1 318
Subscribers
No data24 hours
+207 days
+14930 days
Posts Archive
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በዚህ ክረምት እረፍትዎን ወደ ገቢ ምንጭነት ይቀይሩ!
የዘመኑን ተፈላጊ ክህሎቶች በመማር እራስዎን ለስራ ገበያ ብቁ ማድረግ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ መልካም ዜና! የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከ A2B Creatives ጋር በመተባበር ለሁለት ወራት የሚቆይ አጠቃላይ የቪዲዮ ኤዲቲንግ እና ግራፊክስ ዲዛይን ስልጠና አዘጋጅቶላችኋል።
👉 የግራፊክስ ዲዛይን (Graphics Design): ማራኪ የሆኑ የብራንዲንግ ስራዎችን፣ ፍላየሮችን እና የማህበራዊ ሚዲያ ፖስተሮችን ፣ ሎጎዎችን መስራት (Adobe Photoshop,Canva ...)።
👉 የቪዲዮ ኤዲቲንግ (Video Editing): ለዩቲዩብ፣ ለቲክቶክ፣ ለፊልሞች እና ለድርጅቶች ማስታወቂያ የሚሆኑ ፕሮፌሽናል ቪዲዮዎችን ማቀናበር (Adobe Premiere Pro ...)።
ለመማር ምቹ እና ዘመናዊ የሆኑ መሰረተ-ልማቶች የተሟሉለት፦
🖥 Professional Computer Lab: ዘመናዊ የኮምፒውተር ላብራቶሪ።
🌐 Internet Access: ማቴሪያሎችን በነፃነት ለማውረድ የሚያስችል ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት።
👨🏫 Experienced Instructor: በዘርፉ ሰፊ የገበያ እና የማስተማር ልምድ ባላቸው ባለሙያ አስተማሪዎች
https://docs.google.com/forms/d/18NF9YM3GTqrA6aMYC9koNvyKaI8CvBLzr40JbBGUd6o/viewform
የምዝገባ ቦታ:- በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የICT ዲፓርትመንት በአካል ተገኝተው መመዝገብ ይችላሉ::
📞 ለበለጠ መረጃ እና ለምዝገባ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ያግኙን፦
📱 0976315798
📱 0968377071Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮችና አባላትን ያካተተ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት አደረገ፡፡
#EIPC ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮችና አባላትን የያዘው ልዑካን ቡድን የኮሌጁን አጠቃላይ የስራ እቅስቃሴ መቃኘት ሚያስችለውን የመስክና ስራ ጉብኝት በዛሬው እለት በኮሌጁ ማካሄድ ችሏል::
ልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ያስተናገዱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው.. ሰልጥነው የበቁና በሙያቸው ሀገር የሚያሻግሩ አምራች ዜጎች መፍለቂያ ወደሆነው ኮሌጃችን እንኳን በደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ተቋማችን ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት አስተዳደሩ ላይ ለውጥ የሚያመጡ ተግባራትን የማከናወን ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በምጠይቁን ጉዳዮች በሙሉ ከተቋማችሁ ጋር በቅንጅት ለመስራት በኮሌጁ በኩል ሙሉ ዝግጁነት ያለ መሆኑንም ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከምስረታው ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ ያለውን አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴ በኮሌጁ ዲን አማካኝነት ለቡድኑ ገለፃ የተደረ ሲሆን በዚህም የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት አውቅና ከማግኘት ባሻገር በትምህርትና ስልጠናው፣ በቴክኖሎጂ ልማትን ጨምሮ በዲጂታላይዜሽን አተገባበር የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችና የተመዘገቡ ውጤቶችን በዝርዝር ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ቀደም ሲል በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት የተሰሩ የተወሰኑ ስራዎች መኖራቸውን ያስታወሱት በኮሌጁ የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ስራ ሂደት ሀላፊና የኮሌጁ ም/ል ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ በቀጣይም የሁለቱን ተቋማት ግንኙነቶችን በማጠናከርና የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን በማድረግ በአጫጭር ስልጠናዎች፣ በቴክኒካል ጉዳዮች እንዲሁም በቴክኖሎጂ ልማቶች ላይ በጋራ እንሰራለንም ብለዋል::
በተጨማሪም የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መመሪያ አባላትን የያዘው ልዑክ በኮሌጁ የሚገኙ የስልጠና ወርክሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው ጉብኝትም አጠቃላይ በኮሌጁ የስራ እንቅስቃሴ መደነቃቸውን ገልፀው በቀጣይ ስልጠናዎችን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከኮሌጁ ጋር ለመስራት ፅኑ ፍላጎት ያሳደረባቸው ጉብኝት እንደነበርም ገልፀዋል::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
