cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋሕዶን እንወቅ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኩሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድህነነ እምዕለት እኪት ወባልሀነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ፀሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማእታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።

Show more
Advertising posts
947
Subscribers
No data24 hours
+597 days
+25730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!" ይህ ሰላምታ ለሃምሳ ቀናት ይዘልቃል። የዚህ ሰላምታ ልውውጥ ታሪክ የሚጀምረው ከመጀመሪያዋ ምዕተ ዓመት ከነበረችው ከጥንት ክርስቲያኖች ጀምሮ ሲሆን ለትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ሲገናኙ አይሁዳውያን "ሻሎም" ወይም ሰላም ብለው ሰላምታ እንደሚለዋወጡት ሁሉ ክርስቲያኖቹም "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል" ብለው ሰላምታ ሲሰጡ መላሹ ደግሞ "በአማን ተንስአ እሙታን ፤በእውነት ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል" በማለት ይመልሳል። ይህ ሰላምታ በሁሉም በምስራቁም በምዕራቡም ኦርቶዶክሳውያን ብሎም በአንግሊካንም ቤተክርስቲያን ከትንሳኤው ጋር የፋሲካ ሰሞን ሰላምታ እንደሆነ ቆይቷል። አሁንም የሚተገበር ሰላምታ ነው። ነገር ግን መቼ እንደሆነ ባይታወቅም ሰላምታው ከዘወትር ሰላምታ ወደ ዘመነ ፋሲካ ብቻ ሰላምታ ተለወጠ። በምዕራቦቹ ክርስቲያኖች ሰላምታ ሰጪው Christ is Risen!" ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ወይም "The Lord is Risen!" እግዚእ ተንስአ እሙታን ሲል ሰላምታ መላሹም "Truly, He is Risen," በአማን ተንስአ፤በእውነት ተነስቷል "Indeed, He is Risen," ወይም በእርግጥ ተነስቷል "He is Risen Indeed እርግጥ ነው ከሙታን ተነስቷል ይላል። Christ is Risen!" or "The Lord is Risen!", and the response is "Truly, He is Risen," "Indeed, He is Risen," or "He is Risen Indeed. ይህ ሰላምታ ከሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት የእኛ ቤተክርስቲያን የሚለየው ረዘም ብሎ "ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ ዓግአዞ ለአዳም፤ ሰላም፤ እምይእዜሰ፤ ኮነ ፍሰሀ ወሰላም በማለት በጥልቅ ሚስጢር ሰላምታ ላይ ይውላል። በዚህም የሀገርኛ ነገረ ክርስቶስ ትምህርት (Ethiopic Christology) እድገትን አንድ ማሳያም አድርገን መውሰድ እንችላለን። የጌታ ሞትና ትንሳኤ በቤተክርስቲያን ታሪክም ይሁን በነገረ መለኮት አስተምህሮ እድገት (Development of theological teachings) ትልቁን ስፍራ ይይዛል። በስልታዊ ነገረ መለኮት (Systematic Theology) ትምህርት ውስጥ "ዶግማ አይቀየርም ነገር ግን ያድጋል" የሚባለው ለዚህ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ በ367 ዓ.ም በዛሬዋ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፈው ቃለ ምዕዳን (ልፋፈ ጽድቅ) በ45ኛ ደብዳቤው  የኦርቶዶስክ ቤተክርስቲያን በቀኖና የምትቀበላቸውን በዝርዝር 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍትን መሆኑን ያወጀበት ቀን ነው። ከዚያም ወደ ሁሉም መንበረ ፕትርክናዎች (Patriarchate) ልኳል። Priest : Christ is risen from the dead! ካህን    : ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን! People : By the highest power and authority! ሕዝብ     : በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን! Priest : He chained Satan! ካህን    : አሰሮ ለሰይጣን! People : Freed Adam! ሕዝብ     : አግዐዞ ለአዳም! Priest : Peace! ካህን    : ሰላም! People : Henceforth! ሕዝብ     : እምይእዜሰ! Priest : Is! ካህን    : ኮነ! People : Joy and Peace! ሕዝብ     : ፍስሐ ወሰላም      መልካም በዓል!
Show all...
