cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የልደታ ሙስሊም ሴቶች ጀመአ

قال رسول الله (صلي الله عليه وسلم) ،"الدين النصيحة" ، قلنا :لمن؟، قال،"لله ولكتابه ولرسوله ولأءمة المسلمين وعامتهم" رواه مسلم

Show more
Advertising posts
238
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+330 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
340Loading...
02
ኢትዮጵያ ኒቃብ መልበስን ልትከለክል ነው‼ ============================= (የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ 15+ ስጋቶች!) || ✍ የኢትዮጵያ መንግስት ኒቃበ ለብሶ መማርንና መሥራትን የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለማፅደቅ በሂደት ላይ ነው። እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ ኒቃብን በግልፅ የሚከለክል ህግ ባይኖርም፤ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ጠል ኃይሎች ባልተጻፈ ህግ ኒቃብ መልበስን ሲከለክሉ ነበር። ለናሙና ያክል በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኒቃብ ሳቢያ 2000 ገደማ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የታገዱበት ሁኔታ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ለነዚህና መሰል ኒቃብን በግል ጥላቻቸው ተነሳስተው ለሚከለክሉ አካላት ሽፋን የሚሰጥ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለመፅደቅ በሂደት ላይ ነው። ከኒቃብ ጉዳይ ባሻገር በመሰል ተቋማትና አንዳንድ የህዝብ መገልገያ አካባቢዎች በጀማዓህ ሶላት መስገድን የሚከለክል ክፍልም አለው። ረቂቅ አዋጁ ከመዘጋጀቱ በፊት ለግብዓትነት የሚሆን ጥናት ቀድሞ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉ 10 አባላት መካከል ሙስሊሙን የወከለው አንድ ግለሰብ ብቻ ነበር። ግና ከጥናት ዝግጅቱ ጀምሮ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በአግባቡ ያልወከለው ሂደት፤ ጭራሽ ረቂቅ አዋጁ ላይ ግልፅ የሙስሊሙ መብት ጥሰቶች ተካተዋል። በዚህ በባለ 15 ገፅ በንድፍ ላይ ያለ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በቀጥታ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር ከሚጋጩ ነጥቦች መካከል፤ የሚከተሉት አንቀፆችና ንዑስ አንቀፆች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የሚያጋጩና ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው። 1) 13.8 "የተከለከሉ ቦታዎች ቅስቀሳ ማድረግ" ማለት የትኞቹ በታዎች ናቸው? 2) 13.9 other (ሌሎች) ማለት ምን ማለት ነው? 3) 15.1 መስጂድ ሲጠበን ከመስጅድ ውጪ መስገድ አንችልም ማለት ነው? መስጅድ በሌለበት መስገድ አይቻልም? ይህን መሠረት አድርገው ሰበብ ፈላጊዎች ከመስጅድ ውጭ መስገድን እንዲከለክሉ መንገድ ስለሚከፍት ይህን እንደማይመለከት በግልፅ ሌላ ንዑስ አንቀፅ ላይ መስፈር አለበት። 4) 15.4 ሁሉም ቦታ በሚባል ደረጃ ሶላትን ይከለክላል፡፡ 5) 17.4 "በቡድን አምልኮ" በሚል ሽፋን የጀመዓህ ሶላትን ለመከልከል ይውላል። 6) 17.7 ቅጣቶች ለመንግስት መ/ቤቶች ክፍት ሆነዋልና ሌላ ችግር እንዲፈጠር በር ይከፍታል፡፡ ምክንየተቱም የትኛውም መሥሪያ ቤት ተነስቶ የራሱን ቅጣት በጥላቻ ቢያስተላልፍ መብት አለው ማለትን ያሲዛል። 7) 19.1 "ከኃይማኖት ተፅዕኖ ነፃ መሆን" ማለት ምን ማለት ነው? እስከምን ደረጃ? 8) 19.2: የአንዳንድ ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን አሠራር ለማፈን በር የሚከፍት ነገር አለው። 9) 19.5 በትምህርት ቤቶች የጀመዓህ ሶላት ተከልክሏል፡፡ 10) 19.6: "ማንነትን ለመለየት" በሚል ሽፋን  ኒቃብን ይከለክላል። በዚህ ቴክኖሎጂው ባደገበት ዘመን እንደ አሻራ ያሉ ቀላል ወጪ የሚጠይቁ ዘዴዎች እያሉ፣ በተለመደው አሠራርም በሴት የጥበቃ ሠራተኛ ማንነታቸውን መለየት እየተቻለ፣ በቢዝነስ ተቋማት ዘንድ ይህ ጥያቄ ሳይነሳ መኗኗር ሲቻል እያዬን… በዚህ ሽፋን ኒቃብን መከልከል ነውር ነው። 11) 22.2 በተለይም በሸሪዓው ውርስንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ለአንዳንድ ሙጅሪሞች በር ይከፍታል። 12) 24.1 የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ በተለይም በሙስሊሙ ዘንድ ሶደቃ የተለመደ ነውና! 13) 25.1: ይህም የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ 14) 25.3 ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ መጅሊስ በአዋጅ የተቋቋመ ራሱን የቻለ ተቋም ከሆነ በዚህ ደረጃ በሌላ የበላይ አካል control መደረግ የለበትም። 15) 25.4: ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ "በአዋጅ መቋቋም" የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም አሳጥቶ እንደተለመደው ወደ ተራ NGO ከማውረድ አይተናነስም። 16) 26: "ከኃይማኖት ተፅዕኖ የተላቀቀ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚወስኑት የየትምርት ቤቱ ኃላፊዎች ቢሆኑ የተሻለ ይሆናል፡፡ አለበለዚያ የኢስላማዊ ት/ቤቶችን ነፃነት ያፍናል። …  ባለ 15 ገፁ ይህ ረቂቅ አዋጅ በሶፍቲ ኮፒ በዚህ ሊንክ ስለሚገኝ፤ አንብቡትና እናንተም የታዘባችኋቸውን ስጋቶችና ህፀፆች አስፍሯቸው። https://t.me/MuradTadesse/35726 ♠ ይህ አፈና ሳይጻፍ የተበደልነው አንሶን ጭራሽ ተልፎ ሊተገበርብን ጫፍ ሲደርስ በዝምታ ማሳለፍ የለብንምና ሁሉም ሰላም ወዳድና ለእምነቱ ተቆርቋሪ ከወዲሁ ጉዳዩ ሳይጸድቅ ይስተካከል ዘንድ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ግደታችን ነው። መልዕክቱን ለሌሎችም በማሰራጨት ህዝበ ሙስሊሙ እየመጣ ስላለው አዲስ አዋጅ ከወዲሁ በቂ መረጃና ግንዛቤ ኖሮት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ እናድርግ። || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesse
470Loading...
03
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
350Loading...
04
የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ጥናት‼ =================== የመንግስት እና ሃይማኖት ግንኙነት በኢትዮጵያ፤ ትናንት ዛሬ እና ነገ አዘጋጅ፦ የፌዴራል የፍትሕና የህግ ኢንስቲትዩት የሶፍት ኮፒ (PDF) መገኛ ሊንክ፦ https://t.me/MuradTadesse/35708 ♠ እያንዳንዷን መስመር ምን ታሲዛለች፣ ምን ትርጉም አላት፣ ምን ተፈልጎባት ነው ብላችሁ በጥንቃቄና በጥሞና አንብቡት። በተለይም ከኡማው ጥቅምና ጉዳት አንፃር! || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesse ummalife.com/MuradTadesse tiktok.com/@MuradTadesse
360Loading...
