cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፈለገ ሰማዕት-media (felegesemaet media)

ይህ የፈለገ ሰማዕት ሰ/ት/ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነዉ በዚህ ገፅ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች የየዕለት በዓላት በሰ/ሰ/ት/ቤታችን ዉስጥ የሚካሄዱ አበይት ክንዉኖች እንዲሁም ዜና ቤተክርስቲያን ይቀርብበታል ይህንን መንፈሳዊ ቻናለዉ ለወዳጆቾ ሼር በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ ◈◈◈◈✤✤✤✤❖❖❖❖✥✥✥✥✥ አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

Show more
Advertising posts
377Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የ7ተኛ እና 8ተኛ ክፍል አባላት የሆናችሁ የመጋቢትና የሚያዝያን ወርሀዊ መዋጮ ዛሬ በመርሐ ግብር ሰዓት ይዛቹ እንድትመጡ !!!
Show all...
ለማስታወስ እሁድ ኮርስ እንዳለ ለ እህት ወንድሞቹ በደንብ ላልሰሙት አሳውቁ ማንም ሰው እንዳይቀር
Show all...
⭕️⭕️ማሳሰቢያ ⭕️⭕️ በ20/8/2016 ዓ.ም እሁድ ኮርስ አለ ያለፈው እሁድ እንደሌለ ተነግሮ ስለነበር አሁን ሓሳብ ስለተቀየረ ኮርሱ እንደሚቀጥልና ሁላቹም ለጓደኞቹ እሁድ ለት ኮርስ እንዳለ እንድታሳውቁ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን
Show all...
👍 3
የአውስትራሊያው ታዋቂ የአሦሪያ ጳጳስ የግድያ ሙከራ፣ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች (እንደወረደ) ++++++ (ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ) ሀ/ መነሻ የሰኞ የብዙዎች መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የነበረው በአውስትራሊያ የሚገኙ የአሲሪያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ላይ በቤተ መቅደሳቸው እንዳሉ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ ነው። ጳጳሱ በቀጥታ ሥርጭት በሚተላለፈውና በመላው ዓለም ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾቻቸው በሚከታተሉት ዝግጅት ላይ ነው በስለት የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው። አንድ በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሰው ጳጳሱን በስለት ደጋግሞ ሲወጋቸው በቪዲዮው ይታያል። ከእርሳቸውም በተጨማሪ በቤተ መቅደሱ የነበሩ ሌሎች ሰዎች አደጋ ደርሶባቸዋል:: እኒህጳጳስ በፌብርዋሪ ወር 2024ም ተመሳሳይ በስለት የመግደል መኩራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ በፊብሩዋሪ ወንጀሉን የፈጸመው የ 15 ዓመት ወጣት እንደነበር መገለጹ ይታወሳል። ዛሬ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ በጣም አሳዝኖኛል፣ አስደንግጦኛልም:: በርግጥ ወንጀሉን የፈጸመው ሰው ማንነት ግልጽ ባይሆንልኝም ከሊበራሉ ዓለም እስከ አክራሪ ጽንፈኞች ድረስ ጥቃት ሊያደርሱባቸው የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ መገመት ይቻላል። በትምህርታቸው ጠንካራነት ምክንያት። በቅርቡ እንኳን እሥራኤል በጋዛ ፍልስጥኤማውያን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት የተቃወሙበትን ንግግር ተመልክተናል። ይህንን ጽሑፍ እስከጻፍኩበት ሰዓት ድረስ የአውስትራሊያ ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸመውን ሰው ማንነት እና ወንጀሉን ለመፈጸም የገፋፋውን ምክንያት አልገለጸም። ለሁሉም ግን እንኳን እግዚአብሔር አተረፋቸው፡፡ አሁንም ቶሎ አገግመው ወደር ወደሚወዱት አገልግሎት እንዲመለሱ ምኞቴ ነው። ++++ ለ/ ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል (Bishop Mar Mari Emmanuel) ማን ናቸው? ---------- ማር ማሪ ኢማኑኤል በአውስትራሊያ የሚገኘው የ"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን (Christ The Good Shepherd Church) በተባለ ሥፍራ ያገለግላሉ። በ2009 (እ.አ.አ) ቅስናን፣ በ2011 ደግሞ ጵጵስና መቀበላቸውን ታሪካቸው ያሳያል። ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በስብከቶቻቸው የሚያነሧቸው ጉዳዮች በብዙ ሰው ዓይን ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው ይመስላል። በዘመነ ኮሺድ በመላው ዓለም የተጣለውን ከቤት ያለመውጣት እግድ በጽኑዕ በመቃወማቸው ይታወቃሉ። ከዚያም ቀጥሎ በአሜሪካ እና በሩሲያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸው ሐሳቦች በተለይም በሊበራሉ ዓለም "አክራሪ" አሰኝቷል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን "የተመረጡት በሕቡዕ ቡድኖች ይሁንታ ነው" ማለታቸው እንዲሁም "ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ*ማ*ዊነት"ን በጽኑዕ መቃወማቸው ጠላት ያፈራባቸው ይመስላል። ታዋቂነታቸው ከእንግሊዝኛ ተናጋሪው አልፎ ወደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድም ደርሷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ጳጳሱ ያወቅኹት ስለ ቤተ ክርስቲያኒን ጠንካራ ትችት ያቀረቡበትን እና ቤተ ክርስቲያን "ንስሐ ግቢ" የሚል መንፈስ ያለው አጭር ቪዲዮ አይቼ ነው። "እንዴ!!! ቤተ ክርስቲያን ኃጢአት የማይስማማት የክርስቶስ አካሉ መሆኗን የደፈጠጠ የምዕራቡ ዓለም ፕሮ*ቴስ*ታን*ቲዝም ትምህርት የሚናገር ጳጳስ ከየት ተገኘ?" ብዬ ተገርሜ ነበር። የግብጽ/ቅብጥ ጳጳስ መስለውኝም ነበር። ኋላ ነው የአሦር ኦርቶዶክስ ጳጳስ መሆናቸውን የተረዳኹት። ብዙ ኦርቶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ስብከቶቻቸውን ሼር ሲያደርጉ "የተዋሕዶ ጳጳስ መስለዋቸው ይሆን?" እል ነበር። +++++ ሐ/ ስለ ምሥራቅ አሦሪያ ቤተ ክርስቲያን በመጠኑ --------- 1/ ሙሉ ስማቸው:- ## The Assyrian Church of the East (ACOE)፤ ## የፓትርያርኩ መቀመጫ (መንበረ ፓትርያርኩ) ሰሜን ኢራቅ ኢርቢል (Erbil) ነው። 2ኛ/ ሌሎች ሰዎች "ንስጥሮሳዊት ቤተ ክርስቲያን" (the Nestorian Church) ይሏቸዋል። በኤፌሶን ጉባዔ የተወገዘውን የንስጥሮስን አስተምህሮ የሚቀበሉ ቢሆንም ንስጥሮሳውያን መባል አይፈልጉም። ከጽርፈት (ስድብ) ይቆጥሩታል። 3ኛ/ ራሳቸውን "ኦርቶዶክስ" ብለውም አይጠሩም:: በየትኛውም ጽሑፋቸው ላይ "ኦርቶዶክስ" የሚል ቃል አይጠቀሙም። ነገር ግን ብዙ ሰዎች የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በተለይም የተዋሕዶዎቹ "የኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያናት" አካል አድርገው ይቆጥሯቸዋል። ስሕተት ነው። 4ኛ/ Assyrian Church of the East (branch of Syriac Christianity) ከሚባሉት ውስጥ በ1870 የተለዩት/ የተገነጠሉት "The Chaldean Catholic Church" ከሮማ ካቶሊክ ጋራ ውሕደት ፈጽመዋል። በ1994 ባደረጉት ውሳኔ በነገረ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን አስተምህሮም ከሮማ ካቶሊክ ጋራ አንድ አድርገዋል። መንበረ ፓትርያርካቸውም ኢራቅ ባግድዳ ነው። የቅዳሴ ቋንቋቸው ግን ልክ እንደሌሎቹ የሲሪያክ ይትበሐል አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሁንም "አራማይክ" ነው። መ/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎቹ የሦሪያ ክርስቲያኖች —------------- ሙሉ ስማቸው The Syriac Orthodox Church ይባላል፤ West Syriac Church ወይም West Syrian Church ይባላሉ፣ በመደበኛው (official) አጠራራቸው ደግሞ the Syriac Orthodox Patriarchate of Antioch and All the East ይባላሉ፤ በኢመደበኛ (informal) አነጋገርም ቢሆን (the Jacobite Church) ያዕቆባዊት ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ። በትምህርቱ እና በተቀበለው ሰማዕትነት ቤተ ክርስቲያኗን በተዋሕዶ እምነቷ ባጸናት በሊቀ ጳጳሱ በቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ (Jacob Baradaeus ወይም Jacob bar Addai) ስም ይጠራሉ። የቅዳሴ ቋንቋቸው አራማይክ ሆኖ ይትበሐሉ ግን "የምዕራብ አራማይክ (West Syriac)" ነው። ንስጥሮሳውያኑ "የምሥራቅ አራማይክ" ይትበሐል ተከታዮች መሆናቸውን ከላይ መግለጻችንን ልብ ይሏል። የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎች የነዚሁ የያዕቆባውያን ኦርቶዶክሶች አካል ናቸው። ++++++ ሠ/ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና የኤፌሶን ጉባኤ (431 ዓ.