cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🇸🇦 SUNNAH MEDIA 🇸🇦

🇸🇦ቅድሚያ ለተውሂድ🇸🇦 🕋ቁርአን እና ሀዲስ🕋 ✍️የሰሀቦች ታሪክ⚔️🛡️🏹 ✍️ የሰለፎች ታሪክ ✍️የኡለሞች ታሪክ📝 👑የሙስሊም_መንግስታት_ ታሪክ⚔️ ⚔️የሙጃሂዶች_ታሪክ🛡️

Show more
Advertising posts
9 229
Subscribers
-1024 hours
-487 days
-21230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አይ አዳም መከራህ ብዛቱ ሄዋን አንተን ለማሳሳት እረፍት አጥታለች  ከሂጃብ ላይ ፀጉሯ ሲታይ ትልቅ እንዲመስል ፀጉር የሚመስል ትልቅ ፀጉር ማስያዣ ተሸክማ ትሄዳለች፤ ጡቶቿ ያልወረዱ እንዲመስሉ የተኙ ጡቶቿን በጡት ማስያዣ ትወጥራቸውና ቁጭ ቁጭ ያሉ ይመስላሉ.. እሺ ጡት ማስያዣውን ፈተሽ ሲያይሽ ምን ይውጥሽ ይሆን?  ከንፈሮቿ የሚያምሩ እንዲመስሉ ቻፒስቲክ ነው ሊፒስቲክ ተለቅልቃ ትወጣለች  እንግዲህ ተመልከቱ ይሄ ሁሉ ወንዶችን ለማጥመድ ነው አላህ የሰጣት ውበቷ አልበቃት ብሎ በአርቲፊሻል ውበት ደምቃ ወጥታ ወንድሞቻችንን የምታታልለው.............አዳም ሆይ ንቃ ተገላልጣ ተቀባብታ ያየሃት ሁሉ ውበቷ የራሷ ውበት አይደለም ተውሳው ነው ኡኽቲ ምናለ በኒቃብሽ አምረሽ ተሰትረሽ ብትወጪ ቻፒስቲኬ ለቀቀ የተኳልኩት ኩል ተዝረከረከ ጡት ማስያዣዬ ተፈታ እያልሽ መሃል ከተማ ላይ ከምትጨናነቂ እባክሽ በኒቃብ ተሰተሪና አላህ የሰጠሽን ቆንጂዬዋን ፊትሽን ከፀሐይ ጠብቂያት  ኮስሞቲክሱን ደሞ ለአባወራሽ በቤትሽ ውስጥ ድምቅ በይበት ከፈለግሽም ከስራ ለምሳ ሲመጣ ተቀባብተሽ ጠብቂውና ያለፕሮግራሙ አሳስቺው  by ኡሙ ፋላን #Share #Comment 👇👇👇👇👇 @Abu_Umer4 https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1
Show all...
Abu Umer Ibnu Sadik Manhaj Salaf Is My Way(መንሀጀ ሰለፍ መንገዴ ናት)

#ቁርአንእናሀዲስ #ቅድሚያ_ለተውሂድ_እና_ለሱና #የሰለፊይ_ኡስታዞች_ሙሀደራዎች ፡ ፡ ፡ ፡ #የተለያዩ_ዲናዊ_ፅሁፎች #የደጋግ_የቀደምቶች_ታሪክ

👍 2
«እዚህ ሀገር ላይ ባለው ተጨባጭ መመሰረት የአህባሽ፣ የሱፍያ፣ የተብሊግ፣ የዳዒሽ፣ የኢኽዋን፣ የሙመይዓ፣ የሀዳድያ አፈንጋጭ አካሄድ እስከሚጠፋ ድረስ ታግሎ አንድነትን ለማምጣት መጣር የሁሉም የዲን ተቆርቋሪ ሀላፊት ነው።» http://t.me/Abdurhman_oumer
Show all...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

« በዱንያ በስልጣን በጥቅ-ማጥቅም በመሰል ነገሮች አቋሙን የለቀቀ፤ በአቋማቸው የፀኑ ሠዎች የሚተነፍሱት ሁሉ ሰላሙን ይነሳዋል። ፊትና ነው የሚሆንበት። በመሆኑም እሱ ፊትና ውስጥ መግባቱንና የፊትናው ሰበብ መሆኑን ዘንግቶ ለፊትና መፍትሔ ፈላጊ ሆኖ ያርፋል።   የፊትና ሠዎች የፊትናው መፍትሔ ፈላጊ ተብለው ከታሰቡ የተሰረቀን እቃ ከሌባው ጋር እንደ-መፈለግ አምሳያ ነው። በዚህም የተነሳ ችግር መፍትሔ አጥቶ ይቀራል። ማንኛውም የቢድዓ ባለቤቶች የሚያመጡት ጥፋት ባይኖር የሱና ሠዎች አይናገሩም ነበር። በመሆኑም ችግሩን ተስፋፍቶ ስለሚያዩት ብዙን ዝም እያሉ የተቻላቸውን ያህል ይታገላሉ። በጥቅሉ የአንድነት እጦትና የፊትና መስፋፋት ምክንያት የቢድዓ ባለቤቶች ናቸው። » http://t.me/Abdurhman_oumer
Show all...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