ለጣሊያን ሀገር የሥራ ዕድል የምዝገባ ጥሪ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በጣሊያን ሀገር በሆቴልና መስተንግዶ (Hospitality) ዘርፍ የሰው ኃይል ይፈለጋል።
የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ጣሊያን ሄደው መስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን።
🏨 የሥራ መደቦች፦
🔹ጸሐፊ(Commis de Rang / F&B Server) – 19 ቦታዎች
🔹 የፅዳት ሰራተኛ (Room Attendant / Housekeeping) – 20 ቦታዎች
🔹 ረዳት ሼፍ (Commis Chef) – 13 ቦታዎች
🔹 የእቃ አጣቢ (Kitchen Steward / Dishwasher) – 11 ቦታዎች
🔹 የወለል ረዳት (Floor Porter / Houseperson) – 3 ቦታዎች
🔹 የቢሮ አስተናጋጅ (Front Office Agent / Receptionist) – 4 ቦታዎች
🔹 የጥገና ቴክኒሺያን (Maintenance Technician) – 1 ቦታ
🔹 የስፓ ቴራፒስት / የማሳጅ ባለሙያ (Spa Therapist / Masseuse) – 1 ቦታ
📌 የማመልከቻ መስፈርቶች
✅ ከስራው ጋር ተያያዥ የስራ ልምድ ያላቸው ተመራጭ ናቸው።
✅ ለአብዛኛዎቹ የስራ መደቦች የእንግሊዝኛ እና/ወይም የጣሊያንኛ ቋንቋ እውቀት ያስፈልጋል።
✅ ለአንዳንድ የሙያ መደቦች ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫ ወይም የሆቴል እና መስተንግዶ ትምህርት ተመራጭ ነው።
📅 የሥራ ቆይታ
አብዛኛዎቹ የስራ መደቦች ለ2026/2027 የክረምት የቱሪዝም ወቅት የሚቀጠሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የስራ መደቦች ዓመቱን ሙሉ ወይም በበጋና በክረምት ወቅት የሚሰሩ ናቸው።
✅ ለመመዝገብ
1.Labor ID ካሎት በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ያመልክቱ።
2.Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦
1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ።
በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ።
1. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ https://forms.lmis.gov.et/italy-hotel/ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ።
ማሳሰቢያ
• ምዝገባም ሆነ ስምሪቲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ብቻ የሚከናወን ሲሆን ሚኒስቴሩ ለየትኛውም አካል ውክልናም ሆነ ፈቃድ አለመስጠቱን እንገልፃለን።
• ምንም አይነት ክፍያም የለውም
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ለኮሌጁ ሰራተኞች በISO 9001:2015 QMS ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ::
#EIPC ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት ትግበራን በተመለተ ለኮሌጁ አዲስ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል::
በኮሌጁ የጥራት ደረጃን አስጠብቆ የአገልግሎት እርካታን በዘላቂነት የማረጋገጥ ሚናው የሁሉም ሰራተኛ እንደሆነ የገለፁት በኮሌጁ የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ሀላፊና የኮሌጁ ም/ል ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ በተቋሙ ከአመራር ጀምሮ በየደረጃው የሚገኝ ሁሉም ሰራተኛ በISO 9001:2015 QMS ትግበራ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል ታልሞ ስልጠናው መዘጋጀቱንም ገልፀዋል::
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የኮሌጁን የISO 9001:2015 QMS አተገባበር ሂደትና የሰራተኛው ሚናን አስመልክቶ በኮሌጁ የISO Task Force ባለሙያዎች አማካኝነት ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ መስጠትም ተችሏል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አለም አቅፍ ተወዳዳርነቱን ለማረጋገጥ በቁጠኝነት ባከናወናቸው ተግባራት የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት እውቅና የተሰጠው በምስራቅ ኢትዮጵያ ብቸኛው የመንግስት ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን ትምህርትና ስልጠናውን ጨምሮ አጠቃላይ የደንበኞች አገልግሎቱን በጥራት እየሰጠ የሚገኝ ተቋምም ነው::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
ክረምትን በክህሎት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በሚል መሪ ቃል ኮሌጁ በክረምቱ መርሃ ግብር በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናዎችን በዘንድሮ አመት እንደሚሰጥ ገለጸ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 በቀንና በማታ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ የአካባቢው ማህበረሰብ በሙያ የበቁ ዜጎች እንዲሆኑ በተለያዩ የሙያ መስኮች ገበያ ተኮር አጫጭር ሰልጠናዎችን በማዘጋጀት ወጣቶች የሙያ ባለቤት ብቻ ሳይሆኑ በሰለጠኑት ሙያም የኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንዳለና በዚህም የተሸለ ስኬት እንዳስመዘገበ የሚታወቅ ነው፡፡
