cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቃልኪዳን አለም አቀፍ መረጃ✍🗣

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። ለአስታየት @kali_tube

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

👉ውድ በብዙ ችግር አልፋችሁ የ2013ዓ/ም ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የ12 ዓመት ልፋታችን ላይ ለፖለቲካ ዓላማቸው ሲሉ ወድቃችሁ ቤት ለቀራችሁ በሙሉ. በሀገራችን ጥሩ የትምህርት ዕድል (access) አለበተ ከሚባሉ የሃገራችን ክፍሎች ውስጥ የሲዳማ ክልል አንዱ ነው። በዚህም የተነሳ ይህ ክልል ብዙ ተማሪዎችን አስተምሮ ለጥሩ ውጤት በማብቃት ግንባር ቀደም ነበር። ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ 21,961 ተማሪዎች መፈተናቸው የታወቀ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 3118 የሚሆኑ ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸው ታውቋል። ይህም 14.2% ያህሉ ብቻ ነው ያለፈው ማለት ነው። በክልሉ በ6 ወረዳ፣ ማለትም ዳራራ፤ ማልጋ፤ ሆኮ፤ ጫቤ ጋንቤልቶ እና ጎርቼ ወረዳ አንድም ተማሪ የመንግሥት ዩንቨርስቲ አለመግባቱ ተረጋግጧል። ለዚህም እንደምክንያት የተጠቀሰው፣ የተማሪዎች ውጤት አተያይ በጥንቃቄ አለመታረም እንደምክንያት ይነሳል ለዚህም አንዳንድ ክልሎች ከከፍተኛ አመራር እስከ ተማሪው ጡሩ ሚባል ንቅናቄ እያደረጉ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የሲዳማ ክልል አመራሮች ዝምታ ስለመረጡ፣ ይህ የሲዳማ ተማሪዎች ንቅናቄ ግድ ብሎዋል። በዚህም መሠረት 25/7/2014 በሲዳማ ክልል በሚገኙ ከተሞች በነቂስ በመውጣት ድምፃችንን እናሰማለን።💪💪 ይህ ጉዳይ ለሚመለከተው ሁሉ በማሳወቅ፣SHARE በማድረግ ሃላፊነትዋን ይወጡ🙏🙏🙏 ፍትህ ለሲዳማ ተማሪዎች💪💪 ********************************* 👉Dear In many cases, you have taken the 2021 national exam and have fallen to our country sake of their political purpose. one of our countries' areas, which has a good academic opportunity is our region. As a result, this region taught many students and was at the forefront of promoting good results. However, the 12th National exam, which has been unprecedented, has been recognized by 21,961 students, of which only 3118 students have passed.This means that only 14.2% have passed.In the region, 6 districts, i.e. Darrara Malga,Hoko, chabe Ganbelto and Gorsche district No One student of the university's dispute was confirmed. To this end, the reason for the fact that the student's perspective is that I will be motivated to be carefully corrected is that some regions are acquainting from senior leadership to student. However, because the leaders of the Sidama region chose silence, this push sidama student movement was concerned. Accordingly, On the 3/3/2022, We will vote most city and district in the Sidama region.💪 💪 Notify everyone concerned, take responsibility by doing SHARE🙏🙏🙏🙏 Justice for sidama student💪💪💪💪
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጉዳይ የከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ውሳኔ እንደሚያስፈልገው ተጠቆመ! ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጉዳይ ለመፍታት የከፍተኛ ፖለቲካ አመራሩ ውሳኔ እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ፡፡ የአማራ ክልል 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ 2ኛ ቀኑን የከሰዓት ውሎ በምክር ቤቱ አባላት ለተጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጠ ነው። ትምህርት፣ ግብርና፣ ሥራ ፈጠራና ኑሮ ውድነትን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ እየተሰጠባቸው ይገኛል። በትምህርት ዘርፉ በተለይም የ12ኛ ክፍል ውጤት ከተጠበቀው በላይ መሆኑ ተማሪዎችን፣ የተማሪ ወላጆችን፣ መምህራርንና የትምህርት ማኅበረሰቡን ጎድቷል ተብሏል፡፡ ተማሪዎች በጦርነቱ ውስጥ ስለቆዩ በሥነ-ልቦና ለፈተናው ዝግጁ ባለመሆናቸውና በጦርነት ውስጥ ሆነው ስለተፈተኑ ተማሪዎች ውጤቱ ዝቅተኛ ሆኗልም ነው የተባለው፡፡ በዚህም የሥራ ኃላፊዎቹ ለምክር ቤቱ አባላት በሰጠው ምላሽ የተማሪዎቹን ጉዳይ ለመፍታት የከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ ውሳኔ ያስፈልገዋል በሚል ምላሽ ሰጥቷል። @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት በመቃወም በደብረማርቆስ ከተማ ሰልፍ ተካሄደ፡፡ በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤትን ተከትሎ ብዙዎች ቅሬታዎች እያቀረቡ ሲሆን ፤በተለይ ውጤቱ በጦርነት ውስጥ የቆዩ አካባቢዎች የሚማሩ ተማሪዎችን ለምን ታሳቢ አላደረገም በሚል አሁንም ጥያቄዎች መቀጠላቸው ይታወቃል፡፡ በዛሬው እለትም የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት በመቃወም በደብረማርቆስ ከተማ ሰልፍ ተካሄዷል፡፡ በሰልፉ ላይ መምህራንና ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ “በ12ኛ ክፍል ውጤት ተስፋቸውን የተነጠቁ ተማሪዎችና ወላጆች ፍትህ ይሰጣቸው” በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የደቡብ ክልል ወጣቶች ማህበር እና የአማራ ተማሪዎች ማህበር ለመጪው እሁድ፣ መጋቢት 18/2014 ዓ.ም.በመላው የደቡብ ክልል ባሉ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረጉ ተገልጿል፡፡ ለበለጠ መረጃ ቻናላችን ይቀላቀላሉ 👇👇 @kali_tube @kali_tube @kali_tube @kali_tube
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና ሂደት የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን አስታወቀ። የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሉ የተፈጠረውን ከፍተኛ ቅሬታ የሚያጣራ ቡድን ወደ አዲስ አበባ መላኩን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ ቡድኑ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮቸና ባለሙያዎች፣ ከአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፣ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና መምህራን የተውጣጣ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! https://t.me/temhert_bebete https://t.me/temhert_bebete
Show all...
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ጠየቀ። ቢሮው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ በመሆኑ ቢሮው የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል። ለበለጠ መረጃ ቻናላችን ይቀላቀላሉ 👇👇 @kali_tube @kali_tube @kali_tube @kali_tube
Show all...
To all kombolcha institute of technology regular students ===========//========== የ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ1ኛው ወሰነ ትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ከመጋቢት 12-13/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በምዝገባ ጊዜ 1⃣ ኦንላይን ሲስተም ላይ ገብታችሁ የምዝገባ ጥያቄ (request) መላክ 2⃣ ከተመደቡላችሁ አማካሪ (advisor) መምህራን ጋር በአካል በመቅረብ ማረጋገጥ (approved) ማስደረግ 3⃣ ከሬጅስትራር ባለሙያወች ጋ በመቅረብ ጉርድ ፎቶ መስጠትና የድሮውን መታወቂያ ካርድ (ID) መመለስ 4⃣ በተቀጠራችሁበት ሰዓት በመቅረብ ምዝገባ ካካሄዳችሁበት ቢሮ አዲሱን መታወቂያ መውሰድ ⏰ማሳሰቢያ ✅ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች መታወቂያ የምትመልሱት፡ ፎቶ የምትሰጡት እና አዲሱን መታወቂያ የምትወስዱት ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 106 መሆኑን እናሳውቃለን ✅ ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እና ✅ ከምዝገባ በኋላ አዲሱን መታወቂያ ያልያዘ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ To all kombolcha institute of technology regular students ===========//========== የ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ1ኛው ወሰነ ትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ከመጋቢት 12-13/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በምዝገባ ጊዜ 1⃣ ኦንላይን ሲስተም ላይ ገብታችሁ የምዝገባ ጥያቄ (request) መላክ 2⃣ ከተመደቡላችሁ አማካሪ (advisor) መምህራን ጋር በአካል በመቅረብ ማረጋገጥ (approved) ማስደረግ 3⃣ ከሬጅስትራር ባለሙያወች ጋ በመቅረብ ጉርድ ፎቶ መስጠትና የድሮውን መታወቂያ ካርድ (ID) መመለስ 4⃣ በተቀጠራችሁበት ሰዓት በመቅረብ ምዝገባ ካካሄዳችሁበት ቢሮ አዲሱን መታወቂያ መውሰድ ⏰ማሳሰቢያ ✅ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች መታወቂያ የምትመልሱት፡ ፎቶ የምትሰጡት እና አዲሱን መታወቂያ የምትወስዱት ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 106 መሆኑን እናሳውቃለን ✅ ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እና ✅ ከምዝገባ በኋላ አዲሱን መታወቂያ ያልያዘ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ ቻናላችን ይቀላቀላሉ 👇👇 @kali_tube @kali_tube @kali_tube @kali_tube
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" በትምህርት ሚኒስቴር የተቆረጠው ማለፊያ ነጥብ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ እና ችግር ታሳቢ ያላደረገ ነው " - አቶ አለሙ ደባሽ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 229 ተማሪዎች 30 ተማሪዎች ወይም 13 በመቶ ብቻ ማለፋቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቋል። በወረዳው ቤላ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፈተናው ከተቀመጡ 44 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሁለት ተማሪዎች ብቻ ያለፉ ሲሆን ፈተናውን ከወሰዱ 139 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች 28 ተማሪዎች ብቻ አልፈዋል። በተመሳሳይ በወረዳው በመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፈተናው ከተቀመጡ 10 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 36 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምንም ተማሪ ማለፍ አለመቻላቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አለሙ ደባሽ ገልጸዋል። አካባቢው ከአንድ ዓመት በላይ በጦርነት ቀጠና ውስጥ መቆየቱ እና ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ተማሪዎቹ ሙሉ ጊዜያቸውን እና ህይወታቸውን ለጦርነት አሳልፈው በመስጠት ላይ የነበሩ በመሆኑ ለፈተናው ያለበቂ ዝግጅት መቀመጣቸውን ኃላፊው ገልጸዋል። ተማሪዎቹ የነበሩበት ሁኔታ እየታወቀ በትምህርት ሚኒስትር ውሳኔ ካሉበት እና ተፈናቅለው ከተሰደዱበት እንዲመጡ በማድረግ ያለምንም ዝግጅት ለፈተና መቀመጣቸውን ኃላፊው ተናግረዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የተቆረጠው ማለፊያ ነጥብ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ እና ችግር ታሳቢ ያላደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በመሆኑም ሚኒስቴር ለአካባቢው የተወሰነውን የከፍተኛ ትምህርት ማለፊያ ነጥብ #በድጋሜ_በማጤን ማስተካከያ እንዲያደርግ ሲሉ ጠይቀዋል። More : @tikvahuniversity
Show all...
