en
Feedback
Joseph Math Tutor

Joseph Math Tutor

Open in Telegram

Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/D8K0MVqynVA?si=y_uFeHG7awC1oX9Y Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580

Show more
1 857
Subscribers
No data24 hours
+57 days
+2130 days
Posts Archive
ስለ እያንዳንዱ ኮርስ detail ማብራሪያ ይዤላችሁ እየመጣሁ ነው ... 🥰 .

📌 ወደ ካምፓስ ስንሔድ ምን ምን ነገሮችን ይዘን መሔድ አለብን❓ 👉 ከበሶ እስከ ዳቦቆሎ 👉 ከለውዝ ቅቤ እስከ ማርማራታ 👉 ከሻንጣ እስከ ፒኪኒ ቢኒያም ከፋለ(ዞግ) አስፈላጊ የሚባሉ ሸመታዎችን እንደሚከተለው አቅርቦላችሗል። ሰላም ውዶቼ እንደምን አላችሁ ❓ 📚 እስቲ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ካንፓስ ሲገቡ መያዝ ያለባቸው ነገሮች እንመልከት ፦    📌 በምግብ ዘርፍ ፦ 📚 እናትህ በር አንኳኩታ ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ልጄ ቁርስ ደርሷል ብላ መጥራት ወፍ በቃ ቀርቷል ። አሁን ጠዋት 1:30 ተነስተህ ለሻይ እና ዳቦ መሰለፍ አለብህ በቀን 3 ካልተሰለፍክ ዶርም ድረስ በሰሃን አይቀርብልህም መቼስ ደሞም እንደማሚ WOW የሚያስብል ግሪስ እንዳይመስል.... ናላ የሚያዞር ፈውስ ነው ሚቀርብልህ... ኮብል ከምስር ጋር ፥ ሽሎ ያለ ዘይት  ፤ ስጋ ወጥ ያለ ስጋ ለመብላት ነው ተሰልፈህ የምትውለው ። አስበው በዛ ላይ ችከላ አለ ይሞረሙረሃል ከዛ እናትህ ትናፍቅሃለች ታዲያ በበሶ ካልሆነ በምንም አታገኛትም ። በሶ ሆድ ብቻ መሙላት አይደለም ናፍቆት ማረሳሻም ነች ። ብትወድም ባትወድም በሶ ያዝ ፤ ኩኪስ ፤ ዳቦቆሎ ፤ የመሳሰሉ በባህላቹ ያሉ ደረቅ የስንቅ ምግቦች በደንብ ያዙ ታመሰግነኛለህ ። 💡 በሶ 💬 በሶ ብትወድም ባትወድም ጥቂትም ቢሆን ያዝ መበጥበጡ ልሹ LIFE አለው ፤ ለአንድ ሴሚስተር ከ2-5 ኪሎ በቂ ነው ብዬ አስባለሁ ፍሬሽ ስትሆኑ ግን የካፌ ምግብ ስለማይስማማቹ እስከ 6 አርጋቹሁ ያዙ ። በሶ ስትይዙ ከቻላቹሁ በማሸጊያ ፌስታል አሽጋችሁ ብትይዙ ለመያዝም ያመቻቹሃል ለሙዱም አሪፍ ነው ። 