cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Show more
Advertising posts
29 968Subscribers
+224 hours
+287 days
+53230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዛሬም በፍትወት ከመቃጠልና ከመበሳጨት የተነሣ ብዙ መንፈሳዊያንና ዓለማውያን ብልቶታቸውን በመቁረጥ አደጋ ላይ እየወደቁ ይገኛሉ:: ድንግልናዋ እንዲጠበቅ በማለት ለሙጻኣ ስንት (ለሽንት መውጫ) ያህል ብቻ በመተው የልጃገረዶችን ብልት የሚተለትሉና የሚሰፉ ጎሳዎች በሀገራችን መኖራቸው ይታወቃል፡፡ በእርግጥ ብልትን ቆርጦ መጣል እንደ ጽድቅ ይቆጠር ይሆን?
   በምንም ዓይነት መመዘኛ ቢሆን የወንድ ብልትን መቁረጥም ሆነ የሴቶችን ብልት መስፋት የጽድቅ መንገድ ሆኖ አይቆጠርም፡፡
ደዌያት እንደ አሸን በሚፈሉበት በዚህ ዘመን ምንም ዓይነት ቅዱስ መጽሐፋዊ መሠረት የሌለውን የሴት ልጅ ብልት መተልተልና መስፋት በልጃገረዶች ላይ የሚፈጸም ከባድ ስሕተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ጭምር ነው::   ፍትወት ከልክ በላይ ሆኖ ቢያስቸግርህ አካልህን በመቁረጥ ወይም በማቁሰል ለማምለጥ አታስብ፡፡ ይህ የሰይጣን ወጥመድ ነውና። «በምኞት ለሚቃጠሉ» ሰዎች ፈጣሪ የሰጠው መፍትሔ ማግባት ነው እንጂ ብልትን መቁረጥ አይደለም፡፡ ሐዋርያው «በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ» በማለት መክሯል፡፡ 1ቆሮ7፥9 በፍትወት የተቸገረ ሰው ብልቱን መቁረጡ ሰርቆ የተያዘ ሰው ከሚደርስበት ድብደባ ጋር ይመሳሰላል:: ያ ሌባ በመደብደቡ እንደ ሰማዕት ተቆጥሮ ጸጋ እንደማያገኝበት ሁሉ ይህም ሰው ከመቁሰልና ከመታመም በቀር የሚያገኘው ምንም ጸጋ የለምና፡፡    በራስ ላይ «ምትረተ እስኪት» መፈጸም ራስ አጥፊ ራስ ቀጪ መሆን ነው:: በዝሙት ጊዜ ሰው የሚበድለው በአባለ ዘሩ ብቻ ሳይሆን በልቡናውና በሕሊናውም ጭምር ነው:: ስለዚህ የበደለው በሁለመናው ሰውዬው ነው እንጂ አንድ አካሉ ወይም አባለ ዘሩ ብቻ አይደለም፡፡ ታዲያ አባለ ዘርዕ ብቻ ተቆርጦ የሚጣለው በምን ዕዳው ነው? አባለ ዘር በመቆረጥ ከተወገደ ከእርሱ ጋር የበደሉ ልቡናና ሕሊና እንዲሁም ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ምን ሊደረጉ ይችላሉ? ሰው ሁሉ የበደለ አካሉን በመቁረጥ የሚያስወግደው ከሆነ አልበደለም ተብሎ ሳይቆረጥ ለሰው የሚቀርለት አካል ይኖር ይሆን? ዝሙት ሲታሰብና ሲፈጸም ሰው የሚበድለው በሁለንተናው ስለሆነ ብልትን መቁረጥ ራስ አጥፊ ራስ ቀጪ ከመሆን በቀር ጥቅም የለውም፡፡   በዚህም ላይ ሰይጣን ብልትን መቁረጥ ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ ካሳመነን በኋላ ቆየት ብሎ ደግሞ እንደ ይሁዳ በሠሩት ኃጢኣት ሲጸጸቱ ራስን መግደልም ተገቢ እንደ ሆነ ሳያሳምነን አይቀርም፡፡ ራስን የማጥፋት ሓሳብ ብልትን ከመቁረጥ ይጀምራልና። ማቴ 27፥3-5፤ የሐዋ 1፥16-20   በፍትወት መቃጠል የሚመነጨው ከውስጥ ነው:: ስለሆነም ውጫዊ ሕዋስ ኀፍረተ አካልን በመቁረጥ ከፍትወት መገላገል አይቻልም፡፡ ሲራክ «ፈቃዱ ላይፈጸምለት ጃንደረባ ቆንጆ ይመኛል (ያቅፋል)» በማለት ተናግራል፡፡ ይህም ምንም ጃንደረባ (ስልብ) ቢሆኑ ፍትወት ከልብ አለመራቁን ያመለክታል፡፡ አካልን ቆርጦ ፍትወትን እንዳራቁ ማሰብ ጠብ መንጃ ተኩሼ ሰይጣንን እገላለው እንደ ማለት ነው::    ሰይጣን አካልህን እስክትቆርጠው ድረስ በልዩ ልዩ መንገድ እያደፋፈረ ያነሣሣሃል፡፡ እንደ ጀግናና ቁርጠኛ ሰው ለመታየት ብልታቸውን የሚቆርጡ አሉ፡፡ ይህ በትዕቢትና በከንቱ ውዳሴ መሻት የተነሣ የሚመጣ ነው:: ሆኖም «ምትረተ እስኪት» ሁልጊዜ መጠን የሌለው ጸጸት ማስከተሉ አይቀርምና ከወዲሁ ማሰብ ብልህነት ነው:: ሰው የሚሠራው ኃጢአት ዝሙት ብቻ አይደለም፡፡ ራሱን ቢመረምር ከዝሙትም የከፋ ኃጢአት ይገኝበታል:: ለወሬ ካልሆነ በቀር ከኃጢኣት ነጻ ሊያወጣ የማይችልን አማራጭ መከተል ምን ይጠቅማል? ከማንኛውም ኃጢአት ለመለየት ኃጢአትን ከልብ መጥላትና እግዚአብሔርን መፍራት ያስፈልጋል:: እነዚህ ንስሐንና በጎ ሥራን ይወልዳሉና፡፡    «ምትረተ እስኪት» ስሜታዊነትን፣ ሽንፈትን፣ ስንፍናን፣ ስልቹነትን፣ ታካችነትን፣ አርቆ አለማሰብን ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደትና በመሳሰሉት መንፈሳዊ ተግባራት እየታገሉ ከዝሙት ለመለየት ከመጣጣር ይልቅ በቅጽበት ለመገላገል ከመፈለግ የሚመነጭ ሐሳብ ስለሆነ ነው:: የሚያስከትለውን የጤና ቀውስ፣ ጸጸትና እስከ ሞት የሚያደርስ ሥቃይን ከዚህ በተጨማሪም ከእግዚአብሔር ሕግ አንጻር ተቀባይነት እንደ ሌለው አለማወቅ አርቆ አለማሰብ መሆኑንም ያስረዳል፡፡    ፍትሐ ነገሥት (ፍትሕ መንፈሳዊ) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ራሳቸውን ጃንደረቦች ያደረጉ አሉ» በማለት በወንጌል የተናገረውን ቃል ሲያብራራ «ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ቃል አባለ ዘርን ስለመቁረጥ አልተናገረውም እንዲህ ያለ ሥራ ከመንግሥተ ሰማይ ያርቃልና» ይላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ «ኀፍረተ አካሉን የቆረጠ ሰው ካህን ቢሆን ይሻር» ይላል፡፡ ካህን ካልሆነ ደግሞ ክህነት እንዳይሰጠው ያግዳል፡፡ በሕገ ኦሪት ደግሞ ብልቱ የተቆረጠ ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ እንዳይገባ ይከለከል ነበር። ዘዳ 23፥1    ያለውድ በግድ፣ በጦርነትና በልዩ ልዩ ደዌ ምክንያት አባለ ዘራቸው የተቆረጠ ሰዎች ከላይ የተጠቀሰው እገዳ አይመለከታቸውም:: ማለትም ክህነት መቀበልና በክህነታቸው መቀጠል ይችላሉ።    