cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🇪🇹South Wollo Zone Education Department🇪🇹

🇪🇹SWE "ይህ የቴሌግራም ቻናል በደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የሚከናወኑ ሁነቶችን የምናሥተዋውቅበት ገጽ ነው። ተቀላቀሉን አብረን እንሠራለን እንማማራለን ለችግሮቻችን አብረን መፍትሔ እንፈልጋለን::" 🇪🇹

Show more
Advertising posts
1 613
Subscribers
-124 hours
-107 days
-3230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር የተባበሩት አረብ ኤምሬት  ስኮላርሽፕ አሸናፊ ተማሪ ወላጅ ተወካዮች ጋር ምክክር አደረገ፡፡ ————————-//—— በትምህርት ሚኒስቴር የአለማቀፋዊነትና ስኮላርሺፕ ዴስክ ሀላፊ  ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ  የተባበሩት አረብ ኤምሬት  ስኮላርሽፕ አሸናፊ ከሆኑ የተማሪ ወላጅ ተወካዮች ጋር ሂደቱን አስመልክቶ በልዩ ልዩ  ጉዳዮች ላይ ምክክር አድረገዋል፡፡ ቪዛና ፓሰፖርት፤ የጉዞና የክትትል ሁኔታን፣ የወጭና የትምህርት መስክ ምርጫ ጨምሮ ሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ የተማሪ ወላጅ ተወካዮች ምላሽ እንዲሰጣቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ተጠይቀዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የአለማቀፋዊነትና ስኮላርሺፕ ዴስክ ሀላፊው ጉዳዩን አስመልክቶ በሠጡት ማብራሪያ ተማሪዎች ከመሄዳቸው በፊት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  ትምህርታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የስነ-ልቦና ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በስልጠናው ላይም ለተማሪዎቹ የአራት ዓመት ቆይታ ጊዜያቸውን እንዴት መሳለፍ እንዳለባቸውና ሌሎች ተጨማሪ ማብራሪያዎችም  ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡ ሃላፊው አያይዘውም ጉዳዩን አስመልክቶ መንግስት አስፈላጊውን ክትትልና ትብብር እንደሚያደርግ ታውቆ ተማሪዎቹም ሆኑ የተማሪ ወላጆች ምንም አይነት ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ ገልፀዋል፡፡ የተማሪ ወላጅ ተወካዮቹም ለጠየቋቸው ጥያቄዎች በተሰጣቸው ምለሽ መደሰታቸውን ገልፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚየያደርገው ትውልድን የመቅረፅ ሃላፊነት አመስግነዋል፡፡ በተጨማሪም የስኮላርሽፕ አሸናፊ የተማሪዎች ስልጠና  ሀሙስ ነሃሴ 4/2015 ዓ.ም ከጧቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሚሰጥ መሆኑን አውቀው ወደ ስልጠናው ሲመጡ ብርድ ልብስ፣ አንሶላና የትራስ ልብስ ይዘው እንዲመጡና ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል፡፡
Show all...
"ፈተናው ከስርቆትና ከኩረጃ ነጻ ሆኖ ተጠናቋል" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ……………………………………………………… ሀምሌ 28/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከማንኛውም ፈተና ስርቆትና ኩረጃ ነጻ በሆነ መልኩ ተጠናቋል ብለዋል። ሚኒስትሩ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን እና ተማሪዎችም ፈተናውን በሰላማዊና በተረጋጋ ሁኔታ መውሰዳቸውን ገልፀዋል። በአጠቃላይ 840 ሺ 859 የማህበራዊ ሳይንስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በ2 ሺ 785 የፈተና ጣቢያዎች ተፈትነዋል። ከሀምሌ 19 እስከ ሀምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር በተሰጠው ፈተና ከ30ሺ 438 የሚበልጡ ፈተና አስፈጻሚዎች መሰማራታቸውንም አመላክተዋል፡፡ ሙሉ ዜናውን 👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0FEcAwTQT2Y1aVsgUaKjJX8a3jbGtZWHRhRCnimHBFNtmGBd9YAMUZ69R4vmTkAkGl&id=100064682287722&mibextid=9R9pXO ያገኛሉ በተጨማሪም :-👇 ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ያስጀመረውን ትምህርት ለትውልድ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ንቅናቄ ለመደገፍ እንዲሁም በቀጥታ የተማሩበትን ትምህርት ቤት ለመደገፍ https://sip.moe.gov.et እንዲሁም ትምህርት ሚኒስትር ለአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቅርብ ያስጀመረውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ፖርታል ለማግኘት https://learn-english.moe.gov.et ዌብ ፖርታሎቻችንን ይጎብኙ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የ2015 ዓ.ም የክረምት ትምህርት መርሃ ግብር አይካሄድም። ሀምሌ 26/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተያዘው አመት የክረምት ትምህርት መርሀ ግብር  እንደማይካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት  በተለያዩ ምክንያቶች  የተዛነፈውን የትምህርት ፕሮግራም መርሃ ግብር/ Academic Calendar/ ለማስተካከል ሲባል  መሠረዙን አስታውቀዋል። የ2015 ዓ.ም የክረምት ትምህርት መርሀ ግብር የቀረው አንድ ወር ብቻ በመሆኑና በቀሪው ጊዜ ትምህርት መስጠት እንደማይቻል ዶክተር ኤባ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የተዛነፈውን የትምህርትፕሮግራም  መርሃ-ግብር  /Academic Calendar/ በ2016 ትምህርት ዘመን ለማስተካከል እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
Show all...
ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተመደቡ የፈተና አስፈጻሚዎች በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን ጎበኙ። =======================//======================== ሀምሌ24/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር) የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የፈተና አስፈጻሚዎች የተለያዩ ቦታዎችን ጎብኝተዋል። በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተመደቡ የፈተና አስፈጻሚዎች ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚገኙበት አካባቢ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን፣ ቅርሶችና ባህሎችን ጎብኝተዋል። በተጨማሪም የዓመታትና የብዙ ባህላዊ ቅርስ፣ የፓለቲካ ሥርዓት፣ የታሪክ፣ የግብርና፣ አኗኗር፣ ወዘተ የፈተና አስፈጻሚዎቹ እንዲጎበኙ ተደርጓል። "ምሁር ድንበር የለውም" በሚል መነሻ የተዘጋጀው ጉብኝት አካባቢን ባህል፣ እሴትና ወግ ለማስተዋወቅ፣ እርስ በርስ ለመተዋወቅ እንዲሁም  ኢትዮጵያዊነት የተላበሰ  አንድነትና መስተጋብር ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል። ይህ አይነቱ ጉብኝት ከተለያዩ አካባቢ ፈተናውን ለማስፈጸም የመጡ ምሁራን  በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችንና አኗኗርን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጻኦ ይኖረዋል ተብሏል። በተለያዩ አካባቢዎች በጉብኚቱ የተሳተፉ የፈተና አስፈጻሚዎችም ጉብኝቱ ሀገራችንን የብዙ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት መሆኗን ያረጋገጥንበትና ስለ ሀገራችን የበለጠ እንድናውቅ ያስቻለን ነው ብለዋል። በዚህም ቱባ ባህል፣ ዕምነቶች፣ ቋንቋዎች፣ በልዩነት ዉበት አይተን የበለጸገ ሀገር ለመገንባት ከሚያልያዩን ይልቅ በርካታ የሚያቅራርቡን ጉዳዮች እንዳሉ ተረድተናል ያሉ ሲሆን በቀጣይም አንድነትን በሚያምጡ ጉዳዮች ላይ ትኩርት ሰጥተው እንደሚሰሩም ገልጸዋል። የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተና ከሃምሌ 25/2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል። በተጨማሪም :-👇 ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ያስጀመረውን ትምህርት ለትውልድ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ንቅናቄ  ለመደገፍ እንዲሁም በቀጥታ የተማሩበትን ትምህርት ቤት ለመደገፍ https://sip.moe.gov.et   እንዲሁም ትምህርት ሚኒስትር ለአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቅርብ ያስጀመረውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ፖርታል ለማግኘት https://learn-english.moe.gov.et  ዌብ ፖርታሎቻችንን ይጎብኙ።
Show all...
