en
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Open in Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Show more
213
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-430 days
Posts Archive
«የሸገር ሲቲ ጭፍን የኢስላም ጥላቻ አሁንም እንደቀጠለ ነው።   ዛሬ በተጀመረው የስምንተኛ ክፍል (ሜኒስትሪ) ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን በጀሞ 2 አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተገኝተው የነበሩ ስድስት ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ኒቃባቹንና  ጅልባባቹን ካላወለቃቹ በሚል ጭፍን የኢስላም ጥላቻ ያለ አግባብ ሲዋከቡ ቆይተዋል። አንዲት ተማሪ እስከመጨረሻው አላወልቅም በሚል በመስፅናቷ የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ሁለት ፈተናዎች መፈተን ሳትችል ቀርታለች።» Via: Murad Tadessa t.me/ReshadIbnuMuzemil

በድንጋይ ጠጠሮች ጨዋታና መሰል ነገሮች መወራወር ስለመከልከሉ! ከአብደላህ ቢን ሙገፈል (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦ ﴿نَهَى النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ و
በድንጋይ ጠጠሮች ጨዋታና መሰል ነገሮች መወራወር ስለመከልከሉ! ከአብደላህ ቢን ሙገፈል (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦ ﴿نَهَى النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ  الْخَذْفِ ، وَقَالَ:  إِنَّهُ لَا يَقْتُلُ الصَّيْدَ وَلَا  يَنْكَأُ  الْعَدُوَّ، وَإِنَّهُ يَفْقَأُ الْعَيْنَ وَيَكْسِرُ السِّنَّ﴾ “ነቢዩ (ﷺ) ጠጠር መወራወርን ከልክለዋል። እሱ የሚታደንን ነገር አይገድልም። ወይም ጠላትን አያጠቃም። ነገር ግን አይንን ያጠፋል፣ ጥርስን ይሰብራል ብለዋል።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 6220 ©️©️ BuhariMuslimAmharic t.me/ReshadIbnuMuzemil

ጉዳዩን ለማጥራት‼ ============== ይህን ዘገባ ትልልቅ ገጾች ላይ ሳየው ደንግጬ ነበር። ግን ከማመኔ በፊት የሆነ የተምታታ ነገር እንዳለ ገምቼ ነበር። ምክንያቱም የቱንም ያክል ድክመት ቢኖር
+1
ጉዳዩን ለማጥራት‼ ============== ይህን ዘገባ ትልልቅ ገጾች ላይ ሳየው ደንግጬ ነበር። ግን ከማመኔ በፊት የሆነ የተምታታ ነገር እንዳለ ገምቼ ነበር። ምክንያቱም የቱንም ያክል ድክመት ቢኖር አቡበከር አሕመድ በህዝባዊ መድረክ ላይ ለቤተ ክርስቲያን መገንቢያ ሰጠ ሲባል በአንደዜ ላምን አልችልም። የማይመስል ነገር ነበርና። ይህን ዘገባ የሚያሰራጩ ገጾችና ግለሰቦች ዘገባቸውን ቢያስተካክሉት መልካም ነው። ማንኛውም ሙስሊም ለሌላ እምነት ተቋም መገንቢያ ምንም አይነት የገንዘብም ሆነ ሌላ አይነት ትብብር ማድረግ በእስልምናችን አይፈቀድም። ባገኘሁት የተጣራ መረጃ መሠረት አቡበከር አሕመድ ዛሬ በሚሊኒዬም አዳራሽ ተገኝቶ ያደረገው የ100 ሺህ ብር ድጋፍ ለሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት ድጋፍ ሳይሆን፤ በጦርነቱ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድጋፍ ለማድረግ እየተደረገ ላለው የድጋፍ መርሃ ግብር ነው። ወደቦታውም የሄደው የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት አማካሪ ስለሆነና ፕሬዝዳንቱ ጥሪ ተደርጎላቸው ስለነበር እርሳቸውን ወክሎ ነው። በርግጥ መድረኩ የተዘጋጀው ለሃገረ ስብከቱም ድጋፍ ቢሆንም፤ እንዳገኘሁት መረጃ ከሆነ ራሱ አቡበከር ይሄን ድጋፍ የሚያደርገው ለገበሬዎቹ መሆኑን ለታዳሚው መድረክ ላይ በግልፅ አስነግሯል። ለማረጋገጥ ይህቺን ቪድዮ አዳምጧት። https://t.me/ReshadIbnuMuzemil/343?single ጫፍ ይዛችሁ ባታሯሩጡና ሰዎችንም ውዝግብና ብዥታ ላይ ባትጥሉ ጥሩ ነው። በተለይም በርካታ ተከታታይ ያላችሁ ገጾች የሠራችሁት ዘገቢያ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድም ሆነ ግለሰቡ ዘንድ አሉታዊ ውጤት ያለው ነውና አስተካክሉት። || MuradTadesse t.me/ReshadIbnuMuzemil

