cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

mars@abc

Teacher's Channel mars@abc

Show more
Advertising posts
1 211
Subscribers
-124 hours
+87 days
+730 days
Posts Archive
ለሁሉም ክ/ከተማ CRRSA ጽ/ቤት አዲስ አበባ ጉዳዩ: የመምህራን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ምዝገባን ይመለከታል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመምህራን ልማት ጋር በተያያዘ በትምህርት ቢሮ በኩል የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርፆ እየሰራ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በነዋሪነት ያልተመዘገቡ መምህራንን ጥያቄ መመለስ ይቻል ዘንድ በተቋሙ ፀድቆና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር በተመዘገበው የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት ምዝገባ እና አገልግሎት አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 145/2016ዓ.ም አንቀፅ 34(7) ኤጀንሲው የሚቀርቡለትን አስተዳደራዊ ጉዳዮች አይቶ ለከተማው ነዋሪ ጥቅም ውሳኔ እንዲሰጥ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህ አሰራር ለመምህራን ልማት ጥቅም በልዩ ሁኔታ ተዘርግቷል። የመምህራን ምዝገባን በተመለከተ ** * መሸኛ ከክ/ሃገር አምጥተው በነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ የሚያቀርቡና አስመዝጋቢ ያላቸው አሰራርን ተከትሎ ለመንግስት ሰራተኛ በተቀመጠው አግባብ አገልግሎት ያገኛሉ። ይሁንና አስመዝጋቢ ኖሯቸው በተለያዩ ምክንያቶች መሸኛ ማቅረብ የማይችሉ በትምህርት ቤታቸው በሚላከው የመንግስት ሰራተኛ የቅጥር ቅፅ ኮፒ አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን በሶስት ወር የግዜ ገደብ ውስጥ መሸኛቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ተከታትሎ ያስፈፅማል። * መልቀቅያ ከክ/ሃገር አምጥተው በነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ የሚያቀርቡ ነገር ግን አስመዝጋቢ የሌላቸው በወረዳው ትምህርት ቤት በሚከፈተው የነዋሪነት ምዝገባ ቅፅ አገልግሎት የሚያገኙ ይሆናል። * መልቀቅያ ከክ/ሃገር በተለያዩ ምክንያቶች ማምጣት የማይችሉ እና አስመዝጋቢ የሌላቸው በትምህርት ቤቱ በሚላከው የመንግስት ሰራተኛ የቅጥር ቅፅ ኮፒ መረጃ አገልግሎቱን የሚያገኙ ሲሆን በሶስት ወር የግዜ ገደብ ውስጥ መልቀቅያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ተከታትሎ ያስፈፅማል። የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እና የትምህርት ቤቶች ተግባርን በተመለከተ **** * በቅድሚያ የትምህርት ቤቱን የህንፃ ይዞታ እና መሰል መረጃ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በፊርማው አረጋግጦ የነዋሪነት ቅፅ በወረዳው እንዲከፈት በደብዳቤ ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ጥያቄ ያቀርባል። የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤትም መረጃውን አረጋግጦ ለወረዳው CRRSA ጽ/ቤት የነዋሪነት ምዝገባ ቅፅ በትምህርት ቤቱ እንዲከፈት በደብዳቤ ጥያቄ የሚያቀርብ ሲሆን ምዝገባ ለሚያደርጉት መምህራንም የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር የግዴታ ውል በአሰራሩ መሰረት ቀርቦ የሚፈርም ይሆናል። * የትምህርት ጽ/ቤቱ በዚህ አሰራር የሚስተናገዱ መምህራንን ሙሉ መረጃ እና የቅጥር ቅፅ በትምህርት ቤቱ ሲቀርብለት መረጃዎችን አደራጅቶና ትክክለኛነታቸውን አረጋግጦ ምዝገባ እንዲያደርጉ ለሚመለከተው የወረዳ  የCRRSA ጽ/ቤት በአባሪ ጥያቄ ያቀርባል እንዲሁም * አጠቃላይ ስራዎችን ከወረዳው CRRSA ጽ/ቤት ጋር መገምገም። የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊነት *** * በየወረዳው ያሉ ትምህርት ቤቶችን ለይቶ በደብዳቤ ለክ/ከተማው CRRSA ጽ/ቤት ማሳወቅ፣ * በወረዳ ጽ/ቤቶች በነዋሪነት የተመዘገቡ መምህራን መረጃ ማጥራት፣  ማረጋገጥ እንዲሁም መረጃዎቹን  በአግባቡ አደራጅቶ መያዝ፣ * አጠቃላይ ስራዎችን ከክ/ከተማው CRRSA ጽ/ቤት ጋር በየግዜው መገምገም። የትምህርት ቢሮ ሃላፊነት *** * በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶችን በደብዳቤ ለማዕከል CRRSA ማሳወቅ፣ * በወረዳ ጽ/ቤቶች በነዋሪነት የተመዘገቡ መምህራን መረጃ ማጥራት፣  ማረጋገጥ እንዲሁም አደራጅቶ በአግባቡ መያዝ፣ * አጠቃላይ ስራዎችን ከመምህራን ማህበር እና ከከተማው CRRSA ጋር በየግዜው መገምገም። ከዚህ ቀደም በተለያየ መልኩ ተከፍቶ የነበረ የት/ቤት ፋየል እንዲዘጋና እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል። በዚህ መልኩ ተመዝግበው አገልግሎት ሲያገኙ የነበሩ መምህራንም ወደ ተሻሻለው ወደዚህ አሰራር የሚገቡ ይሆናል። ማሳሰቢያ: ሃሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ ወይም ዳያጠሩ ለተቋሙ ማስተላለፍ በወንጀል ያስጠይቃል። ይህ አሰራር ከሚያዚያ 24 2016ዓ/ም ጀምሮ የፀና ሲሆን ለሚመለከታቸው ሁሉ በቂ ኦረንቴሽን በመስጠት የኦዲት ስርዓትን ባማከለ መልኩ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንድታስፈፅሙ ኤጀንሲው ያሳስባል። ከሰላምታ ጋር ግልባጭ// * በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር * ለስራ-አስኪያጅ ጽ/ቤት * ለከንቲባ ጽ/ቤት * ለትምህርት ቢሮ አዲስ አበባ **** * ለሃላፊዎች * ለህግ ጉዳዮች ክፍል ሲ/ም/ነ/አ/ኤ ****
