CUSTOMS COMMISSION JIGJIGA BRANCH/በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
Open in Telegram
ራዕይ፡- "በ2022 በአገራችን ደረጃዉን የጠበቀ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደር ተገንብቶ ማየት ስ/ቁ-025-775-72-77
Show more3 409
Subscribers
+324 hours
+107 days
+12030 days
Posts Archive
የጉምሩክ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር ተጠናቀቀ
ጅግጅጋ፣ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
የጉምሩክ ኮሚሽን የሰራተኞቹን ሙያዊ አቅምና ክህሎት ለማሳደግ፣ የሥራ አፈጻጸምን ለማሻሻል እና የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአራት ዙሮች ለጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር ተጠናቀቀ።
ስልጠናው የሰራተኞችን የሙያ እውቀት ለማጠናከር፣ በሥራ ላይ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በተሻለ ሁኔታ ለመፍታት እና ዘመናዊ የጉምሩክ አሠራሮችን በብቃት ለመተግበር የሚደገፍ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ስልጠናው የሰራተኞችን የሙያ አቅም በማሳደግ የተቋሙን የለውጥ ሂደት በተግባር ለማስፈጸም እና የሪፎርም ሥራዎቹን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ ነው።
የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞችም በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በዕለት ተዕለት ሥራቸው በመተግበር፣ የኮሚሽኑን የሪፎርም አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠቁሟል።
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
ጅግጅጋ፣ ኢትዮጵያ