💡 ኩኪሲ ፡ 📚እኔ ኩኪሲ በጣም ነው የምወደው ስለዚህ በኩንታል ልይዝ አስቢያለሁ  እና በሶ ለማትወዱ አሪፍ መፍትኤ ነው ከ2-3 ኪሎ ለሴሚስተር ብትይዙ በጣም አሪፍ ነው ። ኩኩሲ ነፍስ የሆነ ነገር ነው ኩኩሲ በበሶ አስባቹሁታል ። ግን እመኑኝ ካልቆጠባቹሁ የዶርም ጀመኣ 3 ቀን አያቆያትም እና ስንቅ መሆኑን አስባቹሁ ቢያንስ ሁለት ወር ማስቀመጥ ይኖርባቹሃል ። አገኘው ብላቹሁ ጨርግዳቹ ጨርግዳቹ በሳምንት ጨርሳቹሁ ጨላ ሲነጥፍ በኃላ ጉድ እንዳትሆኑ እንደውም ገንዘብ እስኪጠር ኩኩሷን አትንኳት ከነካቹሁም በቁጠባ ። 💡 ዳቦቆሎ ፦ 💬 ይቺም በጣም አሪፍ ነገር ናት እስከ 2 ኪሎ ብትይዙ አትጎዱም ።  ስትተክዙ ማታከዣ ስትቸክሉ ማቻከያ ትሆናለች ። ዳቦ ቆሎም መቆጠብ አለበት እና ለቁጠባ አሪፉ መንገድ ማሸግ ነው ። 2 ኪሎው ዳቦቆሎ 3 እሽግ ፌስታል ቢወጣው አንድ እሽግ በወር የሚል ዕቅድ ይዛቹሁ መቆጠብ ትችላላቹሁ ። 💡 የለውዝ ቅቤ ፤ ማር ፤ ማርማራታ ፤ የመሳሰሉ የሚቀቡ ምግቦችም ፦ 💬 ማር ካልሆነ አብዛኞቹ በከተማ ስለምታገኙ እዛው የዳቦ ዋጋ አጣርታችሁ የማይጎዳ ከሆነ ሸመትመት ማረግ ትችላላችሁ ነገር ግን የማር ሀገር የምትኖሩ ከሆነ በደንብ ያዙ ትፈወሳላችሁ እመኑኝ በተረፈ በቃ (ማር ሀገራቹሁ ምርጥዬ ከሆነ ይዛቹሁ ኑ ሌሎቹን ከመጣቹሁ ወዲህ በተመደባችሁበት መግዛት ትችላላቹሁ) ደሞ አንዳንድ ግቢ ፍራፍሬ በጣም  ርካሽ ነው በተለይ ወደ ደቡብ ታዲያ ደቡቦች ለምግብ እንዳታስቡ ያረጋቹሃል ። ያው የጠገበ ስለትምህርቱ ስለማያስብ አትጎዱ እንጂ ሰርክ ሀሳባቹሁ ፈውስ መሆን የለበትም ተመርቋቹሁ ሾል ስትይዙ ታማርጣለቹሁ ለግዜው ያገኛቹሁትን ጠርጋቹሁ በደንብ ቸክላቹሁ በአሪፍ ግሬድ መመረቅ አስቡ ። ደሞ ክረምት ነው በቆሎም አለ ትግጣላችሁ ..... 💬 ምግብ እንደሙዳችሁ የሚመቻችሁን እና በየሀገራችሁ ለስንቅ የሚዘጋጁ ነገሮችን ያዙ ( ግቢ መግባት የሚችሉትን ) ሽንብራም ፤ በሶም ፤ ማርም ብቻ ይሆናል ያላችሁትን እና የሚሞዳችሁን ፈውስ ያዙ ። 📌 በቁሳቁስ ዘርፍ ፦ 💡 ሻንጣ ፦ 📚 ብዙዎች ቀለል ብለው መግባት ይሞዳቸዋል ፥ አንዳንዶች ደሞ እንደ ሰርግ ካልታጀብን ይላሉ ብዙዎቻችሁ መረዳት ያለባችሁ ነገር ግቢ ስትገቡ የምትገቡ እናንተ እንደሞዳችሁ እና እንደአቅማችሁ ፥ እንደ አስተሳሰባችሁ እና ፍላጎቶቻችሁ እንጂ ሾለ ሰዎች አትጨናነቁ እነሱ የራሳችሁ ቢዝነስ ይወርኩ ። እናንተ በራሳችሁ የሚሞዳችሁን እና የሚያስፈልጋችሁ ነገር አድርጉ ። 