ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more5 362
Subscribers
-224 hours
+627 days
+20130 days
Posts Archive
5 363
•sᴛᴜᴄᴋ ɪɴ ᴀ ɢᴇɴᴇʀᴀᴛɪᴏɴ ᴡʜᴇʀᴇ ʟᴏᴠᴇ ɪs ᴊᴜsᴛ ᴀ ǫᴜᴏᴛᴇ ᴀɴᴅ ʟʏɪɴɢ ɪs ᴛʜᴇ ɴᴇᴡ ᴛʀᴜᴛʜ°•🚬
https://t.me/OFFICIAL_YANET
5 363
🔤🔤 🔤🔤 🔤🔤🔤🔤🔤🔤
🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠
KINGLYGM INSTANT BOT
በየ 24 ሰአት ውስጥ 0.16$ ይሰጣቿል
1️⃣ በመጀመርያ ይሄን ሊንክ ተጠቅማችሁ ቦቱን አስጀምሩት
https://t.me/kingyGMbot/gmgm?startapp=ref_247504
2️⃣ በመቀጠል ከቴሌግራም ዋሌት ቶን ስፔስ ጋር አገናኙት እና ClaimGM የሚለውን ተጫኑ እና ከ 24ሰአት በኋላ መጥታችሁ ፍሪ GM ውሰዱ።
5 363
🔤🔤 🔤🔤 🔤🔤🔤🔤🔤🔤
🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠
KINGLYGM INSTANT BOT
በየ 24 ሰአት ውስጥ 0.16$ ይሰጣቿል
1️⃣ በመጀመርያ ይሄን ሊንክ ተጠቅማችሁ ቦቱን አስጀምሩት
https://t.me/kingyGMbot/gmgm?startapp=ref_247504
2️⃣ በመቀጠል ከቴሌግራም ዋሌት ቶን ስፔስ ጋር አገናኙት እና ClaimGM የሚለውን ተጫኑ እና ከ 24ሰአት በኋላ መጥታችሁ ፍሪ GM ውሰዱ።
5 363
#ግዜ
ጌዜ ዳኛ ሆኖ በሁሉም ይፈርዳል
የሄደው ይመጣል የመጣው ይሄዳል
ያበደው ይድናል ጤነኛውም ያብዳል
ግዜ እንደፔንዱለም በሁሉም ይዞራል
አንድ የሚቀር የለም ሁሉም ይቀየራል
ቀባሪም በተራው ሞቶ ይቀበራል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
#ናፍቀሽኛል_ብዬ
ናፍቀሽኛል ብዬ ለመጮህ አልወጣ
ሰውም ቢያፌዝ እንጅ አንችን ይዞ አይመጣ
ናፍቀሽኛል ብዬ እኔም ግጥም አልፅፍ
ምን ቤቱን ቢመታ ህመም አያሳልፍ
ናፍቀሽኛል ብዬ ከአንቺ ዘንድ አልደርስም
ከፊትሽ የመቆም ድፍረቱም የለኝም
ናፍቀሽኛል ብዬ እምባም አይወርደኝም
ያንችን ሲያስነባ አይቷል ዓይኔም እሽ አይለኝም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
#እንዲህ_ብለሽ_ጻፊ
በፍቅሬ ተይዞ ስሜን እየጠራ
በየጎዳናው ላይ ብቻውን ሲያወራ
ወፍፎ እየሳቀ አጥቶኝ ሲንከራተት
ለእኔ ፍርቅር ታምኖ ሲሸለመው እብደት
እኔ እስቅ ነበረ በድል ኩራት ጥርሴ
ለእርሱ ጥልቅ ፍቅር ማዘን ትታ ነፍሴ
በሞቀው ከተማ በትርምስ ቀለም
ወድቆ በእኔ ውበት ሲስቅበት ዓለም
አብሬ ስቂያለሁ መውደቁ አስደስቶኝ
ስሜን እየጠራ ሁሌም ሲከተለኝ!!!
ግና ግፌ በዝቶ ሞልቶ ፈሰሳና
እጣውን ቀመስኩኝ በእኔ ደረሰና
እኔም በተራዬ በሌላ ሰው ፍቅር
ወፍፌ እዞራለሁ በወሰድኩት ብድር
እርሱ ዛሬ የለም ለእውነት ኖሮ ሞቷል
ህመም ስቃዩን ግን ለራሴ ውርስ ሆኗል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
ተከታይ ትረካ በ Facebook page ተጀምሯል Follow እያደረጋችሁ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61557221074498
5 363
አንገቴ ጎንበስ በል ይለፍ ይኼ ግዜ
ለሁሉም መልስ አለው ለዛሬው ትካዜ
ነገ ሌላ ቀን ነው ዛሬን አይወክልም
ሀዘን መከራውም በዚህ አይቀጥልም
ቅዝምዝሙ ይለፍ ጎንበስ ልበልና
ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ነውና
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
#ናፈቅሽኝ
ከፍቶሻል መሰለኝ እኔን ሀዘን ዋጠኝ
አልቅሰሻል መሰል ዓይኔን ቆጠቆጠኝ
ሆድ ባሰሽ መሰለኝ ሆዴ ተላወሰ
ትዝ አልኩሽ መሰለኝ ትዝታሽ ፈሰሰ
ካልጠፋው አካሌ ልቤጋ ከበደኝ
ዓይን፣ጥርስ አካልሽ ጨዋታሽ ናፈቀኝ
አቦ ናፍቀሽኛል ብዙ አታስለፍልፊኝ
መምጣት ባትችይ እንኳን ባሳብሽ እቀፊኝ
ያንችን ልክ የያዘው....
የልቤ ላይ ጥጉ ብርድ አንዘፍዝፎታል
አለሁልህ በይው ያ ድምፅሽ ናፍቆታል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
#ማዘንስ_ለከዳ!
ወዳጅ ሸርተት ሲል ጊዜ ሲያዳልጠው
ሰው ከመሆን ወርዶ ገንዘብ ሲለውጠው
አትከፋ ከቶ ወቀሳ አታብዛበት
ጉዳቱ ለእርሱ ነው ከጠላ ሰውነት
በገንዘብ መዝኖ ውብን ጓደኝነት
ሲያረክሰው በንዋይ ያንተን ታማኝነት
ማዘን ለከዳ ነው ለተከዳ አይደለም
ለቃል ያልታመነ ሰላም አያገኝም
ወርቅን አበድረህ መዳብ ቢመልሱ
ይብሳል ፀፀቱ አይተኙም እነርሱ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
#በላቡ_ጠብታ
የከበረ ካለ በላብ በጥረቱ
በተሰጠው ጸጋ እዲሁም በእውቀቱ
የእግዚአብሔርን ገንዘብ ደፍሮ ያላነሳ
ከድሃ ጉሮሮ ነጥቆ ያላገሳ
በላብ በጉልበቱ ለፍቶ የከበረ
ለእውነተኛ ድካም ለቃሉ ያደረ
እስኪ ሰው ፈልጉ ጀግና ባለጸጋ
በቅጡ የሚሰጥ የእግዚአብሔርን ዋጋ
ከእናቶች መቀነት ነጥቆ የማይበላ
በተሰጠው ወንበር ከቶ ማያዳላ
በህጻናት ጉልበት በአባቶች ሳይነግድ
በእውነተኛ ድካም ሀብቱን የሚያሳድግ
በላብ በጉልበቱ በጥረቱ ደክሞ
ሀገሩን ሳይቀማ ለማደጓ ቆሞ
በላቡ ጠብታ ለክብር የበቃ
ለስራ ለትጋት ገስግሶ የነቃ
እርሱ ነው ሰው ማለት ትልቅ ባለዋጋ
ሲጠሩት ደስ የሚል የእውነት ባለጸጋ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
#ምን_አለበት?
ኮንትራት ለሆነ ለዚች ዓለም ኑሮ
ዘመን ላይሻገር ዕድሜ ተበድሮ
ሁልጊዜ እንደሮጠ በሕይወት ጎዳና
በከንቱ ሲባዝን ብሎ ጎንበስ ቀና
ጭቅጭቅ ቅራኔ ሰንቆ ጥላቻ
መዋደድን ጠልቶ ሲኖር ለየብቻ
ላያስከፍል ዋጋ ቅንነት ደግነት
ሰው በክፋት መንገድ ባይሄድ ምን አለበት?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
#ይልቅስ_ልብን_ላክ ❤
ልባችን ሳይማር የፍቅር አቡጊዳ
እንዲሁ እንደ ዘቀጥን ሰው ሳይሰናዳ
አትምጣ ጌታ ሆይ በጎችን ፍለጋ
ትከፍላለህና ዛሬም ሌላ ዋጋ።
ይልቅስ ልብን ላክ ለልብ አልባው ትውልድ
ከመምጣትህ በፊት እርስ በእርስ ይዋደድ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 363
የድሀ ፍቅር
ክፍል15
የመጨረሻው ክፍል
አሪፍ ውጤት ስለነበረ ያመጣሁት ከዮኒቨርሲቲያችን ውስጥ እኔና ሌላ ሁለት ልጆች ለትምህርት እድል ወደ ውጪ ለመሄድ ተመረጥን ነገር ግን ሜላት ደስተኛ እንደማትሆን ሳስብ ግራ ገባኝ ከተመረቅሁ በኃላ እኔና ሜላት እንደድሮው አይደለንም በቃ አብዛኛን ጊዜ እኛ ቤት ስለምትውል በቃ ፀባይዋ ተቀያይሯል የት ወጣህ የት ገባህ ማለትም ጀምራለች እኔ በፍፁም ሜላቴን ማስከፋት አልፈልግም ምክንያቱም ሜላት ሁሉ ነገሬ ናት ፍቅር ሀ ብዬ የጀመርኩባት ብቻ ሳትሆን ዛሬ ላይ ለመድረስ ትልቅ አስተዋፆ ያበረከተችም ጨምር ናት በቃ የምትለኝን ከማድረግ ውጪ ምንም ነገር አላገርግም በፍፁም ከፍቷት ማየት አልፈልግም ሜላት አንዳንዴ በነገር ወጋ ታደርገኛለች እዚህ አድርሼህ ትለኛለች ግን እኔ ምንም መናገር አልፈልግም ብትልም እውነቷን ነው በሷ ሀይል ነው እዚህ የደረስኩት ግን አንዳንዴ ይሄንን ሳስብ የትምህርት እድሉን መጠቀም እንዳለብኝ ይሰማኛል ምክንያቱም ነገ አብረን መኖር ስንጀምር ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ የኔ የሆነ ነገር ሳይኖረኝ አብረን መኖር እንደማንችል ይሰማኛል ሜላት አብረን እንድንኖር ትፈልጋለች በተለይ ታላቅ እህቷ በሚያምር ሰርግ ካገባች በኋላ የማግባት ትዳር የመመስረት ፍላጎቷ ጨምሯል እኔ ደግሞ ይሄንን የማድረግ አቅሙ የለኝም ሜላቴ ሁሌም በስልክም ሆነ በአካል ወሬዋ ትዳር አብሮ መኖር ከዛም ባለፈ ስለ ገንዘብ ሆኗል የእሷ ገንዘብ እንደሚያኖረን ትነግረኛለች ግን ይሄ ለእኔ አላስደሰተኝም እስካሁን ያደረገችልኝ ይበቃል ከዚህ በኋላ እኔ የምትፈልገውን ላደርግላት ነው የምፈልገው ስለዚህ የሷ ሀሳብ አልተስማማኝም ሁሌም በህይወቴ የሚፈጠሩትን ነገሮች ውሳኔ ከመወሰኔ በፊት ለእናቴ አሳውቃታለው በቃ እሷ አድርግ ያለችኝን አደርጋለው እሷ አይሆንም ካለች እተወዋለሁ በቃ አሁንም እናቴን ማማከርና ውሳኔዋን ማወቅ እፈልጋለው እሷ ያለችው ይሆናል ማታ ላይ በረንዳ ቁጭ ብለን እያወራን እያለ ለእናቴ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት ምንም አላስቀረሁም ውሳኔሽን እፍልጋለው ምን ልወስን ግራ ገባኝ አልኳት እናቴ በጣም ስለምታስብልኝ ትክክለኛውን ውሳኔ ነው
የምትነግረኝ ልጄ እዚህ ደረጃ ለመድረስህ የሜላት አስተዋፆ በጣም ትልቅ ነው እሷን በፍፁም እንዳታስከፋት የትምህርት እድልህንም እንዳታጣ ይሄ ላንተ በጣም ጥሩ እድል ነው ለወደፊት ህይወትህ ይጠቅምሀል እኔ የምልህ ከሜላት ጋ ተነጋግራችሁ ውሳኔ ወስኑ ነው አስፋላጊ ከሆነ ነገ ማታ ጥራትና እንመካከር ይሄ ይሻላል ነው የምልህ አለችኝ እሽ እማ አልኳት እናቴ ያለችኝ ነገር ትንሽ ቀለል እንዲለኝ አደረገኝ በማግስቱ ጠዋት ተነስቼ ሜላቴ ጋ ደውዬ ማታ ላገኛት እንደምፈልግና እቤት እንድትመጣ ነገርኳት እሽ አለችኝ ሜላት ጥሩ ስሜት የላትም ብቻ ግን እሽ ስላለች ደስ ብሎኛል ሜላቴ መጥታ ምን እንደምንባባል እያሰብኩ ዋልኩ መምሸቱ አይቀር ሜላትም መጣች እኔም እናቴም ሜላቴም ቁጭ ብለን መነጋገር ጀመርን እናቴ ለሜላት ሁሉንም ነገር ነገረቻት በቃ በመነጋገር የድሮ ፍቅራችሁን አድሱ እኔ እንደድሮው እንድትሆኑ ነው የምፈልገው አለችኝ ተነጋግረን አንድ ውሳኔ ላይ ደረስን እኔም የትምህርት እድሌን እንዳያመልጠኝ መሄድና መማር እንዳለብኝ እኔና ሜላትም ቀለበት ማድረግ እንዳለብን ተወሰነ በሀገር ባህላችን እኔና እናቴ ለሜላት ቤተሰቦች ሽማግሌ ላክን ቤተስቦቿ ትንሽ ቢግደረደሩም እሽ እሉ እኔና ሜላት ቀለበት አሰርን እኔም ወደ አወስትራሊያ ለትምህርት ሄድኩ ፍቅራችን እንደድሮው ሆነ እኔ ያለ ሜላት ሜላት ያለ እኔ ማንንም አንፈልግም ፍቅራችን ችግር ቢበዛውም ችግሩን ተቋቁመን አለፍን::
ተፈፀመ
ውድ አንባቢያን አስተያየትዎን ይስጡን 🙏
@gitm_post
