en
Feedback
ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

Open in Telegram

እንኳን ደህና መጡ ወደዚህ ቻናል የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥምና ስነፅሁፎች ከእራሳችንና ከገጣምያን ተሰብስበው የምናደርስበት ስሜታችንን የምንገልፅበት አውድ ነው። ግጥማቹን ሌላ ችሎታቹን ለማጋራት የምትፈልጉ ላኩልን✍️

Show more
5 666
Subscribers
+824 hours
+207 days
+9830 days
Posts Archive
ሰላም እንዴት ናቹ ✨ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እናም ውድ ቤተሰቦች የራሴን ትንሽዬ የ T-Shirt Brand ጀምሪያለሁ " ሙሉወርቅ | Muluwerk Designs "😊 . እና
+4
ሰላም እንዴት ናቹ ✨ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እናም ውድ ቤተሰቦች የራሴን ትንሽዬ የ T-Shirt Brand ጀምሪያለሁ " ሙሉወርቅ | Muluwerk Designs "😊 . እና Channel ከፍቻለሁ ገባ ገባ እያላቹ ቤቴን መርቁ ORDER ማድረግ የምትፈልጉም ORDER አድርጉ ምትፈልጉት ሁሉ አለን CUSTOM ORDERም እንቀበላለን ✨ . ቤቴን መርቁ ጅማሬዬንም ፍፃሜንም አምላክ ይባርክ🙏 THIS IS THE CHANNEL : @muluwerkdesigns

"ስትጣሉ እንዴት ናችሁ?" (simple - story ) አባቷን "ፍቅር ምንድነው" አለችው ማሰብ አላሰፈለገውም። "ፍቅር ማለት ፍቅር በጠፋበት ጊዜ የምታሳይው መልካምነት ነው።" "ማለት" "ከምትወጂው
"ስትጣሉ እንዴት ናችሁ?" (simple - story ) አባቷን "ፍቅር ምንድነው" አለችው ማሰብ አላሰፈለገውም። "ፍቅር ማለት ፍቅር በጠፋበት ጊዜ የምታሳይው መልካምነት ነው።" "ማለት" "ከምትወጂው ሰው ጋር ስትቀያየሙ የምታሳይው ባህሪ ነው ፍቅር።"አላት "ጥያቄዬ ገብቶሀል?" አለችው "የምትወጂው ሰው ሲያናድድሽ ምን ታረጊዋለሽ ነው ዋናው። ታንቋሽሺዋለሽ? ትንቂዋለሽ? ለፈጣሪሽ ትነግሪዋለሽ? ወይስ ለሰዎች ታሚዋለሽ? ወይስ ትበቀይዋለሽ ? ወይስ  በልብሽ ይዘሽው ትቆይዋለሽ። ወይስ እንኳስ ፍቅርሽን እንደኳስ ጠልዘሽ በሰው ዘንድ ቆንጆ ታሪክ ፈጥረሽ"የልክ ነኝ" ጎል ለማስቆጠር ትጥሪያለሽ? ወይስ በብልሃት ታልፊዋለሽ?" ተቆጣች። "ከተጣላን ከተቀያየምን ብንስ ባረገው? ካስቀየመኝ ደጋግሞ ካስኮረፈኝ ምን አቆየኝ?" ሊመክራት ሳይሆን ሊነግራት አቀፋት። "ልጄ በደጉ ጊዜ መውደድማ መልስ ምት እንጂ ፍቅር አደለም። ፍቅር ማለት አብሮሽ ያለው ሰው የማትወጂውን ባህሪ በሚያሳይሽ ጊዜ የምሰጪው የመውደድሽ መልስ ነው። ሲስምሽማ መውደድ ተፈጥሯዊ ነው። ሲያናድሽ መውደድ ግን ፍቅር ነው። አንቺ ስታናድጂው የሚሰጠው ግብረ መልስ ፍቅር ይባላል" አቀረቀረች። "ሁሌ ፍቅር እንዳለን እንደምንዋደድ በምን አውቃለሁ" "ስትጣሉ በምትመላለሱት ነገር:: " "እኔ ምልሽ?" "አቤት አባዬ" " አንቺና እጮኛሽ ስትጣሉ እንዴት ናችሁ" መልሷ አስፈራት! (elias shitahun)

Check out this TikTok I posted!  👇👇👇👇👇👇👇 https://vt.tiktok.com/ZS4GuYEJp/

Repost from ቶጳዝዮን
ትንሣኤሽን ልየዉ ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣ በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ። ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣ ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ። ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣ አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ። ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣ ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ። ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣ በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ። እንኳን አደረሳችሁ🙏 ✍ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn

SkillMoney Complete tasks and manage your rewards. https://t.me/SkillMoney01_bot/earn?startapp=ref_63792F9D
SkillMoney Complete tasks and manage your rewards. https://t.me/SkillMoney01_bot/earn?startapp=ref_63792F9D