#ዲናችሁን_ከማን_እንደምትወስዱ ተመልከቱ!! 〰〰 ታላቁ ታብዕይ ሙሐመድ ኢብን ሲሪን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ ❝ይህ ዒልም ዲን ነው፤ ዲናችሁን ከማን እንደምትወስዱ ተመልከቱ።❞ 📚ሙቀድመቱ ሶሂሁል-ሙስሊም፣ቁ:26 የሀገራችን ትልልቅ ዑለሞችን መተዋወቁ ቀጥሏል። የተከበሩ ዱክቱር ሸይኽ ሁሰይን ሙሐመድ አል-ኢትዮጵይ ኢትዮጵያ ላይ ያደረጓቸው ወሳኝ ሙሀዶራዎች በጥቂቱ ከዚህ በታች ይገኛሉ። በተውሒድ ላይ መሞት                   👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/3330 "የተውሂድ አንገብጋቢነት"                 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/3525 ወደ ተውሒድ ጥሪ ማድረግ 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/5852 ተውሒድ በመጀመሪያም በመጨረሻም                 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/5471 ሸሪዓዊ እውቀት ያለው ደረጃ"                   👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/3527     ↪️ «መንሀጁ-ሰለፍ» ↩️                     👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/3350 ጊዜን በአግባቡ መጠቀም 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/5787 የልብ መረጋጋትን ለማግኘት 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/5829 የአሕባሽ ማንነት እና ፈተናዎቹ በቁርኣንና በሐዲስ 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/6364 የእውቀትና የአዋቂዎች ደረጃ!! 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/6774 ከትላልቆቹ ፥ ለረጅም አመታት፣ ከስር ቁጭ ብለው ፥ እየቀሰሙ እውቀት!! - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - የብስለት ጥግ ይዘው ፥ የእውቀት አድማስ አዝለው፤ በአደብ ተሸልመው ፥ ተውሒድ ተሰንቀው፤ ከመካ ወጥተዋል ፥ ዶክተሬት ጨርሰው!! - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - ማአረግ ብቻ አይደል ፥ ዶክተሬት በሚል ስም ሰነድን ሸምድደው ፥ ሪጃል በመቅሰም፣ አውቀው ነው ፥ የመጡት በቅድሚያ አልታዎቁም!! - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - ልካቸውን አውቀው ፥ የሰውም ልክ አውቀው፣ ሸምተው መጥተዋል ፥ ሰፊ እውቀት ሰብስበው!! - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - መተናነሳቸው እኔን ፥አይገርመኝም፣ ተማሪኮ ናቸው ፥ የዛ ታላቅ ዓሊም፣ ታላቅ የሐዲሰ ሊቅ ፥ የዚህ ዘመን ኢማም፣ በአደቡ ታዋቂው ፥ ሙሀመድ አሊ አደም!! - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - የአቋም ጥንካሬው ፥ እሱም አድስ አይደል፣ ከረቢዑ ሱና ፥ እውቀት ሸምተዋል!! - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - በአላህ ፈቃድ ተጨማሪ ጥቆማዎችን ለማግኘት 👇 https://t.me/Abdurhman_oumer/7600
Show all...
