cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የማርያም ልጆች ነን

ማርያም ብሂል መርህ ለመንግስተ ሰማያት

Show more
Advertising posts
307
Subscribers
+224 hours
+77 days
+1930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ
Show all...
Show all...
ዝጉ መንገድ ሚዲያ

''ዝጉ መንገድ ሚዲያ '' የዚህ ቻናል ዓላም ተከታዮቹን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው፤ በግል ስብዕናቸው፤ በቢዝነስ ሕይወታቸው እና በሙያዊ ሕይወታቸው ላይ የሚያስፈልጋቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲሁም ጥበብ ለማጎልበት የሚሠራ ድንቅ ቻናል ነው። የ ''ዝጉ መንገድ ሚዲያ''አስተማሪ ቪዲዮችን ለምትፈልጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ!!!

https://youtu.be/OIhbFJUy0Nw?si=6hhr3VOes5XEnZO

የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በ5 ዓቢይ ክፍል ይከፈላሉ። ክፍል1 1. የወንጌል ክፍል ወንጌል ማለት ኢቫንጌሊዩን ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን መልካም ዜና፣ የምስራች፣ ብስራት፣ ስብከት ማለት ነው። ወንጌላት አራት ሲሆን እነዚህም፦ 1.1. የማቴዎስ ወንጌል  የስሙ ትርጉም = ማቴዎስ ማለት በሮማይስጥ ሀብተ አምላክ ማለት ነው። እንዲሁም የአምላክ ስጦታ፣ ከቀራጭነት የተመረጠ ማለት ነው።  ጸሐፊዉ፦ ራሱ ቅዱስ ማቴዎስ ነው። ማቴ 1፡1  የተጻፈበት ዘመን፦ 42 ዓ.ም  የተጻፈበት ቦታ፦ ፍልስጤም ነው።  የተጻፈበት ቋንቋ፦ በዕብራይስጥ ነው።  የተጻፈበት ምክነያት፦  አይሁድ ለጠየቁት ጥያቄ መልስ  ጌታችን የአብርሃምና የዳዊት ዘር መሆኑን ለመግለጽ  ጌታችን አምላከ ነብያት መሆኑን ለመግለጽ  የነብያት ትንቢት በጌታችን መፈጸሙን ለማሳየት ነው።  የተጻፈላቸው ሰዎች፦ አይሁድ ዕብራዊያን ናቸው።  የማቴዎስ ወንጌል 28 ምዕራፎች 1068 ቁጥሮች ሲኖሩት በ6 ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል። 1.2. የማርቆስ ወንጌል  የስሙ ትርጉም = ማርቆስ ማለት ካሕን፣ ልዑክ፣ ታላቅ፣ መዶሻ ማለት ነው።  ጸሐፊዉ= ራሱ ቅዱስ ማርቆስ ነው። ማር 1፡1  የተጻፈበት ዘመን = 44 ዓ.ም  የተጻፈበት ቦታ = በሮም ነው።  የተጻፈበት ቋንቋ = በሮማይስጥ ነው።  የተጻፈበት ምክነያት = ሮማዉያን በዘመናቸው ገናና እኛ ብቻ ነን በማለት ይናገሩ ነበርና የጌታችንን ኃያል፣ ገናና ተአምራቱን ለመግለጽ ነው።  አገረ ስብከቱ = በግብጽ እስክንድርያ በሮምና ሊብያ ናቸው።  የተጻፈላቸው ሰዎች = ለሮማዉያን ነው።  የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል 16 ምዕራፎች 678 ቁጥሮች ሲኖሩት በ6 ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል። 1.3. የሉቃስ ወንጌል  የስሙ ትርጉም = ሉቃስ የሚለዉ ቃል ሊካኖስ ከሚለው የላቲን ቃል የተገኘ ሲሆን መብራት ማለት ነው።  ጸሐፊዉ= ራሱ ቅዱስ ሉቃስ ነው። ሉቃስ 1፡1  የተጻፈበት ዘመን = ከ54-57 ዓ.ም  የተጻፈበት ቦታ = በግሪክ መቄዶንያ ነው።  የተጻፈበት ቋንቋ = በግሪክ ጽርዕ ነው።  የተጻፈበት ምክነያት = ቴዎፍሎስ የተባለ የሮም መኮንን በቃል የተማረዉን የክርስቶስን ነገር እርግጡን/በጥልቀት በሚገባ/ እንዲያዉቅ ለማድረግ ነው።  የተጻፈላቸው ሰዎች = ቴዎፍሎስ ለተባለ የሮም መኮንን ነው።  የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል 24 ምዕራፎች 1151 ቁጥሮች ሲኖሩት በ8 ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል። 1.4. የዮሐንስ ወንጌል  የስሙ ትርጉም = ዮሐንስ ማለት ፍስሐ ወሐሴት ጸጋ እግዚ አብሔር ማለት ነው። እንዲሁም ፍቁረ እግዚእ /ጌታ ይወደው የነበረ/፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ቦኤኔርጌስ የነጎድጓድ ልጆች ማር 3፡17፣ ታዖሎጎስ/ ቴዎሎጎስ/ ነባቤ መለኮት ስለ መለኮት የሚናገር፣ አቡቀለምሲስ ባለ ራዕይ፣ ቁጽረ ገጽ/ ፊቱ በሀዘን የተቋጠረ/ ይባላል።  ጸሐፊዉ= ራሱ ቅዱስ ዮሐንስ ነው። ዮሐ. 21፡20-24  የተጻፈበት ዘመን = በ90 ዓ.ም  የተጻፈበት ቦታ = በኤፌሶን በኤጅያን ደሴት ነው።  የተጻፈበት ቋንቋ = በዮናኒ/ በጽርዕ ቁንቋ ነው።  የተጻፈበት ምክነያት = ሰው ሁሉ የክርስቶስን የባሕርይ አምልካነት አምኖ እንዲድን፣ ይመጣል የተባለው መሲህ ክርስቶስ መሆኑን ለመግለ፣ ክርስቶስ የእግዚ አብሔር የባሕርይ ልጅ እግዚ አብሔር መሆኑን ለመግለጽ ነው።  አገረ ስብከቱ = ከቅዱስ ጲጥሮስ ጋር በኢየሩሳሌምና አከባቢዋ፣ በአንጾኪያና አከባቢዋ፣ በሎዶቂያ፣ በእሲያ፣ በኤፌሶን ሰብኳል።  የተጻፈላቸው ሰዎች = ለኤፌሶን ምዕመናን ነው።  የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል 21 ምዕራፎች 880 ቁጥሮች ሲኖሩት በ7 ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል።
Show all...
ወደኃላ አትመለስ! ብዙዎቻችን ወደፊት መመልከት አቅቶን በትናንት እኛነታችን ውስጥ ነን።ትናንት ያሳለፍናቸው የማይሆኑ,ጊዜያችንን የበሉብን,በሱስ የተጠናወትንባቸው ጊዜያቶች አሁንም ነጋችንን እንዳንኖር እያደረጉን ነው ያሉት። ሁሌም አንድ ነገር አስታውስ አንድ ህይወት ቢቻ ነው ያለችህ። ትላንትናህ ጥሩ ካልነበር ዛሬን ለመኖር ሞክር,ዛሬም ምንም ፈተናዎች ቢበዙብህ ነገን አስብ።ሁሌም አንዲት የመኖር እድልህን በአግባቡ ተጠቀማት።
Show all...
👍 2
Show all...
#ሥነ-ፍጥረት ትምህርት #ክፍል ሰባት #በዲያቆን መዝሙር

subscribe share like Deacon Mezmur Niguse

ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ምክር እና ተግሳጽ 👉 "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ ከዛም ሰማይና ምድር ካንተ ጋር ይታረቃሉ።" 👉 "ያለ ጽናት የምትለማመደው ሥራ ፍሬ አይኖረውም።" 👉 "በመከራ ጊዜ ወዳጅን ማግኘት በጭንቅ ውስጥ ላሉ ትልቅ መጽናኛ ነው።" 👉 "የሚያስደንቅ የሚያዋርድ ኃጢአት ከመሥራት እድን ዘንድ የንስሐ አጋዥ የሚሆኑ አፍአዊ ትህትናን:ውስጣዊ ትህትናን:ጸሎት ዘወትር:ምሕረትና ምፅዋትን:አንብዕ ዘወትርን መያዝ ይገባል።" 👉 "ስለወንድሙ መዳን የማይደክም ድኗል ብዬ አላምንም።" 👉 "በዚህች ምድር ላይ ተስፋ ማጣትህ ለድኀነትህ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል። የምትድነው ግን ተስፋ በማጣትህ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት ነው። በእግዚአብሔር ቸርነት ላይ ተስፋ አትቁረጥ።" 👉 "እግዚአብሔር አንድን የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሰጥህ ቢወድ ፀጋውን ልትጠብቀው ከምትችለው ከትህትና ጋር ይሰጥህ ዘንድ ለምነው አለበለዚያ ግን ከአንተ እንዲያርቀው ጠይቅ።" 👉 "አቤቱ ጌታዬ ንጉሴ ሆይ የራሴን ጥፋት አስመልክተኝ እንጂ በወንድሜ ላይ እንድፈርድ አታድርገኝ።" 👉 "ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እውነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለው።እውነተኛ ትህትና ትሩፋትን መሥራት ነው።" 👉 "ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ጸሎትን የማታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም ንጹሕ ፀሎትን አድርግ ይኸውም በሀጢአት ለዓለም መሞት ነው። 👉 "የክርስትና ትክክለኛ ሕግ ቀጥተኛ ትርጉም ከፍተኛ ጉልበት ይህ ነው። ይኸውም የሁሉ ጥቅም የሆነውን ነገር መሻት ነው።"      የአባታችን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ረድኤት በረከቱ አይለየን ምልጃና ጸሎቱ ይጠብቀን አሜን።
Show all...
ተመራቂ ተማሪዎች ከዚህ እየገባችሁ የራሳችሁን የመውጫ ፈተና ማግኘት ትችላላችሁ(2015 ዓ. ም )
Show all...