ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Open in Telegram
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 t.me/FinoteBooks1623
Show more3 283
Subscribers
No data24 hours
-247 days
-4930 days
Posts Archive
+1
#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት
ለረጅም ግዜ ከገቢያ ጠፍቶ የነበረ
ቀደም ሲል በተስፋ ገብረ ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋ ታትሞ የነበረ ገድለ ተክለሃይማኖት ተአምረ ተክለሃይማኖት መልክአ ተክለሃይማኖት በግዕዝና በአማርኛ።
በግዮን መጻሕፍት መደብር የተለያዩ
ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!
ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
t.me/GhionBooksGhionBookStore1623
#ቅምሻ
"በዚህ ዓለም ገዢ የኾኑ ስዎች የማሰር ሥልጣን አላቸው፤ ማሰር የሚችሉት ግን ሥጋን ብቻ ነው፡፡ የካህናት የማስር ሥልጣን ግን ነፍስን ጨምሮ ሰማያትንም ዘልቆ የሚገባ ነው፡፡ ካህናት እዚህ ታች የሚያደርጉትን እግዚአብሔርም በላይ ያጸድቀዋልና፤ የአገልጋዮቹን ውሳኔ ጌታቸውም ያጸናዋልና፡፡ “ለእለ ኀደግሙ ኃጢአተ ይትኀደግ ሎሙ ወለእለሰ ኢጎደግሙ ኢይትኀደግ ሎሙ - ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ኹሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸውም ተይዞባቸዋል" በማለት ኹሉንም ሰማያዊ ሥልጣን ሰጥቷቸዋልና (ዮሐ.20፡23)። ታዲያ ከዚህ የሚበልጥ ምን ሥልጣን ይኖራል? “አብ ፍርድን ኹሉ ለወልድ ሰጥቶታል" (ዮሐ.5፡22)፡፡ እዚህ ላይ ግን ወልድ ፍርድ ኹሉ ለካህናት ስጥቷቸው እናያለን፡፡ ልክ ወደ ሰማየ ሰማያት እንደ ወጡ፣ የሰዋዊ ባሕርይ ወሰንም አልፈው እንደ ኼዱ፤ እኛንም ከሚማርከን የሥጋ አምሮት አርነት እንደ ወጡ ኾነው ወደዚህ ክብር ተጠርተዋልና፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ በእንተ ክህነት፥ ድርሳን ፫ ቁጥር ፭
___
ግዮን መጻሕፍት መደብር!
አድራሻችን፦ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በምዕራብ በር
+2
#ድጋሚ_የታተሙ_ገድላት
፩. ገድለ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
፪. ገድለ አቡነ አረጋዊ ወአቡነ ጰንጤሌዎን
፫. ገድለ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ መጽሐፍቶችን እናቀርባለን።
📚 #ከማራኪ_መጽሐፍ_ገፆች📚