ም) —------ ጉባኤ ኤፌሶን በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ከተማ በ200 ሊቃውንት የተካሄደ ታላቅ ጉባዔ ነው፡፡ የስብሰባው መሪ ቅዱስ ቄርሎስ ነበር፡፡ የስብሰባው ዋና ምክንያት የንስጥሮስ ክህደት ነው፡፡ የንስጥሮስ ክህደቱም "ቃል ከሥጋ ጋር አልተዋሐደም። ሰው አልኾነም። አምላክም ሰው የሆነው በኅድረት ነው፡፡ ኅድረት ማለትም እመቤታችን የወለደችው ሰውን ብቻ ነው፡፡ ማርያም በወለደችው ሰው ላይ የእግዚአብሔር ቃል አደረበት (ሕድረት)፤ ስለዚህ እርሷም ወላዲተ አምላክ አትባልም" የሚል ነው፡፡ ንስጥሮስን ተከራክሮ የረታውና መልስ ያሳጣው እስክንድርያዊው ሊቀ ጳጳስ ቅ/ቄርሎስ ነው፡፡ የንስጥሮስን የክህደት ትምህርት በመሠረዝ እመቤታችን "እመአምላክ ወላዲተ አምላክ፣ እመ እግዚአብሔር (Mother of God, Theotokos)" መሆኗን እናምናለን፣ እናሳምናለን፣ እናስተምራለን።
Show all...
👍 2
አንድ ዓመት በሞላው ጦርነት ሱዳናውያን ክርስቲያኖች ለውስብስብ ችግር ተጋልጠዋል ! ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) አንድ ዓመት ያስቆጠረው የሱዳን ጦርነት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ ውድመት እያስከተለ ይገኛል።ለስምንት ሚልየን ዜጎች መፈናቀል ምክንያት በሆነው በዚህ ጦርነት አምዱርማን ውስጥ አንድ ቤተ ክርስቲያን ጥቃት ተፈጽሞበታል። የዓይን እማኞች እንደሚሉት ጥቃቱን ያደረሱት የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ናቸው። ሆኖም የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የቀረበበትን ክስ አልተቀበለም። በተጨማሪም ጦርነቱ ክርስቲያኖችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። በጦርነቱ መጀመሪያ አካባቢ ክርስቲያኖች በተለየ መልኩ ተጠቅተዋል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። አቢያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋል፤ አንዳንዶቹም በከባድ መሣሪያ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከአንድ ዓመት በኋላ ብዙዎቹ ወደ ግብፅ ሲሰደዱ፣ ቀሪዎቹም ተጠልለው ከሚገኙበት ፖርት ሱዳን ለመሰደድ አማራጮችን እየፈለጉ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል። #Ethiopia #Tewahedo_Media_Center #TMC_Addia_Ababa ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ ማንኛውንም መረጃዎች እና የዜና ጥቆማ በስልክ ቁጥር +251913502324 በቀጥታ በመደወል ወይም በቴሌግራም መልዕክት ይላኩልን ! የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ https://youtube.com/@TMC1 የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/ የኢንስታግራም ገጻችንን www.Instagram.com/tewahedo_media
Show all...
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC

እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ ! የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልን የቴሌግራም ቻናል ድረ ገፃችንን - www.tmceth.com ይጎብኙ የዩቲዩብ ቻናላችን

https://www.youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q

ሚያዚያ 11 በ2007 ዓ.ም በሊቢያ በርሃ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲኖች መታሰቢያ ቀን "ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡ ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡ ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"        ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Show all...
ሚያዚያ 11 በ2007 ዓ.ም በሊቢያ በርሃ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲኖች መታሰቢያ ቀን "ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡ ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡ ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"        ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Show all...