cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት (mana dilbata firee amentaa)

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታችንን እንድናውቅ የሚረዱ :- ፨ ከተለያዩ መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸውን መረጃዎች አናጋራቹሃለን። ፨ ጥያቄ አና መልስ አንጠያየቃለን። ፨ መንፈሳዊ መፃህፍትን በ አማርኛ ፣ Afaan oromoo አና English language እናካፍላቹሃለን። ሐሳብ አስተያየት ካላቹ @ye_gebriel ላይ አሳውቁን።

Show more
Advertising posts
192
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን  ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም  ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡  በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
Show all...
#የኔ_ትውልድ_ባለውለታውን_ያሳክማል "ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ ታሟል" ብዙዎቻችንን ወደ መንፈሳዊ መንገድ የመራን፣ በሐጢአት የገገረውን ዓለት ልባችንን በመንፈሳዊ መዝሙሮቹ ያቀለጠልን፣ ልንጠፋ ጫፍ ስንደርስ በሚስረቀረቅ ድምፁ የመለሰን፣ በአገልግሎቱ አዋጅ ነጋሪ የሆነ፣ መዝሙሩ ወደ ጸሎት ያደገለት ታላቁ አባታችን ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ ሕክምና ይፈልጋል። ጠንካራ ቤተ ክህነት ቢኖረን ኖሮ ይህ የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ መታከሚያ ባላጣ ነበር። ዳሩ ግን...ሆድ ይፍጀው። እኛ የመዝሙራቱ ተጠቃሚዎች ግን ባለውለታችንን አንተውም። ዘማሪ ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስን ለማሳከም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ....እነሆ በረከት! መርዳት የማትችሉ በማጋራት ተባበሩ። ድጋፋችንን አድርገን ወዳጅነታችንን እንግለጥ CBE 1000481007287 KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL CMC Michael Branch
Show all...
#ግንቦት_11 #ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅድስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት። ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ። ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው። ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ። በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ። ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ። ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ። ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው። የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም። በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም። ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው። ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ። ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
Show all...
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው። በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።" የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን (Orthodox and Bible fb page)
Show all...
#እመቤቴ_ሆይ፤ ባትወለጂ እግዚአብሔርን በሥጋ ተገልጦ እናየው ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ ፍቅር፣ ምሕረት እና ፍጹም መልካምነት በእውነት ሥጋን ነሥተው በክርስቶስ እናይ ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ንጽሕና በሰውነት ተገልጦ እናይ ነበርን? በፍጹም። ይኸውም ያንቺ የቅድስና ሕይወት ነው። ከሊቃውንት አንዱ የአንቺ አንዲቷ ትንፋሽ ከቅዱሳን ሁሉ ገድል፣ ምስጋና እና ምልጃ ሁሉ የከበረች እንደሆነች ተናገረ። ይህ ሁሉ ከሰው ኅሊና ስለሆነው ንጽሕናሽ ነው። በዘወትር ቋንቋችን አንቺን "ንጽሕት" ብቻ ማለት ንጽሕናን ማጉደፍ ይሆናል እኮን። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያንቺ ንጽሕና እና ቅድስና በቃል ከመነገር ይልቅ፤ በዝምታ የልብ ለኆሳስ ቢመሰገን የተገባ ነው። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔር ትእዛዝ በምልዓት ሲፈጸም፤ ሕጉ ሲደረግ ምን እንደሚመስል በምን እናውቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የክህነት ንጽሕና በምን ይጠበቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የንስሐ መንገዱን ማን ያመለክተን ነበር? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ መታዘዝ፡ የእኛን ዐመጸኛነት እንዴት ይገስፀዋል? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ ትሕትና፡ የኔን ትዕቢት ይሰብረው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል? ስለ አምላካዊው ኀይሉ፤ ጠላት ሰይጣን ለልጅሽ ይገዛል። የልጅሽ የክርስቶስን ስም ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። አንቺ ግን በትሕትናሽ ሰይጣንን አራድሽው። እርሱ መንፈስ ሲሆን "ሥጋ ለባሽ" ብሎ በሚንቃት "በአንዲት ሴት" መሸነፉ ሁልጊዜም ግራ ይገባዋል። ስምሽን የሚጠሩ ሰዎች ፊትም መቆም አይቻለውም። ስምሽን ሲጠሩ ኀይላቸውን ትተው ኀይልሽን ይይዛሉና። ይኸውም እግዚአብሔር ነው። ስምሽን ሲጠሩ ትዕቢታቸውን ጥለው በትሕትናሽ ይጋረዳሉና። ስምሽን ሲጠሩ ጥርጣሬያቸውን በሃይማኖትሽ ያሸንፋሉና። በንጽሕና ቀሚስሽ ስለ እድፈታቸው ከሚከሳቸው ይጋረዳሉና። ሰይጣን ከእነርሱ ዘንድ አይቀርብም። እመቤቴ ሆይ አንቺ ባትወለጂ ከመልካሙ ሁሉ በአፍአ በቀረን ነበር እኮን። አሁንም "መጥተን" ሳለን የቀረን አታድርጊን። እኛ ራሳችንን ብንተው፤ አንቺ አትተዪን። እኛ ብንርቅ፡ አንቺ አትራቂን። እኛ ብንዘነጋ፡ አንቺ አትዘንጊን። መሐርነ፡ ወተሣሃልነ! (ምንጭ፦ Micky Asres) #ይቀላቀሉ @beteafework        @beteafework @beteafework        @beteafework @beteafework        @beteafework
Show all...
