cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

✍️ቅድሚያ ለተዉሂድ

የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል: ”طَلَبُ العِلْمِ فَرِيْضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ" "እውቀትን መፈለግ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው” ሸሪዓዊ እውቀት ለህይወታችን ብርሃን ነው።ጊዜያችንን ሰጥተን ልንማር ይገባል። ወደግሩፑ ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇👇 Join & Share https://t.me/joinchat/RKbxKRecTtE0ODY0

Show more
Advertising posts
198
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንዳንዴ በተራዊሕም ይሁን የግዴታ ሶላት ላይ የት እንደሄድክ ሳታውቅ የኢማሙን ተክቢራ እና ማሰላመት ከሀሳብህ ያነቃህ ይሆናል። አላህ ይዘንልን። ያለ ማስተዋልና ያለ ማስተንተን እንደ እንጨት ቆመን የምንሰግዳቸው ሶላቶች ብዙ ናቸው። የቻልከዉን ያህል ቀልብህን ለመሰብሰብ ጣር፣ ከጌታህ ፊትም እንደቆምክ አስብ። ከሶላቱ አምስት ይሁን አሥር ፣ ሀያ ይሁን ሰላሳ፣ ሀምሳ ይሁን ሰባ አጁር የሚፃፍለት አለ። ሰው ሆኖ ከሶላቱ መቶ በመቶ የሚፃፍለት አለ ለማለት ይከብዳል። ለማንኛውም መዳኛህ ነዉና ሶላትህን አጥብቀህ ያዝ። ሕይወት በሁሉም መስክ ትግል ናትና በተሻለ ሁኔታ ለመገኘት ታገል። ~t.me/AbuSufiyan_Albenan
Show all...
☞በሚያፈጥሩበትም ሆነ ፆም በሚይዙበት ጊዜ ዱዓ ይወደዳል። ረመዷን ዉስጥ ከልቡ የለመነ ሸዋል ላይ፣ ከሸዋልም በፊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በርግጠኝነት ዉጤቱን ያያል። ⇛በረመዷን በቀንም ይሁን በማታ፣ በአፍጥር ይሁን በሱሑር በማንኛዉም ሰዓት ከዱዓ አትዘናጉ። የፆመ አንጀት ዱዓ ቢያደርግ ምላሽ አይነፈገዉም። የረመዷንን ዱዓ ችላ ያለ በርግጥ በራሱ ላይ ሰሰተ። ~t.me/AbuSufiyan_Albenan
Show all...
📚ቁርአንን ለመሀፈዝ የሚረዱ 6 ወሳኝ ነጥቦች » ① ኢኽላስ የሁሉም ነገር ቁልፍ ነው ስራ ላይ ኢማን እና ኢኽላስን ማጣት ትልቅ ክስረት ውስጥ ያስገባል ። የለፋህበትን የደከምክበት ሁሉ በአንዴ ያወድምብሃል ። ስለዚህ ልብህን ተጫንና በውስጥህ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ እያልክ ወደ 2ተኛው ምክር‥ ② አላማ አንድን ነገር ለመስራት አላማዬ ብለህ ከያዝክ ምንም ነገር አላማህን ከማሳካት አያግድህም ። ብቻ አንተ ውስጥህ ላይ ያለውን ፍላጎት ፣ ቆራጥነት ፣ ሀይልን እና ምኞትህን ቀስቅሰህ እችላለሁ በልና ወደ 3ተኛው ምክር‥ ③ ትኩረት ዛሬ ላይ መለኩል መውት መጥቶ በእርግጠኝነት ከ2 ወር በኋላ ትሞታለህ ቢልህ ምን ታደርጋለህ?? ⇛አንዱ በ2 ወር ቁርአን ሀፍዜ እጨርሳለሁ ይላል።