cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

B-POEMS

Ecclesiastes 12 (አማ) - መክብብ 1: የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ብንኖር በዚህ ቻናል ላይ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች ፣ የተለያዩ ጽሑፎች ይቀርባሉ

Show more
Advertising posts
785
Subscribers
-324 hours
-77 days
-1730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሉቃ 24:5 " ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ "ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም ። እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል!
Show all...
🙏 1
እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት አደረሳችሁ
Show all...
Repost from ያሬዳውያን
ሐሙስ 1.ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል። 2.ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። 3. የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። 4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። 5. የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። 🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈                  👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹       @EOTCmahlet     #Join & share
Show all...
+ አንዲት ዘለላ እምባ   + ቅዱሱን መጽሐፍ ለማንበብ ፈልጌ በድንገት ብገልጠው ፣ አየዋት ያቺን ሴት የጌታዬን እግር በእንባዋ ስታጥበው ፣ ምናለ እሷን ብሆን ብዬ ተመኘሁኝ ፣ ለበደሌ ጸጸት እምባንም ላጣሁኝ ፣ ወለል ብሎ ታየኝ ያጠፋሁት ጥፋት ፣ ግልጥልጥ አለልኝ የበደሌም ክፋት ፣ ከዛም በመቀጠል አንድዬ ፈጣሪን እንዲህ ስል ጠየኩት ፣ እባክህን ስጠኝ አንዲት ዘለላ እምባ ፣ ለሰራሁት ስራ ለኀጢአቴ ላምባ ፣ የበደሌን ብዛት የኀጢአቴን ክፋት በማልቀስ ልግለጸው ፣ ፍቀድልኝና ከእግርህ ወድቄ በእምባዬ ልጠበው ፣ በዛውም ይታየኝ የጥፋቴ ብዛት ፣ ደግሜ እንዳልሰራው እንዲያድርብኝ ጸጸት ፣ ከሰጠኸኝ መክሊት አንዱን እምባ አድርገው ፣ ጽድቅን አትርፌበት ነፍሴን አድኜበት ላንተው ልመልሰው ፣ ✍ ብሩክ መለሰ @orthopoems @orthopoems @orthopoems
Show all...
1
Repost from ያሬዳውያን
#ዕረቡ በማቴዎስና በማርቆስ ወንጌል መሠረት በዚህ እለት ሦስት ነገሮች ተደርገዋል። 1. የካህናት አለቆች ጸሀፍትና ፈሪሳውያን በጌታ ላይ ተማክረዋል ሊያስገድሉትም ወስነዋ። 2. ጌታችን በስምኦን ዘለምጽ ቤት ተገኝቶ አንዲት ሴት(ማርያም እንተ ዕፍረት) ዋጋው የከበረ የአልባስጥሮስ ሽቱ ቀብታዋለች። 3. ይሁዳ ጌታን ለመሸጥ ወደ ጸሀፍት ካህናት ጋር በመሄድ ተዋውሏል። በአይሁድ ዘንድ 72 አባላት የነበሩት ሸንጎ ነበር። "ሲናድርየም " ይባላል።አብዛኛዎቹ ሰዱቃውያን ሲሆኑ ጥቂቶቹ ጸሀፎችና ፈሪሳውያን ነበሩ። የተሰበሰቡትና ጌታን እንዴት እንደሚይዙት የተማከሩት በካህናቱ አለቃ በቀያፋ ግቢ ነበር። በዚ ጊዜ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የነበረው ያስቆሮቱ ይሁዳ ወደ ስብሰባው በመሄድ "ምን ትሰጡኛላችሁ እኔ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ" በማለት ጌታን ለመሸጥ ተዋዋለ።ይህን ያደረገው በስምኦን ዘለምጽ ቤት እያሉ አንዲት ሴት ጌታን የከበረ ሽቱ ስትቀባው ለድሀ አዛኝ በመምሰል "ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር "ሲል ጌታ የልቡን መሻት አውቆ ስለተቃወመው አኩርፎ ሄዶ ተዋውሎ በ30 ብር የተስማማ። ከዛም ሊያስገድሉት ወስነዋል። እንዲሁም ሐሙስ በአል ስለነበር በአሉን አክብረው ውለው ማታ ላይ አስይዘው አርብ ጠዋት ሸንጎ ሊያቆሙት ተስማምተው ተለያዩ (ማቴ 26÷3.. ማር 14÷1-11 ሉቃ 22÷1-6) በዚህ እለት በቤተክርስቲያን የሚሰበከው ምስባክ - አንድ ሰአት መዝ 83÷5 - ሦስት ሰአት መዝ 41÷6 - ስድስት ሰአት መዝ 41÷5 - ዘጠኝ ሰአት መዝ 83÷2 - አስራ አንድ ሰአት መዝ 6÷2 © ተግባራዊ ክርስትና
Show all...
👍 2
