en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Open in Telegram
1 326
Subscribers
+224 hours
+67 days
+11030 days
Posts Archive
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የብልፅግና ህብረት የ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ሩብ አመት ኮንፈረንስ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ። በተካሄደው ኮንፈረንስ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ  እንዳሉት የብልጽግና ህብረቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ የፖለቲካ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልፀው  በተለይ ደግሞ ከመንግስት ሥራ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የተገኘው ውጤታማ አፈጻጸም በጥምረት መቅረቡ ፖለቲካው ህብረተሰቡን የሚጠቅም ተጨባጭ ስራ ለመስራት  ወሳኝ ሚና እንዲጫወት አድርጎታል ብለዋል። የብልጽግና ህብረቱ ም/ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ አክለው በአስተዳደሩ ትኩረት የተሰጠውንና የቢሮው ዋነኛና ተቀዳሚ ተልዕኮ የሆነውን ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ አባላት ውጤት ሊያስገኝ የሚችልን ስራ በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በግንባር ቀደምነት ልንሰለፍ ይገባል ብለዋል። በኮንፈረንሱ ፕሮግራም ላይ የብልጽግና ህብረቱ የዘጠኝ ወር የዕቅድ ክንውን ሪፖርት እና የቀጣይ 3 ወር ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት በአባላቱ በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን በመጨረሻም በቀጣይ ህብረቱን እና የኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን አደረጃጀትን የሚመሩ አመራር ምርጫን በዴሞክራሲያዊ መንገድ  በማከናወን ኮንፈረንሱ ተጠናቋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከተማዋን ጽዱና ውብ የማድረግ ዕቅድ አካል የሆነ የጽዳት ዘመቻ  ተካሄደ። በቢሮው ቅጥር ጊቢ እና አካባቢ ላይ በተካሄደው ጽዳት ዘመቻ የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ። በዘመቻው ላይ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለጹት ድሬዳዋን ጽዱ የምናደርገው እኛው እንጂ ሌላ አካል አለመሆኑን በመገንዘብ ሁሉም የቢሮው ማህበረሰብ ቀጣይነት ያለው የአካባቢውን ንጽሕና የመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። የፅዳት ዘመቻው በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል ። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ አገራዊ ጉባዔ ላይ የተሰጡ አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ በድሬዳዋ አስተዳደር በሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች ላይ የተዘጋጀ የሦስት ወራት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡ የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ በቀጣይ ሦስት ወራት ውስጥ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ ስራዎችን በመለየት ዝርዝር የድርጊት መርሃግብር በማዘጋጀት በስሩ ለሚገኙ አንድ ማዕከላት ዕቅዱን በማውረድ በዕቅድ ጊዜያቶች ውስጥ በአጠቃለይ የሚፈጠሩ የስራ እድሎችን በአስተዳደሩ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡ የአስተዳደሩን ሥራ እድል ፈጠራን ከማጠናከር አንጻር ዋናዋና በዕቅዱ የተመላከቱ   ለስራ እድል ፈጠራው በየአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎችን የመለየት ስራ በትኩረት ይከናወናል፡፡   በልምድ ተገኙ ክህሎቶችን የመለየት ስራ ይከናወናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በልምድ የተገኙ ክህሎቶች በምዘና የብቃት ማረጋገጥ ስራ ይከናወናል፡፡   ኢ-መደበኛ የሆኑ አንቀሳቃሾችን የመለየትና መረጃዎቻቸውን የማደራጀት ስራ ይከናወናል፡፡   በገጠርና በከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራው ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን ይሆናል፣   ዜጎች በውጪ አገር የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት ይሰራሉ፡፡   የወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል የስራ ባህል ሊቀይሩና ከፍተኛ ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ የማይንድ ሴት ስልጠናዎች የሚሰጡ ይሆናል፡፡   በተጨማሪ የማህበራዊ ልማቶችን የሚደግፉ ስራዎችን ለመስራት ታቅዷል የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ አገራዊ ጉባዔ ላይ የተሰጡ አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ በድሬዳዋ አስተዳደር በሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች ላይ የተዘጋጀ የሦስት