cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Havan Academy

📚Are You Student? 📌Havan Academy is renovating online tutoring service. ✅we are introducing a revolutionery tutoring service for Ethiopian University students. More Info: @havanacademyinfo Youtube: @havantube Any qs or comments @Drhavan,

Show more
Advertising posts
5 502
Subscribers
+224 hours
+27 days
+2530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ላልሆኑ የተቋሙ ተማሪዎች የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት ከነገ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደማይሰጥ አሳውቋል። ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ግን አገልግሎቶቹ መሰጠት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። @tikvahuniversity
Show all...
የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ̔ፕሬዝዳንሻል ሜንተርሽፕ̔ ሰልጣኞች በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ፡፡ የሜንተርሽፕ ፕሮግራሙ በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶች ማሳደጊያ የማማከር ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ ዙር ስልጠናውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች የምርቃት እና የፕሮጀክቱ ማጠቃለያ መርሐግብር ተካሄዷል፡፡ በአጠቃላይ በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥራቸው 500 የሚሆኑ የፕሬዝዳንሻል ሜንተርሺፕ ስልጠና (Presidential Mentorship Program) ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ ፕሮግራሙ በ Institute of International Education አማካኝነት በአመራር ብቁ የሆኑ ሴቶችን ለማፍራት ከአራት ዓመት በፊት የተጀመረ መርሐግብር ነው፡፡ #AASTU @havanacademy
Show all...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ የአባቶች ቀን እየተከበረ ይውላል። መልካም የአባቶች ቀን ! አስታየት መስጫው ላይ ለአባታችሁ መልካም ምኞት መግለፅ ትችላላችሁ ❤️ @havancademy
Show all...
4 3
ሃቫን አካዳሚ ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል ይመኛል! እንኳን ለኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ! በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን! ኢድ ሙባረክ!! Eid Mubarak!! @havanacademy
Show all...
🥰 5
Photo unavailableShow in Telegram
የዩኒቨርሲቲወች በጀት ከቀጣይ አመት ጀምሮ በማይታመን መልኩ ተሸሽሉአል፣ በዚያ ላይ በየአመቱ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡት ተማሪወች ቁጥር እየቀነሰ ነው፣ ይህ ማለት ወደፊት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገቡ ተማሪወች living standard ይሻሻላል፣ እናንተስ ምን ትጠብቃላችሁ!!! አሁን በደምብ ካነበባችሁ የፈለጋችሁበት ዩኒቨርሲቴ ትገባላችሁ !!! @havanacademy
Show all...
👍 4 4
Photo unavailableShow in Telegram
ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል። በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል። ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ @havanacademy
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ክፍፍል የፌደራል መንግሥት ለ2017 በጀት ዓመት ከያዘው 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 39 ቢሊዮን ብር ያህሉ ከመንግሥት ግምጃ ቤት ወጪ ሆኖ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲከፋፈል መድቧል። ለፓርላማ በቀረበ የበጀት ረቂቅ ሰነድ ላይ እንደሚታየው 13 ዩኒቨርሲቲዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸዋል። ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግሥት መደበኛ በጀት 1.9 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ባህርዳር ዩኒቨርስቲ 1.8 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል። ከመንግሥት ግምጃ ቤት 1.7 ቢሊዮን ብር የሚሰጠው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በክፍፍሉ ሦስተኛውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የሚያገኝ ይሆናል። ጅማ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በአራተኛ እና በአምስተኛነት ይከተላሉ። የፌደራል መንግሥት በጀትን የሚያዘጋጀው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ባለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ባካሄደው የበጀት ስሚ መርሐግብር ዩኒቨርሲቲዎች “በተቀመጠላቸው ጣሪያ መሰረት” የበጀት ዕቅዳቸውን አስተካክለው እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር አይዘነጋም። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር @tikvahuniversity
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ከፍለው ለመማር የማይችሉ ተማሪዎች የባንክ ብድር እንዲያገኙ የሚረዳ ሕጋዊ አሠራር እንዲመቻች ተጠየቀ፡፡ በ2015 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ የገባውና ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የሚያደርገው አዋጅ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከስምንት ወራት በፊት ወደ ሥራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ ገዝነት ለማሸጋገር ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ምንም እንኳ ተጠያቂነቱ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መንግሥት በገንዘብ የሚደግፋቸውም ቢሆኑም፣ ራሳቸውን በራሳቸው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የፋይናንስ፣ የአስተዳደር፣ የአካዴሚክ፣ የሰው ሃብት እና መሰል ነፃነት አዋጁ ያጎናፅፏቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ራስ ገዝ ሆኖ ሥራ በጀመረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ከፍለው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ክፍያው በከፍተኛ መጠን እንደጨመረባቸው እየተናገሩ ነው፡፡ ወደፊት ራስ ገዝ የሚሆኑ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ሲገቡ አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ከፍለው እንዳይማሩ ይገድባል የሚል ሥጋት እየተሰማ ነው፡፡ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ለተማሪዎች የሚሰጥ ብድር መመቻቸት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) በተመሳሳይ፤ መንግሥት በውጭው ዓለም የተለመደውን ለተማሪዎች ብድር የሚቀርብበት አሠራር ሊያስብበት ይገባል ብለዋል፡፡ ሙሉውን ያንብቡ 👇 https://www.ethiopianreporter.com/130161/ @havanacademy
Show all...
👍 5
Second semester class👇👇 @havanReg_bot
Show all...
👀 2
⏰ ፈተና ሲደርስ ከሚስተዋሉ ገጠመኞች ውስጥ ጥቂቶቹ⚡️    👉 ካፌ ላይ መፎገር 🤧    👉 ስልክን library, class, cafe etc መርሳት ወይም መጣል   👉 Calculator መርሳት / መጣል   👉 PC መርሳት ለዛውም space ( class)   👉 ያነበቡትን መርሳት   👉 ራስን መሳት ( በተለይ ሴቶች)   👉 ወዘተ....           😜  ታድያ ምን ይሻላል ❓                📌ፈተና ሳይደርስ ሁሉንም course cover ማድረግ 📌 ከጭንቀታም ጓደኛ መራቅ ( በሰላሙ ሰአት እናንተ ስታነቡ ከማያነበው ማለቴ ነው ።) 📌 ከጎበዝ ተማሪ ጋር መጎዳኘትና አብሮ ማንበብ 📌 ጥያቄዎችን በgroup መስራት 📌 ስለ ፈተና አወጣጥ ከታላላቆቻችን መጠየቅ ( from seniors)🕵️‍♀️ 📌 Information gather ማድረግ ፦ 📌 ከበግ ተራ በመራቅ ሴቶችን info መጠየቅ ( affirmative ምናምን ብለው ....) 📚 በተረፈ Tension መጠኑ ይለያይ እንጂ አይቀሬ ነገር በመሆኑ ፈታ በሉ። እንደኔ እንደውም Tension ምንም የማይዘው ተማሪ ካሮት አምራች ገበሬ ይመስለኛል፤ ምክንያቱም አንብቦ ሳይሆን የሚፈተነው position አስተካክሎ ነው ። ሲበዛ ነው እንጂ የማይነፋው ተማሪ ካነበበ እስከሚፈተን ድረስ Tension Normal ነው። @havanacademy
Show all...
👍 5
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.