en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Open in Telegram
2 370
Subscribers
+1124 hours
+997 days
+37430 days
Posts Archive
የኮሌጃችን የቀድሞ አሰልጣኝ መምህርት የተለያዩ መፅሃፍቶችን በስጦታ መልክ ለኮሌጁ አበረከቱ:: ላለፉት 30 አመትና ከዚያ በላይ በቢዝነስ መምህርነት በኮሌጃችን እንዲሁም በተለያዩ የትምህርት ተቋማት
የኮሌጃችን የቀድሞ አሰልጣኝ መምህርት የተለያዩ መፅሃፍቶችን በስጦታ መልክ ለኮሌጁ አበረከቱ:: ላለፉት 30 አመትና ከዚያ በላይ በቢዝነስ መምህርነት በኮሌጃችን እንዲሁም በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ሲያገለግሉ የቆዩትና በቅርቡ የአገልግሎት ዘመናቸውን አጠናቀው በክብር የተሸኙት መ/ርት ገነት መኮንን በመምህርነት ዘመናቸው ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተያዩ ከ200 በላይ መፅሃፍቶችና የተለያዩ ዶክመንቶችን በማሰባሰብ የኮሌጁ ማህበረሰብ እንደግብዓትነት ይጠቀምባቸው ዘንድ በዛሬው እለት በአካል በመገኘት መፅሃፍቶቹን ለኮሌጁ አስረክበዋል:: መፅሃፍቶቹን የተረከቡት የኮሌጁ ም/ዲን እና የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስራ ሂደት ሀላፊ አቶ ኤልያስ አህመድ ሲሆኑ ይህ አይነት ተግባር የሚያስመሰግንና ለሌሎችም አርዓያ የሚሆን ተግባር መሆኑን በመግለፅ ለመ/ርት ገነት መኮንን ላበረከቱት በዋጋ የማይተመን ስጦታ በኮሌጁ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል:: ኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ነሃሴ 11/2016 ዓ.ም

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ "ክረምትን በክህሎት"በሚል በተዘጋጀው የክረምት ስልጠና ለመሰልጠን የተመዘገቡ የአስተዳደሩ ወጣቶች በኮሌጁ ተገተው ስልጣናቸውን ጀመሩ:: ወጣቶቹ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የክህሎት ስልጠና ለመሰልጠን የተመዘገቡ ሲሆን ወደ ስልጠና ከመግባታቸው አስቀድሞ በኮሌጁ ስለሚሰጡ ስልጠናዎችና በክረምቱ በሚወስዱት የሙያ ክህሎት ስልጠናዎች ዙሪያ በኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና ሀላፊና በኮሌጁ ም/ዲን አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃ ተደርጎላቸዋል:: የክረምት ሰልጣኞቹ ይበልጥ ግንዛቤው እንዲኖራቸው ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥባቸውን ወርክሾፖች ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በዚህም በትምህርትና ስልጠና ክፍሎቹ በሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ሙያዊ ገለፃና ማብራሪያ በመስጠት ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጏል:: "የክረምትን በክህሎት" ሰልጣኝ ወጣቶች ቀጣዮቹን ወራት በኮሌጁ በመረጡት ሙያዊ ስልጠና እየወሰዱ የሚቆዩ ሲሆን በስልጠናው ማጠናቀቅያ ላይም ለቀጣይ ምዕራፋቸው መሰረት የሚሆናቸውን ሙያዊ ክህሎት ጨብጠው እንደሚወጡም ተገልፇል:: ኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ነሃሴ 7/2016 ዓ.ም

አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በSolar PV Installation Maintenance በመጀመርያ ዙር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኝ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። የዛሬ ተመራቂዎች በአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ከኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በአጫጭር ስልጠና በSolar PV Installation Maintenance ላለፉት 8 ወራት ሲሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን በዚህም 30 ወንድ እና 18 ሴት እንዲሁም 3 አካል ጉዳተኞች በድምሩ 48 ሰልጣኝ ተማሪዎች በዛሬው እለት ለምረቃ በቅተዋል:: ተመራቂ ተማሪዎቹ በሰለጠኑት ስልጠና የሶላር ሲስተም ጥገናን በሚፈለገው ልክ ተደራሽ ለማድረግ የብቃት ምዘና(COC) በብቃት በማጠናቀቅ ወደ ስራ አለም ለመግባት መዘጋጀታቸውም ተገልፇል:: በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ለመገኝት የአድራ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ ሀላፊዎች ከአዲስ አበባ የተግኙ ሲሆን ከምረቃ ፕሮግራም መጠናቀቅ በኃላ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በኮሌጁ አካሂደዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ነሃሴ 2/2016 ዓ.ም

የአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ፕሮጀክት የ2016ዓ.ም የፕሮጀክቱን አመታዊ አፈፃፀም ሪፖርት ለኮሌጁ ማኔጅመት አቀረበ:: በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ)ፕሮጀክት በአመቱ የተሰሩ ስራዎችንና የተመዘገቡ ውጤቶች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም በፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ መፍትሄዎችም ጭምር በፕሮጀክቱ ሀላፊ አማካኝነት ለኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: የማኔጅመንት አባላቱ በመቀጠል በአመቱ የአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ፕርጀክት በሰልጣኝ ተማሪዎቹ የተሰሩ ፕሮጀክቶችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል:: በመጨረሻም አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በዘንድሮ ዓመት በSolar PV Instalation ያሰለጠናቸውን 48 ሰልጣኝ ተማሪዎቹን ነሃሴ 2/2016 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ የሚያስመርቅ መሆኑም ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ሰልጣኝ ተማሪዎች በጋራ በመሆን "ደም በመለገስ ህይወት እንታደግ" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አካሄዱ፡፡ በደም ልገሳው መርሃ-ግብር ወቅት ደማቸውን የለገሱ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ሰልጣኝ ተማሪዎች በሚተካ ደም የማይተካውን የሰው ሕይወት መታደግ የሚያስችል ተግባር ላይ መሳተፋቸው ደስታ እንደፈጠረላቸው ገልፀው በቀጣይ ዙር በሚኖረው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ተሳታፊ እንደሚሆኑም ገልፀዋል፡፡ የደም ባንክ አገልግሎት ሰራተኞችም በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ደማቸውን ለለገሱት የኮሌጁ ሰራተኞችና ተማሪዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣ እንዲህ አይነት መርሃ ግብሮችን በጋራ ከኮሌጁ ጋር እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ሀምሌ 25/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል
#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል። ምን መማር ይቻላል ? - Android Kotlin Development Fundamentals - Data Science Fundamentals - Programming Fundamentals ትምህርቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል ? ስልጠናዎቹ በዩዳሲቲ (Udacity) በተሰኘው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው የቀረቡ ናቸው። ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራቸውን ወይም ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ይችላሉ። ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል። የስልጠናዎቹን ይዘት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ ( https://ethiocoders.et/ ) ላይ መመልከት ይችላሉ።

በማዕድናት፣ በፈጠራዎች፣ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ እና አይ ሲ ቲ ዘርፍ  ላይ እየሰራችሁ ላላችሁ ኢንተርፕራይዞች በ3ኛው ዓመታዊ የመካከለኛ አነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ/MSME/ መድረክ ላይ በመገኘት ልምድና ተሞክሮአችሁን እንዲሁም ሥራችሁን  ለማጋራት ትልቅ ዕድል ተመቻችቶላችኋል ፡፡ በማዕድናት፣ በፈጠራዎች፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና አይ ሲቲ ዘርፍ  የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ሁለት ዓመትና በላይ የቆያችሁ ኢንተርፕራይዞች ይህ ዕድል እንዳያመልጣችሁ፡፡ ፎረሙ የሚካሄደው በአፍሪካ ናሚቢያ ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ ኢንተርፕራይዞች በፍጥነት ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት መመዝገብ ትችላላችሁ ፡፡ ሊንክ   https://msmeforum.africa/ የዚህ የአፍሪካ ኢንተርፕራይዞች አውታረ መረብ ስብስብ ፕሮግራም አባል መሆንም ትልቅ ዕድል ነው፡፡