cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን መዝሙሮች ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። 👥 ✅ @yemezmurgetemoche 📝ለማንኛውንም ሀሳብናአስተያየት ✅ @KIDAN_MEHRET_ENATEbot ለማስታወቂያ ስራዎች ✅ @gutaitagu16 የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን

Show more
Advertising posts
18 920
Subscribers
+10124 hours
+4327 days
+1 39230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

06:48
Video unavailableShow in Telegram
Show all...
0df9ffe3409286b22413edbc533e7372.mp431.87 MB
9🙏 2💯 2
Photo unavailableShow in Telegram
​​✝️🌹 በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ ቅዱስ ላሊበላ: ቅድስት አፎምያና ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ ይከበራሉ:: እንኳን አደረሳችሁ፣አደረሰን። አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ በረከት ይክፈለን:: አሜን:: ❤️🌹❤️.....................🕯
Show all...
🙏 20 15🥰 8👏 8🕊 4

06:09
Video unavailableShow in Telegram
Show all...
13cd8662ab5c7a31857b3dedd0372161.mp425.98 MB
9👍 2
! #ሰኔ_12_ቅዱስ_ሚካኤል ! 🔴👉ሚካኤል ማለት <<መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር)፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው›› ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እርሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ፣ ርኀሩኅ፣ ኃያልና ረቂቅ ማንም እንደሌለ የሚያመለክት ነው፡፡ 🔵👉ቅዱስ ሚካኤል ሌሎች መጠሪያዎች አሉት፤ እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣...›› ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸና ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡ 🔶👉መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡ መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታልና በእርሱ አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡ 🔷👉ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ፣ በጸሎቱ ተማጽኖና በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ሙሴንና እስራኤልን በሲና በረሃ (ዘፀ.23÷20-22) (ዘፀ.12÷15-20) በኢያሪኮ (ኢያ.፭÷፲፫-፲፭) ፤ ከአሞራውያንም እጅ ሕዝቅያስን እንደረዳቸው ተጽፏል (ኢሳ.፴፯÷፴፮) :: 🔸👉በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፫ ላይ << የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል፡፡ 🔴👉በዚሁ የመጽሐፍ ክፍል ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩ ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ታላቅነቱን፣ ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡ ❗️👉በአጠቃላይ በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ፤ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ 🔵👉በዘመነ ሰመዕታትም ሰማዕታትን በተጋድሎ ያጸናቸው ይህ ሩኅሩኅ መላክ እንደሆነ በእነ ቅዱስ ፋሲለደስ እንዲሁም በእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገድላት ላይ በሰፊው ተገልጿል፡፡ 🔵👉የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ12 ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዓበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡፡ 🔹👉እነዚህም ኅዳር 12 ቀን ቀጥሎ ሰኔ 12 ቀን ከዚያም ነሐሴ 12 ቀንና ታኅሣሥ 12 ቀን ናቸው፡፡ 🔴👉 ሰኔ 12፡- በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው እንላለን፤ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፤ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል፡፡ (ሄኖ.፮÷፭፣፲÷ ፲፪) 🔻👉ሰኔ 12 ስለምንድን ነው የምናከብረውው ካልን :- 🔹👉ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ዕለት እና ለፍጥረታት ሁሉ ምህረትን ከእግዚአብሔር የሚጠይቅበት ዕለት ነው፡፡ 🔷👉ቅድስት አፎሚያን ከእደ ሰይጣን ያዳነበትና የረዳበት ዕለት ነው፡፡ 🔹👉ግብፅ ውስጥ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት ነው፡፡ 🔹👉የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ፣ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን፣ ርኀሩኀና ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከሞት ያዳነበት፣ የሞቱን ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት የመታሰቢያው ዕለት ነው፡፡ 🔹👉ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ያሳረገበት ዕለት ነው። 🔵👉መልአኩ የሠራውን ሥራ፣ የክብሩንና ገናንነቱን ጽፈንለመጨረስ የሚቻለን አይደለም፡፡ እንዲሁ በጥቅሉ ጸሎቱ እና በረከቱ፣ ተራዳኢነቱም ሀገራችንና ሕዝባችንን ይሁንልን🙏 አሜን! ! እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን !
Show all...
29🙏 9👍 7
#ኦ_ሚካኤል ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/ ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/ ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/ የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን
Show all...
ኦ_ሚካኤል_O_Mikael_edgXuyv_smM_140.mp37.91 MB
_ይበራል_በክንፉ_Yiberal_Bekinfu_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_us_uu9Tw0eQ_140.mp39.33 MB
🥰 33👍 16🙏 12 4🔥 2👏 2💘 2👌 1

🌷እንኳን አደረሳችሁ!!! ===================
✨ሚካኤል አባቴ ✨ሚካኤል ወዳጄ ✨ሚካኤል ሞገሴ ✨ትልሀለች ነፍሴ!! የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት፣ በረከት፣ ጥበቃና ምልጃው አይለየን ሕዝባችንን ከመከራ ሀገራችንን ከጥፋት ይታደግልን
Show all...
🙏 47 19🥰 15😘 6🕊 4👍 3

“እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ” - ትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እንኳን ለሊቀ መለአኩ ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። መልካም በዓል! ❤️🙏🏽
Show all...
69🙏 24🥰 5❤‍🔥 4👍 2