ይህን መንፈሳዊ አስተምህሮ ከመገንዘብ አስቀድሞ እስኪታቸውን ለቆረጡ ሰዎች ሌሎች ሰዎች ሊያደርጉላቸው ስለሚገባው ነገር መጽሐፈ መነኮሳት «ኢታስተኀቅሮ ወኢትመንኖሙ ለምቱራነ ኣባል>> ይላል፡፡ «አካል ብልት የጎደላቸውን ሰዎች አታዋርዳቸው» ማለት ነው:: ምክንያቱም ምንም ስሕተት ቢሆን አንድ ጊዜ ፈጽመውታል:: በተጨማሪም ከማወቃቸው በፊት መልካም መስሏቸው ስለንጽሕና ብለው አድርገውታልና ነው:: ማር ይስ አን2ምዕ13    ስለ ኀፍረተ አካል መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘዳግም እንዲህ ይላል፡፡ «ሁለት ሰዎች እርስ በእርሳቸው ቢጣሉ የአንደኛውም ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ እጅዋንም ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ እጅዋን ቁረጥ፤ ዓይንህም አትራራላት፡፡» ዘዳግም 25፥11 እንዲህ ዓይነት ሕገ ርትዕ በአዲስ ኪዳን በሕገ ትሩፋት የተተካ ቢሆንም ኀፍረተ አካል ምን ያህል ጥንቃቄ የሚደረግለት መሆኑን ያሳያል፡፡ እንኳን ቆርጦ መጣል ይቅርና በማይገባ የሚነካው እንዳይኖር ማስጠንቀቂያ ነው:: እንኳን ቆርጦ መጣል ይቅርና በማይገባ የነካችው ሴት እጇ ያለርኀራኄ እንዲቆረጥ መታዘዙ ኀፍረተ አካል በመንፈሳዊ አይታ ከ«እጅ» ምን ያህል የበለጠ ክብር እንዳለው አያስረዳምን?   «እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ» በማለት ሐዋርያው ተናግሯል:: ነገር ግን «ብልቶች» በማለት የጠቀሰው የአካልን ልዩ ልዩ ክፍሎች ሳይሆን ልዩ ልዩ ክፉ ክፉ ፍላጎቶችን ነው:: ኀፍረተ አካልን ለማመልከት ቢሆን ኖሮ «ብልቶቻችሁን» ከማለት ይልቅ «ብልታችሁን» ይል ነበር፡፡ ለምን ቢባል ለአንድ ሰው ብዙ ኀፍረተ አካል የለውምና፡፡ ይኸው ሐዋርያ «ብልቶች» ያለውን እነዚህም፡ «ዝሙትና ርኩሰት፣ ፍትወትም፣ ክፉ ምኞትም፣ ጣዖትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው» በማለት በግልጽ ትርጓሜውን አስፍሯል፡፡ ቆላ3፥5 ስለዚህ ክፉ ክፉ ፍላጎትን መዋጋት እንጂ አካልን ቆርጦ በመጣል ሰይጣንን ማጥቃት አይቻልም።
Show all...
👍 4 1
          ምዕራፍ አምስት             ምትረተ እስኪት   «ምትረተ እስኪት» ማለት አባለ ዘርዕን መቁረጥ ማለት ነው:: በሀገራችን ሌላውን መስለብ እንደ ባህል የሚነገርላቸው አንዳንድ ጎሳዎችና ብሔረሰቦች ይገኛሉ:: በዘመነ ኦሪትም ቅዱስ ዳዊት ሜልኮል የተባለች የንጉሥ ሳኦልን ልጅ ለማግባት የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ሰልቦ በማምጣት ማጫ መስጠት ነበረበት፡፡ 1ሳሙ 18፥25-27
Show all...