#የፍቅር_ ቀን# ❤❤❤❤❤ እኔ የማከብረው ሁሌ ምዘክረው አለኝ የፍቅር ቀን አለኝ የማረሳው ልቤን አሸንፎት በእንባ የማወሳው የኔ ውድ አፍቃሪ በቀጠሮው ሰአት በቀጠሮው ቦታ ሳያረፍድ ተገኝቶ በዛች በከፍታ በደሙ ቀለበት ገብቶልኝ ቃልኪዳን በእውነተኛ ፍቅር ለእውነተኛ መዳን ልሙትልሽ ብሎ በፅኑ መሀላ መውደዱን ገልጦልኝ እንድኖር በተድላ በዛች በለተ አርብ በፍቅር ቀናችን ፍቅሩን ገልጦልኛል ቀይ አበባ ሳይሆን ቀይ ደም ሰቶኛል ስለዚህ ያቺ ናት እርሷ ናት የኛ ቀን የኔና የውዴ ለአለም የታየበት በርሱ መወደዴ።       ወስብሐት ለእግዚአብሔር! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ክብርና ምስጋና ይግባው በእለተ አርብ ለተሰቀለው ⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅
Show all...
+ የሚያምር እግር + በጸሎተ ሐሙስ ልብን የሚሰውር አንድ ነገር ተፈጽሞ አለፈ፡፡ ይህም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር የማጠቡ ነገር ነው፡፡ የሰውን የቆሸሸ እግር እያሸ የሚያጥብ አምላክ ፣ የተማሪዎቹን እግር የሚያጥብ መምህር ፣ የባሪያዎቹን እግር የሚያጸዳ ጌታ ማየት እንዴት ያስጨንቃል? እስቲ ለአንድ አፍታ ወደዚያ ቤት በሕሊናችን ተጉዘን እንግባና ጌታን እግር ሲያጥብ አብረን እንመልከተው፡፡ የአምስተኛው ክፍለ ዘመን ባለቅኔ የቅዱስ ኤፍሬም ተማሪ ሶርያዊው ቄርሎና በመንፈስ ሆኖ ያንን ቤት በዓይነ ሕሊናው እንዲህ ቃኝቶት ነበር ፦ 'ጌታ ውኃ ቀዳና መታጠቢያውን ተሸከመ። የማበሻ ጨርቅ ያዘና ታጠቀ፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ፡፡ ሕሊናዬን አንዳች ነገር ሲወጋው ተሰማኝ ዕንባዬም ፈሰሰ። በፍርሃት ፊቴን ሸፈንኩ ዓይኖቼንም በመሳቀቅ ዞር አደረግሁ፡፡ ሲያጥባቸው ለማየት አቅም የለኝምና ብወጣ ተመኘሁ' ይላል፡፡ (Hymns of Cyrillona, On The Washing of the feet, Gorgias Press pg 72)እውነትም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጎንብሶ ማጠብ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ @diyakonhenokhaile ጌታችን ሐሙስ ዕለት ያደረገውን ነገር መጥምቁ ዮሐንስ ቢያይ ኖሮ ምን ይል ይሆን? ጌታ ሊጠመቅ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ ዮሐንስ 'አንተ እንዴት ልትጠመቅ ወደ እኔ ትመጣለህ?' ብሎ አልነበር? መጥምቁ ዮሐንስ ሆይ ና ተመልከት! በአንተ በባሪያው እጅ ሊጠመቅ ሲመጣ ስለ ትሕትናው የተደነቅህበት ጌታ ዛሬ ደግሞ አጥምቁኝ ከማለት አልፎ የባሪያዎቹን እግር ሲያጥብ አጎንብሶ ታየ፡፡ አንተ 'የጫማውን ጠፍር ተጎንብሼ ልፈታ አይገባኝም' ያልክለት ጌታ አጎንብሶ የሐዋርያቱን ጫማ ሲፈታና እግራቸውን ሲያጥብ ብታይ ምን ትል ይሆን? በዮርዳኖስ ዳር 'አንተ እንዴት ልትጠመቅ ወደ እኔ ትመጣለህ?' ያልከውን ጌታ ቅዱስ ጴጥሮስ 'አንተ እንዴት የእኔን እግር ታጥባለህ?' ሲለው ተመልከት! በእርግጥ በዮርዳኖስ ወንዝ ከታየው ትሕትና የበለጠ ትሕትና በዚያች የመታጠቢያ ወኃ ውስጥ ታየ፡፡ ውኃ በተሞላ በአንድ ማስታጠቢያ ውስጥ የፍጡር እግርና የፈጣሪ እጅ አንድ ላይ ሆነው የታዩበትን ያን ቅጽበት እጅግ ታላቅ ትሕትና ተማርንበት፡፡ ፍጡር ፈጣሪውን ሲያጠምቀው ከማየት በላይ ፈጣሪ የፍጡርን እግር ሲያጥብ ማየት ድንጋይ ልባችንን የሚሰብር ቅጽበት ነው፡፡ ከመጥምቁ ዮሐንስ በፊት የነበሩት ነቢያትስ ይህንን ቢያዩ እንዴት ይደነቁ ይሆን? ኢሳይያስ ሆይ 'ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ሆኖ አየሁት' ያልክለት ጌታ ዝቅ ባለ መቀመጫ ላይ ቁጭ ብሎ የአሳ አጥማጆችን እግር ሲያጥብ ተመልከተው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ሆይ 'እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን' ብለህ የዘመርክለት ጌታ እግር እያጠበ ነው፡፡ የሚገርመው እግር ከማጠቡ በፊትም ውኃ አስቀረበ አይልም ምክንያቱም ውኃውን የቀዳውም እርሱ ራሱ ነበረ፡። አብርሃም ለእንግዶቹ እንዳለው 'ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ' ብሎ ውኃ አላስቀዳም፡፡ (ዘፍ. 18፡4) ራሱ ወኃወን ቀድቶ በመታጠቢያው ሞልቶ የባሪያዎቹን እግር አጠበ። ለነገሩ በትሕትና የተጠመቀበትን የዮርዳኖስን ወንዝስ ቢሆን በወኃ የሞላው እርሱ አልነበረምን? ... ጴጥሮስ ተጨነቀ ፤ 'ጌታ ሆይ አንተ እንዴት የእኔን እግር ታጥባለህ?' አለና ተከላከለ፡፡ የጴጥሮስ ጭንቀት ብዙ ነገር ከማሰብ የመነጨ ነው፡፡ 'ኪሩቤል በፊትህ ግርማ እንዳይቃጠል ፈርተው በፊትህ ሲቆሙ በክንፎቻቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ፡፡ ታዲያ እኔ እጠብልኝ ብዬ እንዴት ደፍሬ እግሬን እሠጥሃለሁ? ሱራፌል የልብስህን ጫፍ የማይነኩህ ጌታ የእኔን እግር እንዴት ታጥባለህ? በባሕር ላይ በአንተ ትእዛዝ የተራመድሁት አይበቃኝም? እንዴት እግርህን ልጠብህ ትለኛለህ? ይህንን ዕዳ እንዴ እሸከመዋለሁ?' የሚል ጽኑ ጭንቀት ያዘለ ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታ ግን ዕውር ባበራባቸው እጆቹ እግር አጠበባቸው፡፡ ሸክላ ሠሪው አጎንብሶ የሸክላውን እግር አጠበ፡፡ ሰውን ከምድር አፈር የፈጠረው አምላክ ትቢያውን በክብር አስቀምጦ እግሩን አጠበው፡፡ ጌታችን ያጠበው ከሰዓታት በኋላ እግሬ አውጪኝ ብለው ጥለውት የሚሸሹትን የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ነበረ፡፡ ለአንድ ሰዓት እንኳን አብረውት ሊተጉ የማይችሉትን ተማሪዎቹን እግር አጠበ፡፡ ጥለውት እንደሚሔዱ እያወቀ 'ንጹሐን ናችሁ' ብሎ አወደሳቸው፡፡ 'ወደ አብ እንደሚሔድ አውቆ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው' እንደሚል ምድር ላይ በቀረችው ጊዜ ያልከፈለው የፍቅር ዕዳ እንዲኖርበት አልፈለገምና ጊዜውን ለመውደድ ተጠቀመበት፡፡ የሚወዳቸውን ደቀ መዛሙርት እግራቸውን አጥቦ በፍቅር ተሰናበታቸው፡፡ ጌታ ሆይ የእኔንስ እግር የምታጥበው መቼ ነው? በእውነት በምድር ላይ ከእኔ እግር በላይ የቆሸሸ አለ? ያልረገጥሁት የኃጢአት ጭቃ ፣ ያልነካሁት የበደል ቆሻሻ እንደሌለ አታውቅምን? 