ወራት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡ የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ በቀጣይ ሦስት ወራት ውስጥ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ ስራዎችን በመለየት ዝርዝር የድርጊት መርሃግብር በማዘጋጀት በስሩ ለሚገኙ አንድ ማዕከላት ዕቅዱን በማውረድ በዕቅድ ጊዜያቶች ውስጥ በአጠቃለይ የሚፈጠሩ የስራ እድሎችን በአስተዳደሩ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡ የአስተዳደሩን ሥራ እድል ፈጠራን ከማጠናከር አንጻር ዋናዋና በዕቅዱ የተመላከቱ   ለስራ እድል ፈጠራው በየአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎችን የመለየት ስራ በትኩረት ይከናወናል፡፡   በልምድ ተገኙ ክህሎቶችን የመለየት ስራ ይከናወናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በልምድ የተገኙ ክህሎቶች በምዘና የብቃት ማረጋገጥ ስራ ይከናወናል፡፡   ኢ-መደበኛ የሆኑ አንቀሳቃሾችን የመለየትና መረጃዎቻቸውን የማደራጀት ስራ ይከናወናል፡፡   በገጠርና በከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራው ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን ይሆናል፣   ዜጎች በውጪ አገር የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት ይሰራሉ፡፡   የወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል የስራ ባህል ሊቀይሩና ከፍተኛ ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ የማይንድ ሴት ስልጠናዎች የሚሰጡ ይሆናል፡፡   በተጨማሪ የማህበራዊ ልማቶችን የሚደግፉ ስራዎችን ለመስራት ታቅዷል የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት የስርዓተ-ፆታ ትግበራ መመሪያን ለማዘጋጀት የተሰራው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ:: የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ ላለፉት ወራት ለዚህ ተግባር በተዋቀሩ ባለሙያዎች ሲዘጋጅ የቆየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዛሬው እለትም ለኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: የEASE ፕሮጀክት በቀጣይ አመታት በሚኖረው ትግበራ በHard Skills ላይ የሴት ሰልጣኞችን ቁጥር በተቻለ መጠን ለማሳደግ ትኩረት እድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም ይህንን የዳሰሳ ጥናት በከፍተኛ ተነሳሽነት ያዘጋጁ ባለሙያዎችን አመስግነው በቀጣይም የስርዓተ-ፆታ መመሪያው ተዘጋጅቶ በአጭር ጊዜ ወደ ትግበራ እንዲገባ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል:: ፕሮጀክቱ በዚህ የትግበራ ማእቀፍ በዋነኛነት የሴት ሰልጣኝ ተማሪዎችን እንዲሁም የኮሌጁ ሴት ሰራተኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ የምንሰራበት ነው ያሉት ደግሞ የEASE ፕሮጀክት ዋና ኮርድኔተር ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ ይህ ትግበራ በትክክል ግብ እንዲመታ ከማድረግ አኳያም የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱን የጉዳዩ ባለቤት በሆኑት ሴት አሰልጣኝ መምህራን እና ሴት አመራሮች እንዲዘጋጅ እድርገናልም ብለዋል:: በEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5አመት ውስጥ በስርዓተ-ፆታ ላይ ለሚከናወኑ ተግባራት መነሻ የሚሆን መመሪያ ለማዘጋጀት የተሰራው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በወ/ሮ ራሄል እሸቱ እንዲሁም በኢንጂነር ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በHard Skills ላይ የሴት ሰልጣኞችን ውስነት መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ ጥናትም በዋነኛነት የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት ሴት ሰልጣኞች የተሳተፉበት ሲሆን በተጨማሪም ዲፓርትመንት ተጠሪዎች፣ ሴት አሰልጣኝ መምህራን፣ የኮሌጁ ዲኖች እንዲሁም እንዱስትሪዎችንም በጥናቱ ተሳታፊ እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ ለሚስተዋለው ችግር መንስኤ ናቸው ያሏቸው ጉዳዩችም ለጥናቱ በግብአትነት ተካተውበታል:: በመድረኩ በቀረቡት የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቶች መነሻነት ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት የተካሄደ ሲሆን ጥናቱንም ለማዳበር ተጨማሪ ግብአቶች የተገኘበት መድረክም ነበር:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም

በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ከአስተዳደሩ የገጠር ወረዳዎች ምክትል ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አካሄዱ። በዚህም በአጠቃላይ የሥራና ክህሎት ስራዎች
በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ከአስተዳደሩ የገጠር ወረዳዎች ምክትል ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አካሄዱ። በዚህም በአጠቃላይ የሥራና ክህሎት ስራዎች ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ተቀናጅቶ እና ተናብቦ የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በሚሰሩበት አግባብ ላይ ውይይት አድርገዋል። በተለይም በገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ትኩረት በመስጠት  የገጠር ስራ ዕድልን ስርዓትን ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን ማረምና መለወጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በተጨማሪም አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደተናገሩት የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት (LLRP) ወጣቶችን ፣ ሴቶችን ብሎም ሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎችን በማህበር በማደራጀት አዋጭ በሆኑ የስራ መስኮች ተሰማርተው የገቢ ምንጫውንም በማስፋት ኑሯቸውን የሚያሻሽሉበትን መንገድ ለማመቻቸት እየተሰራ ያለውን ስራ ትርጉም ባለው መልኩ የገጠሩን ነዋሪ ህይወት ቀያሪ ሆኖ ማሳየት ይገባል ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በሥራና ክህሎት ቢሮ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገነቡት የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለሚሰሩ የቀን ሰራተኞች በስራ ቦታ ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ ለ2ኛ ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ። መድረኩን በመክፈት ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ኤች አይ ቪ ኤድስ ሴክሬተሪያት ባለሞያና የፅ/ቤቱ ተወካይ የሆኑት አቶ የኋላሸት ውብሸት ሲሆኑ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ስራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል ከተለያዩ ቦታዎች በስራ የሚገናኙ እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ይህ ሀይል ወጣቶችንና ሴቶችን በከፍተኛ ቁጥር ያካተተ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የዛሬው መድረክ እንደተዘጋጀ ገልፀው መድረኩን አስጀምረዋል። በመቀጠል የዕለቱን ስልጠና የሰጡት አቶ ፈቲ መሀመድ ሲሆኑ የስልጠናውን ሰነድ ካቀረቡ በኋላ መድረኩን ለውይይት ክፍት በማድረግ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎችን ተቀብለው ምላሾችንም ሰጥተዋል። በመጨረሻም የሥራና ክህሎት ቢሮ የሴቶች ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ማርታ በዛብህ  ይህ አይነቱ መድረክ በተከታታይነት እንደሚዘጋጅና ተጨማሪ ስራዎችም ቢሮው እንደሚሰራ ገልፀው መድረኩ ተጠናቋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የትምህርትና ስልጠና ስርዓቱን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ወቅቱን ያማከለ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በICT ዲፓርትመንት የተጀመረውን የትምህርትና ስልጠና ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝድ የማድረግ ስራ በስፋት እንዲከናወን ለማድረግ ያለመ የውይይት መድረክ ተካሄደ:: በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አንደኛው በትኩረት ከተያዙ ጉዳዮች ውስጥ የትምህርትና ስልጠና አሰጣጡን ዲጂታላይዝድ ማድረግ ነው ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም እሁን ላይ የትኛው ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሲደረግ የአይ.ሲ.ቲ መሰረት ልማትና የግሪን ኢነርጂ ላይ ትኩረት እዲደረግ ይጠይቃልም ብለዋል:: ICT ላይ ቀድሞ የተጀመረና የዲጂታል ኮንቴንት (E-learning System) ላይ የተሰራ ስራ መኖሩን ያስትትወሱት የEASE ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ የተጀመሩትን ስራዎች ኮሌጁ የልህቀት ማዕከል በሆነባቸው ዘርፎች ላይ እያሰፋን እስከ ፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ድረስ በኮሌጁ ያሉትን እንቅስቂሴዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ለመቀየር እሰራለንም ብለዋል:: በኮሌጁ የICT ዲፖርትመንት አማካኝነት የትምህርትና ስልጠናውን ለማዘመን እየተሰራ ያለው ስራ ይበልጥ ለማስፋት የተዘጋጀውን ሰነድ በዲፓርትመንቱ ተጠሪ አሰልጣኝ መ/ር አቤል ፋንታሁን አማካኝነት የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይም በICT አሰልጣኝ መምህራን እንዲሁም በኮሌጁ ሀላፊዎች ውይይት የተካሄደበት ሲሆን በተቀመጠው Action plan መሰረትም ወደ ትግበራ እንደሚገባ ከመድረኩ ማወቅ ተችሏል:: የE-Learning system/ የትምህርትና ስልጠናውን ከማዘመኑም በተጨማሪ ሰልጣኝ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ቆይታቸው ስልጠናቸውን እንኪያጠናቅቁ ድረስ ሙሉ የትምህርትና ስልጠና መረጃቸውን ሲሰተሙ የሚይዝ በመሆኑ የስልጠናቸውን ሁኔታና አፈጻጸም እንዲሁም የትምህርትና ስልጠናውን ጥራት በማስጠበቅ ረገድ የራሱን እስተዋፅኦ እንደሚያደርግም ይታመናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ሚያዚያ 2/2017 ዓ.ም