መሰንቆን ለመጫወት የሚያገለግለውና በጅራቱ ላይ የሚሸራተተው መሳሪያ ምን ይባላል?
መሰንቆን ለመጫወት የሚያገለግለውና በጅራቱ ላይ የሚሸራተተው መሳሪያ ምን ይባላል?

https://t.me/bet_begena ለእርሶም ለስጦታም የሚሆኑ ጥራታቸውን የጠበቁ በገና ክራር መሰንቆ እዚህ ማግኘት ይችላሉ

‎ብታጭ ለምስራች ታበስረኝ ብትመጣ ‎ስለ አለማመኔ ‎እንደ ዘካርያስ ዲዳነት ነው የኔ ዕጣ ‎ይኩነኒ አላልኩም እንደ እመአምላክ ‎ከአምላክ ፊት የሚቆም ቢላክልኝ መልዓክ ‎ታንኳ ተሰዶልኝ ማህበሉን ማለ
ብታጭ ለምስራች ታበስረኝ ብትመጣ ‎ስለ አለማመኔ ‎እንደ ዘካርያስ ዲዳነት ነው የኔ ዕጣ ‎ይኩነኒ አላልኩም እንደ እመአምላክ ‎ከአምላክ ፊት የሚቆም ቢላክልኝ መልዓክ ‎ታንኳ ተሰዶልኝ ማህበሉን ማለፊያ ‎እኔን ሚያሳስበኝ ወጀቡን መቅዘፊያ ‎ገብርኤል ገብርኤል መልዓከ ራማ ‎ለደረቀ ልቤ ቃሉን ለተጠማ ‎ላላመነ ነፍሴ ገድሉን እየሰማ ‎ድረስለት ፈጥነህ! እርዳው አለማመኔን ‎ለውጥልኝ ስሜን ! ‎ [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

ሰው ሲሞት ብቻ ሳይሆን በቁሙም አበባ ይሰጠዋል እዘዙ 😊😁

ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ ገላሽን ይንካና ወዮለት ሰማዩ ወዮለት ደመና ። ወፍ አይዘምርልሽ ዛፍ አያስጠልልሽ በቃ እኔ አለሁልሽ ። ደግሞ ይሄን እወቂ ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ እንቅልፍ እንደማጣ በፀሐይ ስትፈኪ ምራቄ እንደሚመር በእግዜር ስትመኪ ። እኔ ጠባቂሽ እኔ ነኝ ደስታሽ እኔ ነኝ ፈገግታሽ ሁሉንም የምሆን እግዜር አላህ ሰማይ ንፋስ ውሃ ድንጋይ ያንቺ ብቻ አገልጋይ ያንቺ ብቻ ታጋይ ። ክነፍ በዪኝ ልክነፍ እረፍ በዪኝ ልረፍ ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ። By Hab Hd @topazionnn @topazionnn

<< ስትሞት ቀድመህ ምታደርገው ምንድነው >> ስትል ጠየቀችኝ ! መጨረሻዬ ምንም ሆነ ምን ለአምላኬ የማቀርበው አንድ ተማፅኖ ይኖረኛል! << ምን የሚል ? >>
<< ስትሞት ቀድመህ ምታደርገው ምንድነው >> ስትል ጠየቀችኝ ! መጨረሻዬ ምንም ሆነ ምን ለአምላኬ የማቀርበው አንድ ተማፅኖ ይኖረኛል! << ምን የሚል ? >> በማርያም አንድ ጊዜ መታቀፍን ! በማርያም አንድ ጊዜ መነካትን ! በማርያም አንድ ጊዜ ልጄ መባልን ! በማርያም አንድ ጊዜ መዳሰስን ! ተማፅኖዬ ይሄ ነው ! << መንግሥትህን አውርሰኝ ትላለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር ! >> አቅፋ ለገሃነም እንደማትሰጠኝ አውቃለሁ! በእሷ ተዳስሼ ሲዖልም ብገባ ጠረኗ ገነት ሆኖ ያቆየኛል! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

ዛሬ የ ስሜትን በግጥም Channel Owner የሆነችው አ....ፊት ቤዛ......ድ......ማ.... ልደት ነው 😁😁😁 አንቺ የግጥም አርበኛ አንቺ የስንኝ ጦረኛ እሰይ እልልል እንኳን ተወለድሽ
ዛሬ የ ስሜትን በግጥም Channel Owner የሆነችው አ....ፊት ቤዛ......ድ......ማ.... ልደት ነው 😁😁😁 አንቺ የግጥም አርበኛ አንቺ የስንኝ ጦረኛ እሰይ እልልል እንኳን ተወለድሽ 😁😂😂 መወለድሽን ብጠራጠርም መልካም ልደት . . የዕድሜሽ ጉዳይ እየተጣራ ነው 🙏መልካም ልደት በሏት @smetnbegetm

Check out this TikTok I posted!  https://vt.tiktok.com/ZSQKKP8tt/

#ከተውሽኝ_ቦታ_ላይ እኔ እዚያው ነኝ ! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel