cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰበር ዜና ET🇪🇹

መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Akiyas21bot የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Show more
Advertising posts
18 691
Subscribers
-424 hours
-327 days
-10730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የመአድን ቁፋሮዉ ዳግም ተጀምሯል፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ አለኋት ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውሀ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት በቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸን ሰዎች ህይወት ለማዳን ሲደረግ የነበረው ጥረት በመቋረጡ የተጎጂ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ ለቅሶ መቀመጣቸዉ የሚታወስ ነው፡፡ የአካባቢው ማሕበረሰብም ተስፋ በመቁረጥና እርሙን በማውጣት ወደ መደበኛው የኦፓል ማዕድን የማውጣት ስራ የተሰማሩ መሆኑን የገለጹት የደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የማዕድን ስራዎች ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር ቡድን መሪ አቶ በሪሁን አበረ ናቸው፡፡ አሐዱም የአካባቢው ማሕበረሰብ ከተፈጠረው አደጋ ለምን መማር አልቻለም ማዕድኑንስ ለማውጣት ከበፊቱ በተለየ የሚጠቀሙበት የተሻለ መሳሪያ አለ ወይ ሲል አሀዱ ጠይቋል፡፡ ኃላፊውም የአካባቢው ማሕበረሰብ ኑሮውን የሚያስተዳድረው የኦፓል ማዕድን በማውጣት በመሆኑ ያለ ምንም መሳሪያ ቀደም ሲል በነበረው በባህላዊ መንገድ ስራቸውን የሚያከናውኑ መሆኑን አንስተዋል፡፡ (አሀዱ ሬዲዬ) ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 6🤔 2
በ19 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ በኮንሶ፣ኩሱሜ እና ደራሼ ብሔረሰቦች መካከል ግጭት በማስነሳት ከ11 ሺህ በላይ ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ እንዲሁም የሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ ያደረጉ ተከሳሾች በ19 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ። በጽኑ እስራት እንዲቀጡ የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አርባ ምንጭና አካባቢው ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የፌዴራል የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በሰባት ግለሰቦች ላይ ተደራራቢ ክስ አቅርቦ ነበር። ክሱ ቀርቦባቸው የነበሩ 1ኛ አበበ አያኖ፣2ኛ  ከበደ አርሳይዶ፣ 3ኛ ግርማ ባንሶ፣ 4ኛ በቀለ ባልቻ፣ 5ኛ አባተ ዱቡ፣ 6ኛ ታምሩ ዳጋቴ እና 7ኛ ወገኔ ጋሃኖ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው። ቀርቦባቸው በነበረው አንደኛው ክስ ተከሳሾቹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነበር። በዚህም ተከሳሾቹ ለጊዜው እጃቸው ካልተያዙ ግብረ-አበሮቻቸው ጋር በመሆን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረውን የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ ጋር በተገናኘ መነሻ በማድረግ በኮንሶ፣ኩሱሜና ደራሼ ብሔረሰብ መካከል ለግጭት በማነሳሳትና በመቀስቀስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸው በክስ ዝርዝሩ ተጠቅሷል። በተለይም በየካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 አካባቢ በደራሼ ልዩ ወረዳ፣ጋቶ ቀበሌ፣በኮንዞ ዞን ሰገንና ካራት ዙሪያ ወረዳ፣ገርጩና አይሎታ ደከቱ ቀበሌዎች መካከል የሚገኝ ቱርባ ኮልባ አልባጮ የተባለ ለም የእርሻ ማሳዎች መነሻ አድርገው ባስነሱት የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ በመሳተፍ መንደር ሁለት ወደ ሚባል አካባቢና ወደ ሌሎች የገጠር አካባቢዎች የእርስ በርስ ግጭቱን ማስፋፋታቸውን ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አስፍሯል። ባስነሱት ግጭት በመሳተፍ ከሚያዚያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ገጀራ፣ቆንጨራ እና የተለያዩ የጦር መመሪያዎ ችን በመያዝ የጋቶ ቀበሌና የሌሎች ነዋሪ የነበሩ 10 ሰዎች ላይ ጥቃት በመክፈትና ሕይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡ በዚህም 864 ሚሊየን 142 ሺህ 575 ብር ከ 57 ሳንቲም የሚገመቱ የመንግስት፣የህዝብና የግለሰብ ንብረቶች ላይ ጉዳት በማድረስና 11 ሺህ 624 ሰዎችን ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸው ተጠቅሶ በዝርዝር ክሱ ላይ ተመላክቷል። ዐቃቤ ሕግ  በሌላኛው ክሱ ደግሞ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በሚያዚያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም  ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ  በጋቶ ቀበሌ መንደር 1 ጤና ጣቢያ አካባቢ ይዘውት በሚንቀሳቀሱት የጦር መሳሪያ ተጠቅመው የጋቶ ቀበሌ ቀጠና 9 አመራር የነበረ አስማረ ዳጉ የተባለ ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ  ሕይወቱ እንዲያልፍ  ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡ እንዲሁም በደራሼ በመንደር አንድና በመንደር ሁለት ተከስቶ የነበረ የእርስ በርስ ግጭትን ቅራኔ የነበራቸው ነዋሪዎችን በሚያዝያ 2 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገ የእርቅ ሥነ-ስርዓት ላይ ሽማግሌ ሆኖ በማስታረቅ ሚና የነበረው ወንጃላ ከፒኖ  የተባለ ግለሰብን ለምን ዕርቅ እንዲፈጸም አደረክ በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱ እንዲያልፍ ማድረጋቸውን ተጠቅሶ በግድያ ወንጀል ተከሰዋል። ተከሳሾቹ ክሱ ከደረሳቸውና በችሎት በንባብ ከተሰማ በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምንም በማለት የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ከ10 በላይ  የሰው ምስክሮች በችሎት አቅርቦ አሰምቷል፡፡ ተዘዋዋሪ ችሎቱ በተከሳሾች ላይ የተሰሙ የምስክሮችን ቃል እና ተያያዥ የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ  በክሱ ዝርዝር ላይ የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጡን ጠቅሶ ተከሳሾቹ  እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል። በተሰጠው ብይን መሰረት ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክሮችን ያቀረቡ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን ግን በተገቢው መከላከል አለመቻላቸው ተገልጾ አምስት ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል። ከእነዚህ ተከሳሾች ጋር አብረው ተካተው የነበሩ 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ፍርድ ቤቱ የቀረበባቸውን ክስ በተገቢው የተከላከሉ መሆኑን ገልጾ በነጻ አሰናብቷቸዋል። ከዚህም በኋላ ተዘዋዋሪ ችሎቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን በመያዝ ጥፋተኛ የተባሉትን ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። (Via FBC/ታሪክ አዱኛ) @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 10
ብሔራዊ ሎተሪ የትንሳኤ ሎተሪ ትናንት ምሽት መውጣቱን እወቁልኝ ብሏል።ማውጫው ከላይ ተያይዟል። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 15 1
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።መልካም በዓል‼ ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 10 5🙏 2😍 2
በ #አማራ ክልል የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 2.5 ሚሊዮን ማሻቀቡ ተገለፀ‼️ በአማራ ክልል በድርቅና በተለያዩ የፀጥታ ችግሮች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 2 ሚሊዮን 500 ሺህ ማደጉን የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ። መንግስት ለእነዚህ ወገኖች በየወሩ 2 ቢሊዮን 2 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግም ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን፣ ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል እንደሚሉት የአማራ ክልል በ2016 ዓ.ም  ሦስት ዋና ዋና ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ “... አንደኛው በክልሉ ያለው ግጭት ነው፣ የሰዎችን እንቅስቃሴ በመገደቡ ምክንት ግብዓትና የምግብ እህል በወቅቱ እየቀረበ አይደለም፣ የቀን ሰራተኛው ሰርቶ እየበላ አይደለም፣ አርሶ አደሩ የምርት ስራውን በተሟላ መንገድ እየሰራ አይደለም፣” ብለዋል፡፡ ሁለተኛው እንደችግር የሚወሰደው ደግሞ እንደ ኮሚሽነሩ፣ የዝናብ እጥረቱን ተከትሎ በክልሉ ያጋጠመው ድርቅ ነው፡፡ “ ሶስተኛው እንደ ችግር የሚወሰደው በተለያዩ አካባቢዎች በተነሱ ግጭቶች ክልሉ በርካታ በርካታ ተፈናቃዮችን መቀበሉ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ በዚህ ዓመት በአማራ ክልል የተከሰተው ድርቅ ሰፊ ቦታ የሸፈነ ሲሆን 1 ሚሊዮን 850 ሺህ ያህል ወገኖችን የእርዳታ እህል ጠባቂ አድርጓቸዋል ብለዋል ኮሚሽነር ተስፋው፡፡ ኮሚሽነር ተስፋው ትናንት በሰጡት መግለጫ በዚህ ዓመት የተከሰተው ድርቅ በአማራ ክልል በዘጠን ዞኖች፣በ43 ወረዳዎች፣ በ429 ቀበሌዎች የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን 846 ሺህ 955 ሰዎች የድርቁ ቀጥተኛ ተጠቂ ሆነዋል ማለታቸውን ዶቸ ቨለ ዘግቧል፡፡ ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 13💯 2 1
የትግራይ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ‼️ ለሶስት አመታት ከስራ ውጪ ተንሳፈው የቆዩት የትግራይ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ተሰምቷል። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 6