🌸MOTIVATE ለመሆን ሱረቱል ዩሱፍ በቂ ነው ምን ያህል በችግር ላይ ችግር ቢደራረብ አንድ ቀን ይመጣልህ ይሆናል በምቾት ላይ ምቾት ተደራርቦብህ ምትደሰትበት። ታገስ ታገስ ታገስ!! ወዳጄ ዱኒያ ላይ ስትኖር ትእግስት ከሌለህ አንተ ልክ ጦር ሜዳ ገብቶ ያለ ሰይፍ እና ያለ ጎራዴ ሊዋጋ እንደ ሚፈልግ ሰው ነህ ማለት ነው። ስለዚህ ዱኒያ ላይ የሚመጡብህን ችግሮች ለመጋፈጥ ትእግስታዊ ሰይፍ እና ትእግስታዊ ጋሻ ያስፈልግሃል።👌 #አቡ_ኡመር #መልካም_ቀን #Share #Comment 👇👇👇👇👇 @Abu_Umer4 https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1
Show all...
👍 4
قَـالَ الـشيخ ربيع بن هادي عمير المدخلي حفظَهُ الله : - الـذي يدْعـو غـير الله ويذبـح لـغير الله ويستغـيث بغـير الله ويطـوف حـول الـقبور ويسجـد للـقبـور ، ويعتقد في الأولـياء أنـّهم ينفعـون ويضـرّون ... هـل قـال لا إله إلا الله خـالصـا من قلـبه ؟ هـل قـالهـا صادقـًا !؟ كـلا والله ، ثم كـلا والله ، مـا قـالهـا صادقـًا ولا خرجـت خالـصة من شَفَتيـْه ، لأنّـه يقـول لا إلا الله وعنده فلان يدعـى لـه ويذبـح لـه ... فـهذا يهـدم معنى لا إله إلا الله . يـا إخوتـاه الـتوحيد ، الـتوحيد ، نحـن لا نتكلـم في موضـوع من الـمواضيع إلا ونتكلـم في توحـيد الله ، لأننـا نـَرى كـثيرا من المسلمين واقعين في أخطـر الأخطـار . والـذي يتحمل مسؤولـيّة هذه الـملايين وهذه الـقوافـل الـتي يذهـب كـثير منهـا إلى الـنار ، يتحمل مسؤولـيتهم هـؤلاء الـدعاة الـذين يكتمـون أعظـم مـا أنـزل الله 📚 ( مرْحبًـا يا طالـب العلْم : ١٠٨ )
Show all...
#በመተናነስ_ዙሪያ #ከደጋግ_ቀደምቶች_ንግግሮች_!! 〰〰〰  قالت عائشة، رضي الله عنها: إنكم لتغفلون أفضل العبادة التواضع؛ (📚التواضع؛ لابن أبي الدنيا، صـ107، رقم: 80). አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላት እናታችን ዓኢሻህ(እንዲህ) ትላለች «እናንተ ትልቅ የሆነ ዒባዳ ትዘነጋላችሁ መተናነስን።» 📚 አተዋዱዑ ሊብኒ አቢ ዱንያ)    سئل يوسف بن أسباط رحمه الله: ما غاية التواضع؟ قال: أن لا تلقى أحدًا إلا رأيت له الفضل عليك؛ 📚سير أعلام النبلاء؛ للذهبي، جـ9، صـ 170).  አላህ ይዘንለት ዩሱፍ ኢብኑ አስባጥ የመተናነስ ምንነት ግቡ ምንድን ነው ተብሎ ተጠየቀ «አንድም ሰው አታገኝም እሱ ባንተ ላይ ብልጫ እንዳለው ብታስበው እንጅ" ብሎ መለሰ!!» 