9👍 1
    «ምትረተ እስኪት» ከፍትወት ፆር ለመዳን ሲሉ ልዩ ልዩ አካላቸውን ከቆረጡ ለምሳሌ፡ እጁን እንደ ቆረጠ እንደ አባ አትናቴዎስ፣ ዓይኑን በወስፌ እንዳወጣ እንደ ስምዖን ሰፋዬ አሣዕን፣ እግሩን በእሳት እንዳቃጠለ እንደ አባ መርትያኖስና እንደ ሌሎች ቅዱሳን አበው የተጋደሎ ሥራ ልንመለከተው አንችልም:: (ተአምረ ማርያም፣ ማቴ 5፥29 ትርጓሜ) ምክንያቱም፦ አንደኛ ከላይ የተጠቀሱት አበው ዓይናቸውን፣ እግራቸውንና እጃቸውን ቆርጠው ሲያስወግዱ በዋናነት የተሰናካሉት እነርሱ ራሳቸው አልነበሩም፡፡ ሌሎች የእነርሱን ሕዋሳት በማየት ስለተሰናከሉ መሰናክል የሆነውን አካላቸው በማስወገድ ለሌሎች ያላቸውን ፍቅርና ኀዘኔታ ሕዋሳታቸውን እስከ ማስወገድ ደርሰው አሳዩ፡፡ ሁለተኛ እጅ፣ ዓይን፣ በድሮ ጊዜ አለባበስ ደግሞ በአጭር ሲታጠቁ የእግር ባት በቀላሉ ለእይታ የተጋለጡ ናቸው:: በዚህም ምክንያት ተመልካች እነዚህን በማየት ሊሰናከል መቻሉ ግልጥ ነው:: ኀፍረተ አካል ግን በድሮ ጊዜም ቢሆንም በልብስ ይሸፈናልና ሌሎችን ያሰናክላል ተብሎ አይታሰብም:: ስለዚህ ሌሎችን ሕዋሳት ቆርጦ መጣል አባለ ዘርን ቆርጦ ከመጣል ጋር ማመሳሰል አይገባም:: ገንዘብን ለአዝማሪና ለዘዋሪ እየበተኑ ብሉልኝ ጠጡልኝ ማለት ከመመጽወት እንደማይቆጠር አካልን እስከ መቁረጥ ደርሰው አበው የፈጸሙት ገድል እስኪትን (ብልትን) ከመቁረጥ ጋር በምንም አይመሳሰልም፡፡ ሦስተኛ ኀፍረተ አካል ከሌሎች ሕዋሳት በላይ ሊታይ ይገዋባል:: ሌሎች ሕዋሳት እንደ ንዑስ የአካል ክፍል ሲታዩ እርሱ ግን እንደ ሙሉ ሰው ይቆጠራል:: ምክንያቱም የሕይወት መተላለፊያ በመሆኑ ነው:: ሐዋርያው «በምናፍርባቸው ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል» በማለት የተናገረው ቃል ከሌላ ሕዋሳት በላይ ኀፍረተ አካል ተጨማሪ ክብር እንዳለው ያመለክታል፡፡ 1ቆሮ 12፥23 ስለዚህ እጅና እግርን መቁረጥና ብልትን መቁረጥ አንድ አይደለም፡፡    እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን ንጉሥና የሾመውን ካህን መግደል ምንም እንኳን ሰው ቢሆኑ ተራ ሰው ከመግደል ጋራ እኩል ተደርጎ አይታይም፡፡ ይህም በንጉሥ ዳዊት ይታወቃል፡፡    እግዚአብሔር ቀብቶ ሳኦልን ስላነገሠው ብቻ ጠላቱ ሆኖ ሳለ መግደል በሚችልበት ጊዜ «እግዚአበሔር የቀባው ነውና፣ እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር አደርግ ዘንድ እጄንም እጥልበት ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው::» ብሏል:: 1ሳሙ 24፥6 ነገር ግን ዳዊት ከዚህ በፊትና በኋላ ጎልያድን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሰዎችን እንደገደለና እንዳስገደለ ተጽፏል፡፡ እንደዚሁም ኀፍረተ አካል እንደ ሌሎች ሁሉ አካል ቢሆንም ከሕዋሳት መኻል እንደ ካህንና ንጉሥ ነው:: ስለዚህ ኀፍረተ አካልን ቆርጦ መጣልና ሌላ አካልን መቁረጥ በእኩል አይታይም::    ቅዱሳን አበው የእግዚአብሔር ፍቅር አስክሯቸው አካላቸውን ቆረጡ ሆኖም ጽድቅ ሆኖ ሲነገርላቸው ይኖራል:: ሆኖም በልዩ ልዩ መንፈሳዊ መጻሕፍት ኀፍረተ አካላቸውን ስለቆረጡ ሰዎች ቢነገርም እየተነቀፉ እንጂ ሌላ ሕዋሳቸውን እንደቆረጡ አበው ጽድቅ ተደርጎ የተነገረበት ቦታ የለም:: ዛሬ ዛሬ በእውነተኛ መንፈስ እንኳን ኀፍረተ አካሉን ይቅርና ጣቱን ለመቁረጥ የሚያበቃ ፍጽምና ያለው ሰው አይገኝም:: ስለዚህ አካልን በጽድቅ ሰበብ ለመቁረጥ ማሰብ እርካብ (ደረጃ) ሳይረገጡ ወደ ሰገነት (ፎቅ) ለመውጣት እንደ መሞከር ይቆጠራል፡፡ አካልን እስከ መቁረጥ መድረስ የፍጹማን ሥራ ነውና:: እነርሱ ከዚህ ጋር ሌላውንም የጽድቅ ሥራ ሠርተው የተገኙ ናቸው:: ዛሬ ኀፍረተ አካሉን ለመቁረጥ የሚያስብ ሰው ግን ከሱ በፊት ሊፈጽመው የሚገባ ብዙ ነገር ይቀረዋል፡፡ ስለዚህ ነው ይህን መሞከር «ያለ ሀቅም መወጣጠር» ያሰኘው::     መጽሐፈ መነኮሳት አሞንዮስ የተባለ ጻድቅ የዝሙት ፈተና በተነሣበት ጊዜ «ያውዕዮ ለአባለ ዘር» ፥ «አባለ ዘሩን በእሳት ይተኩሰው ነበር» ይላል፡፡ ኣሞንዮስ እንዲህ ያደረገው ፍጽምናን ገንዘብ አድርጎ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ነው እንጂ ደረጃው ሳይሆን ቀርቶ ጸጸት በሚያስከትልበት መልኩ ያለማገናዘብ አድሮበት በብስጭት አይደለም፡፡ አሞንዮስ ይህን ለማድረግ መወሰን የሚያስችል ብቃት እንደ ነበረው የሠራቸው ሌሎች ሥራዎቹ ምስክሮች ናቸው:: በተጨማሪም «መተኮስ» እና «ቆርጦ መጣል» በጣም የተራራቁ ነገሮች መሆናቸውን ልብ ማለት ይገባል፡፡    ይህ ደግ ሰው ጵጵስና እንሹምህ በተባለ ጊዜም «ቀረጸ ዕዝኖ ዘጸጋም፣ ግራ ጆሮውን ቆረጣት› ተብሎለታል:: ይህን ያደረገው መልከ ጥፉ ለመሆንና መምህራቸው ጎራዳ ነው ይሉናል በማለት እንዳይሾሙት ስለፈለገ ነው:: አንድም ይህንንማ ከሾምነው በግራው ሆነን ብናናግረው «ተጠቃቀሱብኝ (ዘበቱብኝ)» በቀኝ ብናናግረው ደግሞ «አይሰማም ብለው ነው» ይለናል ብለው እንዳይሾሙት ፈልጎ ነው:: የአሞንዮስ በጎ ሥራ አካሉን በመጉዳት የሚያበቃ አይደለም:: እንዲያውም ይህን ለማድረግ የበቃው ሌሎች የሚጠበቁበትን ሥራዎች በአግባቡ ስላከናወነ ነው:: ስለ ሌላ መልካም ሥራው አባ ወቅሪስ እስኪመሰክርለት ድረስ እንዲህ የሚል ተጽፏል፡፡ «በእንተ ተጋድሎ ሕሊናት ይጸመድ ጸሎታተ ወአጽዋማተ በቅጥቃጤ ነፍስ በትሕትና በጻማተ ሥጋ በምግባራት አንተ ለቅኔ እግዚአበሔር ወሰብእ» ፊልክ ክፍ 1 ተስእ 7    ከሰይጣነ ዝሙት ፈተና የተነሣ እንኳን አባለ ዘርን መቁረጥ ይቅርና «ምነው ከማኅፀን ጃንደረባ ሆኜ በተወለድሁ ኖሮ!» በማለት መመኘትም ስሕተት ነው:: ለዚህም በፊልክስዩስ መጽሐፍ የተጻፈው ቃል ምስክር ነው:: ኃይለ ቃሉም «ሦበ አጥወቀከ ሰይጣን በእንተ ተቃጥሎ ዝሙት ኢትቅርፅ አምኔከ አባለ ዘርዕ ወኢትፍቅድ ከመ ትኩን ሕፅወ እም ከርሠ እምከ» ይላል፡፡ ይህም «ዝሙትን እንድትፈጽም ሰይጣን ባስጨነቀህ ጊዜ አባለ ዘርዕን አትቁረጥ፡፡ ከእናትህም ሆድ ጀምሮ ጃንደረባ መሆንን አትፈልግ» ማለት ነው:: ፊልክ ተስእ 186  ከዚህ አልፎ ራሱን የሰለበውን ፍትሕ መንፈሳዊ «እመቦ ዘሐፀወ ርእሶ በፈቃዱ ይሰደድ ሠለስተ ዓመተ» ይለዋል:: ይህም «በፈቃዱ ራሱን የሰለበ ለሦስት ዓመት ከቤተ ክርስቲያን ይሰደድ» ማለት ነው:: ፍትሐ ነገ አን24 በቀጣይ ምዕራፍ ስድስት <<ለዐቅመ ሔዋን የመድረስ ምልክቶች>> በሚል ይቀጥላል..... ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
13👍 6🙏 4😱 2🥰 1
በሰሙነ ሕማማት ባሉ ቀናት የግዝት በዓላት(12፣ 21 ወይም 29) ቢያጋጥሙ እንኳ ስግደት ይሰገዳል!! ያዳምጡት! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
19👍 8👏 3🙏 2
<<የተዋሕዶ ልጆች>> አዲስ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል በልዩ አቀራረብ፤ ኑ ተቀላቀሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido
Show all...
የተዋሕዶ ልጆች

ሁሉንም ለተዋሕዶ ልጆች፦ 📚 የየዕለቱ ስንክሳሮች በጠዋት ❄ ትምህርቶች 🎤 ስብከቶች 🎶 መዝሙሮች 📄 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፎች በpdf 💒የቅዳሴ ምስባክ 🎤 ወቅታዊ የቤ/ክ ዜናዎች ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችን እንዲሁም የሚፈልጉትን ነገር በ @Ethiop_tewahido_bot ይጠይቁን።

👍 7 3
<<የተዋሕዶ ልጆች>> አዲስ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል በልዩ አቀራረብ፤ ኑ ተቀላቀሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido https://t.me/Ethiop_tewahido
Show all...
የተዋሕዶ ልጆች

ሁሉንም ለተዋሕዶ ልጆች፦ 📚 የየዕለቱ ስንክሳሮች በጠዋት ❄ ትምህርቶች 🎤 ስብከቶች 🎶 መዝሙሮች 📄 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፎች በpdf 💒የቅዳሴ ምስባክ 🎤 ወቅታዊ የቤ/ክ ዜናዎች ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችን እንዲሁም የሚፈልጉትን ነገር በ @Ethiop_tewahido_bot ይጠይቁን።