በአዲስ አበባ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መፀዳጃ  ቤት ውስጥ እርድ ሲከናወን ተገኘ‼️ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ከወረዳ እስከ ማዕከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ከ805 በላይ የሚሆኑ ተቋማት ላይ የቁጥጥር ስር መስራቱን አስታውቋል።በዚህም ባለስልጣኑ ባከናወነው የቁጥጥር ስራ ለ251 ተቋማት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ሶስት ድርጅቶችን ማሸጉን አስታውቋል። ከታሸጉት  ተቋማት ውስጥ አንዱ  በፆም ወቅት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ህግ እና ደንብ በማይፈቅድ መልኩ መፀዳጃ ቤት ውስጥ በግ እና ፍየል እርድ ሲያከናውን መያዙ ተገልፆል፡፡ በተጨማሪም የባለስልጣኑ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው ፅዳቱን ያልጠበቀ ዶሮዎች ለሱፐርማኬት ሲያከፋፍሉ የተገኙ የስጋ ማቀናባበሪያ እና ሱፐር ማርኬት መታሸጋቸው ተገልፆል፡፡ በፍተሻው የተገኙት ምርቶች በአጠቃላይ የተወገዱ ሲሆን በኮልፌ፣በለሚ ኩራ እና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ናቸው፡፡ በቀጣይ ቀናቶች የበዓል ወቅት በመሆኑ  ህብረተሰቡ ህገ ወጥ እርድ የሚያከናውኑ ተቆማቶች በሚመለከትበት ጊዜ በነፃ የስልክ መስመር 8864 ላይ በመደወል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ እንዳለበት የባለስልጣኑ የምግብና የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው  ተናግረዋል። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 9
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ‼️ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሲከናወን ቆይቷል። ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከ28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መራዘሙ ተነግሯል። ተጫራቾች ፦ - የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ - ሲፒኦ፣ - የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ - ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ - ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉ እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ተብሏል። ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ  እንደሚከፈት ተገልጿል። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 7 1
ለኢትዮጵያ ኢምግሬሽን አገልግሎት❗👇 በሰመራ እንዲሁም በጋምቤላ የሚገኙ የኢምግሬሽን ሰራተኞች ቢፈተሹ መልካም ነው። ከሁለቱም ቦታዎች በርካታ ጥቆማዎች ደርሰውኛል። ሰመራ ኢምግሬሽን ያለ ገንዘብ አይሰሩም፣ከዚህ አልፎም ውስጥ ላይ በደላሎች ተሞልቷል ብለዋል። ጋምቤላ ሰራተኞቹ ጭራሽ አይገቡም ብለዋል። በርካታ ህዝብ እየተጉላላ ስለሆነ አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 2
የተሻለ ወርሀዊ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው? ሲሸልስ ሊቢያ እና ሞሮኮ በአንጻራዊነት የተሸለ ደመወዝ የሚከፍልባቸው ሀገራት ናቸው። 👉በኢትዮጵያ አማካኝ ወርሃዊ ደመወዝ 150 ዶላር ነው። የተሻለ ወርሀዊ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው? የዓለም ላብ አደሮች ወይም ሰራተኞች ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 23 ቀን የሚከበር ሲሆን የዘንድሮውም በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ዓለም አቀፉ የስታትስቲካ ጥናት ከሆነ በአፍሪካ ሲሸልስ ሊቢያ እና ሞሮኮ በአንጻራዊነት የተሻለ ደመወዝ የሚከፍሉ ሀገራት ናቸው፡፡ በሲሸልስ አንድ ሰራተኛ በአማካኝ በወር 432 ዶላር ደመወዝ ሲከፈል በሊቢያ 322 ዶላር እንዲሁም በሞሮኮ ደግሞ 281 ዶላር ይከፈላል፡፡ ሌላኛዋ አፍሪካዊት የተሻለ ደመወዝ ከፋይ ሀገር ጋቦን ስትሆን 256 ዶላር በወር ለአንድ ሰራተኛ ስትከፍል ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሪሺየስ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ 200 ዶላር እና ከዛ በላይ የሆነ ገንዘብ ለሰራተኞቿ ትከፍላለች ተብሏል፡፡ እንደ ወርልድ ሳላሪ ድረገጽ መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ አንድ ሰራተኛ በአማካኝ 150 ዶላር የሚከፈለው ሲሆን በዓመት ደግሞ 1 ሺህ 800 ዶላር ይከፈላቸዋል፡፡ የመንግስት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የደመወዝ አከፋፈል ስርዓቶችን እና ጥናቶችን ዋቢ አድርጎ መረጃ መሰብሰቡን የገለጸው ወርልድ ሳላሪ ድረገጽ በኢትዮጵያ ከ2 ሺህ ብር ጀምሮ እስከ 470 ሺህ ብር ድረስ ወርሀዊ ደመወዝ ይከፈላል ብሏል፡፡ ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት     👉 @Akiyas21bot    @ET_SEBER_ZENA @ET_SEBER_ZENA
Show all...
👍 11