cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM

በደ/ነ/ቅ/ዮሐንስ እና መ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው https://www.facebook.com/Fikureegzi4 √ ዌብሳይታችን www.fikureegzi.com √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/channel/UCXceln4wpQhIVS42O02kAWg ለሀሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!! @FikureEgzi04

Show more
Advertising posts
7 262
Subscribers
+124 hours
+647 days
+45330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ጉባኤ ኤፌሶን               ዝክረ ቅዱስ ያሬድ እንኳን ለሰንበት ት/ቤታችን 56ኛ  ዓመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! የሰንበት ት/ቤታችንን የምስረታ በዓል እና የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ልዩ የዓመታዊ ጉባኤ መርሐ ግብር ዝክረ ቅዱስ ያሬድ 🗓 አርብ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም        🕰ከቀኑ 11:00 ሰዓት               💒 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ                ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
Show all...
🥰 11👍 3 2
ወንበዴ ነህ፣ ነፍሰ ገዳይ ነህ፣ ዘማዊ ነህ፣ በሱስ ተይዘሀል፣ ወይስ በባዕድ አምልኮ ነህ…ምንድነዉ ከእግዚአብሔር የለየህ እና ያስጨነቀህ? እግዚአብሔር እንዲህ ይልሀል ‹‹ ወደኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ›› ዘካ 1፤3፡፡ ስለዚህ ምክንያትህን ተዉና ዝም ብለህ ወደ እግዚአብሔር ና ፈልገዉ ሲፈልግህ ታገኘዋለህ፡፡አባ ሙሴ በሚኖርበት ገዳም ዉስጥ የሚኖሩ 500 የሚሆኑ ወንድሞች መነኮሳትን በአበ ምኔትነት እያስተዳደረ እያለ በማህበረ መነኮሳቱ ለሚበልጥ አገልግሎት ለቅስና ማዕረግ ተመረጠ፡፡ ሊሾሙት ወደ ቤተ መቅደስ ባቀረቡት ጊዜ ሊቀ ጳጳስሳቱ የቅስና ማዕረግ ሊሰጡት አልወደዱም ነበርና ‹‹ ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት? ከዚህ አዉጡት›› ብለዉ በዘመኑ ቋንቋ የዘረኝነት ጥቃት አደረሱበት፡፡ አባ ሙሴ ይህን ቃል ሲሰሙ ‹‹ መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ መልካም አደረጉብህ›› እያሉ እራሳቸዉን እየገሰጹ ከቤተ መቅደስ ወጡ እንጂ ለራሳቸዉ ጥብቅና አልቆሙም፡፡ ከዚሁ ጋ የሚመሳሰል አንድ የመነኮሳት ታሪክ እናንሳ፡፡ በአንድ ገዳም የሚኖሩ ምግባረ ሰናይ በሁሉ የሚወደዱ አባት ነበሩ በዚህ የቀና አንድ መነኮስ ወንድም በአንድ ቀን እሳቸዉን ለማሳጣት አስቦ በጉባኤ መካከል ይሰድባቸዉ ያንቋሽሻቸዉ ጀመር በዚህ ጊዜ እኚያ አባት ‹‹ወንድሜ ሆይ አንተ ልታዉቅ የምትችለዉ በኣፋ ያለዉን ነዉ ዉስጤን ብታየዉ ከዚህ ይከፋል›› ብለዉ በትህትና ድል ነሱት፡፡ እዉነተኛ ትህትና እኔ አልረባም ማለት ሳይሆን አትረባም ሲባል መታገስ ነዉ ብሏል አፈ አፈዉ ዮሐንስ፡፡ በአንዲት ዕለትም አባ ሙሴ ከአረጋዉያን ጋር ወደ አባ መቃርስ በሔዱ ጊዜ አባ መቃርስ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸዉ ‹‹ ከእናንተ ዉስጥ የሰማእትነት ክብር ያለዉ አንድ ሰዉ አያለሁ በማለት ለአባ ሙሴ ስለተዘጋጀዉ የሰማእትነት ክብር አስቀድመዉ ትንቢት ተናገሩ፡፡ አባ ሙሴም ይህን ቃል ሲሰማ ‹‹ እኔ እሆናለሁ በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይሙት የሚል ጽሑፍ አለና›› ብለዉ መለሱ፡፡ ‹‹ኀጢያታአችንን እኛ ስናስታዉሰዉ እግዚአብሔር ይተዉልናል እኛ ስንረሳዉ እግዚአብሔር ያስብብናል›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡፡ ራሳችንን ብንመረምር ግን እግዚአብሔር ባልፈረደብንም ነበር 1ኛ ቀሮ 11፤31
Show all...