💬 ጀለስ 4 ግብዳ ሻንጣ ተሸክሞ ግቢ ስለሚቆሰው እኔም የሚል ፎክክር ትታችሁ ምንድነው ሚያስፈልገኝ ❓አቅሜ የቱ ያክል ነው ❓በሉ  ቤተሰብ አታስቸግሩ ከሌሎች እኩል ለመሆን በሚል የFamily ኑሮ አታናጉ ። እናም እንደሙዳቹሁ ተራመዱ ። 📚 ሻንጣ (እንደኔ) አንድ በጀርባ የሚነገት Bag ብትገዙ ( ከሌላችሁ ካላችሁ ግልግል ) እና ሌላ ትንሽዬ (የምትጎተተዋ)  ብርድልብስ እና የመሳሰሉ ትልልቅ ነገሮች የምትይዙበት ሻንጣ ቢኖራችሁ አሪፍ ነው ። 💬 ለበዓል እና ለዕረፍት ወደ ቤተሰብ ስትመጡ ለቀናት የሚሆን ልብሳችሁን በጀርባ ሚነገተው Bag ትይዛላችሁ የተቀሩትን ደሞ በቀረችው ቦርሳ ግቢ ታስቀምጣላችሁ ( ሙሉ ዕቃ በየግዜው ስለማታንኳትቱ ማለት ነው) ነገር ግን እንደ ግቢው ርቀት ፥ እንደ እናንተ የሸመታ ብዛት ፥ እንደ ያዛችሁተ ዕቃ ነው የሚወሰነው  ስለዚህ በፍላጎታችሁ መሰረት ብትይዙ መልካም ነው ። 🎗በተረፈ እንደኔ ከቻላችሁ ለክላስ የምትሆን አነስ ያለች 250 -300 ብር የምትገዛውን Bag እዛው ግቢ ብትገዙ አሪፍ ነው ( በፊት ካላችሁም ስትመጡ ዕቃ ነገር ያዙባት እና በዛው ትማሩባታላችሁ ። ) 📌 የልብስ ሸመታ ፦ 📚 ይሄም የሚወሰነው እንደደረሳችሁ ግቢ የአየር ንብረት እና የእናንተ ሙድ ነው ፤ መቼስ ሰመል ደርሶህ መርጦ ሳትይዝ አትሄድም ፤ መቼስ ደብረብርሃን ደርሶህ  ከጋቢ ማይተናነስ ጃኬት መያዝ አትረሳም ፤ ብቻ እንደግቢው እና ሙዳችሁ እና አቅማችሁ ይወሰናል ፤ ፋሽን ተከታይ ናችሁ ❓ዘናጭ ናችሁ❓  ደሃ ናችሁ  ❓ቀለል ያለ አለባበስ ይመቻቹሃል ወይስ ቂቅ ካካለችሁ ይጨንቃቹሃል ብቻ ሙዳችሁ ምንድነው ብላችሁ " እንደ ሙዴ " ብሎ መቀወጥ ነው ። ምን ያክል ልብስ ልያዝ ምናምን ለምትሉ  (በግሌ)  💡 ለወንዶች ፦ 📚 3-5 ሹሪ እና 1ቱታ  ፤ 1 ቁንጣ ፤ 2-3 ቲሸርት ፤ 2-3 ሸሚዝ ፤ 1-2 ጃኬት ፤ 6-8 ካልሲ ፤ 3-5 ፓንት ፤ 2-3 ሽፍን ጫማ + 1 ነጠላ ጫማ ፤ 1-2 ቀበቶ ፤ የረሳሁት ነገር ካለ እጨምራለሁ ። 💡ለሴቶች ፦ 📚 ሴቶች ግቢ ሲገቡ በጣም ግብዳ ሻንጣ ሲሸክፉ ሁሌ እመለከታለሁ ብዙ ግዜ በምንድነው የሚሞሉት ብዬ ጠይቄ መልሱ አላገኘሁም ። ለማንኛውም ሴቶችዬ የእናንተ አለባበስ ወዲ በሉት ወዲ ለማለት ትንሽ ይከብዳል ። ብቻ ከታይት እስከ ጉርድ እንዳሻችሁ እና እንደፍላጎቶቻችሁ ሸምቱ (ሂጃብ እና ነጠላውም እንዳይረሳ እህትአለም)  እንደምክር Body ነገር በርከትከት አርጋችሁ ያዙ እኔ ነኝ ያልኳቹሁ ታተርፋላችሁ ።በተረፈ በንፅህና ስለማትታሙ ካልሲ እና ፓንት በርከት አርጎ የመያዝ ግዴታ የለባችሁ (ጭብጨባ ለሴቶች )