05
#እኛስ 3 http://t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
480Loading...
06
~ዛሬ በኢማን ጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘትህ ፣ነገ በዚሁ ላይ መጽናትህን አያመለክትም፣ አላህ እንጂ ራስህ ለራስህ ዋስትና መሆን አትችልም። ስለዚህ የደከሙትን አትናቅ።  ባልገራላቸው አትሳቅ። የሰው ልጅ  ቀልብ ሁሉ በአላህ እጅ ናት። እሱም እንደሻው ይገለባብጣታል። በኃጢአተኛ ላይ አትጀነን። እኔ ከሱ የበለጥኩ ነኝ አትበል። በንቀት ዐይንም አትመልከተው። አላህ ለዚህ ለተከበረው የኢስላም መንገድ ሲመርጥህ አንተ የተለየህ ፍጡር ስለሆንክ አይደለም። ወይም ባንተ ምርጫ አይደለም እስልምናን ያገኘኸው። በእዝነቱ ስለጎበኘህ ነው። ግን ይህን እዝነቱን በሻው ጊዜ ሊወስድብህ ይችላል። ስለዚህ በመልካም ሥራህም ሆነ በዒባዳህ አትመፃደቅ። ጠመሙ የምትላቸዉን አትጠየፍ። ሁሌም አላህ እስልምናን ስለሰጠህ አልሐምዱ ሊላህ በል። የሱ እርዳታ ባይደርስልህ አንተም እንደነርሱ ትሆን ነበር። ኢስቲቃማን ስኬቴ ነው፣ በራሴ ጥረት ነው ለፍቼ የገኘሁት ብለህ አታስብ። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
721Loading...
07
باسم الله 📲👈እህቴ  ከስልክ ፊትና እራስሽን ለመጠበቅ!! ⚡️ይህ የተዘጋጀው ፁሁፍ ለናንተ መስለሃ(ጥቅም)ተብሎ ነው!! ⭕️እኛ በሰለፍይ እህቶቻችን ላይ መጥፎ ግምት ኖሮን ሳይሆን የፊትና በር ከመዝጋት አፃር ነው። 👉1'አካውንትሽን በራስሽ ስም ወይም በኩኒያሽ አትክፈቺ አትፃፊ ተፅፎም ከሆና ቀይሪው!! ስትጠቀሚ በልጅሽ ወይም ሴትነትሽን በማያሳይ በሆነ መልኩ አድርጊ‼      ይህን ማድረግሽ በሰልክ ከሚመጣ ፊትና ለመጠበቅ ሰበብ ይሆናል። 👉2' ሴትነትሽን የሚያሳዩ ፕሮፋይሎችን በጭራሽ አትጠቀሚ በቪድዮ ይሁን በፎቶ, አደራ ለክብርሽ የምትጨነቂ ከሆና ይህንን ነገር ተጠንቀቂ ብዙዎች ይህንን አይቶ ልፈተኑብሽ ልፈትኑሽ ይችላሉ ለምን መልካም ሷልህ ቁጥብ ናት ብሎ በውጥ ልመጣብሽ ይችላል ፕሮፋይ ማድረግም ካስፈለጋ የዑለማኦችን የሰለፎችን ቀዉል ተጠቀሚ።አንዳንድ እህቶች የሚጠቀሙት ስታይ በጣም አሳፋሪ የሆነ በራሷ ላይ የፊትና በር የሆነ ነገር ነው። 👉3' ጉሩፕ እና ቻናል አለማብዛት  በተለይ በተለይ ጉሩፕ አድ (የሚደረግ) እዛ ላይ አካወንታችሁ በግልፅ ስለሚታይ አንቺን በፊትና ላይ ለመጣል የቀረባ ነው   እዛ ሆን ብለው ሴቶችን የሚፈልጉ በውሰጥ መስመር ገብተው የሚረብሹ አሉ። ሌላ ደሞ በጉሩፕ ላይ 👍ላይክ አታድርጉ የማንም ብሆን ጉሩፑ ውስጥ ያለው ሰው ላይኩን ጫን አድርጎ ከያዛ ስማችህ አካወንታችሁ በግልፅ ስለሚታይ ተጠንቀቁ። ቻናል ለዚህ ጥሩ ነው አድሚኑ እራሱ ማየት አይችልም አያሳይም። ወስን የሆኑ ወደ አሏህ የሚያቃርቡሽ መካሪ የሰለፊዮች ቻናል ካሉሽ በቂ ናቸው ከሌላው ውጪ። 👉4' በየ ኮሜንት መስጫ ገብታችሁ አለመፃፍ (ዲናዊ ና የግል ጥያቄ ካላችሁ እንኳ በኮመንት መስጫ አትጠይቁ)ይህ ደሞ ወሏህ በሴት ልጅ ትልቅ ትልቅ ሙሲባ ፊትና የሆነ ነገር ነው በሱ ሰበብ ነው ብዙዎች የሚረበሹት (የተበላሹትም) አንዳንድ እህቶች አሏህ ሂዳያ ይስጣቸው ና በዚህ በጣም የተፈተኑ አሉ በየ ኮሜንት መስጫ ገብታ መፃፍ ከወንድ ጋ መመላለስ መከራከር የሆነ ያልሆነ ጥያቄ መጠየቅ እህቴ አሏህን ፍሪ እራስሽን ለአደጋ አታጋልጪ በኋላ በማትወጪበት ጣጣ ውስጥ ትገብያለሽ!! ጥያቄ ካለሽ ያልገባሽን ነገር ለመጠየቅ (በቦት#bot በኩል መጠየቅ አለበሽ  በጭራሽ በኮሜንት መስጫ አትጠይቂ።ይህም ለናንተ መስለሃ ነው!! 👌እኛ በሰለፍይ እህቶቻችን ላይ መጥፎ ግምት ኖሮን ሳይሆን፣ በተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲዙ ከመገፋፋት አንፃር ነው።    ✍አቡ ፋ***        ©አል_ቀመር_ሚድያ© ለመቀላቀል👇https://t.me/abumuazibrahim/3242
931Loading...
08
#እኛስ 2 ?
680Loading...
09
#እኛስ 1 ?
610Loading...
10
★ጌታዬ ያኔ ሲጠይቀኝ እያለ " ምነው ማታፍር አንተ እኔን ስታምፀኝ"★ ~~ አማሙ አህመድን ያስለቀሰ ልብ የሚነካ ግጥም ትርጉም #ኡስታዝ_ኢብኑ_ሙነወር →ጌታዬ ያኔ ሲጠይቀኝ →እያለ " ምነው ማታፍር አንተ እኔን ስታምፀኝ" →"ከፍጡሮቼ ሁሉ ወንጀልህን እየሸሸግክ →እኔ ጋር ግን መጣህ አመፅክን ተሸክመክ" →ወይኔ! ምን ይውጠኛል →ማንስ ይጠብቀኛል →ጊዜ ሄዶ አልፎ ጊዜ ሲተካ →ነፍሴ በምኞት ሲረካ →ዘነጋሁ የወዲያኛውን →ከሞት ከፈኔ የሚከተለውን →ዘላለም ለመኖር ቃል እንደተገባልኝ →ሞት የሚባል ነገር እንደማይመጣብኝ →ይሄው ጣእረ–ሞት መጣ →ማን ያተርፈኛል ከዚህ ጣጣ? →ዙርያየ ያሉን ቃኘሁኝ →የሚጠቅመኝ ግን አጣሁኝ →ምን እንዳስቀደምኩ ልጠየቅ ነኝ →ለዚህ ግዜየ የሚሆነኝ →ያኔ ምን ይሆን መልሴ →በእምነቴ ችላ ያልኩትን እራሴ →ወይኔ! ከቶ ምን ይብቃኝ →ሰምቼ አልነበርን የጌታዬ ቃል ሲጠራኝ? →በቃፍም፣በያሲን ያለውን →ምነው አልሰማሁ ተግሳፁን →ምነው አልሰማሁ ትንሳኤውን →የፍርዱን ቀንና መሰብሰቡን? →መለከል–መውት ሲፈልገኝ →አልሰማሁም ወይ ሲጠራኝ? →ጌታ ሆይ! እኔ ባሪያህ ተመለስኩኝ →ማን አለ ከለላ የሚሰጠኝ →ከምሕረተ ሰፊው ጌታ ሌላ →እኔን ወደ ሀቅ የሚመራ →በንሰሐ መጣሁ ይቅር በለኝ →መልካም ሚዛኔን አክብድልኝ →ሒሳቤን አርገው ቀና →ተስፋዬ አንተው ነህና ~~ 👇 https://t.me/nhwdr https://t.me/nhwdr https://t.me/nhwdr
780Loading...
11
ጀሀነም የሚገባው ወደ ጀሀነም ጀነት የሚገባውም ወደ ጀነት ከገባ በኋላ አንድ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይጣራል! አንተ ሙሐመድ! ተደሰተክ ወይ? እርሳቸው እንዲህ ይለሉ«ጌታዬ! ወላሂ አልተደሰትኩም። ከኡመቶቼ እሳት ውስጥ የቀረ አለ» አላህም ለመላኢኮች «ቅንጣት ታክል ኢማን በቀልቡ ያለውን ሁሉ ከእሳት አውጡ» በማለት ያዛቸዋል። ከዚያም ጀሀነም በሯ ይከፈትና የተወሰነው የሙስሊሙ ክፍል ወጥቶ ወደ ጀነት ይተማል። አላህ በድጋሚ «ሙሐመድ ሆይ! ተደሰትክ?» ይላቸዋል። «ጌታዬ ባንተ እምላለሁ! አሁንም ከህዝቦቼ የቀሩ አሉ» ብለው ያለቅሳሉ! አላህም ለመላእክቱ «አይኑ የትንኝ ራስ የምታክል እንባም ብትሆን እኔን ፈርታ ያነባችን ሁሉ አውጡ» በማለት ያዛል። ከዚያም «ያ ሙሐመድ! አሁንስ ተደሰትክ?» ይላቸዋል። «ወላሂ አልተደሰትኩም። አሁንም ከኡመቴ የቀሩ ሰዎች አሉ። ይላሉ ረሱላችን ﷺ » አላህ ለመላኢኮች «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ያለውን በጠቅላላ ከጀሀነም አውጧቸው» በማለት ያዛል። ጀሀነም በሮቿ ተከፍተው ሁሉም ወደ መስካሪዎች ጎራ ይነጉዳሉ። ከወርቅና ከሉል በተሰራ ግንብ ውስጥ ይነዳሉ። ባማረ መዓዛ ይታወዳሉ። ውስጥ የነበሩት የጀነት ሰዎች የተበለጡ እስኪመስላቸው ድረስ እነዚህ ሰዎች ውብ ይሆናሉ። ከዚያም ወደ ጀናህ እንዲገቡ ይደረጋል። ይሄኔ ለመጨረሻ ጊዜና ለዘልዓለም ጀሀነም ትዘጋለች!! በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ፦ « ﺭُّﺑَﻤَﺎ ﻳَﻮَﺩُّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ (ሱረቱ አል-ሒጅር- 2) አላህ የርሳቸውን ሸፈዓ የምናገኝ ያድርገን!! ሰሉ ዐለል ሐቢብ!! https://t.me/nhwdr
1053Loading...
12
ጓደኛህ ማነው? ~ ጓደኛህ ወደ ተሻለ የምትወስደው ወይም ወደተሻለ የሚወስድህ ይሁን። ካልሆነ ግን ወይ ያጠፋሀል። ወይ ታጠፋዋለህ። ወይ ተያይዛችሁ ትጠፋላችሁ። ሰው ውሎውን ይመስላል። ውሎህ የት ነው? ከማን ጋር? ሰዎች ጠጪ የሚሆኑት በጓደኛ ሰበብ ነው። ቃሚ፣ አጫሽ የሚሆኑትም በጓደኛ ተፅእኖ ነው። ያለ ምክንያት አይደለም "ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ" የሚባለው። ከመጥፎ ሱስ መውጣት፣ ባህሪህን መግራት ትፈልጋለህ? ከልብህ ከሆነ ውሎህን አስተካክል። ልጅህ ከመጥፎ አዝማሚያ እንዲመለስ፣ መስመር እንዲይዝልህ ትፈልጋለህ? ሰበብ ሳታደርስ ጠዋት ማታ አትጨቃጨቅ። ይልቁንም ውሎው ላይ አጥብቀህ ስራ። ካልሆኑ ጓደኞች ጋር ገጥሞ ከሆነ የምትችለውን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለህ ለየው። ለስንቶች በዲንም ይሁን በዱንያ መቃናት የመልካም ጓደኛ ትልቅ ድርሻ አለው። እስኪ በህይወት ጉዟችሁ ላይ አነሰም በዛ ላገኛችሁ ስኬት ወይም መልካም ለውጥ አስተዋፅኦ ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ለአፍታ አስቧቸው። በተቻለ መጠን ውለታ መላሽ እሱ ቢቀር አመስጋኝ ሁኑ። ከዚያም በላይ በዱዓእ አስታውሷቸው። ጓደኝነት ኣኺራን ከነጭራሹ ሊያጨልም፣ ኩ. ፍ. ር ላይ ሊጥል ይችላል። በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ለተረዱት እውነት እጅ መስጠት አቅቷቸዋል?! በጓደኛ ሰበብ ስንቶች እምነት ቀይረዋል? ስንት ወንዶች ሴት ተከትለው፤ ስንት ሴቶችም ወንድ ተከትለው ዘላለማዊ ህይወታቸውን አጨልመዋል?! የተሰጠን እድል ከእጃችን ሳያፈተልክ፣ ነፍሳችን ሳትሾልክ በፊት ሳይመሽ እናስብበት። እንወስን በጊዜ። ነገ ፀፀት እንዳይበላን። ጌታችን እንዲህ ይላል:- { وَیَوۡمَ یَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ یَدَیۡهِ یَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِیلࣰا (27) یَـٰوَیۡلَتَىٰ لَیۡتَنِی لَمۡ أَتَّخِذۡ فُلَانًا خَلِیلࣰا (28) لَّقَدۡ أَضَلَّنِی عَنِ ٱلذِّكۡرِ بَعۡدَ إِذۡ جَاۤءَنِیۗ وَكَانَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ لِلۡإِنسَـٰنِ خَذُولࣰا (29) } {በዳይም፡ «ምነው ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)። «ዋ ጥፋቴ! ምነው እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ። (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)። ሰይጣንም ለሰው በጣም ለውርደት አጋላጭ ነው።} [አልፉርቃን፡ 27-29] (ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 2/2016) = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
1362Loading...
13
Media files
1101Loading...
14
መሪጌታዎች አጭበርባሪ ደጋሚዎች ናቸው። ድግምት ከኢስላም የሚያስወጣ ቆሻ ሻ ተግባር ነውና ልንርቀው ይገባል። ፌስቡክ ላይ ስታገኟቸው ብሎክ አድርጓቸው። በቴሌግራም ግሩፖቻቸው ውስጥ እንዳያስገቧችሁ setting አስተካክሉ። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
1150Loading...