🔥‹‹በዕለት ከዕለት ኑሯችን ውስጥ የሚደርስብንን ሁሉ ነገር መቆጣጠር አንችልም፤ ነገር ግን ለደረሰብን ጉዳይ ምላሽ የምንሰጥበትን መንገድ መቆጣጠር እንችላለን። አንዳንዴ ሕይወት የቤታችን በር በውስጥ በኩል ትቆልፍና ውጭ ላይ ገልብጣ ታሰጣናለች። ዝናብና ፀሐይ፣ ውርጭና ብርድ፣ ችግርና መከራ እንዲፈራረቁብንም ታደርጋለች። መሰል ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የምናሸንፈው ተስፋን ስንቅ፣ ፅናትን ምርኩዝ፣ እምነትን መሰላል እንዲሁም ትዕግሥትን ጋሻ ጦር በማድረግ ነው።
🔥በሕይወታችን ውስጥ ግጭቶች በጠነከሩ ቁጥር የምናገኘው ድል ይበልጥ ክብር ያለው ይሆናል። ብዙ ጊዜ እንደ እንቅፋትና መሰናክል የምንመለከታቸው ነገሮች ታላቅ የለውጥ እድል የሚፈጥሩልን መሸጋገሪያ ድልድዮች ናቸው። ተግዳሮቶች አዲስ የስበት ማዕከል እንድንፈልግ የሚያስገድዱን ስጦታዎች ናቸው። ሁሌም ራሳችን ከትናንት የተሻልን ለማድረግ ስንጥር በዙሪያችን ያለው ነገር ሁሉ የተሻለ እየሆነ ይመጣል።
🔥ለስኬታማ ሕይወት ትልቁ ሚስጥር ተሰጥኦን መርምሮ ማወቅና በእርሱ ጥላ ስር ፈተናዎችን ተቋቁሞ መሽከርከር ነው። ስለዚህ በቅድሚያ ማን እንደሆን ራሳችን መዝነን አውቀን ያን ሰው በትክክል ልንሆን ይገባል። ነፍሳችን በዚህ ፕላኔት ላይ ያስቀመጠችው ያን እንድንሆን ነው። ያንን እውነት እናግኝ፣ ያንን እውነት በጥልቀት እንረዳ፣ ያንን እውነት በተግባር እንኑር፣ ካለንበት እንጀምር፣ ያለንን እንጠቀም፣ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ። ቀስ በቀስ ሁሉም ነገር ወደ እኛ ይመጣል››
#ኅብር
ከደራሲ መምህር በረደድ ገዳሙ
የደራሲ መምህር በረደድ ገዳሙ አራት መጻሕፍት በገበያ ላይ
#ኅብር
#ሉባር 5ተኛ ዕትም
#ስሙር 2ተኛ ዕትም
ዘወትር በልዩ ቅናሽ በግዮን መጻሕፍት
+2
#በገበያ_ላይ_ዋለ!
ከሳይንስ ጋር የተገናኙ ፍልስፍናዊ ጉዳዮች ለክርስቲያኖች ያን ያህልም አስፈላጊነት የሌላቸው መስለው የሚታዩዋቸው ወገኖች ይኖሩ ይሆናል። ሳይንስ የሚመለከተው ይህን ዐለም ነው፡ ይህ ዐለም ደግሞ ጊዜያዊና ኃላፊ ነው፤ ታዲያ ክርስቲያኖች ኃላፊና ጠፊ ስለሆነው ስለዚህ ዐለም ምን ያስጨንቃቸዋል? የሚሉ ይኖሩ ይሆናል። ሳይንስ ለመንፈሳውያን ሰዎች ምን ያደርግላቸዋል? ሳይንስንስ ከሃይማኖት ጋር ምን ያገናኘዋል? የሚሉ ወገኖች አይታጡ ይሆናል።
እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። ተወደደም ተጠላም የምንኖርበትን ዐለም ለመምራት የሚሻኮቱት እሳቤዎች የየራሳቸው ፍልስፍናዊ መነሻ ያላቸው ናቸው። በአዎንታም ይሁን በአሉታ ልዩ ልዩ አቋሞቻችንና አመለካከቶቻችን የሚቀረጹት ከሳይንሳዊ ቲዎሪዎችና እሳቤዎች አንጻር የሚሆንባቸው ብዙ ሁኔታዎች አሉ = በሳይንስና በፍልስፍና ስም የሚናኙ ዘርፈ-ብዙ የሆኑ ርእዮተ ዐለሞች በየጊዜው ይሰበካሉ፣ እነዚህ የተለያዩ ፍልስፍናዊ አቋሞችም ዐለምን ወደየራሳቸው አመለካከት ለማስገባት ይራኮታሉ።.....
(ከመጽሐፉ መቅድም የተቀነጨበ)
____
መጽሐፉ በመደብራችን እየተሸጠ ይገኛል!