📢 የካንፓስ የመጀመርያ አመት ቆይታ ......በትንሹ ❓ 📚 ፍሬሽማን መሆን እንደእናንተ ስብዕና ይወሰናል ። የተለያየ ሰው የተለያየ experience ነው ያለው ። ግን ብዙዎች ጋር የሚኖረውን የፍሬሾች የጋራ ኑሮ ቆንፅለን ለማየት እንጥራለን ...! 💡 ናፍቆት .....! 📚 አንዳንድ ከቤታቸው ሱቅ ለመላክ ካልሆነ ወጥተው የማያቁ ልጆች ድንገት ከቤተሰብ ሲርቁ ምናምን አይችሉም ይነፋረቃሉ ...ከሰው ጋር የማይግባቡ ዝጋታም ልጆች ስላሉ እነሱም ... ለብቸኝነት ሲጋለጡ ሊከብዳቸው ይችላል ። አንድ ነገር እወቁ ከምትወዷቸው ሰዎች መለየት ይሄ የመጀመርያቹ ሊሆን ይችላል ግን ብርቅ አይደለም ...አቅፎ የሚያስተዛዝን ፤ ህመምን የሚጋራ ደስታን የሚካፈል ጓደኛ ቤተሰብ ወዳጅ መለየት በጣም ከባድ ነገር ነው ። ግን ቻሉት በህይወታችሁ ነፍ ግዜ ከምትወዷቸው የህይወት አጋጣሚ ይለያቹሃል ። ካንፓስም የምታገኟቸው ልጆች ከአመታት ውብ የጓደኝነት ቆይታ በኃላ ትለያያላችሁ ። ናፍቆት ያለ ነው ግን መቻል ነው ። በካንፓስ ጥሩ ጓደኛ ያዙ ...እስክትለምዱት ነው ። ከዛ ይለቃቹሃል ። 💡 ምግብ ....! 📚 እንደ እናትህ ውይ ልጄ ተነስ ቁርስ ብላ ና ትተኛለህ  አቡኪያዬ ...ምናምን የለም በጠዋት ተነስተህ ሰልፍ ካልወጣህ ሲሞረሙር ይውላል ካፌ ሊያልቅም ይችላል ....ሻይ በዳቦ ለመብላት ይሄ ያክል ሰልፍ ልትልም ትችላለህ ግን በመክሰስ ሰዓት 12 ስለሆነ ራት የሚገረሰው ችከላ ካደርክ ይሞረሙራል...ዳቦ ልሹ ስንት ጣዕሙ ..ከረሃብ ይሻላል ። ሩዝ ፤ ፍርፍር ...ስላለ አትቸጋገር ....ግን ጥሩ ነገር መብላት የለመደ ሰው....ወይኔ ግቢው ጥሩ ባልቴት  የሌለው ይመስል ..ጥቅል ጎመን ብለው ቀጭን ሾርባ ጎመን ጣል ጣል ያለበት ሊያቀርቡ ይችላሉ ...ታዲያ አሪፍ ነገር የለመደ አይችልም 500 ብር አከባቢ ይገጨውና ውጪ ይበላል .... ምግቡ እንደ ካንፓሱ ነው  በተለይ በቅርቡ የተከፈቱ አርሲ ፤ ቦንጋ ምናምን ምንም አይልም ባህርዳርም አሪፍ ነው ። ሃሮማያማ በሳምንት አራቴ ነው ስጋ የምትግጡት ...ብቻ ብዙ ልጆች የጣፈጠ ነገር ለምደው እነደ ነገሩ የሚሰራው ምግብ አይጥማቸውም ። 💡 ጓደኛ መረጣ ...! "ጓደኛ መረጣ ላይ መጠንቀቅ አለባችሁ ። በጣም መጥፎ ሰዎችም ጥሩ ልጆችም ይኖራሉ ። ከሱሰኛ ፤ ጨባሽ ፤ ዘረኛ ..ራቁ..በቢሊዮን ማይል ራቁ ...ከእናንተ ጋር የሚሄድ ሰው ፈልጋችሁ ከዶርም ውስጥ አንድ የልብ ጓደኛ በቂ ነው ። ታዲያ ምንም መጥፍ ባህሪይ ቢኖርባቸው ከዶርም ልጅ አትጣሉ ...ትቸገራላችሁ ተንከባክባችሁ ....ተከባብራችሁ በፍቅር አርጉት ...ጓደኛ ምርጫችሁን ተጠንቀቁ ዝም ብሎ ሲያነብ የሚውል የሚተሽንም ሰው አትጠጉ በቃ አራዳ ሆናችሁ ማንበብ ሲኖርበት የሚያነብ ፈታ ግድ ሲል የሚፍታታ ነገሮች የሚገቡ ምርጥዬ ሰው ፈልጉ ። 