en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Open in Telegram
1 329
Subscribers
+324 hours
+87 days
+8330 days
Posts Archive
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የ2017 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ሰልጣኞች ቅበላ በመንግስትና በግል ኮሌጆች ላይ የትምህርት ማስረጃ ጥራትና አግባብነት የማረጋገጥ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤ በዚህም በየአመቱ በአስተዳደሩ የሚገኙ ሁሉም የግልና የመንግስት ኮሌጆች የሰልጣኝ ቅበላ ሲያካሂዱ በተላለፈላቸው የአሰራር መመሪያ ማከናወኛ መሰረት ሲሆን ከዚህ በተለየ ኮሌጆች ለራሳቸው በሚያመቻቸው መንገድ ከተቀመጠላቸው መመሪያ ውጪ በሚገባ ባልተፈተሸና ባልተረጋገጠ ሀሰተኛ ማስረጃ ሰልጣኝ ከተቀበሉ በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያት የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በወቅቱ ለማረምና ለመቆጣጠር የትምህርት ማስረጃ ጥራትና አግባብነት የማረጋገጥ ሥራ የሚከናወን ይሆናል፡፡ በዋናነት ኤጀንሲው ባለው ስልጣንና በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ኮሌጆቹ ከመነሻው በወረደላቸው የቅበላ መመሪያ መሰረት ምዝገባ ማከናወናቸውን የማረጋገጥና ሰልጣኞች ያቀረቧቸው የትምህርት ማስረጃዎች ትክክለኛውን ከሀሰተኛው በመለየት ቅበላው በየደረጃው መቁረጫ ነጥብ መሆኑን ፈትሾ በሚገኙ ክፍተቶችና ከመመሪያ ውጪ በሆኑ አካሄዶች ላይ ፈጣንና አግባብነት ያለው የማስተካከያና የእርምት ስራዎችን ለመስራት አላማው አድርጎ የሚሰራ መሆኑ ታውቋል፡፡ በመሆኑም በመንግስትና በግል ኮሌጆች በ2017 ዓ/ም በአገር አቀፍ ደረጃ በተላለፈው የመቁረጫ ነጥብ መሠረት የ2017 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ሰልጣኞች ቅበላ ላይ የትምህርት ማስረጃ ጥራትና አግባብነት ትክክለኛ መሆኑን በማረጋገጥ በተሰጣቸው ህጋዊ የማሰልጠን ፈቃድ ብቻ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰልጣኞችን በሞያ መስኩና ደረጃ መቀበላቸውን በተቀመጠው የቴ/ሙ/ት/ስ የስልጠና ጥራት ስታንዳርድ መሰረት መሆኑን በማስጠበቅና በማረጋገጥ ተቋማት ህግና ደንብን በሚገባ አክብረው እንዲሰሩ ኤጀንሲው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በመቆጣጠር በህግ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት እንዲወጣ ያስችለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት በተቋሙ በሚከናወኑ Building & Infrastructure Renovation ስራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ:: በመድረኩ በኮሌጁ አጠቃላይ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን 21ኛውን ክፍለ ዘመን ባማከለ መልኩ ሳቢና ለስልጠና ምቹ ከማድረግ አንፃር የሚያስፈልጉ የRenovation ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በባለሙያዎች ተለይቶ ቀርቧል:: በዚህም በቀረበው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ላይ የኮሌጁ ማኔጅመንት ጨምሮ የስልጠና ክፍል ተጠሪዎችና የኮንስትራክሽን ዲፖርትመንት አ/መምህራን በተገኙበት ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በዚህም በጥናቱ ላይ ሊካተቱ ይገባል ያሏቸውን ነጥቦችና ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ለጥናቱ ግብአት የሚሆኑ ሀሳቦችንም አስቀምጠዋል:: የRenovation ትግበራው የEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5 አመት ከሚከውናቸው ትግብራዎች አንዱ ሲሆን ፕሮጀክቱ በተቋሙ በሚኖረው ቆይታም መሰል ተግባራትን የሚያካትት መሆኑም ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም

በድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ እና በቢሮው ስር ለሚገኙ የሚድያ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተሰጠ፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫው መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም ሚድያ ትልቅ አቅም ያለው ኃይል ነው ይህንንም ኃይል ከኮሌጁ ጋር በማስተሳሰር የአካባቢው ወጣቶች ብሎም በመለው ሃገሪቱ ያሉ ማህበረሰቦች እንዲጠቀሙበት ማስቻል ይኖርብናል ብለዋል፡፡አያይዘውም በዛሬው እለት ለሚድያ አካላት የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ስለ ኮሌጁ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጥሩ ግበአት የምታገኙነት ይሆናል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም በስልጠናው ወቅት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ብሩክ ፈለቀ እንዳሉት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ የሚሰጡ ስልጠናዎች ማህበረሰቡን በተለይም ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል ያማከለና በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርትና ስልጠና ሊሰጥ ይገባል ያሉ ሲሆን ከዚህ ረገድ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየሰራ ያለበት አግባብ ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ ለኢትዮጵያ የሚተተርፍ ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም ኮሌጁ ያለውን እምቅ ሃብት ማህበረሰቡ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ የተሳተፉ የሚድያ አካላት በሰጡት አስተያየትም ሰልጣኞች በኮሌጁ ቆይታቸው ወቅት ስልጠና ከማግኘት በዘለለ የስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እንዲሁም ትምህርትና ስልጠናው በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን እየሰራው ባለው ስራ እጅግ እንደተደሰቱና በቀጣይም በተለያዩ ስልጠናዎች ከኮሌጁ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ም/ኮምሽነር ማኦ ተሾመ የተመራ ልኡክ ቡድን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት አደረገ፡፡ ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በመደበኛና በአጫጭር ስልጠናዎ
+4
በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ም/ኮምሽነር ማኦ ተሾመ የተመራ ልኡክ ቡድን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት አደረገ፡፡ ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በመደበኛና በአጫጭር ስልጠናዎች በርካታ ወጣቶችን የስራ ባለቤት ማድረግ የቻለ ተቋም ነው፡፡ኮሌጁ የህዝብ ሃብት እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ይህን እምቅ ሃብት ሊጠቀሙበት ይገባል ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱላሚድ ሲሆን ዲኑ ያይዘውም ኮሌጁ በቀጣይ የባቡር ምህንድስና እና የICT የልህቀት ማእከል እንደመሆኑ መጠን ከድሬዳዋ አስተዳደር እንዲሁም ከፖሊስ ጠቅላይ መምሪያው ጋር በርከት ያሉ ስራዎችን በጋራ የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ በመስክ ምልከታው ወቅት ልኡክ ቡድኑን የመሩት ም/ኮምሽነር ማኦ ተሾመ እንዳሉት አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባልና በኮሌጁ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውም የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት መአከል ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት ተከናውኖ ለሚፈለገው አላማ መዋል እንዲችል እየታየ ያለው ርብርብ በጣም አስደማሚ ነው በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ያላቸው አቅም ከሌሎች ኮሌጆች አንጻር ከድሬዳዋ አልፎ ለምስራቁ የሀገራችን ክፍሎች የሚበቃ ነው ያሉ ሲሆን ይህንን አቅም በተገቢው መንገድ በጋራ እየተጠቀምን ከተማችንን በጋራ የምናለማ ይሆናል ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በአስተደዳደሩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች በስራ ቦታ ኤች አይ ቪ ኤድስት መከላከል ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ። በመድረኩ በመልዕክት ያስጀመሩት የቢሮው ሴቶች ወጣቶችና ኤች አይ ቪ ኤድስ  ፎካል ፐርሰን (ተጠሪ) ወ/ሮ ማርታ በዛብህ ቢሮዉ ሰዉ ተኮር ስራዎችን በተለያየ ዘርፍ  የሚሰራ በመሆኑ የኤች አይ ቪ ተጋላጭነት እና ስርጭት ተገቢዉን ትኩረት እንዲያገኝ በተለይም የዛሬው መድረክ በአሰሪና ሰራተኛ ዘርፉ በኢንዱስትሪዎች ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችን ግንዛቤ ያማስጨበጥ ስራው ማሳያ ነው ብለዋል። ከቢሮው በወረደዉ አቅጣጫ መሰረት ስልጠናዉ በአስተዳደሩ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሰራተኞች ኤች አይ ቪ ኤድስ አሁንም ድረስ ማህበራዊ ቀዉሱ ከፍተኛ  መሆኑን ተረድተው ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በአፅዕኖት ተገልጿል:: በዕለቱ የቀረበዉን ሰነድ እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ከታሳታፊዎች ጋር ዉይይት የተካሄደ ሲሆን በዉይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች  የቢሮው የሴቶች ወጣቶችና ኤች አይ ቪ  ፎካል ፐርሰን (ተጠሪ) ወ/ሮ ማርታ በዛብህ  እና ስልጠናዉን የሰጡት አቶ ፈቲህ መሀመድ ምላሽ ሰጥተዉበታል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የብድርና ዋስትና ፈንድ አሰጣጥና አመላለስ ዙሪያ ለድሬ ማይክሮ ፋይናንስ እና ለቀበሌ አመራሮችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ አዘጋጀ፡፡ በመድረኩም በድሬዳዋ አስተዳደር ከብድርና ዋስትና ፈንድ አሰጣጥና አመላለስ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መድፈን እንዲያስችል ከድሬዳዋ ማይክሮ ፋይናንስ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡ ከተሳታፊዎችም ከብድር ተጠቃሚዎች ምልመላ አንስቶ እስከ አመላለስ ድረስ የታዩ እና እየታዩ ያሉ ችግሮችና ተግዳሮቶችን በተለይም በብድር ተጠቃሚዎች ዘንድ ያለው ለሚያገኙት ብድር ያላቸው አመለካከት እና ተከታትሎ እንዲመለስ በማድረጉ ረገድ የሚመለከታቸው አካላት ቁርጠኝነት ላይ የሚታየው ከፍተት በሰፊው ተነስቷል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው የሚመለከታቸው አካላት በሚመለከታቸው ልክ ትኩረት በመስጠት ክፍተቶችን በመሙላትና እርምት በመውሰድ በቅንጅት የማስተካከሉን ስራ ቅድሚያ እንዲሰጡ በማሳሰብ የተጀመረውን ውጤታማ የማስመለስ ሂደት ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ተጀመረ። ከታህሳስ 22/2017 ዓ.ም እስከ 27/2017 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ ላይ የሚካሄደውን ይህን ኤግዚቢሽን እና ባዛር የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል። በመክፈቻ ስነሥርዓቱ ላይ የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደተናገሩት ቢሮው ለኢንተርፕራይዞች ከሚያመቻቻቸው የድጋፍ ማዕቀፎች ውስጥ የገበያ ትስስር አንዱ ሲሆን ኤግዚቢሽንና ባዛር ደግሞ በዚህ ረገድ ወሳኝ ሚና አለው በመሆኑም ኢንተርፕራይዞች ያመረቱትን ምርት ይዘው የሚቀርቡበት ገበያተኛውም በሚፈልገው ልክ ተገበያይቶ የሚወጣበት መድረክ መፍጠሪያ ዘዴ አንዱ ይህ በመሆኑ እንዲሁም  ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋትም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። በዚህም ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ይዘው የሚቀርቡ ሲሆን ወቅቱም የበዓል ሰሞን እንደመሆኑ የአስተዳደሩ ነዋሪ በቦታው በመገኘት ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን በማበረታታት ተጠቃሚ እንዲሆን በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ መልዕክት አስተላልፈዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በበጀት አመቱ የሩብ አመት የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ ተካሄደ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ በሚገኙ ዋና ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎች ላይ በበጀት አመቱት የሩብ አመት የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ መርሃ-ግብር አካሂዷል:: የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ መመሪያው በቼክሊስት መልክ የተዘጋጀ ሲሆን ይህን መነሻ በማድረግም በበጀት አመቱ ለዋና ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎች በተሰጡ የቁልፍ ውጤት አመላካች እስትራቴጂክ ተግባራት አንፃር የተገኘውን አፈፃፀም ለመገምገም እንዲሁም በአተገባር ወቅት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደሌሎች ክፍሎች ለማስፋት የታለመ መሆኑ ተግልፇል:: የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማውን የኮሌጁ ማኔጅመንትና የISO Task force በጋራ በመሆን እንዲሁም ቼክሊስቶችን በማዘጋጀት በስራ ሂደቶችና ክፍሎች በመገኘት የበጀት አመቱ የሩብ አመቱን ግምገማ ያካሄዱ ሲሆን በዚህም ከተሰጡ ዋና ቁልፍ እስትራቴጂክ ተግባራት በተጨማሪ የISO ትግበራን ከማስቀጠል አኳያ ስራ ሂደቶችና ክፍሎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ መመልከት ተችሏል:: በተካሄደው የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማው መሰረት በስራ ሂደቶችና ክፍሎቹ የታዩ የአፈፃፀም ውስንነቶችን እንዲሁም የተለዩ ምርጥ ተሞክሮችን በመሰብሰብ ግብረ-መልስ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ የድጋፍ ክትትልና ግምግማውን መነሻ በማድረግ እንደ ተቋም የተመዘገበው የአፈፃፀም ሪፖርት የሚቀርብም ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም