ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more5 649
Subscribers
+824 hours
+247 days
+11730 days
Posts Archive
5 648
#እኛም_የእኛ_አይደለን!
እንኳንስ ሀገሩ እንኳንስ መሬቱ፤
እኛም የእኛ አይደለን ይኸ ነው አውነቱ።
ቀኑም ድንገት ከድቶ በሞት የሚተካ፤
ገንዘብና ስልጣን ህይወት ላያረካ፤
ለዚህች ከንቱ ምድር ለወረተኛ ዓለም፤
የእኛ ያልነው ሁሉ መቼም የእኛ አይደለም።
በድንገት ለምታልፍ ለኮንትራት ህይወት፤
አፈር ለሚበላው ለከንቱ ሰውነት!።
እንኳን ቁሳቁሱ ተራ ገንዘብ ቀርቶ፤
እኛም የእኛ አይደለን መኖር ነው ተስማምቶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
ሀዘኔ ሀዘናቸው ሳቄ ነው ሳቃቸው
ለሚወዱኝ ሰዎች ጥርሴ ሸልማቸው
ለሚጠሉን ሰዎች ባይሰጥም ደስታ
ለሚወዱን ሁሉ ምግብ ነው ፈገግታ
ፈገግ በል ጥርሴ ለሌሎች ስጥ ቦታ
ውስጣዊ ሀዘኔን በመታገል እርታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#ጠርጥሪ
አንበሳና ነብር በጋራ እየሳቁ
ውበትሽን አጉልተው እያደናነቁ
ወደ አንቺ ሲመጡ ባልነበር ፈገግታ
ባልተለመደ መልክ የወዳጅ ሰላምታ
ያኔ ያንቺ ነገር አክትሟል መኖርሽ
ተማክረዋልና ቀድሞውን ሊበሉሽ።
ስለዚህ ጠርጥሪ
በልማድሽ ፍሪ
ተፈጥሮ ነውና መቀየር ላትችይ
አደነቁኝ እያልሽ ፊን ፊን አትበይ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
ነፍሴ ለስጋዬ ባክሽ አታሽቃብጪ
ነገ አፈር ነው እርሱ አንቺ ስትቀጪ
ይልቅ እንቢ በይው በጸሎት ይረታ
እዳው ላንቺ እንዳይተርፍ የማታ የማታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#አፋልጉኝ?!
ጉድለቴን ሳይቆጥር ድክመቱን ሳልቆጥር፤
ጓደኛ የሚሆን በሰውነት ክብር፤
ሳጠፋ ሚየመክረኝ ሲያጠፋ የምመክረው፤
በጎን የማያማኝ ከጀርባ የማላማው፤
አፋልጉኝ ጓደኛ መስተዋት የሆነ፤
በግልጽ ንግግር አምኖ የዘመነ፤
ግዜ አይቶ የማይጥል ሀብት አይቶ ማይከዳ፤
ውስጡን የምረዳው ውስጤን የሚረዳ፤
አፋልጉኝ ጓደኛ ከወረት የራቀ፤
ሰው መሆን የገባው ሰውነት ያወቀ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
DOGS
Finally
የመጨረሻ ቀን $DOGS Earn ለማድረግ = August 14
Aug 14 ላይ ስለ Listing መረጃ ይለቀቃል!
$DOGS፣ OKX ላይ Premarket ተጀምሯል!
Task ስሩ፣ ሰው Invite አድርጉ፣ Stay Updated
ለመጀመር፡
https://t.me/dogshouse_bot/join?startapp=AeiKTXdIQKmMbGDdO3C3dg
5 648
DOGS
Finally
የመጨረሻ ቀን $DOGS Earn ለማድረግ = August 14
Aug 14 ላይ ስለ Listing መረጃ ይለቀቃል!
$DOGS፣ OKX ላይ Premarket ተጀምሯል!
Task ስሩ፣ ሰው Invite አድርጉ፣ Stay Updated
ለመጀመር፡
https://t.me/dogshouse_bot/join?startapp=AeiKTXdIQKmMbGDdO3C3dg
5 648
ለሆዱ ሲንጫጫ ኮሚቴ በሞላ
ወርቁን አመጣልሽ ያ ታምራት ቶላ❤
ሀገር ለማሳነስ ዘወትር ለሚተጉ
ሀገሩን ለሚወድ ወርቅ ነው ማዕረጉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#ልቤን_መልስልኝ!
ቀንና ሌሊቱ ጊዜም ተሻጋሪ
ትዝታህ ብቻ ነው ከኔ ጎጆ ነዋሪ
ሀምሌና ነሐሴ ይጥላል አብዝቶ
ሰውም ድንገት ያልፋል ትዝታን ተክቶ
አንተስ ካለህበት እንዴት ነው ትዝታ
ከኔ ቤት በርትቷል ጠዋት ሆነ ማታ
ጊዜን እንደዘበት የሗሊት መልሶ
አንተን ያገዝፍሐል እኔን አኮስሶ
በልቼ እንዳልበላሁ
ጠጥቼ እንዳልጠጣሁ
ዛሬም በመራቅህ አለሁ እንደከሳሁ
አመታት አልፈውም አንተን አስባለሁ
ስራመድ ብቻዬን ስተክዝ ለራሴ
በትዝታ ማእበል ስትሰቃይ ነፍሴ
እስቲ ልጠይቅህ ስላንተ ሁኔታ
እኔ አልሰነብትም ሟች ነኝ በትዝታ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
ለብቸኝነቴ ትላንት ሰበብ ሆነው
እብድ ነው ይላሉ ዛሬ ከንፈር መጠው
ልብሴን የወሰዱት እነርሱ ነበሩ
ጨርቅ ጣልክ ለማለት እንዴትስ ደፈሩ?!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#በተስፋ_የማልባት
ወተቷን ባልቀምስም ባትደርስ ለችግሬ፤
ላም አለኝ ከሰማይ ገዛሁ ተበድሬ፤
ጥገት የሆነች ናት ወተቷን የማላይ፤
በተስፋ የማልባት እያየሁ ወደ ላይ፤
ምራቅ የምታሱጥ እርጎ ቅቤ የማትሰጥ፤
ከደመና እርቃ ከላይ የምትቀመጥ፤
ላም አለች በስሜ ከቶ ማትዳሰስ፤
ለረሀብ ለችግሬ ለዛሬ የማትደርስ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
በማሽቃበጥ ትሪ እንጀራ ብንበላ
ሰው ታዘበን እንጂ ሆዳችን መች ሞላ
የማስመሰል ጉርሻ እራብ ላያስታግስ
ስም ነው ያተረፍነው በስስት ስንጎርስ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
በጣም ገራሚ የሆነ Airdrop ነው ስሩት
https://t.me/Tomarket_ai_bot/app?startapp=00006yiD
Farm 🍅 $TOMATO with me and secure your token allocation through Tomarket.ai.
Use my link to get 2,000 🍅 $TOMATO!
5 648
#የስንቱ_ዝምታ
የምላስ ጋጋታ ጀሮን ባይጋርደው
ይደመጥ ነበረ ዝምታም ቃል አለው
በህሊና ከሳሽ በልብ ዳኝነት
የዝምታ ችሎት የተሰየመ እለት
ሁሉም ተናጋሪ ጸጥ! ቢል ላንድ አፍታ
እመኑኝ ይጮሃል ድምጽ አለው ዝምታ
የተፈጥሮ ችሎት በልብ ሚዛን ቢረግጥ
ዓለም ለሴኮንዶች መናገርን ቢል ጸጥ
ያኔ ይደመጣል ቃል አለው ዝምታ
ገለል ሲልለት የምላስ ውካታ
ጆሮ ባይጋረድ በቃላት ጋጋታ
መጮኽ በጀመረ የስንቱ ዝምታ
የሰው ልጅ ቢኖረው ስድስተኛ ህዋስ
ይሰማው ነበረ ዝምታችን ሲፈስ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
5 648
#monorix
✅|| monorix ይባላል።
✅|| ሊለቀቅ 1 ቀን ብቻ ነው የቀረው።
✅|| ከ4.5 ሚልዮን በላይ ተጠቃሚ አለው።
✅|| በቴሌግራም ቻናላቸው ከ3.5 ሚልዮን በላይ ተከታይ አላቸው።
✅|| pre market ተጀምሯል። በ #Bingx pre market የተጀመረ ሲሆን የአንድ ሚልዮን token እስከ 118$ ይሸጣል።
✅|| የተለያዩ Give awayም አላቸው።
✅|| ዋሌታችሁ እዛ ማገናኘት ትችላላችሁ
✅|| አሰራሩ የተወሰኑ ታስኮች አሉ እነሱን መስራት እና ታብ ታብ ማድረግ ብቻ ነው።
አሁኑኑ ለመጀመር
https://t.me/monorixbot?start=5305703538
5 648
የ Notcoin ሁለተኛው Airdrop
በ41 ቀናት ኤርድሮፑ ይጠናቀቃል ያ ማለት 6 ሳምንታት.....ትላንት ነው የተጀመረው ስለዚ 40 ቀናት ብቻ ይቀራሉ ።
የዛሬው ካርድ ምርጫ ከሶስቱ ካርዶች የትኛው በፐርሰንት ሲሰራ በመካከለኛ ደረጃ በተጠቃሚዎች ይመረጣል የሚል ነው 🙌 የትኛውን መረጣቹ ?
ላልጀመራቹ በድጋሚ 👇👇👇
https://t.me/lost_dogs_bot/lodoapp?startapp=ref-u_5305703538__s_573790
5 648
ከግርግር ዓለም ከብዙ ጫጫታ
ግርማ ሞገስ አለው ያስፈራል ዝምታ
ውል ከሌለው ጩኸት ከውሸት ፈግግታ
ልብን ይማርካል ይደምቃል ዝምታ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
