ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more5 370
Subscribers
-224 hours
+627 days
+20130 days
Posts Archive
5 367
#አድዋ
የጥቁር ህዝቦች ኩራት
የነፃነት ተምሳሌት
የማንነት ኩራታችን
የጀግንነት እርስታችን
አድዋ ነው መለያችን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
#እግረ_መንገድ
አላዋቂ ተጓዥ
እግር አለኝ ብሎ
መንገዱን ሳያበጅ ለመሄድ ይነሳል
ወትሮስ መንገድ እንጅ እግር መች ያደርሳል
እግርማ ታዛዥ ነው ባዘዙት ይሄዳል
ምን እግር ቢኖረው
መንገድ የሌለው ሰው ወዴት ይራመዳል
በማያደርስ እግር ሲሄዱ ከማርጀት
አንዴ ቆም ብሎ መንገድ ነው ማበጀት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
የሆዳም ሰው ግብሩ
ሲተፋ ማደሩ!!!
አልጠግብ ባይ ከርሱ
ሁሉን ማግበስበሱ!!!
የሁሉን ሰው ድርሻ አለመጠን ጎርሶ
ህይወቱን ይገፋል ሆዱን ተንተርሶ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
🛡⚔ KURULUS {ዑስማን} OSMAN ⚔🛡
🧨መስራቹ ዑስማን ክፍል 241 & 242 በትርጉም ሊለቀቅ 30 ደቂቃ ነው የቀረው አሁኑኑ join ይበሉት⤵️ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
5 367
🛡⚔ KURULUS {ዑስማን} OSMAN ⚔🛡
🧨መስራቹ ዑስማን ክፍል 241 & 242 በትርጉም ሊለቀቅ 30 ደቂቃ ነው የቀረው አሁኑኑ join ይበሉት⤵️ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
5 367
❤️ #አፈቅርሻለሁ ❤️
አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ
ፈልጌው አይደለም አላበዛም ሰበብ
ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል
ርሃብ ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል
ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ
ለማንም አልፈቅድም እንዲለዪሽ ከእኔ
ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እሰከማይሽ በዓይኔ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
Repost from Moksho.exe
Don't judge a book by its cover. Judge it by the type of person that recommended you read that book
5 367
#ቀኑ_ይለወጣል
የትላንቱ ችግር ነገ ላይ ተረት ነው
ያሳለፍነው ስቃይ ወደ ፊት ክብር ነው
በዛሬ ውስጥ ሆኖ ፈተናው ቢከብድም
ይለወጣል ቀኑ ዛሬ ነገ አይደለም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
Repost from ጥንቅሻ✍🏼🦋
የፈጣሪ እዝነት ግሩም ነው!!
.
ይህን ለመፃፍ እጄን ሳነሳ አይኔ በእንባ ተሞላ፣ግን ከተማርኩት እና ብርታት ካገኘሁት የህይወት ክፍል ትንሽ ላካፍላችሁ፣ባለማወቅ ውስጥ ሁነን ከምንጠፋ ትንሽም ቢሆን ድክመታችንን አውቀን ወደ ጥንካሬ እንቀይረው፥
.
.
የሰው ልግስና ሁኔታን አስልቶ ነውና ይቋረጣል።የፈጣሪ ግሩምነት ግን በሁኔታ፣ ጊዜ እና ጥቅም የተመረኮዘ አይደለም።"በጠየቅነው ልክ የማይመለስ፣ በመለስነው ልክ ያልተጠየቅነው ነገር ብዙ ነው" ስንቱን ሰርቼ፣ ስንቱን አጥፍቼ ይቅር ብሎኝ ይሆን፥
.
አንዳንዴ እጄን ዘርግቼ መጠየቅ አፍራለሁ፥ ብዙ የማይገቡኝ ነገሮችን በመስጠት ውስጥ ያኖረኝ ፈጣሪን፡ለድክመቴ ብቻ መሸሸጊያ ሳደርገው፣ ዳግም ቀና ብዬ መራመድ ስጀምር ፡መሸሼን ሳስብ ያመኛል፥
.
ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው...ብዙ ሰው መሆን አይጠበቅባችሁም ፈጣሪ ዘንድ ዋጋ እንዲኖራችሁ፣ የፈለጋችሁትን ጠይቃችሁ ለማግኘት፣ ወድቃችሁ መሸሸጊያ ለመፈለግ፣ ከምንም በላይ ደግሞ አጥፍታችሁ ምህረት ለማግኘት፥
.
ለመልካም ነገር እንኳን በቂ ላልሆነ እድሜ ክፉ አንስራበት...እስከዛሬ ስንት ቀን ተጨምሮልን ይሆን? ቀን ዕድሜ ነውና ስንኖር የማይገፋን ፈጣሪን ላለማስቆጣት እንኑር!!!