ኒቆዲሞስ የዐብይ ጾም ሰባተኛ እሑድ(ሳምንት) ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ምልክት አሳየን›› እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ ‹‹ሕጋችን ተሻረ›› ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ፣ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ ኒቆዲሞስ ሰምቶ፣ ተመልክቶ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ከጌታው፣ ከመምህሩ ከክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ይገሰግስ ነበር (ዮሐ. ፫፥፩)፡፡ ምስክርነቱንም እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ፤ ‹‹መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከኾነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና፤›› (ዮሐ. ፱፥፳፬፤ ሐዋ. ፲፥፴፰)፡፡ ይህን ምስክርነቱን በሚሰጥበት ጊዜም ጎዶሎን የሚሞላ፤ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፤ ከምድራዊ ዕውቀት ወደ ሰማያዊው ምሥጢር የሚያሸጋግር አምላክ ‹‹ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም፤›› በማለት የአይሁድ መምህር ለኾነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጥያቄ አቅርቧል (ዮሐ. ፫፥፮፤ ፩ኛጴጥ. ፩፥፳፫)፡፡ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፤›› (ኤፌ. ፭፥፳፮) በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ቢያስረዳውም ምሥጢሩ ከአቅሙ በላይ ስለ ኾነበት እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡ አበ ብዙኃን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ ለመማለድ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምሥጢር ከአምላኩ በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስም፡- ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ኾነህ ሳለ ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም … ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመነበት ዅሉ ለዘለዓለም ሕያው ኾኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም ...፤›› እያለ ሰው በመብል ምክንያት የአምላኩን ትእዛዝ አፍርሶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ፣ ስመ ክርስትናን፣ ሀብተ ወልድን ለመስጠት ጌታችን መምጣቱን አስረዳው (ዮሐ. ፫፥፲፬)፡፡ ይህን የክርስቶስን የማዳን ሥራና በሥጋ መገለጥም ‹‹ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረከ ዐመፃ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፤ ልቤን ፈተንኸው፡፡ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንከኝም፡፡ ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤›› (መዝ. ፲፮፥፫) በማለት ቅዱስ ዳዊት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማዛመድ አመሥጥሮታል፡፡ በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ ‹‹ወአልቦ ፍርኃት ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ፣ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል›› (ማር. ፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡  በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -ሮሜ ፯፥፩-፱ -፩ኛ ዮሐ ፬፥፲፰ እስከ ፍጻሜ -የሐዋ ሥራ ፭፥፴፬ እስከ ፍጻሜ ምስባኩም፦ መዝ ፲፮፥፫ "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመጻ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለእመሕያው" "ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘህብኝም የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው" ወንጌሉም፦ ዮሐ ፫፥፩-፳ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 12 12😢 1
"ኒቆዲሞስ" በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ ኒቆዲሞስ/፪/ክቡር፣/፪/ ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር፣/፪/ በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ፣ በመከራው ጽናት ይህን ዓለም ናቀ፣ መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ፣ የትዕቢትን ጅረት : በትህትና : ተዋርዶ አደረቀ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ፍርሀትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ፣ ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ፣ የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ፣ ከመቅደሱ አንቀጽ : ላይረሳ : አምድ ሆኖ ታጠረ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች፣ ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች፣ ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች፣ እንደ ኒቆዲሞስ : ነፍስህም : ተምራ ተመለሰ። °°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°° ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 24 9🥰 7😢 1
"እግዚአብሔር ያጽናናሽ" እግዚአብሔር ያጽናናሽ                  ዕንባሽን ያብሰው፣ ቤተክርስቲያን ሆይ                  እስከመጨረሻው፣ ካህንሽ በመቅደስ           ከበጎቹ ጋራ ስለታረደብሽ፣ እንደ ራሔል ዕንባ                  እግዚአብሔር ያስብሽ። ስለ ጌታ ፍቅር ማህቧተን ይዛ                       አክሊል ተቀዳጀች፣ በደሙ ከዋጃት ከክርስቶስ ጋራ                        እኖራለሁ አለች፣ የእምነት ሰማዕትነት ሲመጣ በገሃ፣ ይሻሙ ነበረ ከእሳቱ ለመንደድ።         አዝ= = = = = በዚህ በእኛ ዘመን ቅዱሳን ተሻሙ፣ አክሊሉን ለመውሰድ ከሁሉ ሊቀድሙ፣ የተክለሃይማኖት የክርስቶስ ሠምራ ሕፃናት ተነሱ፣ በመሞት ህይወትን ከእግዚአብሔር ሊወርሱ፣         አዝ= = = = = አሕዛብ አትድከም በመግደል አትጸድቅም፣ ነፍሰ ገዳይነት አሸንፎ አያውቅም፣ በበቀል ጭካኔ የሰው ልጅን ማረድ፣ እጅግ የወጣ ነው ከሃይማኖት መንገድ።         አዝ= = = = = ይቺ ቤተክርስቲያን የተገነባችው                              በደም ስለሆነ፣ በሞት ሕይወት ሊያገኝ                           ክርስቲያን ታመነ፣ ምድሪቱ ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት፣ ሕዝቧም ሊወድቅ ቀርቧል እንደበግ መስዋዕት።                     በሊቀመዘምራን ይልማ ኃይሉ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
👍 25 6😢 6