🙏 4🥰 1
#ስለሁላችንም_ቤዛ_የተደረገ_ትንሣኤ_ስለሆነ 👉. ከዚህ በፊት ስለሁላችን (ለዓለም) የሞተ የለም። ቅዱስ ጳውሎስ “እስመ ኵሉ ፆሮ ይፀውር – ሁሉም የራሱን ሸክም ይሸከማል” ብሎ እንደተናገረው (ገላ. 6፥5) አባቶቻችን በራሳቸው ዕዳ ሲሞቱ ምንም ዕዳና በደል የሌለበት ክርስቶስ ግን ለፍጥረት ሁሉ ዕዳ ሊደመስስ በፈቃዱ ሞተ። ሞቱ ስለ ሁላችን እንደሆነ ሁሉ ትንሣኤውም የሁላችን ሕይወት ነው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን የአይሁድ ፍርሐት ነው። አይሁድ “በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ” ማለቱን ሰምተናል፤ ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው እንዳይሰርቁት፣ ‘ተነሣም’ ብለው ለሕዝብ እንዳያስተምሩ. . .” ነበር ያሉት። (ማቴ. 27፥62-65) 👉. ይህ የአይሁድ ፍርሐት የዲያብሎስም ጭንቀት ነው። ጌታችን ክብርት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ሲለያት ዲያብሎስ ነፍሱን በሲኦል ውጦ፣ ሥጋውን በመቃብር ረግጦ ማስቀረት እንዳልተቻለው ስለተረዳ አይሁድን እንዲህ እንዲሉ አድርጓቸዋል። 👉. በሌላ በኩል ትንሣኤውን ዐይተው ያምኑ ዘንድ ይህን ማለታቸው የጌታ ፈቃድ ነበር፤ አምነው ባይጠቀሙበትም የጌታ ትንሣኤ ላመኑትም ላላመኑትም ሕይወት ነውና። ስለዚህ ነው የጌታችንን ትንሣኤ በኵረ ትንሣኤያችን የምናደርገው። ትንሣኤ ዘጉባኤ ?. በእሳት ተቃጥለው፣ በአራዊት ተበልተው ወደ ዐመድነትና አፈርነት የተለወጡ ሰዎች፣ በዕለተ ምጽአት ከሞት የሚነሡት እንዴት ነው? እንደገና ሰው ሆነው ይፈጠራሉ ማለት ነው? 👉. በመጀመሪያ ካለመኖር ወደ መኖር እንድንመጣ ያደረገን ጥበበ እግዚአብሔር ነው። ያለዚያማ እንዴት ሆኖ ነው ከአባት የተከፈለው ዘር ከሴት ደም ጋር ተዋሕዶ፣ ብጥብጥ የነበረው ረግቶ፣ የአጥንት ምሰሶ የጅማት ማገር ተሠርቶለት ቅዱስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሆነው? በእርግጥ እንዲህ ሆኖ የተጀመረው ህልውናችን በሞት ሲቋረጥ እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በመቃብር ውስጥ ቀልጦ ለመቅረት እንጂ ተመልሶ ለመብቀል አልነበረም። የሰው ልጅ እንደ አዝርእት ከሞተና ከፈረሰ በኋላ አካል ኖሮት የሚነሣ ነው። ያለ ዝናም አዝርእት ምን ትንሣኤ አላቸው? ያለ ክርስቶስ ደም መፍሰስስ የሰው ልጅን ማን ከሞት ሊያስነሣው ይችላል? የጌታችን ደም ሲፈስ ግን መቃብራት ተከፈቱ፣ ዐለቶች ተሰነጣጠቁ፣ ከሙታን ወገን ብዙዎቹ ተነሡ። በዚህ ጊዜ፦ “ቦኑ ለከንቱ ፈጠርኮ ለኵሉ እጓለ እመሕያው – በውኑ ሰውን ሁሉ ለከንቱ ነገር ፈጥረኸዋልን?” የሚለው የአባቶቻችን ጥያቄ ምላሽ አገኘ። (መዝ. 88፥47) 👉. ሞት እንደ ገበሬ፣ መቃብር ደግሞ እንደ እርሻ ሆኖ የሰው ልጆች በዚህ ምድር በመበስበስ በመፍረስ እንዘራለን። እንዲህ ካልሆንን ትንሣኤ የለንም። በኋላም ተለውጠን በአዲስ ሥጋ እንነሣለን። ባሕርይ መልአካዊ፣ ባሕርይ ሥጋዊ፣ ባሕርይ እንስሳዊ ለሁላችንም በተፈጥሮ ይሰጡናል። ስንሞት ባሕርይ እንስሳዊ እና ባሕርይ ሥጋዊ ይለዩናል። ባሕርይ መልአካዊ ግን በባሕርዩ ሞት ስለሌለበት አብሮን ይኖራል። በምንም ዓይነት ሞት ብንሞትም ይህ የማይቀር ጉዳይ ነው። (1ኛ ቆሮ. 15፥35-44) ትንሣኤ የሰው ልጅ ሠላሳ፣ ስድሳና መቶ ፍሬ አፍርቶ የሚታይበት ወቅት ነው። 👉. ዕፅዋትና አዝርእት ከፈረሱ ከበሰበሱ በኋላ አንዱ በራሱ፣ ሌላው በጎኑ፣ ሌላው በሥሩ ያፈራል። ከሥሩ የሚያፈራው የባለ ሠላሳ፣ ከጎኑ የሚያፈራው የባለ ስድሳ፣ ከራሱ የሚያፈራው የባለ መቶ ምሳሌ ነው። ይህም በቤተክርስቲያናችን “#ዳግም_ልደት” ተብሎ ይጠራል። 👉. የሰው ልጅ ተፈጥሮዎች ሁለት ዓይነት ሲሆኑ እነዚህም #ጥንተ_ተፍጥሮ እና #ሐዲስ_ተፈጥሮ ይባላሉ። ጥንተ ተፈጥሯችን በአዳም በኩል የተደረገው ተፈጥሯችን ሲሆን ሐዲስ ተፈጥሮ የምንለው ደግሞ በክርስቶስ በኩል የተደረገውን የባሕርያችንን መታደስ ነው። ልደታችን ግን ሦስት ወገን ነው፡፡ አንደኛው ሥጋዊ፣ ሁለተኛው መንፈሳዊ፣ ሦስተኛው ደግሞ ትንሣኤ ዘጉባኤ ነው። ይህም “#ልደተ_ሙታን_እመቃብር” ይባላል። ይኸውም የሙታን ከመቃብር መወለድ ማለት ነው። በዕለተ ምጽአት ማለትም በትንሣኤ ዘጉባኤ ከሞት የምንነሣውም በዚህ መልኩ ነው። ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ #በትንሣኤው_ለትንሣኤ_ያብቃን! 🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱 ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን። 🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺 ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜🌺💫🌺💫🌺 ምንጭ -ኰኲሐ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት
Show all...
🙏 3👍 2
⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜🌺💫🌺 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን። ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 💐 ነገረ ትንሣኤ 💐 👇 #በሊቀ_ሊቃውንት_ስምዐ_ኮነ_መልአክ 👉. በዓለ ትንሣኤ #ፋሲካ እየተባለ የሚጠራበት ምክንያት ፋሲካ ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ‘ፓሳህ – ማለፍ’ ማለት ነው። ምክንያቱም በዓለ ትንሣኤ፦ #ሞት_ከእስራኤል_መንደር_ያለፈበት_ስለሆነ 👉. ግብፅ በረሃብ እንዳትመታ ፈርዖናቸው ያደረገው ነገር ባይኖርም መጻተኛውና ወደ ወኅኒ የወረደው ዮሴፍ ግን የረሃብ ሞትን ወደ ግብፅ እንዳይገባ ከለከለው። ዳሩ ግን ዮሴፍ ሲያልፍ የዮሴፍን ታሪክ የማያውቅ ሌላ ፈርዖን ተሾመና በእስራኤል ላይ የሞት ሕግ አወጣ። (ዘጸ. 1፥11) 👉. “በአንተና በሴቲቱ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ። እርሱ ራስ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰና ሰኰናውን ትነድፋለህ” (ዘፍ. 3፥15) ተብሎ የተነገረለት ዲያብሎስ ራስ ራሱን የሚቀጠቅጥ ወንድ እንዳይወለድ በማሰቡ ሕፃናትን ከማሕፀን እያስቀረ፤ ለመቃብርም እያቀበለ እስከ ሙሴ ዘመን ደረሰ። ከሙሴ መምጣት በኋላ ሞት የእስራኤልን መንደር ለቅቆ ወደ ግብፃውያን መንደር እንዲገባ ምክንያት የሆነው ዕለትም #ፋሲካ ይባላል፡፡ በዚህ በዓል ላይ እስራኤላውያን የበግ ጠቦት አርደው የቤታቸውን ጉበን የቀቡትን ደም የተመለከተው ሞት እነርሱን ትቶ የግብፃውያንን የበኵር ልጆች ገደለ። እስራኤላውያን “ቀሳፊያችን ተቀሰፈ” ሲሉ በዓላቸውን ‘ፋሲካ’ አሉት። 👉. እኛም በሐዲስ ኪዳን የጌታችንን ትንሣኤ ፋሲካ የምንለው #ሞት_ከእኛ_ያለፈበት_የመጀመሪያው_በዓላችን በመሆኑ ነው። ስለ ብዙዎች ይቅርታ የፈሰሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም በግብፅ ከተሠዋው በግ ይልቅ የከበረ መሥዋዕት ነውና ያሉትን ከማዳኑም ባሻገር የሞቱትንም ከመቃብር አውጥቷል። በእርሱ ትንሣኤ ሞት ከእኛ ማለፉንና የሰው ባሕርይ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱንም “ለምንት ተኀሥሣሁ ለሕያው ምስለ ምዉታን – ሕያዉን ከሙታን ጋር ስለ ምን ትፈልጉታላችሁ” ከሚለው ኃይለ ቃል እንረዳለን። (ማቴ. 28፥6) 👉. ምዉታን ያላቸውም አጋንንት ናቸው። በጌታችን ትንሣኤ ሰው ከሙታነ ሕሊና ከአጋንንት ተለይቶ ተነሥቷል። “ኦ! አዳም መሬት አንተ ወትገብእ ውስተ መሬት – አዳም ሆይ! ቀድሞም መሬት ነህ፤ ወደ መሬትነትህም ትመለሳለህ” የሚለው አዋጅ አሁን ተቀይሯል። የጌታችን ትንሣኤ ከሚያረጀው ወደማያረጀው፣ ከሚበሰብሰው ወደማይበሰብሰው ሰውነት የተሸጋገርንበት በዓል ነው። ይህ ሁሉ መሸጋገር የተፈጸመው በፋሲካው በግ ምክንያት በመሆኑ ክርስቶስን ፋሲካችን እንለዋለን። (1ኛ ቆሮ. 5፥7) #መሥዋዕተ_ኦሪት_አለፈ_መሥዋዕተ_ወንጌል_ደረሰ #የምንልበት_ወቅት_ስለሆነ 👉. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለደቀ መዛሙርቱ በሰጠበት ዕለት በፋሲካ የተጀመረችውን ሕግ በፋሲካ ይሽራት ዘንድ የሚያልፈውን መሥዋዕተ ኦሪት አስቀድሞ፣ የሚመጣውን መሥዋዕተ ወንጌል አስከትሎ ፋሲካን አደረገ። ለደቀ መዛሙርቱም “ዝ ውእቱ ደምየ ዘይትከአው ለሐዲስ ሥርዓት በእንተ ቤዛ ብዙኃን – ስለ ብዙዎች ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” (ማቴ. 26፥28) በማለት ወደ ሐዲስ ኪዳን መግባታቸውን አስረግጦ ነግሯቸዋል። ስለዚህ የክርስቶስ ትንሣኤ አሮጌውን ትተን ወደ አዲስ ሕይወት የተሸጋገርንበት በዓል በመሆኑ #ፋሲካ እንለዋለን። #የደስታችን_ማረጋገጫ_ስለሆነ 👉. ‹ፋሲካ› ማለት በግእዝ ቋንቋ ‘#ደስታ’ ማለት ነው። ደስታችን የተረጋገጠው በጌታችን ትንሣኤ ሲሆን ፍጻሜውን የሚያገኘው ደግሞ በትንሣኤ ዘጉባኤ ነው። ቤተክርስቲያን ጌታችን በዕለተ ዓርብ በቈረሰው ቅዱስ ሥጋውና ባፈሰሰው ክቡር ደሙ ተመሥርታለች። ምንም እንኳን በሕዝብና በአሕዛብ ፊት ደስታዋን የምትገልጥበት ጊዜ ገና ቢሆንም በትንሣኤው ግን በዝግ ቤት ውስጥ ሆና የክርስቶስን ሰላምታ ተቀብላ ተደስታለች። (ዮሐ. 20፥19) ለዚህም ነው፦ “ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ – ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ደስ ትሰኛለች” እያልን የምንዘምረው። 