ኮሌጁ ከዚህ ቀደም የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ባዘጋጀው የክረምት የወጣቶች ስልጠና እንዲሁም ኮሌጁ በራስ ተነሳሽነት ባዘጋጃቸው የክረምት ስልጠና ወጣቶችን ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆኑና የኢኮኖሚውም ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡
የዘንድሮውን የክረምት በክህሎት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መርሃ ግብርን በተመለከተ የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ የዝግጅት ስራው ምን እንደሚመስል የገለጹ ሲሆን በገለጻቸውም ኮሌጁ እንደከዚህ በፊቱ የዘንድሮውንም የክረምት የስልጠና መርሃ ግብር በተሳካ መልኩ ለመስጠት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል ያሉ ሲሆን አያይዘውም ሰልጣኞችን የመመዝገብና ለስልጠናው ዝግጁ እንዲሆኑ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የመንደር ኮሚቴዎችን በመጠቀም የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን እየተሰሩ እንዳለና የምዝገባ ስራውም ተጠናክሮ እየተሰራ እንዳለ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም የኮሌጁ ዲን እንደገለጹት ኮሌጁ በተቋሙ ውስጥ ከሚሰጠው ስልጠና በዘለለ ወጣቶች ባሉበት ቦታ ስልጠናዎች እንዲያገኙ የMobile TVET ማሰልጠኛዎችን ከተለያዩ ወረዳዎች ጋር በማዘጋጀት ስልጠናዎችን መስጠት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡እንደ ማሳያም በወረዳ 08፣በወረዳ 09 እና በወራዳ 06 ለሚገኙ ወጣቶች ባሉበት ቦታ በተለያዩ ሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት ተችሏል ብለዋል፡፡
ኮሌጁ በተለያዩ የሙያ መስኮች በክረምቱ መርሃ ግብር በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ፣በአውቶ ሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ፣በኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ፣በውድዎርክ ቴክኖሎጂ እና በሌዘርና ፋሽን ዲዛይን
ሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዳዘጋጀ የኮሌጁ ዲን አያይዘው ገልጸዋል፡፡በተያያዘም የMobile TVET ስልጠናዎች የሚፈልጉ ወጣቶች በአካባቢያቸው በሚገኝ ወረዳ ጽ/ቤት በመመዝገብ ስልጠናዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሰኔ 24/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+5
የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማእከል የሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነመረብ ለማስፈተን ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለጸ።
የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገርአቀፍ ፈተና በድሬዳዋ ከተማ በበይነመረብ የሚሰጥ ሲሆን በከተማዋ በበይነመረብ (online) ፈተና ለመስጠት ከተመረጡ ሁለት ተቋማት መካከል ኮሌጁ አንዱ ነው።
የኮሌጁ ዲን የሆኑት አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ በቅድመ ዝግጅቱ ስራ ላይ እንዳስታወቁት በአስተዳደሩ 12ተኛ ክፍልን አጠናቀው በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ በርካታ ተማሪዎች በኮሌጁ በመገኘት በኮምፒውተር የታገዘ online exam ይፈተናሉ ያሉ ሲሆን፡፡እነዚህ ተፈታኞች ምንም አይነት ችግር እናዳይገጥማቸው ፈተናው ከመድረሱ በፊት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡የኮሌጁ ዲን አያይዘውም ከዚህ በፊት ባሳለፍናቸው 2 የፈተና ጊዜያት ያገኘናቸውን ልምዶች በመጠቀም በዘንድሮ አመትም በፈጣሪ ድጋፍ ያለምንም ችግር ፈተናውን የምናጠናቅቅ ይሆናል ብለዋል፡፡ለተፈታኞችም መልካም ፈተና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
በዘንድሮዉ 2018 ዓ.ም በአስተዳደሩ 12ተኛ ክፍልን አጠናቀው በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ ከ1031 በላይ ተማሪዎች በኮሌጁ በመገኘት በኮምፒውተር የታገዘ online exam እንደሚፈተኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሰኔ 24/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
በድሬዳዋ የ“ብሩህ” የንግድ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች እውቅናና ሽልማት ተበረከተላቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለ7ኛ ጊዜ ባዘጋጀው “ብሩህ” የንግድ ፈጠራ ውድድር ላይ አሸናፊ ለሆኑ ወጣቶች የእውቅና ሰርተፍኬትና የገንዘብ ሽልማት አበረከተ።
በዕለቱም ወጣቶች ከሥራ ጠባቂነት ስሜት ወጥተው፣ ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንዳለባቸው ጥሪ ቀርቧል።
አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችና የሽልማት መርሃ-ግብሩ በ2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ከተረፈ ምርት የሚወጣ ነዳጅ እና የተለያዩ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ጨምሮ በርካታ አዳዲስና ዘመናዊ የፈጠራ ሥራዎች ቀርበዋል።
በውድድሩ በተለያዩ ዘርፎች 12 ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። ከቀረቡት ውስጥ 5ቱ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አሸናፊዎቹ በፌደራል ደረጃ በሚካሄደው አገር አቀፍ ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድል እንደሚመቻችላቸው ተገልጿል።
“የድሬ ዲጂታል” በሚል አነስተኛ ነጋዴዎችን ከከፍተኛ ነጋዴዎች ጋር የሚያስተሳስር መተግበሪያ አቅርቦ የሁለተኛ ደረጃን ያገኘው ኢንስፔክተር ብሩክ ተስፋዬ በሰጠው አስተያየት፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ ይህንን የፈጠራ መድረክ ማዘጋጀቱ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጿል።
"ውድድሩ እጅግ ፈታኝና ከባድ ነበር፤ ወደፊትም ለማኅበረሰቡ የሚጠቅሙ ተጨማሪ አዳዲስ ነገሮችን ለመፍጠር ጥረት አደርጋለሁ። ወጣቱም ይህንን የፈጠራ ተነሳሽነት ማስቀጠል አለበት።" ብሏል
የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው፤ ሥራ ፈጣሪዎች የፈጠራ ሐሳባቸውን በማንጸባረቅ ብቻ ሳይወሰኑ በተግባር በመንቀሳቀስ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም ጭምር የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ቢሮው ለአሸናፊዎቹ ዘላቂ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል በመጠቆም፣ አሁን ያለው ወጣት ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ መሸጋገር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተመሳሳይ፣ የሥራና ክህሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰዒድ አሊ ባለፉት ጊዜያት በአስተዳደሩ በርካታ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ አቅም ያላቸው ወጣቶችን መመልከት መቻሉን ገልጸዋል።
ውድድሩና የተሰጠው ሥልጠና ወጣቶች ከሥራ ጠባቂነት ስሜት ወጥተው ራሳቸውንና አገራቸውን እንዲደግፉ ትልቅ ትምህርት የሰጠ መሆኑንም ጠቁመዋል።
©️ DireTvአማርኛ | ሰኔ 24 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ለኮሌጁ ሰልጣኝ ተማሪዎች በISO 9001:2015 QMS ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ::
#EIPC ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት ከትምህርትና ስልጠናው አኳያ የሚጨምረው ጥራት በተመለተ ለኮሌጁ ሰልጣኝ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል::
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የኮሌጁን የISO 9001:2015 QMS ትግበራ በማስቀጠሉ ሂደት ላይ የሰልጣኞች ሚናን አስመልክቶ በኮሌጁ የISO Task Force ባለሙያዎች ስልጠናውን ለሰልጣኞች በተሳካ ሁኔታ መስጠት ተችሏል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አለም አቅፍ ተወዳዳሪነቱን ለማረጋገጥ በቁጠኝነት ባከናወናቸው ተግባራት የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት እውቅና የተሰጠው በምስራቅ ኢትዮጵያ ብቸኛው የመንግስት ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን ትምህርትና ስልጠናውን ጨምሮ አጠቃላይ የደንበኞች አገልግሎቱን በጥራት እየሰጠ የሚገኝ ተቋምም ነው::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ለአዳዲስ መዛኞች ስልጠና አዘጋጀ፤
በዚህም ማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲያስችለው ቀጣይነት ያለውና የማይቋረጥ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዋናነት ከተለያዩ ኢንደስትሪዎች የተወጣጡ መዛኞችን በማፍራት ምዘና እና መዛኝነትን በሚገባ ተረድተው ተመዛኙን በፍጹም ስነምግባር እንዲመዝኑ የሚያስችላቸው እንደሚሆን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ አሚን አብዱላሂ ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም ምዘና ያለ ብቁ መዛኝ የማይታሰብ መሆኑንና ከዚህም በላይ በብዛትም ሆነ በጥራት እንዲፈሩ የማድረጉ ስራ ከተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ የሚገኝ መሆኑንና ከምዘና ጋር ተያይዞ ከተገልጋይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከሚመልሱ ተግባራት አንዱና ዋንኛው አዳዲስ መዛኞችን ማፍራትና ማብቃት እንደመሆኑ ቀጣይነት እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
