Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Open in Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
Show more213
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-430 days
Posts Archive
Prophet Muhammad (ﷺ) said, "My entire Ummah will enter Paradise except those who refuse." It was asked, "O Messenger of Allah, who will refuse?" He said, "Whoever obeys me will enter Paradise, and whoever disobeys me has indeed refused." [Bukhari]
እባክህ አትተወን
በ-1917፣ ሀያል ነኝ ባይ - እንግሊዝ ስታሰፍራቸው
በ-1948፣ 750,000 ፈለስጢያዊያን - ከቄያቸው አባረሯቸው
የህዝቡ 78% - ምድር አልባ አረጓቸው
የገደሉትን ገድለው - የሚያባሩትን አባረሩ
በራሳቸው ምድር - ፈለስጢንን አሸበሩ
በ1967፣ 300,000 ፈለስጢናዊያንን - አፈናቀሏቸው ከቤት
መች ታወቀና - የቆሰለ የሞተው ብዛት
ፈለስጢናዊያን ሲበደሉ - በአይሁዳ ክህደት
አለም ዝም አለች እንጂ - ቃልም አልወጣት
ዛሬም እንደዛው ነው - ልክ እንደ ትላንት
በ-1995 ፈለስጢንን - ለሶስት ከፈሏት
በ2020 በዶናልድ እገዛ - ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት
«ፈለስጢን» ተወገደና - በመንደር “ገዛዕ” አስገቡት።
ኢዩ ወንድሞቼ የፈለስጢንን በደል - የፈለስጢንን ሰቆቃ
በገጋ ቄያቸው መኖር አልቻሉ - እንደው በቡረቃ።
አለም ዝም ጭጭ አለች - ይህንን እያየች
የሙስሊሙን በደል - ችላ ብላም አለፈች
❝ሐማስ ነው ተንኳሹ❞ - ብላም ለፈለፈች
*በአንዳንድ ሙስሊም* - *በንግግር ተደገፈች*።
ከዚህ ሁሉ በደል - በዚህ ሁሉ ግፍ
አውቆም ሳያውቅ - የሁዳን የሚግፍ
ሐማስነው ጥፋተኛ እያለ - ፈለስጢንን የሚነቅፍ
በ1917 ጀምሮ 2020 ድረስ - ኖሮዋል በእንቅልፍ
ወይም ሆኖዋል - ከባጢል ሚሰለፍ።
አእምሮ ያለው - የሚያሰላስል ጭንቅላት
የሚደግፍ አይኖርም - የሁዳን ክህደት
ምሳሌናት እሷ - የጭካኔ የአረመኔነት
ተምሳሌት ናት እሷ - የሙስሊሞች ጠላት
በአላህ ድንበር ያለፈች - እሷ ከኃዲ ናት
ኢሳን (ዐ.ሰ) ሰቀልኩ ያለች - እሷ ቆሻሻ ናት
ይህ ሁሉ ሆኖም - እሷን የሚደግፋት
ወላሂ አቅል የለውም - ተለክፏል በእብደት።
የፈለስጢን ምድር - በደም ተለወሰ
ደም በዝቶበት - ምድርም ከሰሰ
ያውም የሙስሊም - ተጧጧፈ ሬሳ
በፍርስራሽ ቀሩ - አጥንተም ተከሰከሰ።
ፈለስጢን ተጣራች - ሙስሊሞች ሆይ እያለች
ወንድሞች የሰሟት አይመስልም - እሷ እያለቀሰች
ፈለስጢናዊያን አለቁ - እናትም ደማች
ቤቶች ፈረሱ - ወደሙ መስጂዶች።
ሴትችን ተደፈሩ - ህፃናትን ተቀጠፉ
እኛነን የበላይ እያሉ - ቆሻሾች ለፈ።
በቃችሁ የሚለን - ከዚህ ሁሉ ጭንቅ
አላህ ብቻ ነው - በሐሴት የሚያቦርቅ
ዝንጉ አይደለም አላህ - ሁሉንም ያያል
በጌታችን እዝነት - ድሉም ይመጣል
በዱዓ እንበርታ እንጂ - እሱ ይረዳናል
ለነዛ ቆሻሻሽ - የእጃቸውን ይሰጣቸዋል።
የአላህ ያራህማን - እኛን አትተወን
ላንተ ባሪያዎች አሉህ - ለኛ ማንም የለን
ደጋፊያችን አንተነህ - በወንጀላችን አትራቀን
በድል አንበሽብሸን - ነስሩን አቅርብልን
አዎ ወንጀለኞች ነን - አዎ እናጠፋለን
አዛኝ ነህና የራሒም - እባክህ ይቅር በለን
በጌታነትህ ይሁንብህ - እኛን በፈጠርከን
በአንድነትህ ይሁንብህ - ወደዚህ ምድር ባስገኘሀን
ሙስሊሞችነንና ያ! አላህ - እባክህ አትተወን።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን፦ ህዳር 12/2016 E.C [Nov 22/2023 G.C]
https://t.me/SharpSwords1
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
ፍትሃዊው ጌታ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مُؤْمِنًا حَسَنَةً، يُعْطَى بِهَا فِي الدُّنْيَا، وَيُجْزَى بِهَا فِي الْآخِرَةِ، وَأَمَّا الْكَافِرُ فَيُطْعَمُ بِحَسَنَاتِ مَا عَمِلَ بِهَا لِلَّهِ فِي الدُّنْيَا، حَتَّى إِذَا أَفْضَى إِلَى الْآخِرَةِ لَمْ تَكُنْ لَهُ حَسَنَةٌ يُجْزَى بِهَا﴾
“አላህ አማኝን በመልካም ስራው አይበድልም። በዱንያም በሷ ይሰጠዋል። በአኺራም በሷው ይሸልመዋል። ከሃዲ ግን አላህን አስቦ በሰራቸው መልካም ስራዎች ዱንያ ላይ ያበላዋል። ወደ አኺራ ሲሄድ ግን የሚመነዳበት መልካም ስራ የለውም።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2808
قال تعالى: (قَدْ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجْهِكَ فِى ٱلسَّمَآءِ ۖ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبْلَةً تَرْضَىٰهَا ۚ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ ۚ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْ فَوَلُّواْ وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُۥ ۗ).