👉. ቤተክርስቲያን ክርስቶስ የትንሣኤዋ በኵር ሁኖ ተነሥቶላታልና ሊገድሏት በሚጎትቷት ሰዎች ፊት ለሽልማት እንደተጠራ ብላቴና ደስ እያላት ትቀርባለች። (1ኛ ቆሮ. 15፥20) ቤተክርስቲያን ደስታዋን በትንሣኤ ፍጹም እንደምታደርገውም ቅዱስ አርክዎስ በሃይማኖተ አበው 9፥1 ላይ፦ “#በዛቲ_ዕለት_ተፈጸመ_ፍሥሐሃ_ለቤተክርስቲያን – #በዚህች_ቀን_የቤተክርስቲያን_ደስታ_ፍጹም_ሆነ” በማለት ይመሰክርላታል። በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የጌታችን ትንሣኤ ፋሲካ ተብሎ ይጠራል። ጌታችን በኵረ ትንሣኤ የተባለበት ምክንያት 👉. የመጀመሪያው አዳም ለሞትና ለኃጢአት በኵር ሆኖ ነበርና ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ሞት ሲገዛን ኖሯል። (ሮሜ. 5፥10) ቅዱስ ጳውሎስ “ክርስቶስ ላንቀላፉት (ለሙታን) በኵራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል” በማለት ጌታችን የትንሣኤያችን በኵር መሆኑን ነግሮናል። (1ኛ ቆሮ. 15፥20) ከጌታችን በፊት የሞቱና ከሙታን የተነሡ አሉ። ነገር ግን የጌታችን ትንሣኤ ከሌሎች ትንሣኤ የተለየ ነውና #በኵረ_ትንሣኤ (የትንሣኤ መጀመሪያ) ይባላል። 👉. ጌታችን በኵረ ትንሣኤ መባሉም፦ #ሞቱ_ሞትን_ስላጠፋ 👉. የጌታችን ሞት ከሌሎች ሙታን የተለየ ነው። ሞትን በመግደል ድሩን ሳይሆን የችግሩን ምንጭ ሸረሪቱን አጥፍቶታል። ኃጢአት፣ ሞት፣ መቃብር እነዚህ ሦስቱ ተያያዥ ነገሮች ናቸው። ኃጢአት ከሌለ ሞት፣ ሞትም ከሌለ መቃብር አይኖርም። ሞት ሲሞት ሙታን ተነሡ፤ የሞት ጥላ ሲገፈፍ መቃብራት ተከፈቱ። በክርስቶስ ሞት ኃጢአት ከሥሯ እንደተነቀለች ዛፍ ላታፈራ፣ ላትለመልም ለዘለዓለም ተነቀለች። 👉. ሞትም ሙታንን ለቆ ጠፋ፤ መቃብርም ባዶ ሆኖ ተከፈተ። ለዚህ ነው ቤተክርስቲያናችን በቅዳሴዋ፦ “ሞተ ዘቦአ ቀዳሚ ውስተ ዓለም በቅንዓተ ሰይጣን አብጠልከ በምጽአቱ ለዋሕድ ወልድከ መድኃኒነ – በሰይጣን ተንኮል ከልጅህ መምጣት አስቀድሞ ወደ ዓለም የገባ ሞትን በልጅህ ሰው መሆን አጠፋህ” እያለች የምታመሰግነው። (ሥርዓተ ቅዳሴ) #የመጀመሪያው_ሐዲስ_ትንሣኤ_ስለሆነ 👉. ከእርሱ በፊት ከሙታን የተነሡ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በሚበሰብስ ሥጋ ተዘርቶ በማይበሰብስ ሥጋ መነሣት የቻለ ማንም አልነበረም፤ ሌሎቹ ሙታን ለዘለዓለም ሞትን ማሸነፍ በሚችል ሞት የተነሡ አልነበሩምና። (2ኛ ነገ. 13፥21) ክርስቶስ ከመጣ በኋላ የተነሡት እንደነአልዓዛር ያሉትም ዳግመኛ መሞትና መነሣት አለባቸው፤ የጌታችን ትንሣኤ ግን ዘለዓለማዊ ነው። እኛም ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ እንደመላእክት ሆነን እንኖራለን። በሚፈርስ፣ በሚበሰብስ ሥጋ ተዘርተን (ሞተን)፣ በማይፈርስ፣ በማይበሰብስ ሥጋ እንነሣለን፤ የትንሣኤያችን በኵር ክርስቶስ ነውና።
Show all...