❗️❗️❗️ለትምህርት ሚኒስቴር ከተማሪዎች የተላከ መልዕክት በቻናላችን በኩል እንድናደስላቸው ስለየቁ እንሆ 👇👇👇👇 ትምህርት ሚንስቴር የ 2013/14 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ላይ #በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ ነው የሰራው። 1- ገና ሲጀመር የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና ያለ ምንም #ስርቆት ከተጠናቀቀ ቦሀላ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ማለፊያውን በጣም ዝቅ በማድረግ ወዳቂውን ተማሪ እንደገፍ ማሳለፍ። 2- በ11ኛ ክፍል የት/ት ዘመን 2012 በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ 2ኛው ሴሚስተር #ሳይማሩ ቀርቷል፣ እንዲሁ ተማሪዋቹ ከ8 ወር በላይ ያለ ት/ት ቤታቸው እንዲቀመጡ ተደርጓል። እናም ተማሪዎች በ2013 አ/ም የ11ኛ ክፍልን #ሳይጨርሱ 12ኛ ክፍል እንዲገቡ ተደረገ። 4- ከዛም የመንግስት ት/ት ቤት ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን ሲማሩ ግን እንደድሮው በተከታታይ ቀናት አልነበረም፤ በሳምንት #ሶስት ቀናት ነበር የተማሩት፣ በተመሳሳይ የግል ት/ት ቤቶች ግን #ሙሉ ሳምንቱን አንድም ቀን ሳይዘሉ ነበር ሲያስተምሩ የከረሙት። 5- ይህ ታድያ ለአብዛኞቹ የመንግስት ት/ት ቤቶች መፅሀፍትን ለመጨረስ #በቂ ጊዜ አልነበረም። በግል ት/ት ቤቶች ግን መፅሀፍትን በተያዘላችው ጊዜ መጨረስ ችለዋል። 6- እንዲሁም በ2013 በተቀሰቀሰው ጦርነት፥ በጦርነት አካባቢዎች የነበሩ #ተማሪዎች ለጥናት እና ለመማር ማስተማር አስችጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነበር ያሳለፉት። እንደ ከዚ በፊቱ መንግስት የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት #የኢንትርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ነገር ግን አገልግሎቱ በ #VPN እንዲሰራ ተደርጎ ነበር። ፈተናዎቹ ሲሰጡ በነበረው መጭበርበር ሙሉ በሚባል ደረጃ ፈተናዎቹ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገፃች #ተለቀቁ። ላንብብ ብሎ ደብተሩን የያዘው ተማሪ እንደ ጅል ጥናቱን ትቶ ስልኩን ይዞ የነበረው እንደ ብልህ ነው የታየው። ፈተናዎች በ #Telegram #tiktok... በስርአት በቀይ እስብርቶ መልሳቸው ተከቦበት ነበር የወጡት። ከዚህም ባለፈ ፈተናዎቹ ከባድ ነበሩ የመንግስት ተማሪዎች በፍፁም #ያልተማሯቸው የ 11ኛ ክፍል 2ኛ ሴሚስተር እና እና የ12ኛ ክፍል ጥያቄዎች ተካተውበት ነበር። ታድያ ይህን ሁሉ በመረዳት መንግስት ተማሪዎችን መርዳትና መደገፍ ሲገባው ጭራሽ ማለፊያው ታይቶ #በታሪክ የማይታዋቅ ሆኗል። ከዚህም ይባስ ተብሎ በመጨረሻ ቀን የተሰጠው #የCIVIC ፈተና በቀን ብዛት ወሬው ደርሶት ከተለቀቀው የሰራው ምስኪኑ ተማሪ ስለበዛ #የCIVIC ፈተና እንዳይያዝ ተደረገ። ማለትም ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ #600 እንዲያዝ ፤ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ #500 እንዲያዝ ሆነ። አስተውሉ👇 ማለፊያ ለወንድ በ ተፈጥሮ ሳይንስ #363 ይህ ማለት ፈተናው ከ 700 የሚያዝ ቢሆን ማለፊያ #423 ሊሆን ነው ማለት ነው። ከዚ በፊት የሚታወቀው የግል ሴክተሩ በደንብ እንዲሰራበት ማለፊያ ዝቅ ሲደረግ ነበር ባሁኑ ግን እንዲያውም #300 ሆኗል። #የደሀ ልጅ ጎዳና ላይ ይውደቅ የሚል ውሳኔ ተላልፏል። ከአንድ ት/ት ቤት እንዴት ሁሉም ተማሪ ይወድቃል? በአሁኑ የታየው እንግዲ ይሄው ነው ከአንድ ት/ት ቤት አንድም ሰው ማለፍ ያልቻሉባቸው ብዙ የ መንግስት ት/ት ቤቶች ናቸው። ተማሪ እንዳይማር የሚደረግበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ❗️ት/ት ሚኒስቴር በአስቸኳይ ማስተካከያ ያድርግ #ማለፊያ በደንብ ይቀንስ፣ #ለግል መግቢያም ያስተካክል እናም በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች በደንብ ማስተካከያ ይወሰድ። ለበለጠ መረጃ ቻናላችን ይቀላቀላሉ 👇👇 @kali_tube @kali_tube @kali_tube @kali_tube
Show all...
Repost from N/a
#ፍትህ ለ2013 ዓ.ም 12ኛ መግቢያ ፈተና ተፈትነው ውጤት ለተመለከቱ፣❌❌❌ የዜድሮ ከፍተኛ ትምህርት መከታተያ ተብሎ የተወሰነ ውጤት ፍታው ስላደለ ከያለህበት ሰላማዊ ሰልፍ እንድትወጣ ጥሪ አስተላልፋለሁ ።ፍትህ ለ2013 ዓ.ም 12ኛ ተፈታኞች !!!❎❎
Show all...
Repost from N/a
#ፍትህ ለ2013 ዓ.ም 12ኛ መግቢያ ፈተና ተፈትነው ውጤት ለተመለከቱ፣❌❌❌ የዜድሮ ከፍተኛ ትምህርት መከታተያ ተብሎ የተወሰነ ውጤት ፍታው ስለደለ ከያለህበት ለሰላማዊ ሰልፍ እንድትወጣ ጥሪ አስተላልፋለሁ ።ፍትህ ለ2013 ዓ.ም 12ኛ ተፈታኞች !!!❎❎
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.