💡 ሹሾ.... 📚 በዙ ሰዎች ካንፓስ በጓደኛ ምክንያት ያልሆነ ነገር ውስጥ ይገባሉ ይሄ መሆን የለበትም ...ምንም ቢሆን ሹሾ አለም እንዳትገቡ ...ያለባችሁ ችግር ይበቃል ... አንዳንዴ ግዜ ሊተርፋችሁ የምትሰሩት ታጡም ይሆናል ...ሹሾ ከምትገቡ አንዷን/ዱን ጠብሳቹሁ ተጃጃሉ እሱ ይሻላል ... ጭራሽ ሹሰ ውስጥ ራሳችሁን እንዳታገኙ በርቱ ....! 💡 መወዛገብ ......! 📚 ከጠበቃችሁ በጣም የተለየ ነገር ሊገጥማችሁ ይችላል ....ያኔ ውዝግብግብ የተለመደ ነው ።ተሳስታችሁ የሰው ዶርም ከች ትሉም ይሆናል ።ብዙ ግዜ ልጆች እስኪለምዱ ድረስ እንዳይጠፋባቸው አንዴ ባዮት መንገድ ብቻ ነው የሚጓዙት ....ሌላ አጭር መንገድ ቢኖርም አይሄዱም በረጅመ ይሄዳሉ የፍሬሽ ነገር የተለመደ ነው ። በቃ በየስርቻው ሲዋሰቡ ፤ ትምህርት ብሎ መጥቶ አባቱን በሬ አሽጦ ፤ እናቱን ፆም አሳድሮ እሱ ጫት ቤት ፤ ቅምቀማ ስታዮት (2 or 3 ተማሪ እንዳይመስሏቹሁ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ተማሪ  .)...በቃ ላይብረሪው ውስጥ 3 ሰው ብቻ ስታዮ ....ትደነግጣላችሁ ወይኔ ካንፓስ ልትሉም ትችላላችሁ ...!ለምግብ ሰልፍ ስታዮ ..ዋይፋይ ሰዎች ለሊት ሙሉ ሲጠቀሙ ስታዮ....በቃ ትወዛገባላችሁ ...ትምህርት ቤት ያላችሁ መሆኑ ትዝ የሚላችሁ ...የፈተና ሰሞን ነው ላይብረሪ 3 የነበረው ሰው መቀመጫ አጥቶ አንድ ወንበር  ለሁለት ተቀምጦ ስታዮ ...ዶርም አዳር ሲቸከል ስታዮ ይገባቹሃል ። 💡 የአስተማመር አይነት ....!. 📚 እንደ Highschol 40 ደቂቃ ሳይሆን 3 ሰዓት ሙሉ አንድ ሳብጀክት ትዳረቃላችሁ .....እሱም ደህና መመህር ካጋጠማችሁ ነው የሚገባችሁ ።  በቃሉ እየተጀነነ ሲያወራ የሚውል.... ኖት የሚቸከችክ  ...ደብተር ሁላ የሚያርም አለ ። የለመዳችሁት አይነት ...የመማር ማስተማር ሂደት ሲቀየር አትደናገጡ እንደ አየሩ መሆን ነው ። እስከትለምዱት ነው ። 💡 ሙድ መያዝ .....❗️ 📚 ፍሬሾች ገና ከመግባታችሁ ...የሲኒየሪዎች ነቆራ አይጣል በቃ ምንም ስለማታውቁ ...የማይሆን ነገር ሊነግራቹሁ ይችላል የመመዝገቢያ ቦታ ጠይቃችሁ ሽንት ቤት ሊሊሉካችሁ ይችላሉ ። ግን አይደብራችሁ እናንተም በተራቹሁ አየር ስለምትይዙ ....ፈታ በሉበት እስክትለምዱ አየር አታብዙ አትኳትኑ ልጎብኝ እያላችሁ አታካሉ ወሬ ሰብስቡ መጀመርያ ። የመጀመርያ ምግብ ካፌ ማሰታወሻ ፎቶ አንሱት ። 📚 ሁሉንም አውርተን አንጨርሰውም ....በቃ የቀረ ካለ ግቢ ታዮታላችሁ ፥ ብዙ አትጨናነቁ እኛም አለን አዳዲስ ነገር እንነግራቹሃለን ። አይዞን!