👍 4
#ስለሁላችንም_ቤዛ_የተደረገ_ትንሣኤ_ስለሆነ 👉. ከዚህ በፊት ስለሁላችን (ለዓለም) የሞተ የለም። ቅዱስ ጳውሎስ “እስመ ኵሉ ፆሮ ይፀውር – ሁሉም የራሱን ሸክም ይሸከማል” ብሎ እንደተናገረው (ገላ. 6፥5) አባቶቻችን በራሳቸው ዕዳ ሲሞቱ ምንም ዕዳና በደል የሌለበት ክርስቶስ ግን ለፍጥረት ሁሉ ዕዳ ሊደመስስ በፈቃዱ ሞተ። ሞቱ ስለ ሁላችን እንደሆነ ሁሉ ትንሣኤውም የሁላችን ሕይወት ነው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን የአይሁድ ፍርሐት ነው። አይሁድ “በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ” ማለቱን ሰምተናል፤ ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው እንዳይሰርቁት፣ ‘ተነሣም’ ብለው ለሕዝብ እንዳያስተምሩ. . .” ነበር ያሉት። (ማቴ. 27፥62-65) 👉. ይህ የአይሁድ ፍርሐት የዲያብሎስም ጭንቀት ነው። ጌታችን ክብርት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ሲለያት ዲያብሎስ ነፍሱን በሲኦል ውጦ፣ ሥጋውን በመቃብር ረግጦ ማስቀረት እንዳልተቻለው ስለተረዳ አይሁድን እንዲህ እንዲሉ አድርጓቸዋል። 👉. በሌላ በኩል ትንሣኤውን ዐይተው ያምኑ ዘንድ ይህን ማለታቸው የጌታ ፈቃድ ነበር፤ አምነው ባይጠቀሙበትም የጌታ ትንሣኤ ላመኑትም ላላመኑትም ሕይወት ነውና። ስለዚህ ነው የጌታችንን ትንሣኤ በኵረ ትንሣኤያችን የምናደርገው። ትንሣኤ ዘጉባኤ ?. በእሳት ተቃጥለው፣ በአራዊት ተበልተው ወደ ዐመድነትና አፈርነት የተለወጡ ሰዎች፣ በዕለተ ምጽአት ከሞት የሚነሡት እንዴት ነው? እንደገና ሰው ሆነው ይፈጠራሉ ማለት ነው? 👉. በመጀመሪያ ካለመኖር ወደ መኖር እንድንመጣ ያደረገን ጥበበ እግዚአብሔር ነው። ያለዚያማ እንዴት ሆኖ ነው ከአባት የተከፈለው ዘር ከሴት ደም ጋር ተዋሕዶ፣ ብጥብጥ የነበረው ረግቶ፣ የአጥንት ምሰሶ የጅማት ማገር ተሠርቶለት ቅዱስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሆነው? በእርግጥ እንዲህ ሆኖ የተጀመረው ህልውናችን በሞት ሲቋረጥ እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በመቃብር ውስጥ ቀልጦ ለመቅረት እንጂ ተመልሶ ለመብቀል አልነበረም። የሰው ልጅ እንደ አዝርእት ከሞተና ከፈረሰ በኋላ አካል ኖሮት የሚነሣ ነው። ያለ ዝናም አዝርእት ምን ትንሣኤ አላቸው? ያለ ክርስቶስ ደም መፍሰስስ የሰው ልጅን ማን ከሞት ሊያስነሣው ይችላል? የጌታችን ደም ሲፈስ ግን መቃብራት ተከፈቱ፣ ዐለቶች ተሰነጣጠቁ፣ ከሙታን ወገን ብዙዎቹ ተነሡ። በዚህ ጊዜ፦ “ቦኑ ለከንቱ ፈጠርኮ ለኵሉ እጓለ እመሕያው – በውኑ ሰውን ሁሉ ለከንቱ ነገር ፈጥረኸዋልን?” የሚለው የአባቶቻችን ጥያቄ ምላሽ አገኘ። (መዝ. 88፥47) 👉. ሞት እንደ ገበሬ፣ መቃብር ደግሞ እንደ እርሻ ሆኖ የሰው ልጆች በዚህ ምድር በመበስበስ በመፍረስ እንዘራለን። እንዲህ ካልሆንን ትንሣኤ የለንም። በኋላም ተለውጠን በአዲስ ሥጋ እንነሣለን። ባሕርይ መልአካዊ፣ ባሕርይ ሥጋዊ፣ ባሕርይ እንስሳዊ ለሁላችንም በተፈጥሮ ይሰጡናል። ስንሞት ባሕርይ እንስሳዊ እና ባሕርይ ሥጋዊ ይለዩናል። ባሕርይ መልአካዊ ግን በባሕርዩ ሞት ስለሌለበት አብሮን ይኖራል። በምንም ዓይነት ሞት ብንሞትም ይህ የማይቀር ጉዳይ ነው። (1ኛ ቆሮ. 15፥35-44) ትንሣኤ የሰው ልጅ ሠላሳ፣ ስድሳና መቶ ፍሬ አፍርቶ የሚታይበት ወቅት ነው። 👉. ዕፅዋትና አዝርእት ከፈረሱ ከበሰበሱ በኋላ አንዱ በራሱ፣ ሌላው በጎኑ፣ ሌላው በሥሩ ያፈራል። ከሥሩ የሚያፈራው የባለ ሠላሳ፣ ከጎኑ የሚያፈራው የባለ ስድሳ፣ ከራሱ የሚያፈራው የባለ መቶ ምሳሌ ነው። ይህም በቤተክርስቲያናችን “#ዳግም_ልደት” ተብሎ ይጠራል። 👉. የሰው ልጅ ተፈጥሮዎች ሁለት ዓይነት ሲሆኑ እነዚህም #ጥንተ_ተፍጥሮ እና #ሐዲስ_ተፈጥሮ ይባላሉ። ጥንተ ተፈጥሯችን በአዳም በኩል የተደረገው ተፈጥሯችን ሲሆን ሐዲስ ተፈጥሮ የምንለው ደግሞ በክርስቶስ በኩል የተደረገውን የባሕርያችንን መታደስ ነው። ልደታችን ግን ሦስት ወገን ነው፡፡ አንደኛው ሥጋዊ፣ ሁለተኛው መንፈሳዊ፣ ሦስተኛው ደግሞ ትንሣኤ ዘጉባኤ ነው። ይህም “#ልደተ_ሙታን_እመቃብር” ይባላል። ይኸውም የሙታን ከመቃብር መወለድ ማለት ነው። በዕለተ ምጽአት ማለትም በትንሣኤ ዘጉባኤ ከሞት የምንነሣውም በዚህ መልኩ ነው። ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ #በትንሣኤው_ለትንሣኤ_ያብቃን! 🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱🍀🔱 ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን። 🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺🌻🌺 ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜🌺💫🌺💫🌺 ምንጭ -ኰኲሐ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት
Show all...
እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡ በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡  በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡ መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡ ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡ መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡ ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ  በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡ በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡ ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት! ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት! [መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤  ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም! ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ? ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ! ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ! ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ! ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች! ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች! ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡ (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)
Show all...
🥰 1
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችኹ! • ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን • አሰሮ ለሰይጣን ~ አግአዞ ለአዳም • ሰላም ~ እምይእዜሰ • ኮነ ~ ፍሥሐ ወሰላም። ▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️ • Christ is risen from the dead ~With rhe highest power and authority • He has bounded satan ~And freed Adam • Peace hence forth ~Let there be joy and peace. ▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሣ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍጹም ሰላምና ደስታ ሆነ! ✝☦▪️☦✝▫️✝☦▪️☦✝ “…እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው” (መዝ 78፥65) “…እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን” (ሮሜ 6፥4-5) “…አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።” (1ኛ ቆሮ 15፥20-22) መልካም በዓል ይኹንላችኹ!
Show all...
🙏 3
“…እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው” (መዝ 78፥65) “…እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን” (ሮሜ 6፥4-5) “…አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።” (1ኛ ቆሮ 15፥20-22) እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችኹ!
Show all...
መልካም በዓል ይኹንላችኹ!
Show all...
“ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና፤ …አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።” (ሮሜ 6፥9፤ 1ኛ ቆሮ 15፥20) እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችኹ! «ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችኹ? ተነስቷል እንጂ በዚኽ የለም!» (ሉቃ. 24፥5)
Show all...
👍 7🙏 3