15
ከፈጅር ከግማሽ ሰዓት በፊት ንቃ፣ ዊትርን ስገድ ዱዓ አብዛ! ለፈጅር አዛን ሲል መስጊድ ሄደህ ሁለት ረከዓህ ስገድ። (ሴት ከሆነች እቤት ውስጥ ትሰግዳለች።) ከዚያም ሁለት መዳፎችህን ወደ ላይ ዘርጋና  ለሶላቱ ኢቃም እስኪደረግ ድረስ ዱዓውን አስረዝም፣ ከዚያም ከሶላት በኋላ  የጠዋት ዚክርዎችን አንብብ። በአላህ እምላለሁ! የአላህ ውዴታ፣ ስኬት፣ ሲሳይ እና  ደስታ በሁሉም የሕይወትህ ዘርፍ ውስጥ ታያለህ። ዶ/ር ያሲር አል ዒነዘይ
1151Loading...
16
በሳውዲ መማር ለምትፈልጉ! በተለያዩ ዘርፎች ለባችለር ዲግሪ እና ከዛ በላይ የሳውዲ ስኮላርሺፕ ለማግኘት በሚከተለው ኦፊሴሊያዊ ድረገፅ https://studyinsaudi.moe.gov.sa ላይ ማመልከት የምትችሉ ሲሆን፤ የማመልከቻ ግዜው ከአፕሪል 21 እስከ ጁላይ 28 / 2024 ድረስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እንመክራለን። አላህ ይወፍቃችሁ _ 🏷 Nesihajobs http://t.me/nesihajobs
3369Loading...
17
https://youtube.com/shorts/t4TAmnou3-w?si=bPqOtFvTCnVcFdEi
1040Loading...
18
👆አስተማማኝ ሂፍዝ ለመሀፈዝ ከሚረዱን ነገሮች 5ቱን
1386Loading...
19
ከሶፍ ውጭ ለብቻ መቆም ~ ሶፍ ሳይሞላ ለብቻ መቆም ክልክል ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ لا تصح صلاة المنفرد خلف الصف "ከሶፍ ኋላ ተነጥሎ ለሚሰግድ ሰው ሶላት የለውም።" [አሕመድ፡ 15862] ስለዚህ:- 1- ሶፍ ያልሞላ ከሆነ ለብቻ መቆም በጥብቅ የተከለከለ ነው። 2- ሶፉ የሞላ ከሆነ፣ ዘርዘር ብለው በመሰለፋቸው ሳያስቸግር የሚያስገባው ክፍተት ካገኘ አጠጋግቶ ይግባ። 3- የሚያስገባው ክፍተት ከሌለ ብቻውን ቆሞ ይሰግዳል። አላህ እንዲህ ይላል፦ { فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُمۡ } "አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት።" [አተጋቡን፡ 16] ከዚህ ውጭ ሶፍ ላይ ያለን ሰው ወደ ኋላ መሳብ አይቻልም። ምክንያቱም ይህንን የሚደግፍ ሶሒሕ ማስረጃ የለምና። በዚህ ላይ የሚጠቀሰውም ሐዲሥ ደካማ ነው። በዚያ ላይ ከሶፍ አውጥቶ ወደ ኋላ መጎተት ጥፋቶች አሉበት። * ሰውን መወስወስ አለበት። * የሚሳበውን ሰው የተሻለ ደረጃ ካለው ፊተኛው ሶፍ ዝቅ ማድረግ አለበት። * የፊተኛው ሶፍ ላይ ክፍተት መፍጠር አለበት። ይህም በጥብቅ የተከለከለ ነው። አዋቂው አላህ ነው። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
2591Loading...
20
Media files
1250Loading...
21
ماذا تفعل المرأة إذا انقطع صوت الإمام أثناء صلاة الجمعة؟ 📮 #السؤال : صليت مع الإمام ودخلت معه في تكبيرة الإحرام وسمعت قراءة الفاتحة ، ثم فجأة انقطع صوت الإمام ولم أسمع التكبيرة للركوع بسبب خلل في مكبر الصوت ، فلم أستطع متابعة الإمام وأكملت صلاتي منفردة. فهل الصلاة صحيحة بمخالفتي للإمام؟ 📑 #الجواب : الصلاة #صحيحة ، إذا انقطع صوت الإمام وانفرد الإنسان عن الإمام فصلاته صحيحة ؛ لأنه #معذور. 👈 لكن لو فرضنا أن هذا في صلاة الجمعة وانقطع الصوت في الركعة #الأولى وانفرد الإنسان عن الإمام فإنه لا يصلي جمعة ؛ لأنه لم يدرك منها ركعة. 👈 ولو انقطع في الركعة #الثانية وانفرد عن الإمام #أتمها جمعة ؛ لأنه أدرك ركعة كاملة. #ولكن لا ينبغي للمأموم -ذكراً كان أو أنثى- إذا انقطع الصوت أن ينوي الانفراد في الحال ، بل عليه أن #ينتظر ؛ لأنه أحياناً ينقطع الصوت ثم يصلحونه ، فإذا #أيس حينئذٍ ينفرد. 📄 الموقع الرسمي للشيخ ابن عثيمين 📄 http://binothaimeen.net/content/1349 📖 قـنـاة فـتـاوى الـمـرأة 📖 https://telegram.me/Fatwa_Feqh
1350Loading...
22
📹 የሀጅ ተጛዦች ስንቅ (10 የቪድዮ መማሪያዎች) ስኬታማ ሀጅ ከመማር ይጀምራል! 📼 በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉመው በስእላዊ መግለጫዎች የተዘጋጁ አስር አጫጭር የመማሪያ ቪዲዮዎች Share  Share Share ሊንኮቹን በመጠቀም ሀጅ ለነየቱ ሰዎች እናድርስ! 1) ሐጅን የሚመለከት የትውውቅ መቅድም http://youtu.be/YBVaAPCw0bo 2) ሐጅና ዑምራን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች http://youtu.be/UIxUyDy7_6E 3) የሐጅ ማእዘናት ዋጅቦችና ሱናዎች http://youtu.be/DOPX-zlTcTk 4 ) የዑምራ ማእዘናት ዋጅቦችና ሱናዎች http://youtu.be/pxHnlxWRJnQ 5) ሚቃቶች: http://youtu.be/tPmaOJd6iUQ 6) ኑሱክና ተልቢያ http://youtu.be/QI9k3Lv6GBE 7)  ኢሕራም http://youtu.be/G5dGhSAdsNo 8) ፍድያ (ቤዛ) እና ሀድይ http://youtu.be/jcA2HJtyylU 9) የሐጅና ዑምራ አፈጻጸም http://youtu.be/dCvfiz4q2Rc 10) የመዲና ጉብኝት የመዲና ትሩፋትና የላቀ ደረጃዋ http://youtu.be/AYQIPAI3lC8 በተለይ ሐጅ ለነየቱ እናድርስ... አላህ ይቀበላቸው! ሀጅ መብሩር ያድርግላቸው! © t.me/sultan_54
1231Loading...
23
https://youtube.com/shorts/5GbCTWjPe3o?si=eiSZ-d2mZygibK9i
1040Loading...