#ASTU #PC 💻 PC ይዛችሁ ብትመጡ ጥሩ ነው። Python Course ያለ PC አስቸጋሪ ነው። በተጨማሪም ደግሞ አብዛኞቹን አሳይመንቶች በኮምፒውተር ጽፋችሁ ፕሪንት አድርጋችሁ አስጠርዛችሁ ስለሆነ የምትሰጡት PC ከሌለ ይከብዳል። ይዘረፋል ይባላል ፤ ዋናው የእናንተ ጥንቃቄ ነው። ካፌ ስትሄዱ ፣ ክላስ ስትገቡ እናም ሌላም ጊዜ ይዛችሁ መዞር ግድ ነው።

Fast track ASTU ላይ ብቻ ነው ያለው።     ሌላው ደግሞ ነጥብ አያያዝ ላይ ASTU ከ100 ከ39 በታች ካመጣችሁ ነው F (0) የሚሆነው AASTU ላይ ግን ከ50 በታች ካመጣችሁ F ነው🤯

#ASTU 📚 College of Electrical Engineering and Computing (#CoEEC) #Departments                            #Years 1. Computer Science                      5      and Engineering 2. Electronics and                           5     communication     engineering 3. Software Engineering                5 4. Electrical power and control engineering                       5

📚 College of Mechanical, Chemical and Material Engineering (#CoMCME) #Departments                      #Years 1. Chemical Engineering          5 2. Material Science and            5     engineering 3. Mechanical Engineering      5

ከ Freshman ጋር ነው 5 የሚሆነው

#ASTU 📚 College of Civil Engineering and Architecture (#CoCEA) #Departments                      #Years    1. Architecture                           5 2. Civil Engineering                   5 3. Water Resource                     5      Engineering

📚 College of Applied Natural Science (#CoANS) #Departments                       #Years 1. Applied Biology                       4 2. Applied Chemistry                  4 3. Applied Geology                      4 4. Applied Mathematics             4 5. Applied Physics                       4 6. Industrial Chemistry               4 7. Pharmacy                                 5

#ASTU #ለምትገቡ #ተማሪዎች 📚 አንድ surprise አለ Engineering ለምትገቡ የአምስት ዓመቱን ትምህርት በአራት አመት የመማር ዕድል ሊያጋጥማቹህ ይችላል ግን በጣም ትልቅ ጥረት ያስፈልጋል (ፈተና አለው)  ለApplied science ተማሪዎችም የአራት ዓመቱን ትምህርት በሶስት ዓመት ማጠናቀቅ የሚችሉበት መንገድ በተመሳሳይ መልኩ ማለትም በቅድመ ፈተና ተፈትነው በማለፍ ብቻ ✅Fast track✅ pre  Engineering ሳይማሩ መመረቅ ይችላል።         ፈተናው ምን ምን ይይዛል❓  ፈተናው 3 ብቻ ነው።      Mathematics      Chemistry      Physics ፈተናው ይከብዳል? አዎ በጣም ይከብዳል የማይካድ ሐቅ ነው እስከዛሬ ከተፈተኑት ያለፉት 10 አይሆኑም🤭      Mathematics ላይ የሚመጡ   1. Limit & Continuity   2. Integration (ለዚያውም ገገማው part)😂   3. Epsilon-delta definition of limit (በተአምር የማይቀር)   4. Differentiation of different functions     12 ብትማሩም ባትማሩም ይመጣል አየት አየት አርጉ ከአሁኑ ባለፈው በለቀኩላችሁ መጽሐፍ (Begashaw I)    Chemistry & physics የተማራችሁት ነው 11 እና 12          

The Path 👇 ENGINEERING 1st_Sem: Pre Engineering 2nd_Sem: Pre Engineering 3rd_Sem: College 4th_Sem: Department APPLIED 1st_Sem: Pre Science 2nd_Sem: Pre Science 3rd_Sem: Department

#ሌባ 🥷 አንድ የተረሳች ማስጠንቀቂያ አለች እሱም ሌባ ወይም ስርቆት ነው። በፍፁም መዘናጋት አያስፈልግም በተለይ ፍሬሽ ስትሆኑ ይበረታል።
ማድረግ ያለባቹ ጥንቃቄ
👉 የበር ቁልፍ ወዲየው ገዝታቹ መቀየር Seniors ሰለሚኖራቸው 👉 በር መዘጋቱን እርግጠኛ መሆን 👉 መስኮት ላይ ጫማ አለማስቀመጥ 👉 ዶርም ማታቁትን ሠው አለማስገባት 👉 ስተኙ locker መቆለፍ / laptop ከ locker ውጭ አድርጎ አለመተኛት ይህን የምላቹ እንዳትዘናጉ ነው። ሁለት ጊዜ ስልክ የተሠረቀ አለ። ልብስ ጫማ laptop ብዙ ሠው ተሠርቋል። ጊቢውም ለእናንተ የሚያደርገው ነገር የለም። ስለዚህ ሁሌ ጥንቃቄ አይለያችሁ።