የገመዱን መቅጠን ዐይተህ እንዳትበጥስባቸው!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ስታያቸው በወንጀል ባህር የሰመጡ ይመስልሃል :_
እነርሱ ግን ወንጀሉ እየቀፈፋቸው መውጣትም ተስኗቸው የሚገላገሉበት ቀን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
💫አጫሽ ነው =>ሰላት አያመልጠውም;
💫አጫሽ ነው =>ቁርኣን ያዘወትራል;
💫ተገላልጣ እየሄደች =>በኤርፎን ቁርኣን ትሰማለች;
💫ተገላልጣ እየሄደች =>ሰላት ሲደርስ አታስመልጥም ለብሳ ትሰግዳለች;
💫በብልሽት ያነጋል =>ፈጅር ላለ ማስመለጥ በቀዝቃዛ ውሃ ይታጠባል።
ባየሃቸው ጊዜ “ዲን ላይ የሚያላግጡ ሙናፊቆች” ብለህ እንዳትገለምጣቸው።
👉እነዚህ ማለት፦
ሸይጣን በሚሰሩት ወንጀል ምክንያት ከአላህ ተስፋ እንዲቆርጡ ማድረግ ተስኖት ፍልሚያ ላይ ያሉ ምስኪኖች ናቸው።
ወንጀሉን ይሰሩታል:
ግን ሁሌም ልባቸው ይጣበባል። የሆነ ቀን ከዚህ ወንጀል ተላቀው ንፁህ የአላህ ባሪያ እንዲሆኑ ይጠባበቃሉ።
ታድያ………
በእነርሱ እና በአላህ መሃል ያለው ገመድ መቅጠኑን ዐይተህ ተስፋ አስቆርጠህ እንዳትበጥስባቸው።
📖{وَآخَرُونَ اعْتَرَفُوا بِذُنُوبِهِمْ خَلَطُوا عَمَلًا صَالِحًا وَآخَرَ سَيِّئًا عَسَى اللَّهُ أَن يَتُوبَ عَلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ}
{ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ: መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አሉ፡፡ አላህ ከእነሱ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጀላል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡}
መልካም ስራ አላቸው::
ትልቁ መልካም ስራ ተውሒድ ነው። ተውሒዳቸው አልተነካም።
በተቃራኒው ሌሎች አላህ እርም ያደረጋቸው ስራዎች ይዳፈራሉ።
ከእነዚህ ሰዎች መልካምነት;
በወንጀላቸው ያምናሉ, ይፀፀታሉም።
💎 ወንጀል እየሰሩ የሚፀፀቱ ውስጣቸው የሚረበሽ ከሆነ ያማረ መጨረሻ ይከጀልላቸዋል።
💎 ወንጀል እየሰሩ በዝያ ወንጀል ሀሴት የሚያደርጉ ከሆነ ትልቅ አደጋ ላይ ነውና ያሉት ይፈራላቸዋል።
©️©️©️
አዛኙ ጌታ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿إِذا هَمَّ عَبْدِي بحَسَنَةٍ وَلَمْ يَعْمَلْها، كَتَبْتُها له حَسَنَةً، فإنْ عَمِلَها كَتَبْتُها عَشْرَ حَسَناتٍ إلى سَبْعِ مِئَةِ ضِعْفٍ، وإذا هَمَّ بسَيِّئَةٍ وَلَمْ يَعْمَلْها، لَمْ أَكْتُبْها عليه، فإنْ عَمِلَها كَتَبْتُها سَيِّئَةً واحِدَةً.﴾
“ባሪያዬ አንድን መልካም ስራ ለመስራት አስቦ ባይሰራት እንደሰራት አስቤ አንድን ምንዳ እፅፍለታለሁ። ከሰራት ደግሞ ምንዳውን ከአስር አስከ ሰባ ድረስ እጥፍ አድርጌ እፅፍለታለሁ። መጥፎን ስራ ለመስራት አስቦ ካልሰራት እንደ መልካም ስራ አስቤ አንድን ምንዳን እፅፍለታለሁ። መጥፎ ስራውን ከሰራት ደግሞ እንደ አንድ ወንጀል አድርጌ እፅፍበታለሁ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 128
©️©️
መስጅዶች የአላህ ናቸው ፤ እኛም ሙስሊሞች ነን
------------------------------------------------
ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
በ ቲክ ቶክ
@huda4eth
ያግኙ
መልካም ስራ ለመጥፎ ስራ ማበሻ ትሆናለች
-------------------------------------------------
ኡስታዝ ኸድር አብደላህ
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
በ ቲክ ቶክ
@huda4eth
ያግኙን
📃የረመዿንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር
ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-
“የረመዿን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”
ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-
"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዿን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።
ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-
"ረመዿንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"
በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:
"ረመዿንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"
ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።
ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።
ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዿን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።
ረመዿን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"
አላህ የረመዿንን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!