24
🎉ታላቅ የደውራ መዝጊያ ፕሮግራም! ~የውጪ ሀገር መሻይኾች እንድሁም የሀገራችን ኡስታዞች የሚሳተፉበት ድንቅ ፕሮግራም! 📃ተጋባዥ ኡስታዞች እና እንግዶቻችን፦⇩⇩ ①👤በጣፋጭ ምክራቸው የሚታወቁት ከየመን የሰለፊያ ታላላቅ መሻይኾች መካከል አንዱ የሆኑት ሸይኽ አቡ አብዲላህ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ ባጀዕላ፣ ②👤ኡስታዝ ሑሴን ዓሊ፣ ③👤ኡስታዝ አቡ ሻኪራ አህመድ ኑር፣ ④👤 ቃሪእ ኡስታዝ አቡ ዚክራ፣ ⑤👤ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ አል-ባጂ፣ ⑥👤 ኡስታዝ አቡ ፈውዛን አብዱ ሹኩር፣ ⑦👤 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ መሀመድ አሊ፣ ⑧👤 ኡስታዝ አቡ ዑሰይሚን፣ ☞እንድሁም ሰሞኑን ደውራው ላይ ኮርስ ሲሰጡን የነበሩ ኡስታዞችና ሎሎች ወንድሞችም ይገኙበታል! 🗓ነገ ቅዳሜ ሸዋል 25―ከምሽቱ  2:40ጀምሮ የሚተላለፍ ይሆናል ! 🎙ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት አድራሻ↓↓ t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan
1260Loading...
25
ሸዋልን ያልፃማችሁ ወይም ፆማችሁ ያልጨረሳችሁ እህቶቼ ሆይ! ሸዋል ወር እያለቀ ነውና እንዳያመልጣችሁ።
8103Loading...
26
🎙2ኛ ዙር ኮርስ የተሰጡ ደርሶች ስብስብ ! ~ «ዓቂዳ፦ ወንድም አቡ ሱፍያን» ☞ክፍል ⓵ t.me/AbuSufiyan_Albenan/5958 ☞ክፍል ⓶ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6026 ☞ክፍል ⓷ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6103 ☞ክፍል ⓸ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6140 ☞ክፍል ⓹ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6225 ≤ነህዉ፦ ኡስታዝ ሰዒድ ሙሀመድ ኑር≥ √ክፍል ➀ t.me/AbuSufiyan_Albenan/5957 √ክፍል ➁ t.me/AbuSufiyan_Albenan/5975 √ክፍል ➂ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6025 √ክፍል➃ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6084 √ክፍል➄ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6139 √ክፍል ➅ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6166 ∥ሙስጠለሃ አል_ሀዲስ፦ ኡስታዝ ሙሀመድ አብዲላህ ባቲ∥ ∼ክፍል ❶ t.me/AbuSufiyan_Albenan/5976 ∼ክፍል ❷ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6002 ∼ክፍል ❸ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6085 ∼ክፍል ❹ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6167 ∼ክፍል ❺ t.me/AbuSufiyan_Albenan/6195 ⦅አዳብ ፦ኡስታዝ አብዲረዛቅ አል_ጃቢ⦆ ⭞ክፍል 01 t.me/AbuSufiyan_Albenan/6003 ⭞ክፍል 02 t.me/AbuSufiyan_Albenan/6196 = ሌሎችም በርካቶች አሉ 👆👆
1631Loading...
27
ህይወታችሁ የሚያበላሹ  ነገሮች፦ 1)አነሳሽ ነገርን መጠበቅ ! 2)ሰዎች ለሚሉት ነገር መጨነቅ ! 3)ስለ ሁሉም ነገር ማማረር ! 4)ሁሉንም ሰዉ ለማስደሰት መሞከር ! 5)ራስን ከሌሎች ጋር ማነፃፀር ! 6)አንድ አይነት ስህተትን መድገም ! 7)ቅድሚያ ለሚሰጣቸዉ ነገሮች ቅድሚያ አለመስጠት ! 8)ዉድቀትን መፍራት ! 9)የራስን ሂወት አለመኖር ! = t.me/https_Asselefya1
1385Loading...
28
"የሰው ልጅ ሆይ ስማ!" ዛሬ በምድር ላይ እንደፈለግክና ያሻህን እየሰራህ ልትኖር ትችላለህ ነገር ግን ነገ ሞተህ ከምድር ስር እስረኛ ትሆናለህ! 👌 ልብ በል ! ✍ ምድር ላይ እየኖረ ዕድሜውን በጥሩ ነገር ያሳለፈ ሰው ሞቶ ምድር ውስጥ ሲገባ በሰላምና በደስታ ይኖራል ቀብሩም ይሰፋለታል የጀነት በርም ተከፈቶለት ፀጋዎቿን እያየ -ያረብ ቂያማን ቶሎ አቁማት-!እያለ በተስፋ ይኖራል ✍ ምድር ላይ እየኖረ በወንጀልና በግዴለሽነት ህይወቱን ያሳለፈ ሰው ሞቶ ምድር ውስጥ ሲገባ የሆድ እቃው ካፍንጫው እስኪወጣ ድረስ ምድር ታጣብቀዋለች ከላይዋ  ላይ እየኖረ አላህን በማስቀየሙ ትጠላው የነበረውን ያክል ከስሯ ሲገባ ዋጋውን ትሰጠዋለች! ✍ ይህም ቀን መች እንደሆነ ማንም በትክክል አያውቅም አሁን ከቅፅበት በኋላም ሊሆን ይችላል!
4505Loading...
29
"ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ" ~ የልጅ አእምሮ ነጭ ወረቀት ማለት ነው። እኛ ዋዛ የሚመስሉንን ብዙ ነገሮች እንደ ቁምነገር ይይዛል። በልጅነቱ የሰው ጅብ ወይም ጭራቅ የሚባል አለ ብለው ስለነገሩት ካደገ በኋላም እንዲህ የሚባል ነገር አለ ብሎ የሚያምን ብዙ ሰው አለ። በርግጥ ከእድገት ጋር የሚቀየሩ ነገሮች አሉ። ቢሆንም ኋላ ተቀየረም አልተቀየረም ለህፃናት ያልሆነ ነገር እየነገርን አእምሯቸው ውስጥ የተዛባ ነገር እንዳንተክል መጠንቀቅ ይገባል። ከዚህ ጋር የተያያዙ እንደየሃገሩ እንደየባህሉ ብዙ ልማዶች አሉ። ለምሳሌ፦ * ህፃናት ሲጫወቱ "ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ" እያሉ መዘመር። ይሄ ሺርክ ነው። * ጥርሳቸውን ሲጥቅሉ "አይጢቷ! የኔን ወስደሽ ያንቺን ስጪኝ" ብሎ ጣራ ላይ መጠል። ይህም ሺርክ ነው። * ጆሮ ደግፍ ሲያዛቸው የሰው ቤት በድንጋይ እንዲመቱ መላክ። በዚህም ውስጥ ትንሹ ሺርክ አለ። * የቀብር አፈር ቤት ላይ መበተን። ልጆች ውጭ ላይ አጥፍተው ሲመጡ ቤተሰብ እንዳይቀጣቸው ሲፈሩ የቀብር አፈር ይዘው በመምጣት ቤት ላይ ይበትናሉ። በቃ ይህን ሲያደርጉ ቤተሰብ ስለዚያ ጉዳይ አይጠይቅም ብለው ያምናሉ። በዚህም ውስጥ ሺርክ አለ። መስጠት የፈለግኩት ጥቆማ ነው። እነዚህና መሰል ባህሎች ዛሬ ከተማ ውስጥ በብዛት አይኖሩም። ግን አንዳንዴ የማንጠብቀው ነገር ይዘው እናገኛቸዋለን። ስለዚህ ልጆቻችንን በጨዋታም ይሁን በቁም ነገር፣ በእምትም ይሁን በልማድ መልክ የተዛባ ነገር እንዳይዙ መጠንቀቅ መልካም ነው። በሺርክ መቀለድ በእሳት መጫወት ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
1330Loading...