📚 ሲየር አዕላሙ ኑበላአ ሊዘሀብይ) قال إبراهيم بن الأشعث رحمه الله: سألت الفضيل عن التواضع، قال: التواضع أن تخضع للحق وتنقاد له، ولو سمعته من صبي قبلته منه، ولو سمعته من أجهل الناس قبلته منه؛ 📚التواضع؛ لابن أبي الدنيا، صـ117، رقم: 88). ሁለታቸውንም አላህ ይዘንላቸው ኢብራሂም ኢብኑ አሽሀብ #ፉዶይል_ኢብኑ_ዒያድን ስለ መተናነስ ጠየኩት፣ «መተናነስ፦ ለሀቅ (ለእውነት) ዝቅ ልትልና ለርሱ ልትጎተት ነው። ምንም እንኳ ከህጻን ልጅ ብታገኘው ልትቀበል ነው። ከሰዎችም ሁሉ መሀይም የሆነ ሰው ዘንድም ብታገኘው ልትቀበል ነው።» (አለኝ ይላል) 📚አተዋዱዑ ሊብኒ አቢ ዱንያ)    قال يحيى بن الحكم رحمه الله لعبدالملك بن مروان رحمه الله: أي الرجال أفضل؟ قال: من تواضع عن رفعة، وزهد عن قدرة، وترك النصرة عن قوة؛ 📚 تاريخ دمشق؛ لابن عساكر، جـ37، صـ144).  ሁለቱንም አላህ ይዘንላቸው የህያ ኢብኑ ሀኪም አብዱል መሊክ አል መርዋንን ከወንዶች ሁሉ በላጩ ማን ነው ብሎ ጠየቀ «ትልቅ ደረጃ ኖሮት ሳለ የተናነሰ፣ (ሞልቶት ተርፎት) እየቻለ ሳለ ዛሂድ የሆነ (ዱንያን ችላ ያለ)፣ ቅዋ /ሀይል እያለው ድል አድራጊነትን (መበቀልን) የተወ" ነው ብሎ መለሰ» 📚ታሪኹ ድመሽቅ ሊብኒ አሳኪር • قال الشافعي رحمه الله: أرفع الناس قدرًا مَنْ لا يرى قدره، وأكبر الناس فضلًا من لا يرى فضله؛ 📚 شعب الإيمان؛ للبيهقي، جـ10، صـ 515، رقم: 7914).  አላህ ይዘንላቸው ኢማሙ ሻፍዕይ እንዲህ አሉ፦ «ከሰዎች በደረጃ በኩል ከፍ ያለ ማለት ትልቅነቱ የማይታየው ነው፣ ከሰውች ዘንድ ትልቁ ማለት  በላጭነቱ የማይታየው ነው።» 📚ሸዕቡል ኢማን ሊል በይሀቂይ) قال يحيى بن كثير رحمه الله: رأس التواضع ثلاث: أن ترضى بالدون من شرف المجلس، وأن تبدأ من لقيته بالسلام، وأن تكره المدحة والسمعة والرياء بالبر؛ 📚التواضع؛ لابن أبي الدنيا، صـ154، رقم: 118).  አላህ ይዘንላቸው የህያ ኢብኑ ከሲር የመተናነስ ዋና-ዋናዎቹ ሶስት ናቸው ይላሉ። እነሱም፦ « ከከፍተኛው ይልቅ ዝቅተኛ የሆነ መቀመጫ ላይ መቀመጥ መውደድ፣ የተገናኘህን ሰው  በሰላምታ መጀመር (መቅደም)፣ በመልካም ሥራ መሞገስንና ይስሙልኝን እንዲሁም ይዩልኝን መጥላት ነው።» 📚 አተዋዱዕ ሊብኒ አቢ ዱንያ: 118  قـــال الإمــام إبـن حـبــان  رحمـہ اللـہ تعالـﮯ : التَّواضُع يُكْسِب السَّلامة، ويورث الألفة، ويرفع الحقد، ويُذْهِب الصَّد، ثمرة التَّواضُع المحبَّة، كما أنَّ ثمرة القناعة الرَّاحة، وإنَّ تواضع الشَّريف يزيد في شرفه، كما أنَّ تكبُّر الوضيع يزيد في ضِعَتِه.📚روضة العقلاء ٦١  አላህ ይዘንለት ኢማም ኢብኑ ሂባን እንዲህ ይላል፦ « መተናነስ ሰላምን ያስገኛል፣ መስማማትን ያወርሳል፣ ጥላቻን ያነሳል፣ መዘጋጋትን ያስወግዳል፣ የመተናነስ ፍሬው መዋደድ ነው። ልክ የመብቃቃት ፍሬው ረፍት ማገኘት እንደሆነ ሁሉ። መተናነስ ታላቅነት ነው። ከትልቅነት ላይ (ትልቅነት) ይጨምራል። ልክ በዝቅተኝነት መኩራራት ዝቅ ማለት እንደሚጨምረው ሁሉ።» 📚 ረውዶቱል ዑቀላእ 61 በድጋሜ የተለጠፈ! https://t.me/Abdurhman_oumer
Show all...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

👍 1
የሰዎችን ደረጃና ጥበብ እንዲሁም መልካም ነገር በመመልከት፤ መድኃኒት ወደሌለው ምቀኝነት ከመግባት ይልቅ፤ እውነተኛ በመሆን ነው ይሄን ፀጋ መጎናፀፍ የሚቻለው።قَالَ الْفُضَيْلُ بْنُ عِيَاضٍ: وَإِيَّاكُمْ وَالْحَسَدَ فَإِنَّهُ لَيْسَ لَهُ دَوَاءٌ , مَنْ عَامَلَ اللهَ عَزَّ وَجَلَّ بِالصِّدْقِ أَوْرَثَهُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ الْحِكْمَةَ» 📚رواه أبو نعيم في الحلية، (8/ 99). አላህ ይዘንላቸው ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ የሚከተለውን ብለዋል«አደራችሁን ከምቀኝነት ተጠንቀቁ ለሱ መድኃኒት የለውም። ለአላህ ብሎ በእውነተኝነት የሚሰራ ሰው አላህ ሂክማ (ጥበብን) ያጎናፅፈዋል።» 📚 አቡ ኑዓይም (ሒልየቱል አውሊያ: 8 / 99) ላይ አውስቶታል http://t.me/Abdurhman_oumer
Show all...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

#ለዲኑ_ጥበቃ ጀሊሉ እሱ አለበት!! 〰 አትድከም አትልፋ ፥ መናገር ስለቻልክ፣ እጅህ ስለፃፈ ፥ አትትጋ ለማወክ፣ በያገሩ አታሲር፣ ባጢል እያጠመድክ ዲን ለማደናቀፍ ፥ አትድከም እየዞርክ!!               \\\ ወደ ዲን መመለስ ፥ ሲገባ እሱን ማክበር፣ ለትግል መነሳት ፥ ለመፋለም መጣር ባጃቢ መታለል ፥ በቲፎዞ መስከር፣ ቀኑ ሲደርስ ጊዜ ፥ የውሳኔው ቀደር፣ ተጥሎ ያስቀራል ፥ ወድቆ በመንገድ ዳር!!                  /// ከላይ የታዘዘን፥ ፍትህ ላይናወጥ፣ የተፃፈን ነገር፥ ጽፈህ ለመለወጥ፣ ጠንካራውን ድልድይ፣ ልንድ በማሽሟጠጥ፣ አትድከም አትልፋ፥ ቀደርን መጋፈጥ፣ ገና ሲደነገግ፣ ለሰው ልጅ ሲገለጥ፣ ቃል የተገባለት፥ ከሁሉም እንዲበልጥ፣ ነቅነቅም አይልም፣ የወጣ ቢወጣ፣ የቀለጠ ቢቀልጥ፣ በውሸት በቅጥፈት፥ ዲን ሱናን መጋፈጥ፣ የሱና ሰዎች ላይ፥ መጫን የበደል ሸፍጥ፣ ትርፉ ነዳማ ነው፥ እውነታው ሲገለጥ!! ይታገሳል እንጅ ፥ ጀሊል ጊዜ ሲሰጥ፣ ሁሉን አስተካክሎ ፥ በቦታው ማስቀመጥ፣ ከድሮም ሱናው ነው፣ ሀቅን ከፍ አድጎ፣ ባጢልን ማርመጥመጥ!!! بَلْ نَقْذِفُ بِالْحَقِّ عَلَى الْبَاطِلِ فَيَدْمَغُهُ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٌ ۚ {{በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፡፡ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፡፡ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፡፡}} (አል-አንቢያ - 18 ) وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا {{በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»}} (ሱረቱ አል-ኢስራእ - 81 )            /// #ሰለፍዩ_ይህ_ነው!! ለአላህ የሚወድ ፥ ለአላህ የሚጠላ፣ ጀግና የሱና ሠው ፥ ደሊል የተሞላ፣ ለእውነት የሚጨነቅ ፥ የሚርቅ ውንጀላ፣ #ለቂም_ለጥላቸው፣ #ሁኔታም_ቢያመቸው፣ የሰው ስጋ አቅርቦ በግፍ የማይበላ፣ አጣርቶ የሚጓዝ ፥ ያልሆነ ቸኳላ፣ አቋሙ ግልፅ ነው፥ ትግሉ በጠቅላላ!!          /// ቁጭት ለመበቀል፥ ነገር የሚያተላ፣ አይደለም ግብስብስ፥ የማይረባ አተላ፣ ለስልጣን ለጥቅም፥ ከአቋሙ የማይላላ፣ በመረጃ ሚዛን፥ ለእውነት የሚያደላ፣ አውጥቶ ይጥላል፥ ወረተኛን  ሁላ!!                 \\\ ፊት አይሰጣቸውም፥ ለነዛ ማጠልሸት፣ ቁም ነገር የላቸው፥ የተሞሉ ኮተት፣ ሱንይ ለዲን ሲሮጥ፥ ጥመትን ለማጥፋት፣ ለመዘርጠጥ ብቻ፥ የዋኙ በቅጥፈት፣ ሀሜት ነው ትርፋቸው፥ የሠው ስጋ መብላት!! ብድር ለመመለስ ፥ ዲን የለም በስሌት፥ ቁስልን ለመጠገን ፥ ቁጭት ለመወጣት፣ ቃላት በመጠምዘዝ ፥ ገልብጦ በማውራት፣ ቀን ከለት መወትወት ፥ ታጅበው በውሸት፣ እኩል ለማሰለፍ ፥ ባጢልን ከእውነት፣ ይፍጨረጨራሉ ፥ ሁሌም ማታና ጧት፣ ጥቅምን ለማስቀጠል ፥ ዲን ሱናን በመምታት!!               /// በጀርባ ደብቀው ፥ ብዙ አይነት መርዞችን፣ ናላ.ቸው እስኪዞር ፥ ዱኒያን ወደው ከዲን፣ አለ-ቅጥ ቆሽሸው ፥ በገንዘብ በስልጣን፣ ከሱንዩ አናት ላይ ፥ ይላሉ ካልወጣን!!                /// ባጢል ላይነገር ፥ እንዳይወጣ እውነት፣ “አትተች ትተቻለህ!” የሚል አጉል ብሂል እነሱ ባመጡት፣ በዚህ ጅል ቃዒዳ፣ በዚህ ውልግድ መስፈርት! መርጨት ቀጥለዋል ፥ በዲን ውስጥ ብልሸት፣ ሱንዩ ሲጀምር ፥ ሀቅን ለማብራራት፣ ጅስማቸው ይግላል ፥ ያመነጫል ግለት፣ ማከክ ይይዛሉ ፥ ደርሰው ለማጠልሸት፣ ጥፋትን ቶሎ አምኖ ፥ ፈጥኖ እንደመቶበት፣ ጥልሽት እያስፋፉ ፥ ማደብዘዝ አንድነት፣ ሚዲያ ማናወጥ ረብሻ ማስፋፋት፣ ይህ ነው ከነሱ ዘንድ ፥ ስራ ያደረጉት፣ ሱንይ ቦታ አይሰጥም ፥ ለእንዲህ አይነት ዝቅጠት፣ በግሉ ጉዳይ ላይ ፥ ያሻቸውን ቢሉት፣ አላማው ሱና.ን ነው፥ እንዳያቆሽሹት፣ ዲኑን አያስነካም ፥ እስካለ በህይወት፣ ሰበቡን ያደርሳል ፥ በአላህ በመመካት፤ ለዲኑ ጥበቃ ፤ ጀሊሉ እሱ አለበት!! ✍ አብዱረህማን ዑመር የቴሌግራም ቻናል፦ 👇 http://t.me/Abdurhman_oumer
Show all...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

👍 1