ተዋሕዶን እንወቅ።
Open in Telegram
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኲሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድኅነነ እምዕለት እኪት ወባልሐነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ጸሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማዕታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።
Show more2 369
Subscribers
-124 hours
-117 days
+330 days
Posts Archive
2 369
Repost from SSC ቅድመ ግቢ ጉባኤ
+1
#ድምጸ_ናብሊስ መጽሔትን ይህን QR Code Scan አድርጋችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ ወይም ከታች በምናስቀምጣቸው ማስፈንጠሪያዎች ማግኘት ትችላላችሁ። በPDF መልኩ ከጥቂት ቆይታ በኋላ እዚሁ ይለቀቃል።
በCanva ለማግኘትና ለማንበብ | በGoogle Drive ለማግኘት
2 369
Repost from SSC ቅድመ ግቢ ጉባኤ
የSSC ቅድመ ግቢ ጉባኤ ምን እንዳዘጋጀ ሰምታችኋል ኣ?!🤩 የተለያዩ ነፍስን የሚያለመልሙ፥ መንፈስን የሚያድሱ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችን በውስጧ የያዘችውን #ድምጸ_ናብሊስ የተሰኘች ድንቅ መጽሔት አቅርቦላችኋል።
ስለ ድምጸ ናብሊስ ይዘት ጥቂት እንንገራችሁ። በመጀመሪያዎቹ ገጾቿ እንዴት ስያሜዋን እንዳገኘች በመተረክ የጉባኤውን አሁናዊ ሁኔታ ከምስሎች ጋር በአጭሩ ታስቃኘናለች። ቀጥላም ቤተክርስቲያን ሐምሌ 24 ቀን መታሰቢያውን አድርጋለት የምትዘክረውን የ12 ዓመት ብላቴና በሆነው በአባ ኖብ የሕይወት መዓዛ ትማርከናለች።
የቤተ ክርስቲያናችን ውበት ከሆኑት ፍሬ ቅዳሴያት መካከል ቅዳሴ ባስልዮስን በጥቂቱ ትዳስሳለች። አክላም እናስተውል በሚል አምዷ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ጥቅስ ይዛ ሕይወታችንን በቅዱሱ መጸሐፍ መነጽር እንድንገመግምው ታሳስባለች። ዘመነ ክረምትን የሚመለከት ጽሑፍንም አካታለች።
በመቀጠልም በግቢ ጉባኤያችን በአገልግሎት ከቆየችዋ ከእኅታችን ቡሩክታዊት ጋርም ለብዙዎቻችን አስተማሪ የሆነ ቃለ መጠይቅን ይዛለች። በመጨረሻም ከአበው አንደበት ስለ ንስሐ የተጻፉ ጽሑፎችን አስነብባን ለአሁኑ በዚህ አበቃን ለቀጣዩ ቅጽ ያድርሰን በማለት ታጠናቅቃለች።
2 369
Repost from SSC ቅድመ ግቢ ጉባኤ
+3
#ድምጸ_ናብሊስ ነገ ኃሙስ ሐምሌ 24 ትለቀቃለች። ከቀኑ አሥር ሰዓት በማኅበራዊ ሚዲያ ትሥሥር ገጾቻችን ይጠብቁ።
2 369
Repost from SSC ቅድመ ግቢ ጉባኤ
“ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ። — እናቴ ሆይ! ገድላችንን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ።”
ዛሬ የምናከብረው በዓል ቅዱስ ገብርኤል የሦስት ዓመቱን ብላቴና ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን በክርስቶስ በማመናቸው ምክንያት አላዊው ንጉሥ እንዲቀጡበት ያዘዘውን የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ ያዳነበትንና የእግዚአብሔርን ኃይል ያሳየበትን በዓል ነው። ያንን ሁነት በቅድስት ኢየሉጣ ቦታ ሆነን ከዚያ ሁነት ልንማር የምንችለውን እናያለን።