የእድሜ ዘመን ባለውለታ የቀለም አባቶች መምህር ካሳው ታመነ እና መምህር ሃይሉ ቦጋለ :: ኩታበር፣ ሃምሌ 21/2015 ዓ.ም (ኩታበር ወረዳ ኮሙኒኬሽን) የነዚህን የስራ አርበኞ የቀለም አባቶች ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ለማስቃኘት ወደናል ። ከ40 አመታትን በላይ ትወልድን በእውቀት ለማነጽ የተከፈለ መስዋዕትነት እና ውጣውረድ የተማረ ዜጋን ፀንሶ ለመውለድ ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፉ ለሀገር ባለውለታ የቀለም አባት ናቸው። እነዚህ የብዙዎች የእውቀት አባት መምህር ካሳው ታመነ አደም እና መምህር ሃይሉ ቦጋለ የተወለዱት ብዙ ሙህራን እና ቅን አሳቢ ሀገር ወዳድ ዜጎች የትውልድ ቦታ በሆነችው የደቡብ ወሎዋ ኩታበር ወረዳ ነው። ብዙዎችን በእውቀትና በስነምግባር በማነጽ አንቱታን እና ከበሬታን ያገኙ የእውቀት አባቶች በመምህርነት ሙያ ባገለገሉባቸው ከ40 አመታት በላይ የሰሯቸው መልካም ሰራዎች በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን እና አንቱታን አትርፈዋል። የህዝብን ክብር እና ፍቅር ደመወዛቸው ያደረጉት እነዚህ አባቶች በትምህርቱ እና በተለለያዩ ዘርፎች በመሰማራት ሙያ ባለቤት እና ታታሪ ሰራተኝነታቸውን አስመስክረዋል። በዘመናቸው ወረዳው ውስጥ የነበረዎን የትምህርት ቤቶች እጥረት ለመቅረፍ የበኩላቸውን ሚና ከመጫዎት ባለፈ አካባቢው በትምህርት ጥራት ገዝፎ እንዲታይ በተግባር ከሰሩ የእውቀት አባቶች መካከል የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ ። ጡረታ ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ሰዎችን የሚያስታርቁ ፣በተለያየ ማህበራዊ ጉዳዪች ላይ ስማቸው ጎልቶ የሚጠቀስና በብዙዎች ዘንድ በመልካም ስም የሚወሱ ረፍት አልባ አባቶች ሲሆኑ በማህበራዊ አገልግሎቶች ንቁ ተሳታፊም ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወድህ ደግሞ እውቅናና እውቀታቸውን በመጠቀም ለብዙዎች የተቸገሩ ወገኖች መፍትሄ ለመሆን የተለያዩ ወጣቶችን እና የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር እርዳታ በማድረግ ለወገን ደራሽነተዎን አስመስክረዋል ። የቀለም አባቶቹ ለሀገር ለከፈሉትን ምስጋና እያቀረብን የእነርሱ አይነት ጀግኖችን ሀገራችን ትሻለች እና የዛሬ ትውልዲ ከእነርሱ በመማር ዘመን ተሻጋሪ ስራን መስራት ይገባል መልእክታችን ነው። **** የኩታበር ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃዎችን ተደራሽ የምናደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ሲሆኑ ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ! ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100064621272287 ቴሌግራም:- https://t.me/kutabercommunication ኢንስታግራም:- https://www.instagram.com/kutaberkominication/ ዩትዩብ፦ https://youtube.com/channel/UC-zLIshK7J1Jd9NO8zvwHeA
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

"የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል ሁሉም ህብረተሰብ ሊረባረብ ይገባል " ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ሕዝባዊ የንቅናቄ መድረክ በባሕርዳር ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በአማራ ክልል ውስጥ ለትክክለኛ መማር ማስተማር የሚመጥን ደረጃ ያላቸው ትምህርት ቤቶች ከ17 በመቶ እንደማይበልጡ ተናግረዋል። አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መኾናቸውን በመገንዘብ ሕዝቡ፣ ባለሃብቶች እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች ከመንግሥት ጎን በመቆም መረባረብ እንደሚገባቸው ገልፀዋል። ትምህርት ቤቶች ሕጻናትን የሚስቡ እና ከአካባቢ ንጽህና እና ውበት ጋር የተላመዱ ኾነው እንዲገነቡ ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበትም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። "የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ትልቁ አቅማችን ትብብራችን ነው" ሲሉም ተናግረዋል። ዶክተር ይልቃል በመምህራን ሥልጠና ላይ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው መምህራንን በአግባቡ አሰልጥኖ እና ተገቢውን ክብር በመስጠት ወደ ሥራ በማሰማራት ትውልድ የመቅረጽ ተግባርን ማሳለጥ ያስፈልጋል ብለዋል። ሕዝብ የሰጠውን ኃላፊነት ሳያዛንፍ የሚወጣ ትውልድ ለመፍጠር የመምህራን ሚና ጉልህ ስለመኾኑም ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። የአማራ ክልል መንግሥት ካለው ሰፊ የመልማት ፍላጎት አንጻር ለትምህርት ቤቶች ደረጃ መሻሻል እና ለትምህርት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ስለመኾኑም ዶክተር ይልቃል አመላክተዋል። "የምናልመው እድገት ላይ ለመድረስ ትውልዱን በዕውቀት ማነጽ ግድ ይላል" ሲሉም ተናግረዋል። በክልሉ በርካታ ባለሃብቶች በግል ተነሳሽነት ዘመናዊ ትምህርት ቤቶችን ገንብተው ለትውልድ ማበርከታቸውን አንስተው ሌሎች ባለሃብቶችም እንዲህ አይነት የማይዘነጋ በጎ ተግባር እንዲፈፅሙ ጥሪ አስተላልፈዋል። ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ 1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/ 2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w 3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau 4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse ያግኙን
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተመለከቱ ። .........//.............................. ሀምሌ/17/2015 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒሰቴር) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል። በዩኒቨርሲቲዎቹ ያለውን የተማሪ አቀባበል፣የመኝታና የመመገቢያ ቦታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በምልከታቸውም ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ ሚኒስትሩ አበረታተዋል ። የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሀምሌ 19 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።
Show all...