30
🌹 بشرى سارة 🌹 📢 አዳዲስ የኪታብ ትምህርቶች ማስታወቂያ 📚 አዲስ የሚጀመሩቱ ኪታቦች :- 1, فتح المجيد شرح كتاب التوحيد 2, رياض الصالحين من كلام سيد المرسلين 🎙 ኪታቦቹን የሚያቀሩት :- አሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም 🕌 ትምህርቶቹ የሚሰጡበት ቦታ:- ፉሪ(በፉሪ ሜዳ ፊት ለፊት ባለው ቅያስ ገባ ብሎ) አቡበክር አስሲዲቅ መስጂድ 🕐 ትምህርት የሚሰጥበት ቀንና ሰዐት :- 1, ፈትሑል መጂድ ከሰኞ እስከ እሮብ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ 2, ሪያዱ ሷሊሒን ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከፈጅር ሰላት በኋላ 🗓 ትምህርቶቹ የሚጀመሩት :- እሮብ ሸዋል 15 - 1445 ሂጅሪየን (ሚያዚያ 15 - 2016) ይሆናል። * በአካል ተገኝታችሁ መከታተል ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል እንዲሁም ሪከርዱም ይለቀቃል ኢንሻአሏህ። https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam
1350Loading...
31
✍መጥፎ ጓደኛ እንደዚህ ነው ምንም ያህል ጠንካራ አቋም ቢኖርሽ ከመጥፎ ሰዎች ጋር ከዋልሽ መበላሸትሽ አይቀሬ ነው የምትወጃትን ጓደኛ ጠንቅቀሽ ማውቅ ግድ ይልሻል አሏህ መልካሞችን ያጎናፅፈን🤲
1160Loading...
32
በዝሙት ላይ ዘመቻ ነው አሰራጩት /////////////////// 📮የሴት (ልጅ) ፊትና ////////////////// በሚል ርዕስ⤵️ 🔖 መካሪና ገሳጭ የሆነ መደመጥ ያለበት ሙሐደራ። ሙሐደራው ላይ ከተነሱ ነጥቦች⤵️ 👉የሸይጧን ጉትጎታ በሰው ልጆች ላይ፤ 👉የሸይጧን ሴራ በሴቶች ላይ ወንዶችን ለመፈተን፤ 👉በአሁን ዘመን ከሞባይል በተያያዘ የመጣ የዝሙትና የሴት ፊትና ስለ መብዛት፤ 👉በሴት ልጅ ፊትና ምክንያት ከቀጥተኛው መንገድ የተንሸራተቱ ሰዎች ታሪክ፤ 👉በተለይ ሙስሊም ሆነው የለበሱ ሆነው ያለበሱ ተራቁተው የሚሄዱ ሴቶች አኼራ እንዳለባቸውና ምን እንደሚጠብቃቸው⤵️ 👌ሌሎችም ተያያዥነት ያላቸው ነጥቦች የተወሳበት የሆነ⤵️ መካሪ፣ ገሳጭና ወሳኝ የሆነ መደመጥ ያለበት ሙሐደራ። 🎙️ በ ኡስታዝ አቡ ዒክሪማ ዓብዱረዛቅ አላህ ይጠብቀው። https://t.me/nhwdr https://t.me/nhwdr https://t.me/nhwdr
1254Loading...
33
እህቶቻችን አሏህን ፍሩ እህቴ ሆይ! ጥሩ ባል የሚገኘው አላህን በማመፅ አይደለም፡፡ ከእለት እለት የአብዛኛዎቹ እህቶቻችን አለባበስ በጣም ቅጥ እያጣ፤ የአሏህ መልእክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለብሰው ያለበሱ ያሉዋቸውን እየሆነ ነው፡፡ ታድያ ይህ ነገር ወዴት እያመራ ነው??? ጠባብ ቀሚስ፤ 8 ቁጥር፤ የውስጥ እስፖንጅ ሰውነትን ለወንዶች አጉልቶ ለማሳየት፤ ቅንድብ መቀንደብ፤ዊግ መቀጠል፤ ሊፒስቲክ፤ሜክ አፕ፤ በእጅ ልብስን ከፍ አድርጎ እግርን ለአጅነቢ ወንዶች ማሳየት፤ በየሲኒማ ቤት በር ላይ ከአጅነቢ ወንድ ጋር ... ፤ ሽቶ እና ሽታ ያለው ነገር ተቀብቶ መውጣት፤ አጅነቢ ወንዶችን መጨበጥ እና ሌላም ….. እህቴ ሆይ! አላህ ከተቆጣብሽ ከባድ አደጋ (hard) ላይ ነሽ፡፡ ሁለት አገር ሳይበላሽብሽ ቀድመሽ ተመለሽ ውበትም ይረግፋል ዘረናም ያከትማል፡፡ ይህንን መልእክት ለሴቶች ሁሉ እንድታደርሱልኝ በአላህ ስም እጠይቃለሁ፡፡ ቻናላችን https://t.me/tubaliligurebae ግሩፓችን https://t.me/Tuba_Lil_Gurebae
1310Loading...
34
Media files
1194Loading...
35
🔖ጥሩ ትዳር እና መልካም የሆኑ ልጆችን እንዲሰጠን ዱዓ እናድርግ !!   ~ ~ ሶሓቦቹ አላህን ሲለምኑት የጫማቸዉን መሠሪያ ሳይቀር  ለምነዉታል ። እስከዚያ ድረስ ይጠይቃሉ ይለምናሉ ።አሏህን መጠየቅ እንልመድ ።እንጠይቀዉ ከምንጠይቃቸዉ ነገሮች ዉስጥ ዋነኛዉ ነገር ዋና ከሚባሉ የዱኒያ መሠረታዊ ጥያቄዎች ዉስጥ ትዳር ሊሆን ይችላል ትዳር የሚባለዉ የሆነ ወንድ ማግኘት ወይም  የሆነች ሴት ማግኘት አይደለም። ለዚህ ነዉ  ያረቢ ብለን ለምነን  አንዳንዴ አላህ  እንዲያስወግደዉ  ልንለምን እንችላለን ስለዚህ ሷሊህ የሆነን ትዳር አላህ እንዲሠጠን እንለምን።ያገባን ሠዎች ልጅ እንዲሠጠን ብቻ አይደለም ሷሊህ መልካም ልጅ እንዲሠጠን ልንለምን ይገባል።አንዳንዴ ልጅ ብቻ የጠየቁ ከዚያ አላህ የፈተናቸዉ ስንት አሉ ።መልካም ዝርያዎችን እንዲሠጠን ፦ሪዝቃችን እንዲሠፋልን ፦አፊያችን የተሟላ እንዲያደርግልን እንለምን እንጠይቅ። እነዚህ ሁሉ ትክክለኛ ምኞቶች ሁነዉ ቁርአን ላይ እናገኛቸዋለን። وقوله : ( والذين يقولون ربنا هب لنا من أزواجنا وذرياتنا قرة أعين ) አንዳንዴ ትዳሮች መተዉ ዱኒያ ይዘዉ ሊሄዱ ይችላሉ ።አንዳንዶቹ ትዳሮች ደግሞ ዲንን ነዉ የሚያፈርሱት..ስለዚህ ልጅ ሳይሆን የሚጠየቀዉ ሷሊህ (መልካም )ልጅ ትዳር ሳይሆን መልካም ትዳርን እንዲሠጠን እንለምን አጠያየቃችንን እናሳምር።      ~ t.me/https_Asselfya
1331Loading...