በክርስቶስ በማመኗ ምክንያት እለእስክንድሮስ የሚያደርስባትን ፈርታ ከሀገር ሀገር ስትሸሽ የነበረችውን ኢየሉጣ አንዲት ሀገር ላይ ስትደርስ ያዛት። ክርስቶስን ትታ የሱን ጣዖቶች እንድታመልክም ጠየቃት። ልጇን አስጠርታ እንዲጠየቅ ስታደርግም ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው። በዚህም ንጉሡ ተበሳጭቶ ብዙ መከራንና ሥቃይን አደረሰባቸው። የታመኑለት ክርስቶስ ግን አልተዋቸውም፤ ምንም ጉዳት እንዳልነካቸው አድርጎ ያስነሣቸው ነበር።
ከዚህም በኋላ በትልቅ ጋን ውኃ ጨምረው እንዲያፈሉት አዘዘ፤ እናቱ ኢየሉጣም የፍላቱ ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጎድ ነበርና ድምጹን ስትሰማ ፍርሃት አደረባት። በዚህ ጊዜ ልጇ የእምነቷን መጉደል አይቶ “አናንያን፥ አዛርያን ሚሳኤልንም ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ይችላልና አትጠራጠሪ” አላት፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ። በዚህ ጊዜ ፍርሃቷ ጠፋላት፤ እንዲህም አለችው፤ “ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፥ አባቴ፥ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም።”
ተያይዘውም ወደ ጋኑ ገቡ። ስለ ስሙ መከራን የተቀበሉለት አምላክም “ያገለገሉትን አይረሳምና” ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው። ደርሶም በትዕምርተ መስቀል ጋኑን ቢባርከው ቀዘቀዘላቸው። አንድም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጋኑ በደኅና ወጡ። ከወጡም በኋላ ንጉሡ ብዙ መከራን አድርሶባቸው ጥር 15 ቀን አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው የክብር አክሊልን ተቀብለዋል።
ጌታችና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ዘሪውን ምሳሌ ሲያስተምር በጭንጫ ላይ ስለ ወደቀው ዘር ሲናገር እንዲህ ይላል፤ “በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው፤ ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፥ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።” (ማቴ. 13፥20-21) የቅድስት ኢየሉጣ ፍርሃት በጭንጫ ላይ እንደወደቀው ፍሬ ናት ለማለት ባያስደፍረንም (አይደለችምም) ወደኛ ሕይወት ለማምጣት ሁነቱን እንጠቀመው።
በዚህ ዓለም ስንኖር ብዙ የሚያስጨንቁን የሚያሳስቡን ነገሮች አሉ፤ ስለነዚያ ነገሮች ብለን ግን ያመነውን ጌታ መካድ አይገባንም - በጭንጫ ላይ የወደቀውን ዘር እንዳንመስል። እስካሁን ድረስ በሕይወት ያቆየን አምላክ አሁንም እንደማይተወን እስካሁን ማቆየቱ ምልክት ነው። ቅዱስ ቂርቆስ “አናንያን፥ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል” እንዳለ እነርሱን ያዳነ አምላክ እኛንም አይረሳንም - አይተኛም፤ አያንቀላፋም። በተስፋ ከተጠባበቅነው ለነ ኢየሉጣ ቅዱስ ገብርኤልን እንደላከ ለኛም የሚረዳንን መልአክ ይልክልናል። ለኛ እንደ ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጸናን የሚያበረታን አጠገባችን ያለው ጓደኛችን ነው፤ ስንዝል “አይዞህ/አይዞሽ” እያለ የሚያበረታን እሱ ነው።
“በኃይሉ ብዛት በትዕግሥቱ ጽናት የጸጋውን ብዛት ለእናቱ መምህር በሆነ በሦስት አመት ሕጻን የገለጠ እግዚአብሔር ይመስገን።”
2 369
በተቻለ አቅም የአምልኮአችንን ውበት ለማሳየት እንሞክራለን ... ያው ይሄ ሁሉ ችግር የመጣው ካህኑም ምዕመኑም በአብዛኛው አምልኳችንን በደንብ ስላልተረዱት ነው ብዬ አስባለሁ ...Daily አንድ አንድ ጣል እናደርጋለን እንደ እስካሁኑ
@amlake_birhan
@amlake_birhan
ተቀላቀሉ!
