cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

◆የሃጃዊራ ጥመት በየመንና በሀበሻ◆

ألا إن التحجر خبيث قد بان خبثه                       المجموعة تختص بالرد على الحجاورة ونشر التوحيد والسنة والتحذير من الشرك والبدع والمبتدعة. ★كيف نطهر زيف شبه حجاورة اليمن والحبشة ومن دونهما؟ !!!! فستبصر ويبصرون!!! ቻናላችንን ለመቀላቀል: t.me/hajuriyaa

Show more
Ethiopia6 612Amharic6 364The category is not specified
Advertising posts
772
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-1930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቀጥታ ስርጭት በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሃፊዘሁላህ ይግቡና ይከታተሉ https://t.me/IbnuMunewor?livestream
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

በዑዝር ቢልጀህል ጉዳይ ሚዛን መጠበቅ ያስፈልጋል ~ አላዋቂ ሰው ከኢስላም የሚያስወጣ ጥፋት ቢፈፅም "ከኢስላም ወጥቷል ተብሎ ይበየንበታል ወይስ ባለማወቁ ይታለፋል?" የሚለው ጉዳይ ንትርክ ያለበት ርእስ ነው። ትክክለኛውን አቋም መለየት እንዳለ ሆኖ በጉዳዩ ላይ ሁለት #ጫፍ የወጡ አቋሞች ይስተዋላሉ። 1ኛው ጫፍ፦ "ዑዝር የለም" የሚሉ ሰዎችን በተክ^ፊርነት ወይም በኸዋ ሪጅነት መፈረጅ ነው። ይሄ ስህተት ነው። ከዑለማዎች ውስጥ "ዑዝር የለም" ያሉ እንዳሉ የሚታወቅ ነው። ይህንን ርእስ በማራገብ የሚታወቁት በብዛት የጥመት አንጃዎች ሆነው ስላየን ብቻ በደፈናው ዑዝር የማይሰጡ አካላትን ሁሉ በኸዋ ሪጅነት ከመፈረጅ መጠንቀቅ ይገባል። 2ኛው ጫፍ:- "ዑዝር መስጠት ይገባል፣ አላዋቂን ማክ^ ፈር አይገባም" የሚሉትን በሙርጂአነት የሚፈርጁ ከዚህም አልፎ ከኢስላም የሚያስወጡ ናቸው። ይህም የለየለት ፅንፈኝነት ነው። በኢስላም ታሪክ ከጥንት እስከ ዛሬ ዑዝር የሚሰጡ ዓሊሞች አንድና ሁለት አይደሉም። ዑዝር መስጠትን የሚደግፉ ማስረጃዎችም ብዙ ናቸው። ሐቁ ያለውም እዚህ ላይ ነው። "ዑዝር የለም" የሚለው አቋም ጥቅል መረጃዎችን ያላግባብ የሚመነዝር፣ መረጃዎችን ያለ አውዳቸው የሚያውል፣ ከሙግቱ ውጭ ያሉ መረጃዎችን ያላግባብ የሚያዛምድ ነው። በዚያ ላይ በመረጣ የሚፈፀም እንጂ በወጥነት የሚተገበር አይደለም። "ዑዝር የለም" የሚሉ አካላት ይህንን አቋማቸውን ወጥ በሆነ መልኩ ቢተገብሩት ኖሮ የሚያጣቅሱት ዓሊም አያገኙም ነበር። ምክንያቱም ዑዝር የሰጧቸው አካላት በተጨባጭ አሉና። መዝዘንጋት የሌለበት ነጥብ የዑዝር ቢልጀህል ጉዳይ ልክ እንደ ሌሎች የኢጅቲሃድ ርእሶች መሆኑ ነው። ዑለማእ የተለያየ ሃሳቦችን የሰነዘሩባቸውን ሌሎች ርእሰ ጉዳዮችን በልክ እንደምንይዘው ይህንን በልክ መያዝ ይገባል። በሌሎች ጉዳዮች ላይ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃዎችን እያገናዘብን ሚዛን የሚደፋውን ለመምረጥ እንደምንጥረው ሁሉ ዑዝር ቢልጀህል ላይም ተመሳሳይ አካሄድ እንሄዳለን። በሌሎች የኢጅቲሃድ ርእሶች ላይ የአንድ ዓሊም ንግግር በተለየ እንደ ወሕይ እንደማይወሰደው በዑዝር ቢልጀህል ላይም እንደ ወሕይ ተወስዶ በሌሎች ዓሊሞች ንግግሮች ላይ ዳኛ የሚሆን የዓሊም ንግግር የለም። ይህንን የማነሳው በዚህ ጉዳይ ላይ የሸይኽ ፈውዛንን ንግግር በተለየ በማራገብ ሌሎችን በኢር ጃእ ለመወንጀል፣ አለፍ ሲልም ከኢስላም ለማስወጣት የሚጠቀሙ ሰዎችን ስለማይ ነው። ወንድሜ በአልባኒ ማስፈራራት እንደማይቻለው ሁሉ በፈውዛን ማስፈራራትም አይቻልም። የፈውዛን ወይም የኢብኑ ባዝ ንግግር ከኢብኑ ተይሚያ፣ ከአልባኒ ወይም ከኢብኑ ዑሠይሚን ንግግር በተለየ እንደ ወሕይ የሚቆጠርበት ሚዛን የለም። የሁሉም ንግግር የዑለማእ ንግግር ነው። ከማስረጃ ጋር የሚገጥመውን ከመውሰድ ባሻገር አንዱ መዛኝ ሌላው ተመዛኝ የሚሆንበት መመዘኛ የለም። በቃ አንተ የአልባኒ አቋም ስህተት ነው ለማለት አይሰቀጥጥህም አይደል? እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ የፈውዛን አቋም ስህተት ነው ለማለት ቅንጣት አይሰቀጥጠኝም። እንጥፍጣፊ ሚዛናዊነት ካለህ በዚህ ውስጥ ክስና ጩኸት የሚያስነሳ ነገር የለም። የችግሩ አስኳል ጉዳዩ ዑለማእ የተለያየ ሃሳብ የሰነዘሩበት ጉዳይ መሆኑን መዘንጋት ላይ ነው። ይህንን ነጥብ በሚገባ የተነገዘበ ሰው ልክ ነው ብሎ የሚያምንበትን ነጥብ ከመውሰድ አልፎ ፍረጃ ውስጥ ገብቶ ራሱን አደጋ ላይ አይጥልም። የሚያደረገው ልክ በሌሎች የኢጅቲሃድ ርእሶች ላይ እንደሚያደርገው ጉዳዩን ከስሜት ነፃ ሆኖ በመመርመር ሚዛን የሚደፋውን መለየትና የገባውን ማስረዳት ብቻ ነው። Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