The Prophet ﷺ said: “Whoever is offered perfume, let him not refuse it for it is easy to carry and smells good.” [Sunan an-Na
The Prophet ﷺ said: “Whoever is offered perfume, let him not refuse it for it is easy to carry and smells good.” [Sunan an-Nasā'ī 5259 | Grade: Ṣaḥīḥ] #Perfume #Gift Join:- t.me/ReshadIbnuMuzemil t.me/InspiresWorld ▬▬▭▭▬▬▭▭▬▬▭▭▬▬▭▭ 〽️ Facebook ⭕️ Fb.com/ReshadIbnuMuzemil ⭕️ Fb.com/ReshadMuzemil2 ⭕️ Fb.com/ReshadIbnuMuzemil1

Islam allows non-Muslims to help their problems. There is empirical evidence to suggest this. But to spread a faith contrary to Islam, to cooperate in apostasy is a very dangerous sin. The values ​​of tolerance and coexistence are not defined in this way. The crime is to set a bad example when it is committed by people known to the public. All those of you who engage in such disgraceful activities, fear Allah. = ⭕️ Ibnu Munewor t.me/ReshadIbnuMuzemil ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ኢስላም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ለችግራቸው መርዳት ይፈቅዳል። ይህንን የሚጠቁሙ ማስረጃዎች በተጨባጭ አሉ። ነገር ግን ከኢስላም ተቃራኒ የሆነን እምነት ለማስፋፋት ፣ በክህደት ላይ መተባበር እጅግ አደገኛ የሆነ ጥፋት ነው። መቻቻልና አብሮ የመኖር እሴት በዚህ መልኩ አይደለም የሚገለፀው። ጥፋቱ ህዝብ በሚያውቃቸው ሰዎች፣ ባደባባይ ሲፈፀም ደግሞ ክፉ ምሳሌ መሆን ነው። በእንዲህ አይነት ነውረኛ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ ሁሉ አላህን ፍሩ። = ⭕️ Ibnu Munewor t.me/ReshadIbnuMuzemil ⭕️ Fb.com/ReshadIbnuMuzemil ⭕️ Fb.com/ReshadMuzemil2 ⭕️ Fb.com/ReshadIbnuMuzemil1

WHAT HAVE YOU PREPARED FOR IT? Narrated Anas (رضي الله عنه‎): "A man asked the Prophet (ﷺ) about the Hour (i.e. Day of Judgment) saying, "When will the Hour be?" The Prophet (ﷺ) said: "What have you prepared for it?" The man said: "Nothing, except that I love Allah and His Apostle." The Prophet (ﷺ) said: "You will be with those whom you love." ••• We had never been so glad as we were on hearing that saying of the Prophet (ﷺ) (i.e. "You will be with those whom you love.") Therefore, I love the Prophet, Abu Bakr and Umar, and I hope that I will be with them because of my love for them though my deeds are not similar to theirs." Bukhari 3688 #Day_Of_Judgment #Powerful_Reminder Join:- t.me/ReshadIbnuMuzemil

«ጫት በሚዛን ላይ‼ 🔅በዒድና መሰል አጋጣሚዎች በብዛት ከሚታዩ ትልልቅ ስህተቶች መካከል አንዱ ሰዎች በጋራም፣ ለየብቻም ሆነው ጫት መቃም ነው!። 🔅ጫት ካለው ጤናዊ ጉዳት፣ የገንዘብ ብክነትና ከሰላት ማዘናገት አንጻር ኢስላም የትኛውንም ጎጂ ነገሮችን እንደመከልከሉ ጫትም "ክልክል/ሐራም" ነው ማለት እንችላለን፤ በርካታ የዲን ሊቃውንትም ሐራምነቱን በግልጽ ተናግረዋል። ነገር ግን ብዙ ሰዎች ስሜታቸውን ማሸነፍ ስለሚከብዳቸው የሚወዱትና የለመዱትን ነገር በቀላሉ መተው ይከብዳቸዋል!። የብዙዎች ልባቸው ከማወቁም ጋር ሐራምነትና ጎጂነቱንም አምኖ ላለመቀበል ሲጥሩ ይታያል!። 💥ጫት ለሚቅሙ ሰዎች ጥያቄ አለኝ፥ ▪️ጫትን እንደምግብ ከሆነ የምትጠቀሙት የስነ-ምግብ ወይም የስነ-ጤና ባለሙያዎች ጫት ጠቃሚ ወይም አስፈላጊ ነው ሲሉ ሰምታችኋልን?! ▪️ወደ አላህ የሚያቀርብና የዲን አካል ነው ብላችሁ ከሆነ የምትጠቀሙት ደግሞ በቁርኣን ወይም በሐዲሥ "ጫት ቃሙ" የሚል መመሪያና ትዕዛዝ ይገኛልን?!   ▪️እንዲሁ ዝም ብዬ ለመዝናናት ነው የምቅመው ካላችሁም አቅል ያለው ሰው ለፍቶ-ደክሞ ያመጣውን ገንዘብና ጀነት የሚገዛበትን ውድ ጊዜ ወይ ለዲን ወይ ለዱኒያ በማይጠቅም ነገር ያጠፋልን?!   ▪️ዲንና ጤናውን የሚጎዳ ነገር እያደረገ የሚዝናና (የሚደበር) ሰውስ ሞኝነቱ ያጠራጥራልን?!   ▪️ደስታና መዝናናት ከውስጥ የመነጨ ካልሆነስ ራስን ማታለል አይሆንምን?!   ▪️እውነተኛ ሙስሊምስ ያዝናናኛል የሚለውንና ለሱ ደስ ያለውን ሁሉ ዝም ብሎ ያደርጋልን?! 🔅ወንድሜ ሆይ፥ የሸሪዓህ ብይን ካላቆመህና ካልገዛህ የጫትን ጉዳትና አደንዛዥነት በዕውቀት የበሰሉና ሙያቸውን አክባሪ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችን ጠይቅ! 🔅ብዙ ትልልቅ ጥምጣም የጠመጠሙ <ሼኮች>ም ይቅማሉ ካልክ ሸይኽ የተባለ ሁሉ እውነትም ሸይኽ እንዳልሆነ እወቅ፤ ሙስሊም በእምነቱ ጉዳይ የሚከተለው ነቢዩን ﷺ እንጂ ግለሰቦችን እንዳልሆነም ተረዳ!። ሰዎች ሊሳሳቱ፣ በስሜት ሊሸነፉ፣ ይሉኝታ ሊያጠቃቸው ይችላልና። 🔅እውነተኛ ሙስሊም ነቢዩ ﷺ እና ሰሓባዎቻቸው ያላደረጉትን ነገር ሰው አደረገ ብሎ አያደርግም፤ ሰው ተሳሳተ ብሎም አይሳሳትም፤ ይልቅ ሁሉንም ነገር ሸሪዓን መሰረት አድርጎ፣ ጥቅምና ጉዳቱን አነጻጽሮ፣ አላህ ሲጠይቀኝ ይህን መልስ እሰጣለሁ ብሎ ነው ማድረግ ያለበትን የሚያደርገውና መተውም ያለበትን የሚተወው። ☄አላህ ጠቃሚና ጎጂውን የሚለይ ልቦና ይስጠን። ©: ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 13/12/1444 ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ "ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197» t.me/ReshadIbnuMuzemil t.me/ReshadMuzemil 〽️ Facebook ➘➘➘ ⭕️ Fb.com/ReshadIbnuMuzemil ⭕️ Fb.com/ReshadMuzemil2 ⭕️ Fb.com/ReshadIbnuMuzemil1

It's not how much we GIVE but how much LOVE we put into giving. t.me/ReshadIbnuMuzemil
It's not how much we GIVE but how much LOVE we put into giving. t.me/ReshadIbnuMuzemil

🔰 የነገን አስቤ ቦርሳውን ሸክፎ - ቤት ሲደርስ ተማሪ፤ ቤቱ ግን ፈርሷል - በድንቁርና ቀማሪ፤ ሰው በራሱ ሀገር - ባዳ ሲሆን አየን፤ የቀለሳት ጎጆ ፈርሳ - ሜዳ ላይ ሲበተን፤ ህጋዊ ድሃም - አ
🔰 የነገን አስቤ ቦርሳውን ሸክፎ - ቤት ሲደርስ ተማሪ፤ ቤቱ ግን ፈርሷል - በድንቁርና ቀማሪ፤ ሰው በራሱ ሀገር - ባዳ ሲሆን አየን፤ የቀለሳት ጎጆ ፈርሳ - ሜዳ ላይ ሲበተን፤ ህጋዊ ድሃም - አደረግናቸው አሉን። ይመጣል ጥሩ ወቅት - ይህ ጊዜ ያልፋል⁉️ ለሊቱስ አይረዝምም - ግን ቶሎ ይነጋል⁉️ ግን ምን አለ - ቀኑ ራሱ ባይመሽ፤ እግሬ አውጪኝ ብለን - ከፍርሃታችን ልንሸሽ፤ ማምለጥ ይቻል ይሆን - ከደቆሮዎች እሳቤ⁉️ እኔስ ተስፋ ቆረጥኩ - የነገን አስቤ፤ እኔስ ተስፋ ቆረጥኩ - የነገን አስቤ። በረሻድ ሙዘሚል t.me/InspiresWorld

⭕️ ውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ይህ ማስታወሻ በፈተና ወቅት ይጠቅማችኋል በትኩረት ይነበብ። ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▬▭▬▭▬▭▬▭ 🛑 ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች! ➤ በፈተና ወቅት በተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ውጥረት እና መጨናነቅ ለመቀነስ ይህንን ምክር በማስገንዘብ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን። 🎯 በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች:- 📙 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው። ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት። ♻️ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች ◆ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ◆ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ◆ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አለመሆኑን መረዳት።  ◆ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጁ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ◆ ከጓደኞቻችን ወይም ከወላጆቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ እርማት እንድናረግም ያግዘናል። ◆ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።  ◉ ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ ◉ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። ◉ አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 🔰 ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ  እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። ◉ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር:: ◉ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ ◉ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። ◉ ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። ◉ በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ➚ ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆንና ፈተና ማለት ለጀነትና ለጀኃነም ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን። ▮ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ ሌላውን ለአላህ መተው ነው‼️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ◉ ወቅቱ የፈተና ወቅት በመሆኑ ተማሪዎች እንዳየ እድሜያቸው እና የክፍል ደረጃቸው ይህን ማስታወሻ እንዲጠቀሙበት  አሳስባለሁ። 🎯 አላህ ይርዳችሁ‼️ ወንድማችሁ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ▬▬▬▬ ⭕️⭕️ መልዕክቱን ለአዲስ አበባ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች አድርሱልኝ ▬▬▬▬▬▬▬ t.me/ReshadMuzemil

#የመዲና 🎯 የዓለም ውበት በጠቅላላ ያረፈባት ከተማ
#የመዲና 🎯 የዓለም ውበት በጠቅላላ ያረፈባት ከተማ

⭕️ Usman Arshad walked over 4,000 KM 2,485 Miles) from Pakistan to Makkah to fulfill lifelong dream of performing Hajj. t.me/Reshad_Muzemil t.me/ReshadMuzemil

🎯 የሌለህንም መስጠት ትችላለህ‼️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ◆ እኛ የሰው ልጆች ለሰው የሆነ ነገር ለማድረግ የግድ የሆነ ነገር ሊኖረን አይገባም። ➻ እኛ ተማን እያለ ሌሎችን እንዴት ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ሐሳብ መስጠት እንችላለን። ➻ እኛ ድሃ ሆነንም ሌሎችን እንዴት ጠንክሮ መሥራት እንዳለባቸው ልናቅጣጫቸው እንችላለን። ➻ ወላጆቻችን እኛ ዘንድ ባይኖሩ እኳን ለሌሎች ወላጆቻቸውን የመንከባከብ ግዴታ እንዳለባቸው መጠቆም እንችላለን። ➻ እኛ በተለያዩ ምክንያቶች ደካማ ሆነን ሳለ ሌሎች ግን ጠንካራ እንዲሆኑ ምክንያት መሆን እንችላለን። ➵ እኛ ተሸንፈን ወድቀን፤ ሌሎች ግን ድልን እንዲቀዳጁ መንስኤ መሆንና ከወደቁበት እንዲነሱ ብርታትም ልንሆናቸው እንችላለን። 🛑 አዎ! እኛ ጋር ለሰው የምንሰጠው ሳይኖርም መሥጠት ግን እንችላለን። ለዚህ የሚያስፈልገን ለምናደርገው እገዛ ምንም ምላሽ ሳንጠብቅ ለአላህ ብለን ብቻ በንፁህ ልብ ሰዎችን በሐሳብም ሆነ በጉልበት መርዳት ነው‼️ ⬛️ በአለም ትልቅ ክብርና ዝና ያገኙ ምንም ነገር ሳይኖራቸው መስጠት የቻሉ ናቸው። ለሰብዓዊነት ብለን ሰውን የምንረዳ እጅግ በጣም ሲበዛ ጥቂቶች ብንሆንም ማለት ነው‼️ ▶ ሳይኖርህ መስጠት.......‼️ ▶ ግን እንዴት⁉️ 🛑 ከሰማኋቸው አንድ አጭር ታሪክ ላካፍላችሁ። ▮አንድ አባት ሁሌም ወንበር ላይ ቁጭ ብለው መፅሐፍ ያነባሉ። ልጅም በአባቷ የዘወትር ተግባር ትገረማለች‼️ በዚህም የተነሳ ይህን ታስባለች « ማንበብ ለብዙ ነገሮች መፍትሔ እንደሆነ» እናም እሷም ጠንክራ ለመማርና አንባቢ ለመሆን ወሰነች። ይችህ ልጅ አደገች ብዙ የክፍል ደረጃዎችንም በተሳካ ሁኔታና በአስደማሚ ውጤትም አለፈች። ይህም ብቻ ሳይሆን ከእድሜዋም ጋር *« ለምን የሚል ጥያቄ »* አብሯት አደገ። 〽️ ከእለታት አንድ ቀን ግን አባቷ መፅሐፍ እያነበቡ ሳለ በአጠገባቸው ስታልፍ አንድ ነገር አስደነገጣት። ከዛም ለአባቷ « አባ መፅሐፉ እኮ ተገልብጧል » አለቻቸው‼️ አባትም ልጄ ሁሌም መፅሐፍ ከፍቼ ወንበር ላይ ምቀመጠው አንቺ እንድታነቢ፣ ጠንክረሽ እንድትማሪ፣ ጥሩ ቦታ እንድትደርሺ ነው። እኔ እኮ ማንበብ አልችልም አሏት‼️ ⭕️ ይህ ነው የሌለንንም ነገር መስጠት መቻል ማለት። ከኛ የሚጠበቀው ነገር................ ▼ ቅን ልብ አስተዋይ አዕምሮ፣ ንፁህ ህሊና፣ እንዲሁም የምናደርጋትን ትንሽየም ነገር ትሁን ለአላህ ብቻ ብሎ ማድረግ ነው‼️ Motivation by Reshad ▭▬▭▬▭▭▬▭▬▭▬▭▬ t.me/InspiresWorld ለአስታየት/ጥያቄ:- t.me/ReshadMuzemil

"Saudi" may God protect you! May Allah bless these examples of purity t.me/Reshad_Muzemil
+1
"Saudi" may God protect you! May Allah bless these examples of purity t.me/Reshad_Muzemil

#የኢድ አከባበር ደንቦች! ©️©️ BuhariMuslimAmharic t.me/Reshad_Muzemil

#የኢድ አከባበር ደንቦች! ©️©️ BuhariMuslimAmharic t.me/Reshad_Muzemil
+8
#የኢድ አከባበር ደንቦች! ©️©️ BuhariMuslimAmharic t.me/Reshad_Muzemil