2 369
ጎስቋላ ነፍሴ ሆይ የወደደሽ አንድዬ እርሱ ይፈልግሻል፣ ነፍሴ ሆይ የፈጠረሽ አንድዬ እርሱ ይጠራሻል፣ ድምፁን ያሰማሻል፣ ነፍሴ ሆይ የሞተልሽ አንድዬሽ ይወድሻል፣ ነፍሴ ሆይ ወደ ሞተልሽ ወደ ሚፈልግሽ አምላክሽ ተመለሽ ድምፁንም ስሚ እርሱ ብቻ ይወድሻልና እርሱን ብቻ ውደጅ አንቺም አባቴ በዪው እርሱም ልጄ ይበልሽ ።
2 369
Repost from አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE
5 ሰዎች በዕጣ ለመሸለም አስበናል ።
1ኛ ዕጣ ቅዱስ ጳውሎስ
2ኛ ዕጣ ድርሳን ዘቅዱስ አትናቴዎስ
3ኛ ዕጣ ቅዱስ ኒፎን
4ኛ ዕጣ ፍና ቅዱሳን
5ኛ ዕጣ ፍኖት መንፈሳዊት
ዕጣው ውስጥ ምትገቡት የቻናላችን Link ለ50 ኦርቶዶክሳውያን inbox join አድርጉ ብላችሁ ስትልኩ ነው።
Link👇👇👇👇👇👇
https://t.me/BetMetsahfte
☝️☝️☝️☝️☝☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ለኦርቶዶክሳውያን ከላካችሁ በኃላ የዕጣችሁ Code @orthokiha ውሰዱ! ዕጣው ነገ 10:00 ይወጣል!
2 369
Repost from Orthodox Apologetic Theology
ፖርኖግራፊ እና መዘዙ ፥ ክፍል ፪ሰዎች ለምን ፖርኖግራፊ ይመለከታሉ? ከብዙዎቹ ምክንያቶች ጥቂቶቹን ለመመልከት እንሞክር።
1.ጭንቀት/ድብርትብዙውን ጊዜ በድብርት ውስጥ ያሉ ሰዎች በፖርኖግራፊ ሱስ የሚጠቁ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳዩናል።በስራ ቦታቸው ላይ ፖርን የሚመለከቱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በስራ ያልተወጠሩ ወይንም ስራቸውን እየጠሉት የሚሰሩ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል። በሌላ መልኩ በሕይወታቸው ከባድ ጭንቀት ያለባቸውና ያልፈቱት አስጨናቂ ነገር በልባቸው ያለባቸው ሰዎች ሃዘናቸውን ለመርሳትና ጊዜያዊ ደስታ ለማግኘት ይጠቀሙበታል
2.በጓደኛ ግፊትለ10 አመት ያህል በፖርኖግራፊ ሱስ የተሰቃየች አንዲት እህቴ እንዴት ወደዚህ ሱስ እንደገባች እንዲህ ስትል ትናገራለች
“የዪኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ዶርም ውስጥ ጓደኖቼ ተሰብስበው ፖርን ይመለከቱ ነበር።እኔ ግን ሁሌም እቃወማቸው ነበር።ከሆነ ጊዜ በዋላ ግን ሳላስበው እነሱን መቀላቀል ጀመርኩ። ካዛ በዋላ ከነሱ የባስኩ ተመልካች ሆንኩኝ”።የሰዎች ልጆች በዙዎች በሚያደርጉት የመሳብ ዝንባሌ አለን።ታዳጊዎችና ወጣቶች በጓደኞቻቸው ግፊት ወደዚህ ህይወት ሊገቡ ይችላሉ።
3.ብቸኝነትብዙውን ጊዜ ብቸኝነትን የሚያዘወትሩ በተለያየ ምክንያት ከሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ የማይችሉ ሰዎች በዚህ ሱስ ሊጠቁ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።