ሌላው ደግሞ በ1 ወር ሀፍዤ እጨርስና ቀሪውን ኢባዳ ብቻ አደርጋለሁ ይላል‥ ይህ ሁሉ ችሎታ እና ሀይል አሁን የት አለ? ☞ሰው በተሰጥኦ ምናምን ይለያል ብለህ አታስብ። በተወሰነ % ቢኖርም ግን ሁላችንም ውስጥ ምኞት፣ ፍላጎትና ጉጉት አለ። እያንዳንዳችንም ፍላጎታችን ላይ መድረስ እንችላለን ብለህ እራስህን አሳምነህ ወደ 4ተኛው ምክር‥ ④ የምትሀፍዝበትን ጊዜ ወስነህ ለየው አብዛኛውን ጊዜ ቁርአን ለመሀፈዝ የተሻለ ጊዜ ነው የሚባለው ሰሁር የሚበላበት ጊዜ ነው ። ከዛ ቀጥሎ ከፈጅር ሰላት በኋላ ነው ። ሱሁር ላይ የተሻለበት ምክኒያት፤የሰው ልጅ በዛ ሰአት ከእንቅልፉ ሲነቃ አእምሮው ለመቀበል ክፍትና ዝግጁ ስለሚሆን ነው ። ⑤ አንድ አይነት ሙስሀፍ/ቁርአን ብቻ መጠቀም የአንድ አንድ ሙስሀፎች ገፅ አቀማመጥ ይለያያል ። እዚህኛው ሙስሀፍ ገፅ ላይ ያየኸው አንቀፅ በዛኛው ሙስሀፍ ገፅ ለይ ደግሞ ሌላ አንቀፅ ሊኖር ይችላል እና ሁሌም የምትቀራበትን ሙስሀፍ አዘጋጅ ። ⑥ ወንጀሎችን መራቅ የወንጀል ፅልመት እና የእውቀት ብርሃን በአንድ ቦታ ላይ ሊሰበሰቡ አይችሉም ። ⇛ የሰው ልጅ ወንጀል ሲሰራ ወንጀሉ ሀዘን ፣ ጭንቀት እና የመሰሰሉ ነገሮች ስለሚያመጣበት ሀሳቡ ሁሉ ይቀየርና ከበጎ ነገራቶች ያርቁታል ። ስለዚህም በተቻለን አቅም ወንጀል ከሚባሉ ነገሮች መራቅ ይኖርብናል ። አላህ ሁላችንንም ያግራልን ‥ ~t.me/AbuSufiyan_Albenan
Show all...
☑️ የተራዊህ ሶላት ለምትሰግዱ ስለ አሰጋገዲ ስረአትና ቅደም ተከተል አጭር ጥቆማ ።  ➙እነዚህ ተግባራቶችን በቅደም ተከተል እንስራቸው ኢንሻ አላህ ። ⓵))መጀመሪያ የኢሻ ሶላትን ስገዱ ! ⓶))ከዚያ ልክ የኢንሻን ሶላትን ሰግዳችሁ እደጨረሳችሁ  ወዲያው ከሶላት ቡሀላ የሚባሉትን አዝካሮችን በሉ ➂))ከዚያ ልክ አዝካሮቹን እደጨረሳችሁ የኢንሻን ራቲባ  ,ሁለት ረከአ ሱና ሶላት ስገዱ ። ➃))ከዚያ ተራዊህ ሶላት (8)ረከአ ስገዱ። ሁለት ሁለት ረከአ እያረጋችሁ የቻላችሁትን መስገድ ትችላላችሁ  ። ➄))በየአራቱ (4) እረከአ ጥቂት አጠር ያለች እረፍት ብትወስዱ መልካምነው ። ➅))ተራዊህ በምትሰግዱ ጊዜ ቁረአን ሀፊዝ ካልሆን(ካልሆሽ) ቁረአኑን እያየህ (ሽ)መቅራት ትችላለህ (ሽ) ወይም ትንሽም ቢሆን የሀፈዝከውን (ሽ)ካለህ (ሽ) የን እየደጋገምክም(ሽ) ቢሆን በዚያ መስገዲ ትችላለህ (ሽ) የቻልከውን የምታውቀውን ቅራ (ቅሪ)። ➆))ከዚያ ዊይትር ስገዲ (ሁለት ረከአ እና አንዲ ለብቻ)መስገዲ ትችላለህ (ሽ) _ባጠቃላይ ሶስት ማለትነው ።          ~ዊትር ስንሰግዲ የመጀመሪያ እረካ አላይ ሡረቱል  አእላን .سورةالاْعلى ሁለተኛው እረካአላይ ደግሞ ሱረቱል ካፊሩን سورة الكافرون በሶስተኛው ረከአ ላይ  ሱረቱል ኢህላስን سورة الأخلاص ብንቀራ የተወደደነው ። ⓼)) ከዚያም ልክ ዊትር እንደጨረስን (3)ጊዜ         ሡበሀነል ቁዱስ        ሡበሀነል ቁዱስ         ሡበሀነል ቁዱስ   እንበል ።።።።።።።። https://t.me/https_Asselfya https://t.me/https_Asselfya
Show all...
📚ቁርአንን ለመሀፈዝ የሚረዱ 6 ወሳኝ ነጥቦች » ① ኢኽላስ የሁሉም ነገር ቁልፍ ነው ስራ ላይ ኢማን እና ኢኽላስን ማጣት ትልቅ ክስረት ውስጥ ያስገባል ። የለፋህበትን የደከምክበት ሁሉ በአንዴ ያወድምብሃል ። ስለዚህ ልብህን ተጫንና በውስጥህ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ እያልክ ወደ 2ተኛው ምክር‥ ② አላማ አንድን ነገር ለመስራት አላማዬ ብለህ ከያዝክ ምንም ነገር አላማህን ከማሳካት አያግድህም ። ብቻ አንተ ውስጥህ ላይ ያለውን ፍላጎት ፣ ቆራጥነት ፣ ሀይልን እና ምኞትህን ቀስቅሰህ እችላለሁ በልና ወደ 3ተኛው ምክር‥ ③ ትኩረት ዛሬ ላይ መለኩል መውት መጥቶ በእርግጠኝነት ከ2 ወር በኋላ ትሞታለህ ቢልህ ምን ታደርጋለህ?? ⇛አንዱ በ2 ወር ቁርአን ሀፍዜ እጨርሳለሁ ይላል።ሌላው ደግሞ በ1 ወር ሀፍዤ እጨርስና ቀሪውን ኢባዳ ብቻ አደርጋለሁ ይላል‥ ይህ ሁሉ ችሎታ እና ሀይል አሁን የት አለ? ☞ሰው በተሰጥኦ ምናምን ይለያል ብለህ አታስብ። በተወሰነ % ቢኖርም ግን ሁላችንም ውስጥ ምኞት፣ ፍላጎትና ጉጉት አለ። እያንዳንዳችንም ፍላጎታችን ላይ መድረስ እንችላለን ብለህ እራስህን አሳምነህ ወደ 4ተኛው ምክር‥ ④ የምትሀፍዝበትን ጊዜ ወስነህ ለየው አብዛኛውን ጊዜ ቁርአን ለመሀፈዝ የተሻለ ጊዜ ነው የሚባለው ሰሁር የሚበላበት ጊዜ ነው ። ከዛ ቀጥሎ ከፈጅር ሰላት በኋላ ነው ። ሱሁር ላይ የተሻለበት ምክኒያት፤የሰው ልጅ በዛ ሰአት ከእንቅልፉ ሲነቃ አእምሮው ለመቀበል ክፍትና ዝግጁ ስለሚሆን ነው ። ⑤ አንድ አይነት ሙስሀፍ/ቁርአን ብቻ መጠቀም የአንድ አንድ ሙስሀፎች ገፅ አቀማመጥ ይለያያል ። እዚህኛው ሙስሀፍ ገፅ ላይ ያየኸው አንቀፅ በዛኛው ሙስሀፍ ገፅ ለይ ደግሞ ሌላ አንቀፅ ሊኖር ይችላል እና ሁሌም የምትቀራበትን ሙስሀፍ አዘጋጅ ። ⑥ ወንጀሎችን መራቅ የወንጀል ፅልመት እና የእውቀት ብርሃን በአንድ ቦታ ላይ ሊሰበሰቡ አይችሉም ። ⇛ የሰው ልጅ ወንጀል ሲሰራ ወንጀሉ ሀዘን ፣ ጭንቀት እና የመሰሰሉ ነገሮች ስለሚያመጣበት ሀሳቡ ሁሉ ይቀየርና ከበጎ ነገራቶች ያርቁታል ። ስለዚህም በተቻለን አቅም ወንጀል ከሚባሉ ነገሮች መራቅ ይኖርብናል ። አላህ ሁላችንንም ያግራልን ‥ ~t.me/AbuSufiyan_Albenan
Show all...
