ch
Feedback
ግጥም

ግጥም

前往频道在 Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

显示更多
4 814
订阅者
+1324 小时
+617
+23730
帖子存档
Repost from N/a

#ካልዳሰስኩ_አላምንም ሊነጋ ነው ሲሉኝ ለኮስኩት ፋኖሴን ሊወብቅ ነው ሲሉኝ ደረብኩት በርኖሴን ሰላም ወርዷል ሲሉኝ ጋሻዬን አራገፍኩ ሰው አልሰማ ብል ነው ክፉ ቀኔን ያለፍኩ ቃል ገብቶ ቃል ማፍረስ ያገር ልማድ ሆኗል እንጀራ እንደመብላት በበሬ እንደማረስ ፍቅር ስጋ ለብሶ በጁ ካላቀፈኝ ተስፋም ብብቴ ስር ገብቶ ካልደገፈኝ ኢምንት ነው ምንም ካልዳሰስኩ አላምንም @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_በዕውቀቱ ስዪም

#ፍቅር_የእውነት_ሲፈርድ የሳቅሽብኝ አልፎ መሳቅ መጀመሬ ሳፈቅርሽ ጠልተሽኝ ዛሬ መፈቀሬ ግዜ ዳኛ ሆኖ ፍቅር የእውነት ሲፈርድ ፈላጊው ሲፈለግ ተወዳጁም ሲወድ የህይወት አዙሪት በተራ መዟዟር የወደደው ጠልቶ የጠላው ሲያፈቅር ይኼ ነው ሚዛኑ በሰፈሩት ቁና ትላንት የገፋ ሰው ዛሬ ወድቋልና። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

🙌 አላችሁ? ናፈቃችሁኝ እኮ

የሰው ልጅ ታሪኩ ከውልደት እስከሞት በውል ተፈትሾ መጽሐፍ ቢጻፍለት ቁም ነገሩ ብቻ ተቆጥሮ ቢዳሰስ ከአንድ አንቀጽ አይዘልም ዘመኑ ቢጠቀስ በዋዛ ፈዛዛ ያሳለፈው ግዜ ይበልጣል ስፍረቱ ከኖረበት እድሜ የሰው ልጅ ህይወቱ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ወፍነት_አማረኝ ምነው ወፍ ባረገኝ በሰማይ በራሪ ከዛፍ ዛፍ መርጬ ነፃ ጎጆን ሰሪ! ሳልዘራ ሳላጭድ ሳልጨነቅ ነዋሪ በማለዳ ድባብ በፍቅር ዘማሪ ሰው ሆኜ ሰው ሆኖ መኖር ከከበደኝ እግዚአብሔር በቃሉ ምነው ወፍ ባረገኝ!!! በክፋት በተንኮል ሰው ሆኖ ከመኖር ወፍነት አማረኝ በነፃነት መብረር!!! @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

ሰው የሚሆን እንጅ የጠፋው ዘንድሮ ዘር የሚቆጥርማ ሞልቷል በየጓሮ እያደሩ ማነስ ሰው መሆን እረክሶ በስጋው ይመካል ለሚቀር በስብሶ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ብታመም_ነው_እንጂ!! የማይገኝ ነገር ያምረኛል ዘንድሮ ወተት ወተት አልኩኝ ገዛሁና ዶሮ በእኔ የደረሰው አይድረስባችሁ ዶሮ ገዝቶ ወተት ከቶ አያሰኛችሁ አወይ የእኔስ ነገር ለማን ይነገራል በቅሎ ስቶልድ ማየት አብዝቶ ያምረኛል ብታመም ነው እንጂ ብለከፍ ዘንድሮ እንዴት ሰው ይመኛል ወተትን ከዶሮ @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

Verified ሆኗል በደንብ ስሩት

#አበጀው_በያቸው አንቺ አትሳቀቂ ሀቁን ንገሪያቸው እውነት ነወይ? ሲሉሽ እውነት ነው በያቸው በአንቺ ፍቅር ያጣሁ ማግኘት ያልታደልኩኝ ትህምርቴን አቁሜ እብድት ያጠናሁኝ ውበትና ፍቅር አቅሌን አስጥለውኝ እብደት በሚል ማዕረግ ሰውነት ያጣሁኝ እኔ ያንቺ ምርኮ የፍቅርሽ ቁስለኛ እብድ ነኝ ለሰዎች ያልሆንኩ ወረተኛ እናም ሲጠይቁሽ ሳትሸማቀቂ በአንቺ መወፈፌን ለሁሉ አሳውቂ ልብሴን አሶልቆ በሰፊ ጎዳና የሚያንከራትተኝ ያው ፍቅርሽ ነውና ለሚጠይቁሽም እንዲህ ንገሪያቸው የአበደው በእኔ ነው አበጀው በያቸው። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

ጌታ መምጫኽ ዘመን ከመድረሱ በፊት ልቤን ልብ ስጠው መልሰው ከጥፋት ጴጥሮስን ከክህደት የመለሰው ዶሮ ለእኔም ላከውና ያንቃኝ ልቤን ሰብሮ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!

#ነይ_አብረን_እንማ ባህል እንዲቀጥል በትውልድ ከተማ በፌስቡክ በቲክቶክ ነይ አብረን እንማ የጥንቱ ዘምኖ ከጀበና እርቆ ሀሜት ዲጂታል ነው ትውልዱ ተራቆ በቀጥታ ግቢ ከሀሜት ከተማ በተሻሻለው ህግ ነይ አብረን እንማ @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

7 ቀን ብቻ ነው የቀረው የቻላችሁትን ሰብስቡ https://t.me/Gleam_AquaProtocol_Bot/app?startapp=cmM9ODdkNTk2OWU

ትማራለች ብዬ ሙያ ከጎረቢት አግብቻት ነበረ አድልቼ ለውበት እንኳንስ ልትማር የምታውቀው ጠፋት ሽንኩርት ግዛ አለችኝ ገንፎ ለማገንፋት። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

Eyeserachut new?

#ምዕራፍ_ያጣ_ፍቅር በጅምር የቀረ ያልተቋጨ ፍቅር ሁሌም የሚታወስ ዘመን የሚሻገር በስንቱ ጓዳ ውስጥ አለ ተሸሽጎ ፍርድን ያላገኘ ያልታየ በሸንጎ ደብቆት ነው እንጂ በልቡ ማህደር የፈራው የሸሸው ለሰው ለመናገር የታሪክ ክታቡ ዶሴው ቢበረበር በእያንዳንዱ ህይወት ያልተቋጨ ፍቅር ሳይፈልግ የተወው አለው ቢመረመር በትዝታ ዜማ በእህ! እህ! እንጉርጉሮ በብቻ ጓዳ ውስጥ በልብ ተቀብሮ ምዕራፍ ያጣ ፍቅር በአጭሩ የቀረ ብዙ ታሪክ አለ!!! ያልተመረመረ። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

Be fast guys it is big project

እራሱን አግዝፎ በሌለው ማንነት ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ሲደነፋ ሀሰት ቃላት ሳተነፍስ በዝምታ ጥልቀት ያንን ሁሉ ጉራ ዘረረችው እውነት። @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