36
🟢🟢አስደሳች  ዜና   ለእውቀት ፈላጊዮች በሙሉ። እነሆ ይሄንን ስናበስሮት በታላቅ ደስታ ነው። የሚሰጥበት ቀን፦ 👌በሳምንት  እሁድ እሁድ  ከጠዋቱ  3:00 ጀምሮ እስከ 5:30  ድረስ። ቦታው፦ 🕌  ቦሌ ጃዕፈር ትልቁ  መስጂድ ደርሱ  የሚሰጡን ኡስታዞች፦ 🎤በኡስታዝ  ሙሐመድ  ሲራጅ (አቡ ዒምራን)ሐፊዘሁላህ 🎤በኡስታዝ ናሲር ሙሓመድ (አቡል ዓባስ)ሐፊዘሁላህ የሚሰጡት የእዉቀት ዘርፎች፦ 👉አቂዳ 👉ነሕው እና 👉 ሐዲስ 🌲🌲ከናንተ  የሚጠበቀው  በእነዚህ  እንቁ  የሆኑ ኡስታዞች  ጊዜን አመቻችቶ እውቀትን  መቅሰም  ብቻ  ነው።
1430Loading...
37
የትኛው ይበልጥ ይደንቅችዋል ? የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር? 🥺 ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር ? 😍 ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት? 🥺🥰 አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር? በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም እንደው በመለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት? ❤️ በአዛኙ ነብይ ላይ ሰላዋት እናውርድ ♥️♥️ አላሁመሰሊ ወሰሊም ዓላ ሃቢቢና ሙሐመድ ♥️
1312Loading...
ኢትዮጵያ ኒቃብ መልበስን ልትከለክል ነው‼ ============================= (የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ 15+ ስጋቶች!) || ✍ የኢትዮጵያ መንግስት ኒቃበ ለብሶ መማርንና መሥራትን የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለማፅደቅ በሂደት ላይ ነው። እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ ኒቃብን በግልፅ የሚከለክል ህግ ባይኖርም፤ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ጠል ኃይሎች ባልተጻፈ ህግ ኒቃብ መልበስን ሲከለክሉ ነበር። ለናሙና ያክል በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኒቃብ ሳቢያ 2000 ገደማ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የታገዱበት ሁኔታ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ለነዚህና መሰል ኒቃብን በግል ጥላቻቸው ተነሳስተው ለሚከለክሉ አካላት ሽፋን የሚሰጥ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለመፅደቅ በሂደት ላይ ነው። ከኒቃብ ጉዳይ ባሻገር በመሰል ተቋማትና አንዳንድ የህዝብ መገልገያ አካባቢዎች በጀማዓህ ሶላት መስገድን የሚከለክል ክፍልም አለው። ረቂቅ አዋጁ ከመዘጋጀቱ በፊት ለግብዓትነት የሚሆን ጥናት ቀድሞ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉ 10 አባላት መካከል ሙስሊሙን የወከለው አንድ ግለሰብ ብቻ ነበር። ግና ከጥናት ዝግጅቱ ጀምሮ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በአግባቡ ያልወከለው ሂደት፤ ጭራሽ ረቂቅ አዋጁ ላይ ግልፅ የሙስሊሙ መብት ጥሰቶች ተካተዋል። በዚህ በባለ 15 ገፅ በንድፍ ላይ ያለ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በቀጥታ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር ከሚጋጩ ነጥቦች መካከል፤ የሚከተሉት አንቀፆችና ንዑስ አንቀፆች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የሚያጋጩና ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው። 1) 13.8 "የተከለከሉ ቦታዎች ቅስቀሳ ማድረግ" ማለት የትኞቹ በታዎች ናቸው? 2) 13.9 other (ሌሎች) ማለት ምን ማለት ነው? 3) 15.1 መስጂድ ሲጠበን ከመስጅድ ውጪ መስገድ አንችልም ማለት ነው? መስጅድ በሌለበት መስገድ አይቻልም? ይህን መሠረት አድርገው ሰበብ ፈላጊዎች ከመስጅድ ውጭ መስገድን እንዲከለክሉ መንገድ ስለሚከፍት ይህን እንደማይመለከት በግልፅ ሌላ ንዑስ አንቀፅ ላይ መስፈር አለበት። 4) 15.4 ሁሉም ቦታ በሚባል ደረጃ ሶላትን ይከለክላል፡፡ 5) 17.4 "በቡድን አምልኮ" በሚል ሽፋን የጀመዓህ ሶላትን ለመከልከል ይውላል። 6) 17.7 ቅጣቶች ለመንግስት መ/ቤቶች ክፍት ሆነዋልና ሌላ ችግር እንዲፈጠር በር ይከፍታል፡፡ ምክንየተቱም የትኛውም መሥሪያ ቤት ተነስቶ የራሱን ቅጣት በጥላቻ ቢያስተላልፍ መብት አለው ማለትን ያሲዛል። 7) 19.1 "ከኃይማኖት ተፅዕኖ ነፃ መሆን" ማለት ምን ማለት ነው? እስከምን ደረጃ? 8) 19.2: የአንዳንድ ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን አሠራር ለማፈን በር የሚከፍት ነገር አለው። 9) 19.5 በትምህርት ቤቶች የጀመዓህ ሶላት ተከልክሏል፡፡ 10) 19.6: "ማንነትን ለመለየት" በሚል ሽፋን  ኒቃብን ይከለክላል። በዚህ ቴክኖሎጂው ባደገበት ዘመን እንደ አሻራ ያሉ ቀላል ወጪ የሚጠይቁ ዘዴዎች እያሉ፣ በተለመደው አሠራርም በሴት የጥበቃ ሠራተኛ ማንነታቸውን መለየት እየተቻለ፣ በቢዝነስ ተቋማት ዘንድ ይህ ጥያቄ ሳይነሳ መኗኗር ሲቻል እያዬን… በዚህ ሽፋን ኒቃብን መከልከል ነውር ነው። 11) 22.2 በተለይም በሸሪዓው ውርስንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ለአንዳንድ ሙጅሪሞች በር ይከፍታል። 12) 24.1 የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ በተለይም በሙስሊሙ ዘንድ ሶደቃ የተለመደ ነውና! 13) 25.1: ይህም የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ 14) 25.3 ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ መጅሊስ በአዋጅ የተቋቋመ ራሱን የቻለ ተቋም ከሆነ በዚህ ደረጃ በሌላ የበላይ አካል control መደረግ የለበትም። 15) 25.4: ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ "በአዋጅ መቋቋም" የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም አሳጥቶ እንደተለመደው ወደ ተራ NGO ከማውረድ አይተናነስም። 16) 26: "ከኃይማኖት ተፅዕኖ የተላቀቀ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚወስኑት የየትምርት ቤቱ ኃላፊዎች ቢሆኑ የተሻለ ይሆናል፡፡ አለበለዚያ የኢስላማዊ ት/ቤቶችን ነፃነት ያፍናል። …  ባለ 15 ገፁ ይህ ረቂቅ አዋጅ በሶፍቲ ኮፒ በዚህ ሊንክ ስለሚገኝ፤ አንብቡትና እናንተም የታዘባችኋቸውን ስጋቶችና ህፀፆች አስፍሯቸው። https://t.me/MuradTadesse/35726 ♠ ይህ አፈና ሳይጻፍ የተበደልነው አንሶን ጭራሽ ተልፎ ሊተገበርብን ጫፍ ሲደርስ በዝምታ ማሳለፍ የለብንምና ሁሉም ሰላም ወዳድና ለእምነቱ ተቆርቋሪ ከወዲሁ ጉዳዩ ሳይጸድቅ ይስተካከል ዘንድ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ግደታችን ነው። መልዕክቱን ለሌሎችም በማሰራጨት ህዝበ ሙስሊሙ እየመጣ ስላለው አዲስ አዋጅ ከወዲሁ በቂ መረጃና ግንዛቤ ኖሮት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ እናድርግ። || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesse
Show all...