🙏 19👍 4🥰 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
ምን እንማር አባ ሙሴ ጸሊም ግብጻዉያን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞች ስሙን ጠርተዉ ከማይጠግቡት አባት መሀከል ነዉ ጻድቁ አባ ሙሴ ጸሊም (ጥቁሩ ሙሴ)። በሰኔ 24 ቀን ዓመታዊ በዓሉ ታስቦ የሚዉለዉ አባ ሙሴ ጸሊም ትውልዱ ኢትዮጵያ ሲሆን ኑሮዉ ግን በግብጽ ነዉ፡፡ ቀድሞ የነበረዉ ህይወቱ እንደመልኩ የጠቆረ ነበር።  በግብሩም ሀይለኛ፣ አብዝቶ የሚበላ፣ ነጣቂ፣ አመንዝራ፣ ሰዉ ገዳይ እንዲሁም በባዕድ አምልኮ(ፀሐይን ለሚያመልኩ) ላሉ አገልጋይ ነበር፡፡ ነገር  ግን በጥበበ እግዚአብሔር አባ ሙሴ ከእለታት በአንድ ቀን ‹‹ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ›› ብሎ እንደ ጻድቁ አብርሀም ፈጣሪን በስነ ፍጥረት መፈለግ ጀመረ፡፡ የሰዉ ልጅ ይድን ዘንድ እንጂ መሞቱን የማይፈቅድ አፍቃሬ ሰብዕ ቸሩ እግዚአብሔር ወደ አስቄጥስ ገዳም መራዉ፡፡ በዛም ከካህናቱ አንዱ የሆኑትን አባ ኤስድሮስን ‹‹ እዉነተኛዉን አምላክ ታሳዉቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ›› አላቸዉ፡፡ አባ ኤስድሮስም  ወደ አባ መቃርስ መሩት፡፡ አባ መቃርስም የክርስትናን ሃይማኖት አስተምረዉና አጥምቀዉ  አመነኮሱት፡፡ አባ ሙሴም ጥሙድ እንደ በሬ ቅኑት እንደ ገበሬ ሁኖ ግዙፍ ሰዉነቱን በገድል ቀጠቀጠዉ ከቁመቱ በስተቀር ምንም አልነበረዉም። የአምላካችን ቸርነቱ ምን ያህል ነዉ? ይህንን እንደ አለማወቅስ ያለ ምን ጉዳት አለ፡፡ ተስፋ ያስቆረጠህ፣ እንደተራራ የከበደብህ ኀጢያት በእግዚአብሔር ምህረት ዐይን ሲታይ ምንም እንደሆነ ከአባ ሙሴ ጸሊም ህይወት መማር ይቻልሀል፡፡
Show all...
👍 2 1
04:44
Video unavailableShow in Telegram
80 የእምነቱ ተከታይ አባወራ ብቻ የሚገኙበት በሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አረዳትነትና በ80 አባወራ የጉልበት ስራ እየተገነባ 75 ፐርሰንት የደረሰው የዶርዜ አይራ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን። እነዚህ 80 አባወራ ምእመናን ቀሪውን 25 ፐርሰንት አልቆ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑበት የእኛን የምእመናን ድጋፍ እና እገዛ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ሁላችንም የእምነቱ ተከታይ ከታች ባለው የቤተክርስቲያኑ አካውንት ድጋፍ በማድረግ የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስንን ቤተ መቅደስ ስራ እንጨርስ ዘንድ መልእክታችንን እናስተላልፋለን ። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:– 1000563785571 የዶርዜ አይራ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን።
Show all...
25👍 6🙏 4🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጉባኤ ኤፌሶን               ዝክረ ቅዱስ ያሬድ እንኳን ለሰንበት ት/ቤታችን 56ኛ  ዓመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! የሰንበት ት/ቤታችንን የምስረታ በዓል እና የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ልዩ የዓመታዊ ጉባኤ መርሐ ግብር ዝክረ ቅዱስ ያሬድ 🗓 አርብ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም        🕰ከቀኑ 11:00 ሰዓት               💒 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ                ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
Show all...
👏 4🙏 3🕊 3👍 1🥰 1
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በደ/ ማርቆስ ማረሚያ ቤት ተገኝተው ታራሚዎችን ጎበኙ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ./አዲስ አበባ) ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት ተገኝተው የሕግ ታራሚዎች በቃለ እግዚአብሔር ከማጽናናታቸው በተጨማሪ በጀርመን ከሚገኙት መንፈሳዊያን ልጆቻቸው በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለታራሚዎች የትንሳኤ በዓል ምክናያት በማድረግ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። ©ምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት
Show all...
10👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለሰንበት ት/ቤታችን 56ኛ  ዓመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! " የፈጠራችሁን እስከ ዛሬም ድረስ የጠበቃችሁን እግዚአብሔርን ፍሩት"   መቃብያን ካልዕ 10 ÷1
Show all...
👍 31 10🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጉባኤ ኤፌሶን               ዝክረ ቅዱስ ያሬድ እንኳን ለሰንበት ት/ቤታችን 56ኛ  ዓመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! የሰንበት ት/ቤታችንን የምስረታ በዓል እና የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ልዩ የዓመታዊ ጉባኤ መርሐ ግብር ዝክረ ቅዱስ ያሬድ 🗓 አርብ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም        🕰ከቀኑ 11:00 ሰዓት               💒 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ                በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
Show all...
👏 7 3👍 2🥰 2
ባሕረ ጥበባት ዲጂታል መጽሔት የተለያዩ መንፈሳዊ ርዕሰ ጉዳዮችን እየዳሰሰች እውቀትን የምታስጨብጠን ዲጂታል ባሕረ ጥበባት የእጅ መጽሔት የግንቦት ወር እትም ።          📲   ገጹን ጆይን ያድርጉ!        📱📱  ያውርዱ!       📖📖  ያንብቡ!        👨‍👧‍👦👨‍👦‍👦  ያጋሩ!
Show all...
👏 13👍 6🙏 3🥰 2
13👍 9🥰 2🙏 2