Photo unavailable
አዋጅ ~ ቂም ይዘን፣ በደል ተሸክመን ረመዷን ውስጥ ከመግባት ጥንቃቄ እናድርግ። ለበደለን ሰው - የሚገባው አይነት ከሆነ - ይቅርታ እናድርግ። የበደልነውን ሰው ደግሞ ይቅርታውን ለማግኘት እንጣር። በማህበራዊ መገናኛ "ይቅር በሉኝ" ከሚለው አዋጅ ይልቅ እንደ በደልናቸው የምናውቃቸውን ሰዎች ያለ ምንም ትእቢት፣ ያለ ምንም ሃፍረት፣ ያለ ምንም ግዴለሽነት ይቅርታቸውን ለማግኘት አስፈላጊውን ሰበብ ሁሉ እናድርስ። በርግጠኝነት ከነገ ውርደት ይልቅ የዛሬ ሽንፈት - ሽንፈት ከተባለ - የተሻለ ነው። = የቴሌግራም ቻናል :- t.me/IbnuMunewor
Show all...
በሳዑዲ ዐረቢያህ የረመዷን ጨረቃ ባለመታየቱ በአላህ ፍቃድ ነገ ረቡዕ መጋቢት 13 ሻዕባን 30 ሲሆን ሐሙስ ረመዷን አንድ ይሆናል። አላህ ወሩን ከሚጠቀሙበት ባሮቹ  ያድርገን።
Show all...
📜#የዱዓ . . . #አደቦች ዱዓ ፈጣሪያችን አላህ(ሱወ) የምንማፀንበት፣ ሐጃችን(ጉዳያችን) አላህን በመጠየቅ የምንፈታበት የዕባዳ አይነት ነው፡፡ ይህ ትልቅ ዕባዳ ደግሞ ለአላህ እንጂ ለማንም አይገባውም፡፡ ተናንሰን፣ ዝቅ ብለን ጉዳያችን ለሀያሉ አላህ(ሱወ) ከማቅረባችን በፊት ማሟላት ያለብን ነጥቦች የሚከተሉ ናቸው፡- ✅ 1. ጥሪት ያለች ዱዓ ለአላህ ማድረግ (ኢኽላሱ ሊላህ) ✅ 2. አላህ በማመስገንና በማወደስ ከዛም በነቢያችን ሰለዋት በማውረድ ዱዓን መጀመር በዚሁም መጨረስ ✅ 3. ቁሪጥ ያለ ዱዓ ማድረግ፤ ተቀባይነት እንደምያገኝ ደግሞ እርግጠኛ መሆን ✅ 4. በዱዓ ችክ ማለትና ለመልሱ ግን አለመቸኮል ✅ 5. በዱዓ ቀልብን መሰብሰብ ✅6. በምቾትና በችግር ጊዜ ዱዓ ማድረግ ✅ 7. አላህ እንጂ ሌላን አካል ላይለምን ✅ 8. በቤተሰቡ፣ በልጁ፣ በገንዘቡ፣ በራሱ ላይ ዱዓ እንዳያደርግ ✅ 9. ድምፅን ዝቅ አድርጎ ዱዓ ማድረግ ✅ 10. በሰራው ወንጀል አምኖ መሃርታ(ይቅርታ) መጠየቅ፤ አላህ የዋለለትን ፀጋ አምኖ ምስጋና ማድረስ ✅ 11. በዱዓ ላይ መተናነስ፣ መፍራት፣ መከጀል በልባችን ላይ ማሳደር ... ✅ 12. የተጣሉ (የተበዳደሉ) በማስታረቅ ወደ አላህ መመለስ ✅ 13. ሶስት(3) ጊዜ መደጋገም ✅ 14. ወደ ቅብላ አቅጣጫ መዞር ✅ 15. ዱዓ በሚያደርግበት ጊዜ የመዳፍ እጅ ወደላይ ማንሳት(ከፍ ማድረግ) ✅ 16. ከዱዓ በፊት ውዱእ ማድረግ ✅ 17. በዱዓ ድንበር አለማለፍ ✅ 18. ዱዓ ስጀምር ከነፍሱ(ከራሱ) መጀመር ✅ 19. በመልካም ስሞቹና መልካም ባህሪያቶቹ፣ በመልካም ስራው ወደ አላህ መቃረብ ✅ 20. እምበላው፣ እምጠጣውና እምለብሰው ከሐላል መሆኑን ✅ 21. ወንጀል ለመፈፀም ወይም ዝምድና ለማቋረጥ ተብሎ ዱዓ አለማድረግ ✅ 22. በኸይር ማዘዝና ከመጥፎ ነገር መከልከል ✅23. ከወንጀል መራቅ ✅ 24. ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸውን ሰዐቶችና ቦታዎች መምረጥ ሲሆን እነሱም ብዙ ናቸው፡፡ ከሌሎች ጊዚያ የበለጠ ዱአችን ተቀባይ የሚሆኑባቸው ግዝያቶች 🔹- እኩለለሊት 🔹- አዛን ሲደረግ 🔹- በአዛንና በኢቃም መካከል ባለችው ጊዜ 🔹- በሶላት ወቅት 🔹- በሱጁድ ወቅት 🔹- በጁም አቀን(ከሰላተል ዓስር በኃላ) 🔹- በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር 🔹- ውዱእ ካደረጉ ቡኋላ 🔹- የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት 🔹- በሐጅ ወቅት በተለይ በአረፋ ቀን 🔹- ዝናብ ሲጥል አሏህ ዱአችንን ይቀበለን።
Show all...
⇛አሥራ አንድ ወራት ያበላሸነዉን የአንድ ወር ረመዷን ያስተካክልናል። ረመዷን የለውጥ ወር ነው፣ የተዘበራረቀ ሕይወታችንን መስመር ያስይዝልናል። ከአላህ የተሰጠን ችሮታ ነውና አላህ በሰላም ደርሰው ከሚጠቀሙበት ያደርገን ዘንድ እንለምነው! ~t.me/AbuSufiyan_Albenan
Show all...
بـــــســــم الله الرحـــــمــــن الرحــــيـــم ←اولا اصيكِ ونفسي بتقوى الله يا عزيزتي 📜አላህ ይዘንልሽ እና በመቀጠል የማስታውስሽ፦_ .... 1ኛ, ለምን እንደተፈጠርሽ እወቂ! አንቺ ማለት በለውኸል መህፉዝ ላይ የተጻፍሽ/የምትታወቂ ከሩሁ በመንፋት ሰው የመሆንን፣ የባርነትን ቀንበር አሸክሞ በምድር ላይ ከዘራቸው አንዷ መሆንሽን አስታውሺ! ከሀላፊነትሽ የትም ማምለጥ አትችይም። ይሄን ሀላፊነት ለመወጣት ደግሞ አላህን በትክክል ማወቅ ግድ ይላል። قال ربي { إِنَّمَا یَخۡشَى ٱللَّهَ مِنۡ عِبَادِهِ ٱلۡعُلَمَـٰۤؤُا۟ۗ } ትክክለኛ መፍራትን አላህን የሚፈሩት እኮ ከባሪያዎቹ አዋቂ የሆኑት ባሮቹ ናቸው ይላል። ☞ድንን ማወቅ አምላክ ጋር መዳረሻ ድልድይን መገንባት ነው። ድንን ማወቅ የስኬት መሰረት ነው የተፈጠርንበት ህግ፣ የነብያት አደራ ነው ሰለፎች ያለፉበት ጎዳና እና ዋጋ በመክፈል ለእኛ ያስተላለፉልን (ርስት) ነው። አምኛለው ያለ ሁሉ ሊያውቀው፣ ሊጠብቀው፣ ለቀጣይ ትውልድ ሊያስተላልፈው ግድ ነው ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ ሢባል፦ ቤተሰብሽን ከማስተማር ይጀምራል ግደታ ትላልቅ መድረክ ላይ መገኘት ላይሆን ይችላል--- ድንን መገንዘብ ትክክለኛ ሰው የመሆን ትርጉም ነው።አላህን ለማወቅ ፣መልእክተኛውን ለመከተል ካልተማርን፣ ካልጣርን የመኖራችን ትርጉም ምንድን ነው!? ህይወትስ በውስጧስ ያሉት ነገሮች ምንድን ናቸው ?? قال امام الشافعي وَمَن فاتَهُ التَعليمُ وَقتَ شَبابِهِ فَكَبِّر عَلَيهِ أَربَعاً لِوَفاتِهِ "በወጣትነቱ ዒልምን ሳይማር/ሣይፈልግ ያለፈው ሰው እንደሞተ ይቆጠራልና ለሞቱ አራት ተክቢራን ከብርበት" ብለዋሉ(ኢማሙ ሻፊዒይ)-- መእልክተኛውም እንዳሉት፦ صلى الله عليه وسلم قال أبي هريرة: سمعت رسول الله ﷺ يقول: ألا إن الدنيا ملعونة، ملعون ما فيها إلا ذكرَ الله تعالى وما والاه، وعالماً ومتعلماً رواه الترمذي، وقال: حديث حسن. ☞አዋጅ! ዱንያ በውስጥም ያለው ሁሉ አላህን ማውሳት ወይም የሚማር እና የሚያስተምር{ወደ አላህ የሚያዳርሰውን እውቀት የሚፈልግ}ሢቀር የተረገመች ናት። ብለዋል። 2ኛ ራዕይ ይኑርሽ! ራእይ ያለው ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት ጠንቅቆ ሥለሚያውቅ ግራ በመጋባት፣ በመደበር፣ ራሱን አያባክንምራእይ ከሌለሽ መኖር እጅጉን ያስፈራል፣ ያለ ራእይ የህይወትን ጎዳና ማቋረጥ እጅጉን አድካሚ ነው so የምትኖሪለትን ነገር እወቂ፣ መነሻሽን እና መድረሻሽን ለይ፣ልፋትሽም ድካም ብቻ ሆኖ አይቀርም እናም፦እኔ ማነኝ፣ የት ነው መድረስ የምፈልግ፣ በህይወቴ ላሳካው የምፈልገው ነገር ምንድን ነው!የህይወት መዝገቤ ላይ ምን ተብዬ ነው መሰየም የምፈልገው! ለምንድን ነው የምኖረው! ዛሬን የምሰራው፣ ነገን የማስበው ለምንድን ነው! እያልሽ ራስሽን ጠይቂ መልሱንም አግኚ!። 3ኛ የተመቻቸ ጊዜ እና ቦታ አለመጠበቅ። በምድር ጀርባ ላይ እስካለሽ ድረሽ አንቺ የምትፈልጊውን ለማድረግ ራስሽ ጊዜውን ትፈጥሪዋለሽ እንጂ የተመቼ ጊዜ መቼም አይመጣም። ቆጥ ላይም ተንጠልጠይ፣ ተራራ ላይም ተሰቀይ የምድር ሢኦልም ላይ ሁኚ የትም ሁኚ የት በህይወትሽ መሆን የምትፈልጊውን ለመሆን፣ ማግኘት የምትፈልጊውን ለማግኘት ባለሽበት ሁኔታ ላይ ሁነሽ ታገይ እንጂ የተመቻቸን ጊዜ አትጠብቂ። ምክንያቱም የለም። 4ኛ ለስንፍናሽ፣ እና ለራስሽ ድክመት ምክንያተኛ አትሁኚ! አንድትችይ አድርጎ ፈጥሮሽ ሣለ አስችለኝ እያል ስትጸልይ አትኑሪ ወይም የሆነ ተአምራይዊ ነገር እስከሚከሰት አትጠብቂ ምድር ላንቺ ብላ ገነት አትሆነም ጎበዝ ከሆንሽ በህመሞቿ መካከል ሁነሽ ተዋጊና ድል አድርጊ።እኔኮ ስላልተማርኩ ነው፣ የሚረዳኝ ስለሌለ ነው፣ ፈሪ ስለሆንኩ፣ ድሀ ስለሆንኩ፣ መልኬ ስለማያምር፣ ተወዳጅ ስላልሆንኩ፣ ጊዜ ስለሌለኝ፣ whatever...በህይወትሽ ለውጥ ከፈለግሽ ምክንያትን አስወግጂ።ምናልባት ምክንያትሽ ትክክል ሊሆን ይችላል ነገር ግን መንገድሽን፣ ሀይልሽን፣ ከማጠር ውጪ የትም አያደርስሽም። 5ኛ በቻልሽው መጠን ከራስሽ ጋ እውነተኛ ሁኝ! ከህሊናው ጋ እውነተኛ ያልሆነ እና ራሱን የማይመራ ሰው ማንንም መምራት አይችልም። ከራስሽጋ እውነተኛ ስትሆኚ መማር ያለብሽን፣ መስራት ያለብሽን ነገር ሣትዘናጊ ሰአቱን አክብረሽ ታደርጊያለሽ አደርጋለው ብለሽ ያልሽውን ነገር የራስሽን ህግ በማክበር አድርጊው ካልሆነ ከህሊናሽ ጋ ጦርነት ስለምትከፍቺ በራስሽ አለም ተቀባይነትን ታጫለሽ 6ኛ ጥሩ ጓደኛ መምረጥ! ምንም ጠንካራ ብንሆን ሰው በዙሪያው ባሉ ሰዎች ቀስ እያለም ቢሆን ወደነርሱ ይሳባል እናማ አላማ ከሌላቸው ሰዎች መራቅ ስብእናቸው ካልተገራ፣ ያልሆነ ቦታ ላይ ሢያዩሽ ተይ ከማይሉሽ ሰዎች በመራቅበአላህ መንገድ ላይ የሚያበረታቱሽን ሰዎች መወዳጀት።   7ኛ ጊዜን በፕሮ ግራም መጠቀም! 8ኛ ሰው መሆንሽን እና በቂ መሆንሽን እመኚ! ሰው ማለት አምላክ ከስንት እና ስንት ፍጡሮች በላይ ያላቀው  ከድንቅ ብቃት ጋ የተፈጠረ ግሩም ፍጥረት ነው ﴿ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَى كَثِيرٍ مِمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلا﴾ በመጨረሻም፦ እንደምትችይ በትንሹ ላስታውስሽ ከያዝነው ስልክ ጀምሮ ለእኛ ተአምር የሚመስሉን ነገሮች ሁሉ በሰው አዕምሮ የተቀመሩ የሀሳብ መዋቅሮች ናቸው እመኚኝ የእውነት በትክክለኛው መንገድ እስከጣርሽ ድረስ የምትፈልጊያትን ሴት ትሆኛለሽ አንቺ መሆን ለምትፈልጊው ነገር በቂ ነሽ። እንድትችይ አድርጎ ፈጥሮሻልና። ከሚያነቡት 📜«እህታዊ ምክር ከ እህትሽ ሰልዋ» جعلني الله وإياكِ من الذين يقرؤون فيتبعون أحسنه أقول قولي هذا وأستغفر الله لي ولكِ انه هو الغفور الرحيم
Show all...