አድራሻችን፦ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በምዕራብ በር ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ 0913083816 ላይ ይደውሉ
የምንኖርበትን ሳይንሳዊ ዓለም በክርስትና ዓይን የሚመረምር እና ትክክለኛ ሚዛናዊ እይታን የሚሰጥ ድንቅ መጽሐፍ ነው። የታላቁ መ/ር ያረጋል አበጋዝ
አዲስ መጽሐፍ በገቢያ ላይ
በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
+2
በግዮን መጻሕፍት መደብር የተለያዩ
መጻሕፍቶችን በልዩ ቅናሽ ታገኛላችሁ።
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና
ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍቶችን ያገኛሉ!
ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
#የደብተራ_በአማን_ነጸረ ወልታ ጽድቅ መጽሐፍ ለአራተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል።
የሽፋን ዋጋው 400 ብር ሲኾን
በግዮን መጻሕፍት መደብር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!
ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
+1
#እንደዚህ_አድርግ!
ስትተኛ— ጸልይ!
ስትነቃ— ጸልይ!
ሕይወት ስትከብድ— ጸልይ!
ደስተኛ ስትሆን— ጸልይ!
እርግጠኛ መሆን ሲከብድህ— ጸልይ!
በምንም ሁኔታ ጸልይ. . .
ተአምራቱን ታየዋለህ፤ ምክንያቱም፦
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነውና!!
#ትምህርተ_ሺኖዳ መጽሐፍ
#አቡነ_ሺኖዳ_መልስ_አላቸው መጽሐፍ
ሁለቱም የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ አዲስ መጽሐፍት በገቢያ ላይ በግዮን መጻሕፍት በደብር በልየ ቅናሽ ታገኙታለችሁ።
+1
#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት
፩. የልቡና ችሎት - በዲ/ን በረከት አዝመራው - ዕቅበተ እምነታዊ ይዘት ያለው ሲሆን የሽፋን ዋጋው 700 ብር
፪. አኰቴተ ቍርባን - በቀሲስ ዶ/ር መብራህቱ ኪሮስ - ነገረ መለኮታዊ ይዘት ያለው ሆኖ የሽፋን ዋጋው በ750 ብር ቀርቧል።
በግዮን መጻሕፍት መደብር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!
ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
t.me/GhionBooksGhionBookStore1623
እነዚ ነገረ መለኮትን የተመለከቱ7
መጻሕፍቶች የተወሰነ ቅጂዎች አሉን።
በግዮን መጻሕፍት መደብር
በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
፦ስልክ 0913083816 /0931144330
አድራሻ ምኒልክ አደባባይ መናገሻ ገነተ
ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በምዕራብ በር
ማይክሮ ሊንክ እንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት
ለረጅም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረውና ተወዳጁ ዜና አበው መጽሐፍ ድጋሚ ታትሞ በመጻሕፍት መደብራችን እየተሸጠ ይገኛል።
"የልቡና ችሎት" መጽሐፍ ሦስተኛ እትም ዛሬ ወጥቷል።
***
በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
አድራሻ፦ ገነተ ጽጌ ጊዮርጊስ በምዕራብ በር ማህበረ በኵር ሰንበቴ ፊት ለፊት
ስልክ፦ 0913083816/0931144330
+1
የጎንደር መንበረ መንግስት መድሃኒዓለም የአራቱ መጽሐፍት ቤት መምህር እና አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የተረጎሙት 1044 ገጽ ያለው የሐይማኖተ አበው የትርጓሜ መጽሐፋቸው ድጋሜ ታትሞ ለገበያ ቀርቧል። የመጽሐፉ ገቢ ለጎንደር ጉባኤ ቤት ነው ተብሏል።
በግዮን መጻሕፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
+2
#ድጋሚ_የታተሙ_መጻሕፍት
፩. ኮክሐ ሃይማኖት - የሽፋን ዋጋው 650 ብር
፪. መጽሐፈ ሲኖዶስ - የሽፋን ዋጋው 500 ብር
፫. ባሕረ ሐሳብ (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ) የሽፋን ዋጋው 400 ብር
በግዮን መጻሕፍት መደብር በልዩ ቅናሽ ታገኙታላችሁ።
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና
ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!
እንዲሁም የታሪክና ልብወለድ ሳይኮለጂና
የፍልስፍና መጽሐፍቶችንም ያገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
+1
የክርስቶስ የባሕርይ አምላነት በቅዳሴ ማርያምና በውዳሴ ማርያም
በቅዳሴ ማርያምና በቅዳሴ ማርያም ላይ በስፋት የተነገረው ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ስለና ምሥጢረ ሥጋዌ ነው።በተለይም ቅዳሴ ማርያም ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ጥልቅና ግልጽ በሆነ መንገድ አብራርቶ ያስቀምጣል።ስለዚህ በዓለም የሚኖሩ የሚኖር አንድ ሰው እንኳን ስለ ምሥጢረ ሥላሴ በስፋትና በጥልቀት ማወቅ ቢፈልግ ቅዳሴ ማርያም በጥናትና ምርምር መጠቀም ይችላል ማለት ነው።ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ግን በየግዜው በቅዳሴ ጸሎት ትገለገልበታለች።በምስክርነት ለማሳየት ያህል ከዚህ ከቅዳሴ ማርያም ውስጥ ስለ ምሥጢረ ሥጋዌና ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የተነገረውን በጣም በትንሹ ልጥቀስ፦ <<እሳታውያን የሚሆን ሱራፌልና ኪሩቤል ሊነኩት የማይቻላቸው በእውነት እሳት ነው፣ እውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ የሕይወት መጠጥን ወልሽልናልና ስለዚህ ማርያም ሆይ! እንወድሻለን፣ ከፍ ከፍም እናደርግሻለን። ፦ገጽ 293
የተወሰነ ቅጂዎች አሉን በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
#ዜና_መጽሐፍ
#ርእስ፦ ሐተታ ዘቅዱስ አትናቴዎስ- ተስእሎተ አንትያኮስ
#ይዘት፦ ቅዱስ አትናቴዎስ በዘመኑ የተለያዩ መጻሕፍትን አዘጋጅቷል፡፡ ከሥራዎቹ አንዱ አንትያኮስ የሚባል መኰንን ለጠየቀው ጥያቄ መልስ የሰጠበት ይህ “ተስእሎቶ አንትያኮስ" የተባለ መጽሐፍ ነው፡፡ የመኰንኑ ጥያቄና የሊቁ መልስ በሁለት ክፍል የተከፈለ ነው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ሰባ ስምንት ጥያቄዎችንና መልሶቻቸውን የያዘ ሲሆን የሁለተኛው ክፍል ደግሞ አርባ ጥያቄዎችንና መልሶቻቸውን ይዟል፡፡ መጽሐፉ በድምሩ በሊቁ የተመለሱ የ118 ጥያቄዎች መልሶችን ይዟል ፡፡ በእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ ሥነ ፍጥረት፣ ነገረ መለኮት፣ ሥርየተ ኃጢአት፣ ልዩ ልዩ የምግባር ሥራዎችና ሌሎችም ጥያቄዎች ተካተውበታል፡፡ አብዛኞቹ በዚያ ዘመን የነበሩ መናፍቃን ኑፋቄዎች ለመሆናቸው የጥያቄዎች መንፈስ ያስረዳል።
#የገጽ_ብዛት፦ 180
#የሽፋን_ዋጋው፦ 290 ብር
___
ከግዮን ቅናሽ ጋር እንጠብቅዎታለን - ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
አድራሻችን፦ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ በምዕራብ በር ማህበረ በኩር ፊት ለፊት።
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የየኔታ ገብረመድኅን እንየው መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ።
በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!
ለበለጠ መረጃ በ0913083816 ይደውሉ።
አድራሻችን፦ አራዳ ጊዮርጊስ በምዕራብ በር፥ ማህበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት
አዲስ መጽሐፍ በገያ ላይ
ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ-፦
የሰጠኝን ሰጠሁህ"
ውድ ኦርቶዶክሳውያን በብዙ ፈተና ውስጥ ሁኘ ባለችኝ ትንሽ ጊዜ በትንሿ መረዳቴ ይሄንንን መጽሐፍ፦"ከመዝ ነአምን" በሚል ርዕስ
ለማበርከት ሞክሬያለሁ።
ኦርቶዶክሳዊነትን ለማስረዳት በተቻለኝ መጠን የደከምሁበት ቢሆንም ከአጠገቤ መጻሕፍትን ባለማግኘቴ ግን እንደ ሚገባ ጽፌዋለሁ ብየ አላስብም።
ስለሆነም ርቱዓን ኦርቶዶክሳውያን የጠመመውን አቃንታችሁ፣የጎደለውን ሞልታችሁ፣የገደፍሁትን አርትታችሁ እንድታነቡት እማፀናለሁ።ግድፈተ ቃለ ካለም ግድፈቱ የእኔ ብቻ ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያኗ አይደለም።
ከመጀመሪያው ጀምሮ አንብበን ከጨረስን በኋላ ቆም ብለን ወደ ኋላ ብናስበው ለአባቶች
ትምህርት መግቢያ የሚሆነንን የኦርቶዶክሳዊነት መነሻ ትምህርት እናገኝበታለን ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።
የእኔ ደስታየ አንብበን ወደ ላይ ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት በኅሊና ደርሰን ለልቡናችን
ድጋፍ የሚሆን ኦርቶዶክሳዊ መረዳትን ካገኘንበት ነው።
ስለሁሉም ነገር አሁን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላለው ትውልድ እና ከእኔ በኋላ ለሚነሣው
ትውልድ ኦርቶዶክሳዊ ሐሳቤን በጽሑፍ እንዳስተላልፍ የረዳኝን እግዚአብሔርን
አመሰግነዋለሁ።
“ጸልዩ ለነ ከመ ይሩጽ ቃለ እግዚአብሔር” ፪ ተሰ ፫፥፩
መምህር ገብረ መድኅን እንየው
አዲስ መጽሐፍ በገያ ላይ
ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ-፦
የሰጠኝን ሰጠሁህ"
ውድ ኦርቶዶክሳውያን በብዙ ፈተና ውስጥ ሁኘ ባለችኝ ትንሽ ጊዜ በትንሿ መረዳቴ ይሄንንን መጽሐፍ፦"ከመዝ ነአምን" በሚል ርዕስ
ለማበርከት ሞክሬያለሁ።
ኦርቶዶክሳዊነትን ለማስረዳት በተቻለኝ መጠን የደከምሁበት ቢሆንም ከአጠገቤ መጻሕፍትን ባለማግኘቴ ግን እንደ ሚገባ ጽፌዋለሁ ብየ አላስብም።
ስለሆነም ርቱዓን ኦርቶዶክሳውያን የጠመመውን አቃንታችሁ፣የጎደለውን ሞልታችሁ፣የገደፍሁትን አርትታችሁ እንድታነቡት እማፀናለሁ።ግድፈተ ቃለ ካለም ግድፈቱ የእኔ ብቻ ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያኗ አይደለም።
ከመጀመሪያው ጀምሮ አንብበን ከጨረስን በኋላ ቆም ብለን ወደ ኋላ ብናስበው ለአባቶች
ትምህርት መግቢያ የሚሆነንን የኦርቶዶክሳዊነት መነሻ ትምህርት እናገኝበታለን ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።
የእኔ ደስታየ አንብበን ወደ ላይ ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት በኅሊና ደርሰን ለልቡናችን
ድጋፍ የሚሆን ኦርቶዶክሳዊ መረዳትን ካገኘንበት ነው።
ስለሁሉም ነገር አሁን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላለው ትውልድ እና ከእኔ በኋላ ለሚነሣው
ትውልድ ኦርቶዶክሳዊ ሐሳቤን በጽሑፍ እንዳስተላልፍ የረዳኝን እግዚአብሔርን
አመሰግነዋለሁ።
“ጸልዩ ለነ ከመ ይሩጽ ቃለ እግዚአብሔር” ፪ ተሰ ፫፥፩
መምህር ገብረ መድኅን እንየው
Available now! Telegram Research 2025 — the year's key insights 