4- ሱስአንዳንዶች ፖርኖግራፊን የሚመለከቱት ሱሰኞች ስለሆኑ ነው።ሱስ ማለት ፈልገን የገባንበት እየጠላነውም ቢሆን የምናደርገው ነው። ማንኛውም ሱስ ሲጀመር በፍላጎት ሲሆን የሚቀጠለው ግን ያለ ፍላጎት ሊሆን ይቻላል። ፖርኖግራፊ ልክ እንደማንኛውም አደንዛዥ ዕጽ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ አቅም አለው።በአንድ ወቅት ስለ ፖርኖግራፊ ሱስ ዶክተር ስዩም እንዲህ ይላሉ “ብዙዎች ፖርኖግራፊ ሳያዩ መተኛት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሱስ አይሆንም ብሎ የመናገር ድፍረት አላቸው። ነገር ግን ፖርኖግራፊ ከሌሎች ሱሶች ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ መልኩ ወደ ሱስነት ያድጋል፡፡ አንድ ሰው ፖርኖግራፊ ሲመለከት ደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች [hormons] አሉ የሚገርማቹ እነዚህ ቅመሞች አንድ ሰው ኮኬንና ሄሮዊን የሚባሉትን አደዛዥ ዕፅ ሲጠቀም በደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች ናቸው፡፡ እኚህን እጾች ስንወስድ ደማችን ውስጥ የሚለቀቁት ቅመሞች ፖርኖግራፊ በምናይበት ጊዜ ከተለቀቁ ፖርኖግራፊ ሱስ አይሆንም ማለት አንችልም ፡፡ ሱስ ለመባል የግድ በአፍ በኩል ወደ ውስጣችን መግባት የለበትም፡፡ አሁን ባለን መረጃ pornography is not like a drug it is a drug [ፖርኖግራፊ አንደ አደንዛዣ እፅ ሳይሆን እራሱ አደንዛዥ እፅ ነው] እንዲያውም መልከ ብዙ እፅ ነው፡፡ ሰው ፖርኖግራፊ ሲያይ ብዙ እፅ በአንድ ላይ እንደወሰደ ነው የሚቆጠረው፡፡ አንድ የኒዩሮ ሳይንቲስት[nuro scientist] አንድ ሰው በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሚፈጅበትን ጊዜ ሲናገሩ አንድን ምስል ለግማሽ ሰከንድ ካየን በኋላ በሚቀጥሉት 5 ና 10 ደቂቃ ወስጥ አንጎላችን ውስጥ መሰረታዊ የሆነ የቅርጽ ለውጥ [nerve restruction] ይፈጠራል ይሄ አይነት ለውጥ ልክ አንድ ሰው አደጋ ሲደርስበት የሚፈጠረውን የቅርጽ ለውጥ አይነት ነው፡፡በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሰከንድ 1/3ኛ ይበቃል አስተውላቹ ከሆነ ለሰከንደ ያየነው ፖርኖግራፊክ ምስል ለአመታት ከአይምሮአችን አይወጣም፡፡ ለምን ካላችሁ epimerphine በተባለው ሆርሞን ምክንያት እንዳይጠፋ ሆኖ ተቀርጿል:: ከዚህም የተነሳ ከአመታት በኋላ እንኳን አይረሱትም በዚህም መክንያት “በቃ አይኔንም ስከድን ስተኛም በመንገድ ላይ ስሄድም የሚመጣብኝ እሱ ነው” እያሉ በመንፈስ ጭንቀት የሚሰቃዪ ወጣቶች ገጥመውኛል”። ከዶክተሩ ንግግር የምንረዳው ነገር እንደቀልድ የሚጀመር ነገር ሕይወትን ሊያበላሽ እንደሚችል ነው።አስቀድሞ መጠንቀቅ ብልህነት ነው። ክፍል ፫ ነገ እንቀጥላለን ለብዙዎች ይዳረስ ዘንድ አካፍሉት ..! https://t.me/orthodox_chrstianity
2 369
Repost from Orthodox Apologetic Theology
ፖርኖግራፊ እና መዘዙ [ ክፍል- ፩ ]በቅድሚያ ግን ፖርኖግራፊ ምንድን ነው? ፖርኖግራፊ ቃሉ የተገኘው πορνογραφία [pornographia] ከሚል የግሪክ ቃል ሲሆን በጥንት ጊዜ የቃሉ ትርጉም ግልጽ በሆነ መንገድ ስለ ሴተኛ አዳሪ መጻፍ ማለት ነበር። ነገር ግን በዚህ ሰዓት ከጽሁፍ ወደ ምስል ከምስል ወደ ቪዲኦ ማደጉን እንመለከታለን። ማንኛውም የወሲብን ስሜት የሚቀሰቅስ ነገር ፖርኖግራፊ ይባላል።