cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ATC NEWS

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

Show more
Advertising posts
116 339Subscribers
-724 hours
+2867 days
+45430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተነገረ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነ ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦን ላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ብለዋል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኛች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
#HawassaUniversity ለ2016 ዓ.ም ተመራቂ የማታ እና የእረፍት ቀናት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ፤ የከፍተኛ ትምህርት መወጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ከትምህርት ሚኒስቴር በተገለጸልን መሰረት የማታ እና የእረፍት ቀናት ተማሪዎች በሙሉ 500.00 (አምስት መቶ) እንዲከፍሉ በተቀመጠው መሰረት የ2016 ዓ.ም ተመራቂ የማታ እና የእረፍት ቀናት ተማሪዎችም እስከ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከዚህ በፊት ክፍያዎችን በምትከፍሉበት በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢ አካውንት Gov (1128) 1000013481788 ገቢ እያደረጋችሁ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡ #ዩንቨርስቲው ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
Repost from SKET TRAVEL AGENCY
Are you MECHANICAL, ELECTRICAL, ENVIRONMENTAL or CIVIL ENGINEER ? Do you want to pursue your masters degree in Italy🇮🇹 ? ✅low gpa possible ✅all engineering ✅computer science ✅no proficiency test ✈️no PRE PAYMENT required 🔵Required documents 🔵 ✔️Passport(national id ) ✔️original degree(Temporary) ✔️student copy ✔️recommendation letter ✔️medium of instruction (from the university) ✔️3*4 or DV format photo ☎️ contact us at : @consultfrit 🧡 🌐 https://t.me/consultfrit 🧡 ✈️ 0972859680💠 ✈️ 0934155601💠 https://t.me/studyinitalyconsultant
Show all...
ውድ ተማሪዎች ፣ Learnethiopia advanced ኮርስ በቅናሽ ዋጋ እየሰጠ ይገኛል። በሁሉም ኮርሶቻችን ላይ ለተወሰነ ጊዜ የምቆይ የ80% ቅናሽ እየሰጠን ነው። ዋጋው ከመጨመሩ በፊት ይህንን ቅናሽ ይጠቀሙ። ለድጋፍ፣ እኛን ማግኘት ይችላሉ። ድህረ ገጽ ፡ www.learnethiopia.com ቴሌግራም ድጋፍ ፡ https://t.me/LearnethiopiaCustomerSupport በኢሜል ይላኩልን [email protected] direct contact ፡ +251986258847 ለሁሉም አዳዲስ ዜናዎች እና ይዘቶች ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ይቀላቀሉን። የቴሌግራም ቻናል ፡ https://t.me/LearnEthiopiaDotCom የዩቲዩብ ቻናል ፡ https://www.youtube.com/channel/UChWimtu1bpJEjuzLdohQc1A ትክቶክ ፡ https://www.tiktok.com/@learnethiopia.com Facebook ፡ https://www.facebook.com/ethioexitexam?mibextid=ZbWKwL LearnEthiopia ለቀጣዩ ፈተናዎች መልካሙን ሁሉ ይመኛል። Thanks and regards Team Learnethiopia
Show all...
Are you looking for a place to order from shein?? RUHIYE ONLINE STORE is here for you ◽️Dm us to order anything from shein.com🛍 🇪🇹 ◽️telegram channel https://t.me/ruhiye_online_store ◽️contact: @Rina_abdurahman ◽️No pre payment ◽️Unless sensitive items 🔸Free delivery 🚚 ◽️To addis ababa: 📍bole ( skylight, dembal) 📍torhiloch, 📍lideta, 📍Mexico, 📍Stadium and 📍Adama ◽️Delivery time within 2-4 weeks ◽️follow our tiktok account https://www.tiktok.com/@ruhiye_1online_store?_t=8lnPa8isCgQ&_r=1 ◽️Our priority is our families satisfaction !!!
Show all...
#ይጠንቀቁ "ሰርተፊኬት የሚያሰጡ ነጻ የኦንላይን ስልጠና " የሚሉ ማስታወቂያዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወሩ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ማስታወቂያዎቹ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴርን ስም ይጠቅሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሐሰተኛ መሆናቸውን ዩኒቨርሲዎቹ አረጋግጠዋል፡፡ "የተቋሜን ስም በመጠቀም የሚፈፀም የማጭበርበር ተግባር ሰለሆነ የሚመለከተው ሁሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባለው" ብሏል መቐለ ዩኒቨርሲቲ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ እንደደነበር አይዘነጋም፡፡ "በተለያዩ ድረ-ገጾች እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ስም እና አርማ በመጠቀም ከሚተላለፉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቁ" ብሏል ዩኒቨርሲቲው፡፡ ©tikvahuniversity ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
ለኢንትራንስ ፈተና Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ዝግጅታቹን አጠናክሩ፡፡ 🔷 አፕሊኬሽኑ ከ2008 - 2015ዓም የኢንትራንስ ፈተና ከነመልሱ እና ከነማብራሪያው የያዘ ሲሆን ፤ እነዚህን ፈተናዎች በቀላሉ መለማመድ የምትችሉበት መንገድ አዘጋጅቷል፡፡ 🔷 አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ለማድረግ ታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
Show all...
#አሳዛኝ - ለጥንቃቄ ቲክቶከሯ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች አቢ ትባላለች ቲክቶክ ላይ የምትሸጣቸዉን የባሕል ልብሶች በማስተዋወቅ ትታወቅ ነበር። ጦር ሐይሎች አካባቢ ጂም ቤት ዉስጥ በሚያሠራት አሠልጣኝ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተገድላ ተገኝታለች ተብሏል። የግድያዉ ምክንያት ደሞ ለምን ቲክቶክ ላይ ጂም ቤት ዉስጥ የምሰሪዉን ቪዲዮ ለምን ለቀቅሽ የሚል እንደሆነ ተጠርጣሪው በፍርድቤት ባቀረበው የእምነት ቃል ማቅረቡን የሟች እናት ተናግረዋል።አቢ የ5 አመት ሴት ልጅ እናት ነበረች። ተጠርጣሪው ግለሰብ በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ በመሆን የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ነው የሚገኘው። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመሥራት የተግባባ፣ የጋራ አስተሳሰብ ያለውና የወደፊቱን የተገናዘበ አመራር መስጠት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ። የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የምክክር መድረክ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልል የትምህርት ዘርፉ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በምክክር መድረኩ የተገኙት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገራችንን የትምህርት ሥርዓት የመምራት እድል እንደተሰጠው አመራር በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር በመረዳት የተቀራረበ አመለካከት በመያዝ አመራር መስጠት ይገባል ብለዋል። ከዚህ በፊት ትምህርትን እያየን ባለንበት መንገድ መሥራት አንችልም ያሉት ሚኒሰትሩ በረጅም ጊዜ አቅደን ብቁ ተወዳዳሪ እና በስነ-ምግባር የታነፁ ልጆች ለማፍራት የሚያስችል ትምህርት እየሰጠን ነው የሚለውን ማሰብና መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። በትምህርት ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ በዚህ ረገድ የጋራ አስተሳሰብ በአዲስ መልክና ማዕቀፍ መያዝ ይገባል ብለዋል። አክለውም ከአጭር ጊዜ አስተሳሰብ ወጥተን የሚቀጥለውን ትውልድ በዓለም ተወዳዳሪ፣ ክህሎት ያለው፣ ግብረ ገብነትን የተላበሰ እንዲሆን ለማድረግ የጋራ አስተሳሰብ ይዞ መሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል። አሁን ዓለም ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት የተሻለ ብቃትና ክህሎት ያላቸው እንዲሁም በስነ ምግባር የታነፁ ተማሪዎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል። በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክብርት አየለች እሸቴን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ የሁሉም ክልልና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። #MoE ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ‼️ ትምህርት ሚንስቴር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ተቋማት ስለ ጉዳዩ ከመናገር ተቆጥበዋል የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ። ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል ለአል ዐይን አማርኛ እንዳሉት "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ብለዋል። "ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር ነግረውናል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል። የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም ሲል ሚድያው ገልጿል። ምንጭ ፡ አል-ዓይን ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...