1 328
Subscribers
+224 hours
+87 days
+9730 days
Posts Archive
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+4
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የGRM ኮሚቴ 3ተኛ ሩብ አመት መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት አከናወነ፡፡
የGRM ኮሚቴ ችግሮችን ለመፍታት የሚሰራቸው ስራዎች የልህቀት ማእከሉ በአግባቡ ተገንብቶ ለሚፈለገው አላማ እንዲውል እያስቻለ ነው ያሉት የEASTRIP ፕሮጀክት ኮርድኔተር የሆኑት ወ/ሮ አሽረፊያ አብዲ ሲሆኑ አያይዘውም ኮሚቴው ስራዎችን በትጋትና በጥራት እንዲሁም በታማኝነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ያለፉትን 8 ወራት ህንጻውን እየገነባ ባለው ኮንትራክተር በኩል የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የተፈቱ ቅሬታዎችን ለኮሚቴው በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፡፡ በቀረበው ሪፖርት ላይና በቀጣይ ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የኮሚቴው አባላት በጥልቀት ተወያይተዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 20/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+6
#ዜና| ሴት አሰልጣኝ መምህራንን በማብቃት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን ሁሉን አካታች ተደርጎ ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡
ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት ለኮሌጁ ለሴት የአካዳሚክ ባለሙያዎች፣ ሴት ዎርክ ሾፕ ቴክኒሻን እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች በሥርዓተ-ፆታ ምላሽ የማስተማር ዘዴዎች ላይ(Gender-responsive teaching methods for Female Academic staff , female work shop technician and Department heads )ስልጠናዎችን ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ባለሙያ ሲሰጥ የነረውን ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቀቀ ፡፡
በሰልጠናው ማብቂያ ወቅት ተገኝተው ስልጠናውን በንግግር የዘጉት የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት ኮርድኔተር ወ/ሮ አሽረፊያ አብዲ ሲሆኑ በንግግራቸውም የሃገር ብልጽግና ያለሴቶች ተሳትፎ እንደማይረጋገጥ ሁሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናም ያለሴቶች ተሳትፎ እንዲሁም ሁሉን አካታች በሆነ መለኩ ካልተሰራበት ከግብ ሊደርስ አይችልም ብለዋል፡፡ አያይዘውም ኮሌጁ በሴቶች ተሳትፎ ላይ አካታች እቅዶችን በማዘጋጀት እየሰራ እንዳለ መስልጠናው ማጠናቀቂያ ወቅት ለተሳታፊዎች አስረድተዋል፡፡
በስልጠናው ላይም የተሳተፉ ሴት አሰልጣኝ መምህራን እንዲሁም ወርክሾፕ ባለሙያዎች እና የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች ስልጠናው በመሰጠቱ እንደተደሰቱና በቀጣይም የስልጠናውን ውጤት በሚሰሩት ስራዎች ላይ በማስገባት እንደሚተገብሩት ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በስርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን እንዲሁም የህይወት ክህሎት እና ስራ ፈጠራ በተመለከተ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለሴቶች የአስተዳደር ሰራተኞች መሰጠቱ የሚታወስ ነው፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 20/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ የከተማ ዘጠኝ ወረዳዎች ስር የሚገኙ አስራ አንድ አንድ ማዕከላት ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የመስክ ምልከታና ልየታ ተደረገ።
በዚህም የተለዩ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች በበጀት አመቱ መጨረሻ በአስተዳደር ደረጃ ዕውቅና የሚሰጣቸው ሲሆን በአስተዳደሩ ገጠር ወረዳዎች ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በተመሳሳይ ልየታ የሚደረግ ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+4
#ሁለተኛ ቀን የስልጠና ውሎ|
ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በEASTRIP ፕሮጀክት አማካኝነት በሥርዓተ-ፆታ ምላሽ የማስተማር ዘዴዎች ላይ ለሴት የአካዳሚክ ባለሙያዎች፣ ሴት ዎርክ ሾፕ ቴክኒሻን እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኞች ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
በመጀመሪያው ቀን ስልጠና በኮሌጆች የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራንና ባለሙያዎች ከጀንደር ጉዳዮች ጋር የተገናኙ ሃሳቦችና ተሞክሮዎችን ከስራና ክህሎት ቢሮ፣የሁለቱም የመንግስት ኮሌጆች በጋራ በመሆን የተመለከቱ ሲሆን ከዚህ ባለፈ የእርስበርስ ግንኙነትን ሊያጠናክሩና ወደ መጡበት ተቋም ሲመለሱ ግብ ተኮር የሆነ ውጤት የሚያስገኝ ስራ መስራት የሚያስችላቸውን ግንዛቤ እዲፈጥሩ የሚያስችል ስልጠና እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
