሲቲዎች የሚታለቡ የጥገት ላሞች ናቸው" የሚለው የአንዳንድ ግለሰቦች አባባል አሁን ላይ አይሠራም ብለዋል፡፡ ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የሚያዝ የገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ኃላፊዎቹም በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩንም አክለዋል፡፡ ይህንን አሰራር በመከተል "ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ አመራሮችን በሙሉ እንቀይራለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
Repost from ATC NEWS
የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምርና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ ተገምግሟል፡፡ የበጀት ዝግጅቱ ዋና ትኩረት የሀገሪቱን ሀብትና የመንግስትን በጀት በዕቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል። አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችና የስራ ሀላፊዎችም በጀት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው በሚቀጥለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ጠቅሰዋል። ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት ዕቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጥቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ ማሳሰባቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡ ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠው የፈተና መርሃ ግብር የሚከተለው መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳውቋል፡፡ ትንሽ ሻል የሚለውን ምስል ኮሜንት ላይ አስቀምጠንዋል፡፡
Show all...
👍 1
💬 Anthropology NEW final exams collection. 1.Bahirdar university 2. Adiss ababa 3. Wolkite 4. Diredawa 5. AAstu 6. 40Minch 7. Jimma 8. Hawassa 9. injibara 10. DebreMarkos + And others.. @AAUNEWS1
Show all...