#ዝክረ_ረመዿን
የሻዕባን አጋማሽ…
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنّ اللهَ ليطَّلعُ في ليلةِ النِّصفِ من شعبانَ فيغفرُ لجميعِ خلقِه إلّا لمشرِك أو مشاحنٍ﴾
“አላህ በሻዕባን አጋማሽ ሌሊት ፍጡራኑን ይመለከትና ሁሉንም ፍጡራኖቹን ይምራል። ከሙሽሪክ (ከአጋሪዎች) ወይም ከአመፀኞች በስተቀር።”
📚 አልባኒ በኢብኑ ማጃህ ዘገባ ውስጥ ሀሰን ብለውታል: 1148
መልካም ስራ ለመጥፎ ስራ ማበሻ ትሆናለች
-------------------------------------------------
ኡስታዝ ኸድር አብደላህ
🔰 አውፍ በዪን አቅሳ
ጩሐት ይሰማናል - ከፈለስጢን ጓሮ፣
ለቅሶም ይሰማናል - የህፃናት ሮሮ፣
እጃችን አልነሳ አለ - በወንጀላችን ታስሮ፣
አልቅሶ የሚስቅ - ከሰው ፊት ዞሮ፣
ተስፋ አትጣሉብን - ሌላም ጊዜ ሆነ ዘንድሮ።
ተውጠን በወንጀል - በዱንያዊ ቀመር፣
እየተጎሻሸምን - በዘር በብሄር፣
በሺሆች ሞተው - በአድማ ሲቀበር፣
ጨከነ ልባችን - እንዴትስ አይሸበር⁉️።
ከዱንያዊ ጣጣችን - መላቀቅ አልቻልንም፣
እርሰበርስ ከመበላላት - ሌላን አላወቅንም፣
አውፍ በዪን አቅሳ - ሰቆቃሽ አልተየንም።
አውፍ በዪን አቅሳ - ሰቆቃሽ አልተየንም።
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ummalife.com/ReshadMuzemil
🥀ጁምዐን ከሱረቱል ከህፍ ጋር🥀
ክፍል አስራ አንድ
# ﺳﻮﺭﺓ _ ﺍﻟﻜﻬﻒ
#ሱረቱል_አልከህፍ ( የዋሻው ምእራፍ )
ግቤን ከማሳካት አልወገድም !!!
{وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِفَتَىٰهُ لَآ أَبْرَحُ حَتَّىٰٓ أَبْلُغَ مَجْمَعَ ٱلْبَحْرَيْنِ أَوْ أَمْضِىَ حُقُبًۭا}
«ሙሳም ለወጣቱ «የሁለቱን ባሕሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምኼድ ድረስ (ከመጓዝ) አልወገድም» ያለውን (አስታውስ)፡፡»
⚪️ ግብህን በማሳካት ላይ ነቢዩላህ ሙሳን አርአያህ አድርግ !
لا أبرح "አልወገድም "
▪️ "አልወገድም"… ማለት " እስክደርስ ድረስ" ማለት ነው
🔴 ዋጋው « ብዙን ጊዜ መጓዝ » ቢሆንም እንኳ ግቤን ከማሳካት አልወገድም !
⚪️ ሕልሜ « የሁለት ባህሮች መገናኛ» ድረስ ሩቅ ቢሆንም እንኳ እሱን ከማሳካት አልወገድም !
🔴 ምን አልባትም በዚህ ጉዞዬ « ድካምን» ላገኝ እችል ይሆናል … ቢሆንም ግን ሕልሜን ከማሳካት አልወገድም !
☑️ አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ አንዲትን እርምጃ የምራመድበትም እድል ከሰጠኝ … በእርሱ ፍቃድ የተራራው ጫፍ ድረስ ከመድረስ አልወገድም !
☑️ በጌታዬ እዝነት ጀነት ለመግባት … በዚች ዱንያ ላይ ሁኜ ለአኼራዬ ከመስራት አልወገድም !
©️©️ Toleha Ahmed
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇
t.me/ReshadMuzemil