በሁለተኛው ቀን ደግሞ ለኮሌጁ ለሴት የአካዳሚክ ባለሙያዎች፣ ሴት ዎርክ ሾፕ ቴክኒሻን እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች በሥርዓተ-ፆታ ምላሽ የማስተማር ዘዴዎች ላይ(Gender-responsive teaching methods for Female Academic staff , female work shop technician and Department heads )ስልጠናዎችን ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ባለሙያ ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ በኮሌጁ የሚገኙ ሴት አሰልጣኝ መመህርራኖች፣ሴት ዎርክ ሾፕ ቴክኒሻን ባለሙያዎችእንዲሁም የዲፓርትመንት ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+3
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከGrand group Entrepreneurship, Training and promotion PLC ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በስምምነቱ ላይ በመገኘት የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዋነኝንት ትምህርትና ስልጠናዎችን ከመስጠት በዘለለ የሚያሰለጥኑዋቸውን ሰልጣኞች እውቀት ክህሎት ካገኙ በኃላ ከስራ ጋር ማስተሳሰር ይጠበቅባቸዋል፡፡
ስለሆነም በዛሬው እለት ከGrand group ጋር የተፈራረምነው ይህ የመግባቢያ ስምምነት ሰልጣኞቻችን ከሰለጠኑ በኃላ ከስራ ማስተሳሰር እንዲሁም በአጫጭር ስልጠናዎች የተቀጣሪዎችን ብቃት ከማሳደግና ለቀጣሪዎች ብቁ የሰዉ ሃይል ከማቅረብ አንፃር ስራዎችን በጋራ መስራት እንድንችል ያደርገናል ብለዋል፡፡
አያይዘውም ለሰልጣኞች ከምንፈጥረው የስራ ትስስር ውጪ ለአሰልጣኞችና ሰልጣኞች የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት ሁለቱንም አካላት የሚያሳድጉ ቢዝነስ ተኮር ፕሮጀክቶች በጋራና በትብብር ከማስፋት አንፃር በጋራ በመሆን እንድንሰራ የሚያስችለን ስምምነት ነው ብለዋ፡፡
በመቀጠልም ድርጅቱን በመወከል የጋራ ስምምነቱን የፈረሙት የGrand group ኃላፊ አቶ ኤልያስ አብዲ እንዳሉት በዛሬው እለት የምንፈራረመው ይህ የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በኮሌጁ ውስጥ ብቻ ሳይሆን የአካባቢው ህብረተሰብ የበለጠ የሚጠቅሙ የስልጠና ዘርፎችን በመለየትና ወደ ተግባር በማስገባት እንዲሁም ተጨማሪ ፋይናንስ፣ ቴክኖሎጂ እና የእዉቀት ሽግግር ከመፍጠር አንፃር ትልቅ ፋይዳ ያለው ስምምነት ከኮሌጁ ጋር በማድረጋችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል ብለዋ፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ውስጥ አላሰራ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆችና ከጎል ኮሌጆች ለተወጣጡ በተግባራዊ ጥናትና ምርምር (action research) ስራ ላይ ከሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ጋር እስካሁን የደረሱበትን የመገምገም ስራ ተከናወነ።
በዚህም ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በመጡ አማካሪ ለአጥኚዎች ምክር እና ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በዋናነት የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት የሚጠቅሙ ጥናትና ምርምሮችን ማድረግን አላማው ቢያደርግም እንደ አስተዳደር በሚቀጥለው ወር መጀመሪያ ተከትሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር አስተዳደሩን የሚወክሉ የሚለዩበትም ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 18/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለሴት አሰልጣኝ መምህራንና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ከድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ Eastrip ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለቢሮው ሴት ሰራተኞች፣ ለትምህርት ክፍል ተጠሪዎች፣ ለሴት የኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራንና ባለሙያዎች አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኝ መስጠት ተቸሏል፡፡
በዚህም ስልጠናው በኮሌጆች የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራንና ባለሙያዎች ከጀንደር ጉዳዮች ጋር የተገናኙ ሃሳቦችና ተሞክሮዎችን የተመለከቱ ሲሆን ከዚህ ባለፈ የእርስበርስ ግንኙነትን ሊያጠናክሩና ወደ መጡበት ተቋም ሲመለሱ ግብ ተኮር የሆነ ውጤት የሚያስገኝ ስራ መስራት የሚያስችላቸውን ግንዛቤ እዲፈጥሩ የሚያስችል መሆኑን የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 18/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የግብርና ውብ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት በአነስተኛና ጥቃቅን የአደረጃጀት መመሪያ ዙሪያ ለአንድ ማዕከል ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ያዘጋጀው ስልጠና ተካሄደ
