en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Open in Telegram
1 330
Subscribers
No data24 hours
+97 days
+8030 days
Posts Archive
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የማኔጅመንት አባላት በቢሮውና በኮሌጆች ቅንጅት የሚሰሩ የአቅመ ደካሞችን ቤቶችን ተዘዋውረው ጎበኙ፤ **** በዚህም አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ማኔጅመንታቸው በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 02፣ 05 እና 08  የሚገኙ በአዲስ መልክ እየተሰሩ የሚገኙ እና ተጠናቀው ለርክክብ ዝግጁ የሆኑ የአቅመ ደካሞችን ቤት በአካል በመገኘት ተመልክተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ኮሌጆች የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በአጠቃላይ 7 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በአዲስ ሰርተው ለማስረከብ በዚህም ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የማኔጅመንት አባላት በቢሮውና በኮሌጆች ቅንጅት የሚሰሩ የአቅመ ደካሞችን ቤቶችን ተዘዋውረው ጎበኙ፤ **** በዚህም አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ማኔጅመንታቸው በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 02፣ 05 እና 08  የሚገኙ በአዲስ መልክ እየተሰሩ የሚገኙ እና ተጠናቀው ለርክክብ ዝግጁ የሆኑ የአቅመ ደካሞችን ቤት በአካል በመገኘት ተመልክተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ኮሌጆች የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በአጠቃላይ 7 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በአዲስ ሰርተው ለማስረከብ በዚህም ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የማኔጅመንት አባላት በቢሮውና በኮሌጆች ቅንጅት የሚሰሩ የአቅመ ደካሞችን ቤቶችን ተዘዋውረው ጎበኙ፤ **** በዚህም አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ማኔጅመንታቸው በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 02፣ 05 እና 08  የሚገኙ በአዲስ መልክ እየተሰሩ የሚገኙ እና ተጠናቀው ለርክክብ ዝግጁ የሆኑ የአቅመ ደካሞችን ቤት በአካል በመገኘት ተመልክተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ኮሌጆች የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በአጠቃላይ 7 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በአዲስ ሰርተው ለማስረከብ በዚህም ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን የሚፈልግ መሆኑ ተጠቆ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ ቀጥሎ የሲዳማ ክልል አፈፃ
የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን የሚፈልግ መሆኑ ተጠቆ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ ቀጥሎ የሲዳማ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በዚህ ዓመት የሚደረገው የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን ይፈልጋል ብለዋል፡፡ ዜጎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከመደበኛ እና አጫጭር ስልጠናው በተጨማሪ በልምድ የተገኘ ሙያ ላይ ግብ አስቀምጦ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ ጥቅምት 12፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/ ኤክስ ፡- https://x.com/Jobs_FDRE

ድሬ የሥራና ክህሎት ሀገርህን ዕወቅ ክበብ የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጀ፤ ክበቡ ከተመሠረተ ሶስተኛ አመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት ተከታታይ አመታት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን ከመደበኛ ስራ ጎን ለጎን ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ዕድል የፈጠረ ሆኗል። በዛሬው ዕለትም ክበቡ እንዲመሰረትና ተጠናክሮ የተቋቋመበትን አላማ እንዲያሳካ በቡዙ ያገዙትንና የደገፉትን የቢሮው እና የኮሌጅ አመራሮችን አመስግነዋል። በቀጣይም ካለፉት ጊዜያት በተሻለ የሰራተኛውን መቀራረብና ለተሻለ የተልዕኮ አፈጻጸም መነቃቃትን በሚፈጥር መልኩ እንዲንቀሳቀሱ የክበቡን አባላት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው አበረታተዋል። የሥራና ክህሎት ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ድሬ የሥራና ክህሎት ሀገርህን ዕወቅ ክበብ የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጀ፤ ክበቡ ከተመሠረተ ሶስተኛ አመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት ተከታታይ አመታት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን ከመደበኛ ስራ ጎን ለጎን ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ዕድል የፈጠረ ሆኗል። በዛሬው ዕለትም ክበቡ እንዲመሰረትና ተጠናክሮ የተቋቋመበትን አላማ እንዲያሳካ በቡዙ ያገዙትንና የደገፉትን የቢሮው እና የኮሌጅ አመራሮችን በማመስገን በቀጣይ ካለፉት ጊዜያት በተሻለ የሰራተኛውን መቀራረብና ለተሻለ የተልዕኮ አፈጻጸም መነቃቃትን በሚፈጥር መልኩ የክበቡን አባላት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው አበረታተዋል። የሥራና ክህሎት ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡ በሥራ
+2
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ደ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጻ ሰጥተዋል፡፡ ዶ/ር ተሻለ በመግለጫቸው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ እንደሚዘጋጅ ገልጸው በዚህ ዓመትም የ12 ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 526,683 የሚሆኑት ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ ስልጠና ለመሰልጠን ተቋማቱን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡ ገበያ ተኮር በሆኑ በአጫጭር ስልጠናዎች ደግሞ ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተቋማቱ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ሰልጣኞች በተቋማቱ በቂ ክህሎት ታጥቀው እንዲወጡ በክረምቱ የአሰልጣኞች የአቅም ግንበናታ ስልጠና፣ የማሽነሪዎች ጥገና እና አስፈላጊ የማሰልጠኛ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ይህንን የመቁረጫ ነጥብ መነሻ አድርገው ሰልጣኞችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል፡፡ ለማህበራዊ ሳይንስ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ የተቀመጡ የመቁረጫ ነጥቦች ዝርዝር ከታች ይመልከቱ ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ ጥቅምት 11፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols

☝️☝️☝️የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ፤

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኙት የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በተለያየ የትምህርትና ስልጠና መስክ ያሰለጠኗቸውን ሰልጣኝ ተማሪዎች በጋራ በደማቁ  አስመረቁ። የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሀር በምረቃ መርኃግብሩ ላይ ተገኝተው ለተመራቂ ሰልጣኝ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን ክቡር ከንቲባ በመልዕክታቸው ተመራቂዎች የነገው ህይወታቸውን ለመቀየር መጪው ዘመን ፉክክርና ተወዳዳሪነት የበዛበት በመሆኑ እራሳቸውን በክህሎት፣ በዕውቀትና በቴክኖሎጂ በቴክኒክና ሙያ አብቅተው በተለይ በድሬዳዋ አስተዳደር የተፈጠሩ ዕድሎችን በመጠቀም ለአገሪቷ መጻኢ ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት በ2016 ዓ.ም ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ 447 ሴት 234 ወንድ በአጠቃላይ 681 ሰልጣኞች ተመራቂ መሆናቸውን ገልጸው መጪው ጊዜ በርካታ የሰለጠነ የሰው ሀይል የሚፈልግ በመሆኑ ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና ተመራቂዎች የሚኖራቸው ሚና የላቀ እንደሚሆንና በተለይ በሥራ ዕድል ፈጠራው አቅጣጫ አቅም እንዲፈጥሩ ቢሮው እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን "ትምህርትና ዕውቀት ፍለጋ መጨረሻ የሌለው በመሆኑ በኮሌጅ ያዳበራችሁትን ጥረትና ትጋታችሁን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል" ብለዋል፤ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ካሪኩለም ሰልጥናችሁ የተመረቃችሁ ከፊታቸው ብዙ ዕድሎች እንደሚጠብቋቸው አስታውሰው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በምረቃ ስነስርዓቱም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ፈቲህያ አደን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ሮቤል ጌታቸው፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ክብርት ፈጡም ሙስጠፋ፣ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን፣ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት የተመረቁ ሰልጣኝ ተማሪዎች የዘንድሮ ምረቃ ስነስርዓት ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ በዘርፍ አዲሱ ፖሊሲ መሰረት ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሰልጣኝ ተማሪዎች የተመረቁበት ሲሆን ከፍተኛ አካዳሚክ ውጤት ያላቸው ሰልጣኝ ተማሪዎች ተሸላሚም ሆነዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኙት የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በተለያየ የትምህርትና ስልጠና መስክ ያሰለጠኗቸውን ሰልጣኝ ተማሪዎች በጋራ በደማቁ  አስመረቁ። የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሀር በምረቃ መርኃግብሩ ላይ ተገኝተው ለተመራቂ ሰልጣኝ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን ክቡር ከንቲባ በመልዕክታቸው ተመራቂዎች የነገው ህይወታቸውን ለመቀየር መጪው ዘመን ፉክክርና ተወዳዳሪነት የበዛበት በመሆኑ እራሳቸውን በክህሎት፣ በዕውቀትና በቴክኖሎጂ በቴክኒክና ሙያ አብቅተው በተለይ በድሬዳዋ አስተዳደር የተፈጠሩ ዕድሎችን በመጠቀም ለአገሪቷ መጻኢ ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት በ2016 ዓ.ም ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ 447 ሴት 234 ወንድ በአጠቃላይ 681 ሰልጣኞች ተመራቂ መሆናቸውን ገልጸው መጪው ጊዜ በርካታ የሰለጠነ የሰው ሀይል የሚፈልግ በመሆኑ ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና ተመራቂዎች የሚኖራቸው ሚና የላቀ እንደሚሆንና በተለይ በሥራ ዕድል ፈጠራው አቅጣጫ አቅም እንዲፈጥሩ ቢሮው እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን "ትምህርትና ዕውቀት ፍለጋ መጨረሻ የሌለው በመሆኑ በኮሌጅ ያዳበራችሁትን ጥረትና ትጋታችሁን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል" ብለዋል፤ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ካሪኩለም ሰልጥናችሁ የተመረቃችሁ ከፊታቸው ብዙ ዕድሎች እንደሚጠብቋቸው አስታውሰው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በምረቃ ስነስርዓቱም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ፈቲህያ አደን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ፣ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን፣ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት የተመረቁ ሰልጣኝ ተማሪዎች የዘንድሮ ምረቃ ስነስርዓት ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ በዘርፍ አዲሱ ፖሊሲ መሰረት ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሰልጣኝ ተማሪዎች የተመረቁበት ሲሆን ከፍተኛ አካዳሚክ ውጤት ያላቸው ሰልጣኝ ተማሪዎች ተሸላሚም ሆነዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