ይህም ፊልሞችን፣ ወሲባዊ ታሪኮችን፣ ፎቶዎችን፣ የቃላት ልውውጥን ይጨምራል። ፖርኖግራፊ ሰዎችን በቀላሉ ሱሰኛ የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን ሲጋራና ጫት ሊያደርሱት ከሚችሉት ጥፋት በላይ ከባድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል በግልጽ ለማየት ተችሏል። በዘመናችን ፖርኖግራፊ በቀላሉ ሊገኝ የሚችል መሆኑ ሱሱ እንደወረሽኝ እንዲዛመት አድርጎታል። ስለ ፖርኖግራፊ የተጠኑ ጥናቶች ምን ይላሉ? ስለ ፖርኖግራፊ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ለፖርኖግራፊ ተጋላጭ የሚሆኑት ከ 11 አመት ጀምሮ ነው። ✍️ በየቀኑ ኢንተርኔት ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 25% የሚሆኑት ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ናቸው። ✍️ በአለማችን ላይ ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያገኙ ሰዎች መካከል በፖርኖግራፊ ኢንደስትሪ ውስጥ ያሉ ስዎች ናቸው። [ህሊና የጎደላቸው ሰዎች የሰው ሕይወት በመቅጠፍ ገንዘብ እንደሚያገበሰብሱ አስተውሉ] ✍️ ከኢንተርኔት ላይ download ከሚደረጉ ቪዲዮዎች መካከል 35% የሚሆነው ከፖርኖግራፊ ጋር የሚገናኝ ነው። ✍️ አለም ላይ ካሉ ድህረ ገጾች መካከል 12% የሚሆነው ፖርኖግራፊ ነው። ✍️ ፖርኖግራፊ ወጣቶቿን እየፈጀ ያስቸገራት ሰሜን ኮሪያ በሐገሪቱ ውስጥ ፖርኖግራፊ ነክ የሆኑ ነገሮችን ማሰራጨት በሞት የሚያስቀጣ ነው ስትል ሕግ አድርጋ አውጃለች። በአንድ ወቅት Google አለም ላይ አብዝተው 'sex' የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሀገራት መካከል እናንት ኢትዮጵያውያን ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር። ይህ የሚያሳየን በሀገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ መሆኑን ነው። ይህ ሱስ እንደሌሎች ሱሶች በግልጽ በሱሰኛው ላይ የማይታይ በመሆኑ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት በቂ መረጃ ስለሌለ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነም ይገመታል። ክፍል ፪ ነገ እንቀጥላለን..! ለብዙዎች በማካፈል አድርሱት። https://t.me/orthodox_chrstianity
2 369
Repost from SSC ቅድመ ግቢ ጉባኤ
ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበባችን ጥሩ ሆኖ ሳለ እንዴት መረዳት እንዳለብን ካልተረዳን ለመካዳችን ምክንያት ሊሆን ይችላል። የአበውን የመጻሕፍትን መረዳት ለመያዝ ይህንን ትምህርት ልንማር ይገባናል። ረቡዕ (ሐምሌ 9) ከምሽቱ 2:20 ጀምሮ በዚህ ርዕስ መሠረት እንማማራለን። #እንዳትቀሩ!
“ቅዱሳት መጻሕፍት ማለት የመድኀኒት ሳጥኖች ናቸው፡፡ በመኾኑም አንድ ሰው ለሚያጋጥመው ማንኛውም ዓይነት መከራና ኀዘን ወደ እነርሱ ሔዶ መድኀኒትን ለራሱ ሊወስድ ይገባል።” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
2 369
ዕረፍተ ጴጥሮስ ወጳውሎስን በቅዱስ ጳውሎስ ቤት እናክብር! ቅዳሜ አይቀርም!
#አድራሻ፦ ኮልፌ ልኳንዳ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ አጠገብ
ደርሳችኹ ቦታው ከጠፋችኹ በዚኽ +251922943065 ስልክ ደውሉና ይመራችዃል።