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
Show all...
የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ጥናት‼ =================== የመንግስት እና ሃይማኖት ግንኙነት በኢትዮጵያ፤ ትናንት ዛሬ እና ነገ አዘጋጅ፦ የፌዴራል የፍትሕና የህግ ኢንስቲትዩት የሶፍት ኮፒ (PDF) መገኛ ሊንክ፦ https://t.me/MuradTadesse/35708 ♠ እያንዳንዷን መስመር ምን ታሲዛለች፣ ምን ትርጉም አላት፣ ምን ተፈልጎባት ነው ብላችሁ በጥንቃቄና በጥሞና አንብቡት። በተለይም ከኡማው ጥቅምና ጉዳት አንፃር! || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesse ummalife.com/MuradTadesse tiktok.com/@MuradTadesse
Show all...
~ዛሬ በኢማን ጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘትህ ፣ነገ በዚሁ ላይ መጽናትህን አያመለክትም፣ አላህ እንጂ ራስህ ለራስህ ዋስትና መሆን አትችልም። ስለዚህ የደከሙትን አትናቅ።  ባልገራላቸው አትሳቅ። የሰው ልጅ  ቀልብ ሁሉ በአላህ እጅ ናት። እሱም እንደሻው ይገለባብጣታል። በኃጢአተኛ ላይ አትጀነን። እኔ ከሱ የበለጥኩ ነኝ አትበል። በንቀት ዐይንም አትመልከተው። አላህ ለዚህ ለተከበረው የኢስላም መንገድ ሲመርጥህ አንተ የተለየህ ፍጡር ስለሆንክ አይደለም። ወይም ባንተ ምርጫ አይደለም እስልምናን ያገኘኸው። በእዝነቱ ስለጎበኘህ ነው። ግን ይህን እዝነቱን በሻው ጊዜ ሊወስድብህ ይችላል። ስለዚህ በመልካም ሥራህም ሆነ በዒባዳህ አትመፃደቅ። ጠመሙ የምትላቸዉን አትጠየፍ። ሁሌም አላህ እስልምናን ስለሰጠህ አልሐምዱ ሊላህ በል። የሱ እርዳታ ባይደርስልህ አንተም እንደነርሱ ትሆን ነበር። ኢስቲቃማን ስኬቴ ነው፣ በራሴ ጥረት ነው ለፍቼ የገኘሁት ብለህ አታስብ። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
Show all...
باسم الله 📲👈እህቴ  ከስልክ ፊትና እራስሽን ለመጠበቅ!! ⚡️ይህ የተዘጋጀው ፁሁፍ ለናንተ መስለሃ(ጥቅም)ተብሎ ነው!! ⭕️እኛ በሰለፍይ እህቶቻችን ላይ መጥፎ ግምት ኖሮን ሳይሆን የፊትና በር ከመዝጋት አፃር ነው። 👉1'አካውንትሽን በራስሽ ስም ወይም በኩኒያሽ አትክፈቺ አትፃፊ ተፅፎም ከሆና ቀይሪው!! ስትጠቀሚ በልጅሽ ወይም ሴትነትሽን በማያሳይ በሆነ መልኩ አድርጊ‼      ይህን ማድረግሽ በሰልክ ከሚመጣ ፊትና ለመጠበቅ ሰበብ ይሆናል። 👉2' ሴትነትሽን የሚያሳዩ ፕሮፋይሎችን በጭራሽ አትጠቀሚ በቪድዮ ይሁን በፎቶ, አደራ ለክብርሽ የምትጨነቂ ከሆና ይህንን ነገር ተጠንቀቂ ብዙዎች ይህንን አይቶ ልፈተኑብሽ ልፈትኑሽ ይችላሉ ለምን መልካም ሷልህ ቁጥብ ናት ብሎ በውጥ ልመጣብሽ ይችላል ፕሮፋይ ማድረግም ካስፈለጋ የዑለማኦችን የሰለፎችን ቀዉል ተጠቀሚ።አንዳንድ እህቶች የሚጠቀሙት ስታይ በጣም አሳፋሪ የሆነ በራሷ ላይ የፊትና በር የሆነ ነገር ነው። 👉3' ጉሩፕ እና ቻናል አለማብዛት  በተለይ በተለይ ጉሩፕ አድ (የሚደረግ) እዛ ላይ አካወንታችሁ በግልፅ ስለሚታይ አንቺን በፊትና ላይ ለመጣል የቀረባ ነው   እዛ ሆን ብለው ሴቶችን የሚፈልጉ በውሰጥ መስመር ገብተው የሚረብሹ አሉ። ሌላ ደሞ በጉሩፕ ላይ 👍ላይክ አታድርጉ የማንም ብሆን ጉሩፑ ውስጥ ያለው ሰው ላይኩን ጫን አድርጎ ከያዛ ስማችህ አካወንታችሁ በግልፅ ስለሚታይ ተጠንቀቁ። ቻናል ለዚህ ጥሩ ነው አድሚኑ እራሱ ማየት አይችልም አያሳይም። ወስን የሆኑ ወደ አሏህ የሚያቃርቡሽ መካሪ የሰለፊዮች ቻናል ካሉሽ በቂ ናቸው ከሌላው ውጪ። 👉4' በየ ኮሜንት መስጫ ገብታችሁ አለመፃፍ (ዲናዊ ና የግል ጥያቄ ካላችሁ እንኳ በኮመንት መስጫ አትጠይቁ)ይህ ደሞ ወሏህ በሴት ልጅ ትልቅ ትልቅ ሙሲባ ፊትና የሆነ ነገር ነው በሱ ሰበብ ነው ብዙዎች የሚረበሹት (የተበላሹትም) አንዳንድ እህቶች አሏህ ሂዳያ ይስጣቸው ና በዚህ በጣም የተፈተኑ አሉ በየ ኮሜንት መስጫ ገብታ መፃፍ ከወንድ ጋ መመላለስ መከራከር የሆነ ያልሆነ ጥያቄ መጠየቅ እህቴ አሏህን ፍሪ እራስሽን ለአደጋ አታጋልጪ በኋላ በማትወጪበት ጣጣ ውስጥ ትገብያለሽ!! ጥያቄ ካለሽ ያልገባሽን ነገር ለመጠየቅ (በቦት#bot በኩል መጠየቅ አለበሽ  በጭራሽ በኮሜንት መስጫ አትጠይቂ።ይህም ለናንተ መስለሃ ነው!! 👌እኛ በሰለፍይ እህቶቻችን ላይ መጥፎ ግምት ኖሮን ሳይሆን፣ በተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲዙ ከመገፋፋት አንፃር ነው።    ✍አቡ ፋ***        ©አል_ቀመር_ሚድያ© ለመቀላቀል👇https://t.me/abumuazibrahim/3242
Show all...
#እኛስ 2 ?
Show all...
#እኛስ 1 ?
Show all...
02:12
Video unavailableShow in Telegram