ወጣቶችን ፣ ሴቶችን ብሎም ሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎችን በማህበር በማደራጀት አዋጭ በሆኑ የስራ መስኮች ተሰማርተው የገቢ ምንጫውንም በማስፋት ኑሯቸውን የሚያሻሽሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ያቀደ ስልጠና እንደሆነ ተነግሯል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የአስተዳደሩ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሲሆኑ በአስተዳደራችን የተገኙ የፕሮጀክት ዕድሎች ስኬታማ እንዲሆኑ ማህበረሰባችን ደግሞ ኑሮውን እንዲያሻሽል ሁሉም ሰው ትልቅ ሃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡ከቢሮው እና ስራና ክህሎት ቢሮ ሙያዊ እና በሌሎች መስኮች በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡የስራ ባህል መቀየር ላይም ከፕሮጀክቱ ጋር በመሆን ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል ለውጤታማቱ ልንረባረብ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት ሴት ፣ ወጣቶችንም እንዲሁም አካል ጉዳተኛ የማህበረሰብ ክፍሎችን አጠቃሎ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ከአመራር እስከ ባለሙያ በትብብር ይሰራል ብሏል ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ፡፡
በስልጠናው የስራ ክህሎት ቢሮ ባለሞያዎች፣የወረዳ የአንድ ማዕከል ባለሙያ እና ሃላፊዎች ፣ ፕሮጀክት የወረዳ አስተባባሪዎች ፣ከአስተዳደሩ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ናቸው፡፡
©️ Dire Dawa Agriculture Bureau
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በ3ኛ ዙር የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ላይ ለሚሳተፉ አሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተጀመረ::
የአሰልጣኞች ስልጠናው በዘንድሮ አመት በአስተዳደሩ ለሚሰጠው የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ 3ኛ ዙር ፕሮግራም ላይ ለወጣቶች ስልጠና ለሚሰጡ አሰልጣኝ መምህራን በዛሬው እለት መሰጠት ተጀምሯል::
የ3ኛ ዙር ፕሮግራሙ በስራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት በቅርቡ በኮሌጁ ለሚጀምረው የወጣቶች ስልጠና በኮሌጁ ToT ላላቸው አሰልጣኝ መምህራን በተከለሰው የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲሁም የስራ አፈላለግ ስልጠና ላይ የሪፍሬሽመንት ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን ይህም የ3ኛው ዙር ስልጠና ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት አንዱ አካል እንደሆነም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የካቲት 17/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+3
በ3ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ስልጠና ላይ ለሚሳተፉ አሰልጣኝ መምህራኖች የማነቃቂያ ስልጠና በዛሬው እለት መሰጠት ተጀመረ::
ይህ የ3ኛ ዙር ፕሮግራም በስራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት በቅርቡ በኮሌጁ ለሚጀምረው የወጣቶች ስልጠና በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኩል የአስልጣኞች ስልጠናውን ከዚህ ቀደም ለወሰዱ አሰልጣኝ መምህራን በተከለሰው የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲሁም የስራ አፈላለግ ስልጠና ላይ የማነቃቂያ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ይህም የ3ኛው ዙር ስልጠና ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት አንዱ አካል እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል::
በአምስት አመት ውስጥ 70 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመው እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በአለም ባንክ ድጋፍ እየተገበረው የሚገኘው ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ እድሜያቸው ከ18 እስከ 25 አመት የሆኑ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ወጣቶቹ በዋነኝነት ምንም አይነት የስራ እድል ያላገኙ በትምህርት ብዙም ያልገፉ ወይም ያቋረጡ ከዚህ በፊት ምንም ስራ ሰርተው የማያውቁ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከዚህ በፊት 1ኛ ና 2ኛ ዙር ስልጠናዎችን በስኬት መጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም በድሬዳዋ አስተዳደር በ3 ዙር ውስጥ በአጠቃላይ 2916 ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ መርሃ ግብር እንደሆነ ይታወቃል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 17/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የግማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ ስድስት ወራት የተከለሰ ዕቅድ ላይ ከቢሮው ከሰራተኞችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
በዚህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ስድስት ወራት በዕቅድ ተይዘው ተግባራዊ ሲደረጉ የነበሩ ዓበይት ስራዎችን እንዲሁም በዕቅድ አፈፃፀሙ ላይ የተስተዋሉ አጠቃላይ አውንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎችን በመተንተን የቀጣይ ስድስት ወራት አፈጻጸም በልህቀት ለመፈጸም የሚያስችል መግባባትን የሚፈጥር መድረክ እንደሆነ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች ከብዙ በጥቂቱ፤
የ6 አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤቶችን የመገንባት ስራ ተከናውኗል፣
የአዲስ ሰልጣኞች ቅበላ ወንድ 1955 ሴት 2862 በድምሩ 4817 የአዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ ተከናውኗል፡፡ በእቅድ ከተያዘው 5956 የቅበላ መጠን አንፃር የ80.8 በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡
የነባር ሰልጣኞች ቅበላ ወንድ 2029 ሴት 3053 በድምሩ 5082 የነባር ሰልጣኞች ቅበላ ተከናውኗል፡፡ ይህም በእቅድ ከተያዘው 5380 የቅበላ መጠን አንፃር የ94.4 በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡
2384 የመደበኛ ስልጠና አጠናቃቂዎችን ለመመዘን ታቅዶ 2024 (ወንድ 910፣ ሴት 1114) መመዘን የታቻለ ሲሆን ይህም ከእቅድ አንፃር የ84.9 ፐርሰንት አፈጻፀም አለው፡፡
1000 የአጫጭር ስልጠና አጠናቃቂዎች ለመመዘን ታቅዶ 859 (ወንድ 86፣ ሴት 773) መመዘን የተቻለ ሲሆን ይህም ከዕቅድ አንፃር 85.9 በመቶ አፈፃፀም ተመዝግቦበታል፡፡
በ6 ወራት ውስጥ በሦስቱም ዘርፎች 10,474 ቋሚ ያስራ እድል ለዜጎች ለመፍጠር ታቅዶ ወንድ 4873 ሴት 3981 በድምሩ 8854 የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ይህም ከእቅድ አንፃር የ84.5 በመቶ አፈፃፀም አለው፡፡
ከአንቀሳቃሾች ጋር በተያያዘ 1500 የሚሆኑ የተለያዩ አንቀሳቃሾችን የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 655 ወንድ እና 1067 ሴት በአጠቃላይ 1718 አንቀሳቃሾን የብድር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ይሄም ከ100% በላይ አፈፃፀም የተመዘገበበት ሆኗል፡፡
የስራ ተቆጣጣሪዎችን አሰልጥኖና አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ስራን በ384 ኢንድስትሪዎች ላይ ማከናወን ተችሏል፡፡ በጥናቱም ውጤት መነሻነት 31 የሙያ ደህንነት ባለሞያዎችን አሰልጥነን አስመርቀናል፡፡ ስምሪትም እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ከመንግስትና የግል ማሰልጠኛ ተቋማት፣ ከብቃት ምዘና ማዕከልና ከግል አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር በመቀናጀት ለውጪ አገር ስራ ስምሪት 360 ሴት የግል ሰራተኞች እንዲሰለጥኑ ተደርጓል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 185 የግል ሰራተኞች ወደ አረብ አገር የመላክ ስራ ተከናውኗል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 16/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+4
#ዜና|በፋብሪካዎች ውስጥ የሚሰሩ የተለያዩ ሞያተኞችን በክህሎትና በአመለካከት ብቁ እንዲሆኑ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የተውጣጡ ባለሙያዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናው ለ11 የናሽናል ሲምንቶ መካኒካል ክፍል ባለሙያዎችና 5 የኤሌክትሪካል ክፍል ባለሙያዎች በብየዳ ሙያ በMMAW (manual metal arc welding) Advance welding training module one እንዲሁም በ pneumatic, Electro Pneumatic, Hydraulic & Electro Hydraulic & Advance PLC ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በከፍተኛ ባለሞያዎች በሆኑ አሰልጣኞች እየተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ስልጠናውን አጠናቀው ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ በሰለጠኑት ሙያ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስችላቸው ሰልጣኞቹ በስልጠናው ወቅት ገልጸዋል፡፡
ይህን ስልጠና የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን ኮሌጁ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር ባለው ትስስር ለተለያዩ ፋብሪካ ባለያዎችን ቀጣይነት ባለው መልኩ አቅማቸውን የማጎልበት ስራዎች የሚሰራ ይሆናል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት14/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