የየመኑ ሸይኻቸው እነ ሙስጦፋን ጀርቡዒያዎች አላቸው አኩርፋቸው አታናግሯቸው አላቸው #صراعات_الحجاورة_الداخلية #حجاورة_أثيوبيا عبدالحميد الحجوري يحذر من إحدى فِرق #الحجاورة في الحبشة (أثيوبيا) وهي فرقة مصطفى عبدالله ويسميهم بالفرقة الجربوعية ‼️ ويبدعهم بأنهم خوارج وتكفيريون‼️ ويفتي بهجرهم‼️ (النار تأكل بعضها إن لم تجد ما تأكله) የድምፅ ፋይሉ ያው! t.me/abumuazhusenedris
Show all...
አንድ መልእክት ለዱዓት ~ በደዕዋ ላይ ላይ ከሚታዩ መሰናክሎች ውስጥ አንዱ የዱዓት አለመጣጣም ነው። ለዚህ አለመጣጣም ቀዳማዊ ምክንያት የዱዓት ነፍሲያን መከተል ነው። ለሌላ መትረፋቸው ቀርቶ ጭራሽ ሸክም መሆን። ወንድሜ! ይሄ ህዝብ ሞልቶ የተትረፈረፈ ብዙ አጀንዳ አለው። የግላችንን አመል አደባባይ እያመጣን ሌላ በሽታ አንደርብበት። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አብዛኞቻችን በነፍሲያ የተተበተብን ሆነናል። "ህዝባችን ደዕዋ የተጠማ ነው፣ ደዕዋውን ለማሰናከል አድብተው የሚጠብቁ ሴረኞች ስላሉ በጥንቃቄ ተጓዙ" የሚል አደራ የተሰጣቸው ኡስታዞች አመላቸውን መግራትን እንደ ሸንፈት፣ የሌሎችን ጥንቃቄ እንደ ፍርሃት እየቆጠሩ ጅምር ስራዎችን በታትነው፣ ደዕዋውን አጠልሽተው ያርፋሉ። ብዙ ቦታዎች ላይ የሚያጋጥም ፈተና ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ከሚታዩት ውስጥ ከፊሎቹ ከእድሜ አንፃር የወጣትነትን ግለት የተሻግሩ መሆናቸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በስልት ራስን መኮፈስ፣ ራስን ልዩ አድርጎ ማየት፣ ሌሎችን መናቅና ማጣጣል፣ ሌሎችን በማጣጣል የራስን ስም መገንባት ላይ መጠመድ ብዙዎቻችን ዘንድ ያለ በሽታ ነው። ወንድማለም! ራስህን ልዩ አድርገህ አትመልከት። የእውነት የደዕዋ ጉዳይ የሚያሳሳብህ ከሆንክ ደዕዋ ላይ ያሉ ወንድሞችህን እንደ አጋሮችህ፣ አጋዦችህ እንጂ እንደ ተቀናቃኝ ከመመልከት ውጣ። ሌሎችን በማጣጣል ራስን የመቆለል ቆሻ ሻ በሽታን ከልብህ አውጣ። ሁሌም ትህትናን ተላበስ። ራስህን ዝቅ አድርግ። በሆነ ነገር ከሌሎች እንደምትሻል ከተሰማህ ሌሎቹ በሌላ ነገር ካንተ እንደሚሻሉ አስብ። ሰበር ብትል የእውነትም አንተ ጋር የሌለ ብዙ መልካም ነገር ሌሎች ላይ ታገኛለህ። ራስህን በሚገባ ግራ። በተለይ ክፍለ ሃገር ላይ ያላችሁ ዱዓቶች ከልብ አስቡበት። ደዕዋ ላይ ላሉ ወንድሞች ሞራል እንጂ ውጋት አንሁን። በዚህ ዘመን በደዕዋው ዘርፍ ላይ ያለው ምቀኝነትና ክፋት በዱንያ ጉዳዮች ላይ ከሚታየው በሽታ በጣም የራቀና የባሰ ነው። ይሄ ብንደብቀው እንኳ የማይደበቅ አሳፋሪ ግን በገሃድ የሚታይ ነውር ነው። በግል ጉዳይ በሆነ ወንድሙ ላይ ያቄመው ሁላ በደዕዋ ሽፋን ላንቃው እስኪበጠስ እየጮኸ ህዝብ ማደናገር በጣም የተለመደ ሆኗል። ወንድሜ በዚህ ዘመን ያለው እንቅፋት ብዛት በርብርብ ለመጋፈጥ እንኳ የሚፈትን ነው። ትብብሩ ቢቀር አንዱ ሌላውን ከደዕዋ መስክ ለማውጣት አለፍ ሲልም ለማጥፋት መነሳት ግን ለደዕዋው እዳ መሆን፣ ተያይዞ መክሰም ነው የሚያስከትለው። ከፍትጊያው መጨረሻ ደግሞ የሚያተርፈው ሌላ ነው። ስለዚህ ከወንድምህ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ክፍተቶችን #እየተራረምክ ተደጋግፈህ ለመጓዝ ሞክር። ይሄ ካልሆነልህ ከነ ድክመቱ እያስታመሙ የሆነን ቀዳዳ እንዲሸፍን መተው የተሻለ ሊያተርፍ ይችላል። ልትሰብረው ወይም ከደዕዋው ዘርፍ አሽቀንጥረህ ልታስወጣው ከመነሳትህ፣ ልቡ ባንተ እንዲያዝን ከማድረግህ በፊት ደግመህ ደጋግመህ አስብበት። "እኔስ ብዬሽ ነበር የዓይኔ ጉድፍ አውጪ መዋጥ ይዘሽ መጣሽ ዓይኔን ልታወጪ!" እንዲል አታድርገው። . ማሳሰቢያ፦ የማወራው ሱና ላይ (ተመሳሳይ መስመር ላይ) እንዳሉ ለሚያምኑ ዱዓት ነው። = Ibnu Munewor የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me//IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ስለ ትዳር! (የግል ትዝብት) https://t.me/EzedinSultan14 ገና ካገባው 5 አመቴ ሆኖ ለመምከር ስለቃጣው በመጀመርያ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ሰፋ አድርገን ለመወያየት መነሻ ሀሳብ ይሆነናል ከሚል ነው። ስለ "ወጪ" ነው የምናወራው! ብዙዎች ትዳራቸውን የአሳዳጅና ተሳዳጅ አይነት አድርገውታል። ትዳር መርጊያ፣ ማረፍያና መስከኛ ነው። እያንዳንዱን እርምጃ በመግባባት፣ በመነጋገር፣ በመመካከርና በመተሳሰብ መሄድ ግድ ይላል። ትዳር ላይ የሚፈጠርን ቅራኔ ወደ አንድ ወገን መለጠፍ በፍፁም አግባብ አይሆንም። ለችግሮቻችንም ቋሚ መፍትሄም ለማግኘት አያግዝም። ከነዚህ የጥል መንገዶች ውስጥ የወጭ ጉዳይ አንዱ ነው። ትዳር ላይ ቤቱ የሚያስፈልገውን ወጭ መሸፈን በወንዱ የተጣለ ግዴታ ነው። ሴቷም ባሏ የሰጣትን በአግባቡ መጠቀምና አስፈላጊ ለሆነ ነገር ያለ ብክነት ማዋል ግድ ይላታል። ታድያ ጥቂት የማይባሉ ትዳሮች በወጪ አማካኝነት ተናግተዋል አልፈውም ለፍቺ ተዳርገዋል። ሰከን ብለን ካየነው በሁለቱም ወገን ባለ ችግር አማካኝነት ነው። ወንዱ/ባል፦ ብክነትም ቋጣሪነትም ትዳር ላይ ችግሮች ናቸው። አንዳንዱ ውጭ ብሩን ይዘራል፣ ላለፈ ላጋደመ ሁሉ ብሩን ይበትናል፣ ለቤቱ ከማድረግ ለውጭ ማሳየት ይቀናዋል፣ እየጠራ ይጋብዛል፣ ሂሳብ ካልዘጋሁ ይላል፥ ቤት ውስጥ ሚስቱ ታማራለች ጥሩ ገቢ እንዳለው እያወቀች ቤቱ ውስጥ ባል ወጭ በአግባቡ አይሰጥም። ውጭ ያለ አግባብ በበተነው ቤቱ ላይ ይቋጥራል። አንዳንዶች ደግሞ የቋጣሪነትና የስስታምነት ምሳሌ ናቸው። ሲበዛ ይሰስታሉ፣ ባላቸው ገቢ ልክ ቤተሰባቸውን አያኖሩም። ሚስታቸውን በአባካኝነት ይፈርጃሉ፣ ልጆቻቸውን ከአቻዎቻቸው ያሳንሳሉ። ለከፋ የስነ ልቦና ጫና ዳርገዋቸው ተወሽቀው ይኖራሉ። በራስ መተማመናቸውን አጥተው ያድጋሉ። በአባት ስስታምነት የተነሳ። ውጭ ሩብ የማትሞላ ስጋ(አሁን እንደ ክኒን በፍሬ ሆኗል) 300 ብር ይከፍላል በሳምንት አንዴ አንድ ኪሎ ስጋ ለቤቱ መግዛት ሞት ይሆንበታል። ይህ አይነት ባል ባልሰጠው እንዲስተናገድ ይፈልጋል። ልቡ እያወቀ ሚስቱን ይወጥራታል። እንደ መርየም ቀጥታ ከላይ የሚወርድላት ይመስለዋል። ያልሰጡትን መጠበቅ ምን ያህል ራስ ወዳድነትና የስስታምነት ጥግ ነው!? አንዳንዱ ደግሞ ቤቱ ላይ በሚያደርገው የሚመፃደቅ አለ። ግዴታውን እንደተወጣ ሳይሆን