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ማክሠኞ በዚህ ዕለት አምላካችን ለጥያቄዎች በሙሉ መልስ የሰጠበት እና በስፋት ያስተማራቸው ትምህርቶች የሚታሰቡበት ዕለት ነው። ፩. የጥያቄ ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት አምላካችን ስለ ሥልጣኑ በካህናት አለቆችና በሕዝብ አለቆች"በምን ሥልጣንህ እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?"(ሉቃ፳:፩-፵፩) የሚል ጥያቄ ለፈተና የተጠየቀበት ዕለት በመሆኑ የጥያቄ ቀን ትባላለች፡፡ ጥያቄዎቹ በቁጥር አምስት ናቸው። እነዚህም:- ፩. ሥልጣኑን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፪) ለክፋት የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄውን በጥያቄ መልሶታል። ፪. በወይን አትክልት መስሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል። (ሉቃ፳:፱)ይህ ምሳሌ በቀጥታ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝ ተረድተውም ነበር። ፫. ግብርን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፳፪) ይህንንም በድንቅ ጥበቡ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብሎ መልሶላቸዋል። ፬. ትንሣኤ ሙታንን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፴፫) ከጋብቻ ጋር በተገናኘ ምድራዊ አስተሳሰብ ሰማያዊውን ኑሮ አውርደው ለጠየቁት ለሰዱቃውያን ከሞት በኋላ እንደ መላእክት ያለን ኑሮ የመኖር ዕድል እንዳለው የሰው ልጅ መልሶላቸዋል። ፭. ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ለምን ይሉታል የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።(ሉቃ፳:፵፩) መልስ ላጡበት ጥያቄ ራሱ በመመለስ እርሱ የዳዊት ጌታ መሆኑን አስተምሯቸዋል። ፪. የትምህርት ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት ደቀ መዛሙርቱን ሰፊ ትምህርትን ስለ መጨረሻው ዘመን ምልክቶች አስተምሯቸዋልና የትምህርት ቀን ተብላ ትጠራለች። (ሉቃ፳:፵፬-፵፯) ያስተማራቸው ትምህርቶች ፩. የአምልኮ መልክ ካላቸው ተጠንቀቁ ፪. ታይታን ከሚወዱ ተጠንቀቁ ፫. ለራሳቸው ክብርን ከሚሰጡ ተጠንቀቁ ፬. የባልቴቶችን ገንዘብ ከሚበሉ ተጠንቀቁ ፭. በምክንያት ጸሎት ከሚያረዝሙ ተጠንቀቁ ሌላው በግብረ ሕማማት ካህናት በዚህች ዕለት ስለሚያከናውኗቸው ስራዎች እንዲህ ተብሎ ተገልጿል:-"ከዚህ በኋላ በከበረች ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ከሌሊቱ መጀመሪያው ሰዓት ካህናት ይሰብሰቡ። ተዘከሮ እግዚኦ የሚለውን የዳዊት መዝሙር ወአሰሰልኩ ዕለተ እስከሚለው ድረስ ጸልዩ። ውዳሴ ማርያምም የቀዳሚትን ይድገሙ።" ግብረ ሕማማት (ገጽ፪፻፴፪) የመዝሙረ ዳዊት ምንባባት በ፩ ሰዓት (መዝ፴፬:፬-፭) በ፫ ሰዓት (መዝ፻፲፰:፻፶፬) በ፮ ሰዓት (መዝ፲፯:፲፯) በ፱ ሰዓት (መዝ፳፬:፩) በ፲፩ ሰዓት (መዝ፵፬:፮) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
🙏 1
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ሰኞ ፩. መርገመ በለስ (በለስ የተረገመችበት) ዕለት ነው። አንድምታ፡ ወንጌሉ እና ግብረ ሕማማቱ ላይ እንደተገለጸው ☞በለስ የቤተ እስራኤል እና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌ ናቸው ፡፡ ጌታችን ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ፤ አላገኘም፡፡ ስለዚህም እስራኤል ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡ ☞በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት "ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም፡፡" በማለት ፈጸማት ፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት ፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡ ☞በለስ ኃጢአት ናት ፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ "በአንቺ ፍሬ አይገኝ" ማለቱም "በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር" ማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በአምላካችን እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ ፪. አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተከናወነበት ዕለት ነው። ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት" ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፣ ገርፎም አስወጣቸው...'' እንዲል። (ማቴ ፳፩፡፲፫) ምስጢሩ :- ☞ቤተመቅደስ የሆንን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም በማለት ሊቃውንት ይገልጹታል። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 2
Show all...
"አቤቱ እባክህ አሁን አድን" ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

Ethiopian Orthodox Tewahedo Song By Like Mezemeran Tewodros Yosef "Abetu Ebakeh Ahun Aden" © Mahtot Tube is the only Channel that has exclusive rights for all Lyrics produced by Like Mezemeran Tewodros Yosef