'በክፉዎች ምክር የሔደ' እግሬን የማታጸዳው ለምንድን ነው? (መዝ. 1፡2) 'የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም' ብለህ የለምን? እውነት ነው ፤ እግሬን ከኃጢአት ከከለከልክልኝ ሌላውን አካሌን ማዳንህም አይደል? አጥብቀህ ከምትጠላቸው ነገሮች መካከል አንዱ የሆነውን 'ወደ ክፉ የሚሮጥ እግሬን' የማታጥብልኝ ለምንድን ነው? (ምሳ. 6፡18)እባክህን እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ፡፡ በእርግጥ የሐዋርያትን የቆሸሸ እግር በውኃ እንዳጠብከው አስበን አደነቅን እንጂ በማግሥቱ ደግሞ የዓለምን ኃጢአት በደምህ አጥበሃል፡፡ ከዳንሁ በኋላ የቆሰልሁትን ፣ ከታጠብኩ በኋላ ያደፍሁትን እኔን በከበረ ሥጋና ደምህ ከኃጢአቴ እድፍ ታጥበኝ ዘንድ ነው ልመናዬ፡፡ በጌታ እጅ የታጠበው የሐዋርያት እግር እንዴት የታደለ ነው? በእሱ ስለታጠበ ዓለምን ዞሮ ወንጌል ለማዳረስ የቻለ እግር ሆነ፡፡ ጌታ ያላጠበው እግር ወንጌል ለዓለም አያደርስም፡፡ ባልታጠበ እግራችን ብንዞር እኛ እንጂ ወንጌል ዓለምን አይዞርም፡፡ ስለዚህ ሐዋርያ ሊሆን የሚሻ ሁሉ ጌታ ሆይ እግሬን እጠብልኝ ብሎ መለመን አለበት፡፡ ወንጌሉም 'የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ' ይላልና ክርስቶስ ደቀ መዝሙሩ ሊሆኑ ለሚወዱ ሁሉ እግራቸውን ማጠቡን አሁንም አያቋርጥም፡፡ ጌታ ያጠበው እግር ምን ይሆናል ካልከኝ 'የሚያምር እግር ይሆናል' እልሃለሁ፡፡ ሐዋርያት እግራቸው እጅግ ያምር ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ በእግሩ እብጠት የማይንቀሳቀሰው ቅዱስ ያዕቆብ ሳይቀር እግሩ ያማረ ነበር፡፡ ምክንያቱም 'መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው?' ተብሎ ተጽፎአል፡፡ ሮሜ 10፡15 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሚያዝያ 24 2016 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም ፤ ፳ኤል #share #share ▫️@diyakonhenokhaile https://t.me/diyakonhenokhaile
Show all...
00:20
Video unavailableShow in Telegram
"እጅግም አዝነው እያንዳንዱ፦ “ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን?” ይሉት ጀመር" ማቴ. 26:22 ስንት የአጥቢያ ኮከቦች ለአንተ ዘምረውልህ ወደቁ በሰማይ መቅደስህ አጥነው በትዕቢት ረግፈው አለቁ እፈራለሁ እኔም ለራሴ መንገዴን ንገረኝ ጌታ ጠዋት በዘመርሁበት አፍ እንዳልሳደብ በማታ #share #share ▫️@diyakonhenokhaile https://t.me/diyakonhenokhaile
Show all...
Share 'TORBAN DHUKKUBBII AUHHCAGG.pdf'
Show all...