ምስኪን/ችግርተኛ እንደረዳ ይሰማዋል። እንዲህ አይነቱ ላይ 40 ማዘዝ ነበር! ሴቷ/ሚስት፦ አንዳንድ ሴቶች ያለፈ የተጋደመ ሁሉ ያምራቸዋል። የቤቷን ሳይሆን የጎረቤቷን መኖር ትሻለች። ውጭ ያየችው ሁሉ ቤቷ እንዲሆን ትመኛለች። መመኘት ብቻ ሳይሆን ካላደረክልኝ ብላ ትወጥረዋለች። በቤቷ መርጋትን አትሻም። ገቢውን እያወቀች ከገቢው በላይ ትጠይቀዋለች። ጀገን ያለ ባል ከሆነ ይመክራል፣ ይገስፃል። አልሸነፍ መሳይ ከሆነ ሰርቆም፣ አጭበርብሮ ለዘብ ካለ ተበድሮ ያደርጋል። የሱ ጉዳት ለቤቱ አይመስላትም። የሱ እዳ ላይ መውደቅ ቤቷን የሚያናጋ አድርጋ አታስብም። ብቻ ፍላጎቷና ስሜቷ ይሟላላት። ከተደረገላት በላይ የጎደላት ሁሌ ገዝፎ ይታያታል። ባለሏን ከጎደኛዋ ባል እያወዳደረች ያንስባታል አለፍ ሲልም ትንቃለች። ንቀት ደግሞ ወደ አለመታዘዝ ይመራል። መጨቃጨቅና መጣላት ይከተለዋል። እውነታው፦ አንተም ወንድሜ ወንድነት ወጥሮህ ሚስትህ ላይ ከገቢህ በላይ እንደምታኖራት አትሙላት። እውነታውን አስረዳት ገቢህ ለቤት ወጭ፣ ለቤተሰብ፣ ለህክምና እንዲሁም መቆጠብ እንዳለበት አስረዳት። ሴት ካመነችበት ባይኖርህም ታናኑርሀለች። አሳምናት፣ አላህ ሲከፍትልህ ደግሞ ከፈት አድርገህ አስደስታት። ቁጠባ ለወደፊት ስንቅ ነው። ግን ስስታምነትና ቋጣሪነት ካጠቃህ ግን እመነኝ ጋንግሪን ነው። ካልተቆረጠ አይድንም፣ ቁረጠው። አንቺም እህቴ፦ ባልሽ ያንቺ ነው። ያለብሽን ክፍተት በግልፅ ንገሪው። ገንዘብ ለማያዋጣልሽ የባልሽን ነገር አትዝሪ። አንዴ የዘራሽው ሰዎች ውስጥ ይቀርና ባልሽ ቢለወጥ እንኳ ከነሱ ልቦና አይፋቅም። ገቢያችሁን አብቃቅቶ ለመጠቀምና እራሳችሁን ለመቀየር አልሚ። ብልጭልጭ አይሸውድሽ። የባልሽን ስነልቦና ከፍ ባደረግሽ ቁጥር የመስራት ሞራሉ ይነሳሳል። አቅሙን መጠቀም ይችላል። በየቀኑ ቶርች ካደረግሸው ታዳክሚዋለሽ። ተሰባብሮ ይቀራል። ጣጣው የጋራ ነው። አንባቢ ሆይ! ረጅም ፅሁፍ እንደሆነ ይገባኛል፣ ግና አጭር ኮሜንት ለመስጠት አትሰስት፣ የመሰለህን ከስር አስፍርና እንወያይ! ወንድማችን ኢዘድን ሱልጣን አላህ ኸይር ጀዛክን ይክፈልህ ጥሩ ጥቆማ ነው ለሚመከርበት ብቻ የዚህ ኡማ ችግር ዘርፈ ብዙ ስለሆነ እናመሰግናለን! @JemalEndroAbuMeryem
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
              🌹 * ዒድኩም ሙባረክ * 🌹 عيدكم مبارك! تقبل ﷲ منا ومنكم صالح الأعمال! ኢዳችሁ የተባረከ ይሁን! አላህ ከኛም ከናንተም መልካም ስራችንን ይቀበለን! ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ አቡ መርየም ከወሎ –ወረኢሉ @JemalEndroAbuMeryem https://t.me/tewuhidWereilu/5081
Show all...
ተጀምሯል ቀጥታ ስርጭ በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ 🎤 መግቢያ ኡስተዝ አቡ ሙአዝ 🕌 በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ https://t.me/YeZemzemMesjidJemea?videochat=6b3ea99ffd01e4d183
Show all...
የወረኢሉ ከተማ እና የወረኢሉ ወረዳ አህለልሱና ወልጀመዓ ዘምዘም መስጅድ ገቢ ማሰባሰቢያ የቴሌግራም ግሩፕ

አላማችን ተውሂድን የበላይ ማድረግ ነው ! 1000469868587 ወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ

ዛሬ እሁድ በጧቱ እግሮች ወደ ወረኢሉ ዘምዘም መስጅድ ማሳሰቢያ ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ! ዳዕዋው የሚጀምረው በጧት መሆኑን አይዘንጉ! 11/10/2015 እሁድ https://t.me/YeZemzemMesjidJemea
Show all...
የወረኢሉ ከተማ እና የወረኢሉ ወረዳ አህለልሱና ወልጀመዓ ዘምዘም መስጅድ ገቢ ማሰባሰቢያ የቴሌግራም ግሩፕ

አላማችን ተውሂድን የበላይ ማድረግ ነው ! 1000469868587 ወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ

Show all...
ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ ! "ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? " ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል ! ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር @Haqnfilega_bot @JemalEndro

ቀጥታ ስርጭት በኡስታዝ አቡ ሙአዝ አልወጅዝ ኪታብ ገፅ 123 አል መዋላቱ ሊል ሙዕሚኒነ ወሙዓደቲ ሊል ካፊሪን ወረኢሉ ዘምዘም መስጅድ በይነል መጝሪብ ወል ኢሻእ https://t.me/daewaselefiyaArbaminch?livestream=0a92b40e79d4d35af1
Show all...
ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ ! "ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? " ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል ! ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር @Haqnfilega_bot @JemalEndro