#ለፍሬሾች 🖤 እዚህ ASTU ሁሉም ያማርራል። ከፍሬሽ እስከ 5TH YEAR ሁሉም ያማርራል። ጥሩ ነው ደስ ይላል የሚል ሰው ብታገኙ እንኳን ስሜቱ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ነው 😁 ... ለማን
#ለፍሬሾች 🖤 እዚህ ASTU ሁሉም ያማርራል። ከፍሬሽ እስከ 5TH YEAR ሁሉም ያማርራል። ጥሩ ነው ደስ ይላል የሚል ሰው ብታገኙ እንኳን ስሜቱ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ነው 😁 ... ለማንኛውም ጠንከር ማለት ያዋጣል። ትልቅ ቻሌንጅ እንደሚጠብቃችሁ አውቃችሁ የስነልቦና ዝግጅት አድርጉ። ታሸንፋላችሁ!✊ ይ ቀ ጥ ላ ል . . .

እስኪ ሾለ ASTU አንዳንድ ነገር ልበላችሁ... 1. ትምህርቱ ትምህርቱ ቀላል ሚባል አደለም ፤ ፈተናውም ከሌሎች ግቢዎች ይከብዳል። 2. ዶርም ዶርም 4 ሆናችሁ ሰለምትገቡ ደስ ሚል ነገር አለው። 3. የግቢው ላይፍ ግቢ life ጥሩ ጓደኛ ከገጠማችሁ áŠ áˆŞá እንደሚሆንላችሁ አጠትራጥሩ ካልሆንም እንደዛው። 4. ትግሉ 🥵 ከቤትሰብ መራቅ እና አዲስ ቦታ መሆን ከትምህርቱ ባሻገር ትንሽ የሚያስቸግር ይመስለኛል በተለይ ለሩቅ ሀገር ተማሪዎች። 5. መለስተኛ Zoo 😁 የዱር አራዊት የሌለ የለም ከጅብ አስከ ሚዳቆ ፣ ጃርት... ነፍ ነው national geography በሉት ግን ደሞ ለማዳ ናቸው አይተናኮሉም። 💀 6. Ladies 👩 ግቢው ለሴቶች affirmative action በጣም አለው የሴቶች ብቻ ላይብረሪ ፅዳት ያለው ዶርም እና acadamical support ከወንድ ተማሪዎች በተሻለ ታገኛላቹ እንደውም አንዳንዴ ወንዶችን ውጡ ማለት ደብሯቸው ይመስል ድረስ ልዩነት አለው። 8. ውሃው የምትጠጡት ትኩስ ውሃ ነው። Imagine ሞቆህ ሻወር ገብቼ ቀዝቀዝ ብዬ ልውጣ ብለህ ገላህን ተቃጥለህ ስትወጣ 🥵🤦‍♂️ ... የምትጠጡትም ያው ትኩስ ውሃ ነው። ቀዝቃዛ ወፍፍፍ...🤷‍♂️ 9. አዳማ (ከተማው) አዳማ ከተማዋ ሞቃት ብትሆንም ወጣ ብላቹ ለምዝናናት ከፈልጋችሁ ምቹ ናት ያው ጥናት ሳይረሳ ማለቴ ነው:: 10. ይ ቀ ጥ ላ ል . . . #Share 👇 Join 👇 @astututorials

For ASTU's  2018 freshman students only 👇👇👇          @astututorials

For ASTU's 2018 freshman students only 👇👇👇 @astututorials

#ASTU ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች‼️
#ASTU ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች‼️

#Result_Announcement 👉 በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትናችሁ ፣ በ2018 ዓ.ም በሁለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለመማር የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ እና በአ
#Result_Announcement 👉 በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትናችሁ ፣ በ2018 ዓ.ም በሁለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለመማር የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ እና በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው መመደባችሁን ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ፣ አድሚሽን ቁጥራችሁን እና የመጀመሪያ ስማችሁን በማስገባት የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲን መቀላቀላችሁን መመልከት ትችላላችሁ 👇 🔗 Link 👇
https://stuexam.astu.edu.et/