Show all...
እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዬ በአል በሰላም በፍቅር  አደረሰን አደረሳቹ እያልን  ጤግሮስ ትሬዲንግ ከፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህ/ስራ ማህበር ጋር እና መኪና ከወሰዱ በጎ ፈቃደኛ አባላቶች ጋር በመተባበር  ለበአሉ ለተቸገሩ አረጋውያን እና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አድርገናል መልካም ፋሲካ። #Finot Saving & Tegros Yradong @mars@abc
Show all...
እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዬ በአል በሰላም በፍቅር  አደረሰን አደረሳቹ እያልን  ጤግሮስ ትሬዲንግ ከፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህ/ስራ ማህበር ጋር እና መኪና ከወሰዱ በጎ ፈቃደኛ አባላቶች ጋር በመተባበር  ለበአሉ ለተቸገሩ አረጋውያን እና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አድርገናል መልካም ፋሲካ። #Finot Saving & Tegros Yradong @mars@abc
Show all...
#ትንሣኤ ለመላው #የክርስትና_እምነት_ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ! በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሆን ዘንድ እንመኛለን ! #mars@abc
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ይሸጣል። Nisan Manual Model-2005 Price - 1.2M 0911485896
Show all...
" በየቤቱ የቁም እንስሳት ማረድ / በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል አልተከለከለም " - የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፥ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ " ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑ አሳወቀ። ከዚህም ጋር በተያያዘ #ምንም_ዓይነት_ክልከላ ያልተደረገ መሆኑን አረጋግጧል። ነገር ግን በየአካባቢው #በሕገወጥ_መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል። የከተማዋ ነዋሪዎችም ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። @tikvahethiopia
Show all...
ይሸጣል። Nisan Manual Model-2005 Price - 1.1M 0911485896
Show all...
ቀን:- 22/8/2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና ለነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መምህራን ጉዳዩ: የነዋሪነት ምዝገባ ጥያቂያችሁን ይመለከታል ከመምህራን ልማት ጋር በተያያዘ በነዋሪነት ያልተመዘገቡ መምህራንን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራን ሲሆን የሁላችሁም ጥያቄ የሚመለስበትን ግልፅ አሰራር እየዘረጋን መሆኑን እናሳውቃለን። በዚሁ መሰረት ዝግጅቱን አጠናቀን ከሃሙስ ሚያዚያ 24/2016ዓ. ም ጀምሮ አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑን እንገልፃለን። ከወዲሁ የቅጥር መረጃ ኮፒ እንድታዘጋጁ። ኤጀንሲው CRRSA
Show all...
"የቀበሌ መታወቂያ የሌላቸው የአዲስ አበባ መምህራንን ይመለከታል" የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር። 1. ዛሬ ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባደረግነው ውይይት የአዲስ አበባ መምህራን ተደራጅተው ቤት ለመስራት ማሟላት ከሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ የታደሰ የአዲስ አበባ ነዋሪነታቸውን የሚገልፅ የቀበሌ መታወቂያ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን በተለያዬ ምክንያት የቀበሌ መታወቂያ የሌላቸው መምህራንን በሚመለከት ዛሬ ሁለት አይነት መፍትሄ ተሰጧል(ውሳኔ ላይ ተደርሷል) 2.1. አሁን በፀጥታ ምክንያት መሸኛ ማምጣት የማይችል ክፍለ ሀገር የነበረ ማንኛውም መምህር መሸኛ ሳያመጣ የቀበሌ መታወቂያ እንዲሰጠው ተወስኗል። 2.2.  መሸኛ ማምጣት የሚችል መምህር ደግሞ ሶስት ወር የጊዜ ገደብ ተሰጦት መሸኛ አምጦ የቀበሌ መታወቂያ ይሰጠው ዘንድ ለመምህራን ብቻ ተወስኗል። ስለሆነም በዚህ አግባብ ትምህርት ቤታችሁ በሚገኝበት አካባቢ ባሉ ቀበሌዎች ፎርማሊቲውን በማሟላት የቀበሌ መታወቂያ ታወጡ ዘንድ እናሳስባለል። የትምህርት ቤቱ መሰረታዊ የመምህራን ማህበርም ይሄንን ለማስፈፀም እገዛ ታደርጉ ዘንድ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። መረጃው የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ነው።
Show all...
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ (ቀን:- 21/8/2016 ዓ.ም) የ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (ኦን ላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30 እና ሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6 እና 7/2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጀንሲ አሳውቋል::
Show all...
04:21
Video unavailableShow in Telegram
00:10
Video unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram