en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Open in Telegram
2 332
Subscribers
+1524 hours
+917 days
+37830 days
Posts Archive
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ ልዑክ በዛሬው እለት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ድጋፋዊ የስራ ጉብኝት አካሄደ፡፡ ግንቦት 28/2017 ዓ.ም በሚኒስትር ዴኤታው የተመራው ልዑካን ቡድን በኮሌጁ ሲደርስ በኮሌጁ ዲኖች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ቡድኑ በነበረው ቆይታም በበጀት አመቱ በኮሌጁ የተሰሩ ዋና ዋና ትግባራትን እንዲሁም በተቋሙ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የለውጥ ስራዎችንም ተመልክተዋል:: በበጀት አመቱ በኮሌጁ የተከናወኑ አጠቃላይ ተግባራትን ዝርዝር ሪፖርት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለልዑካን ቡድኑ የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም ኮሌጁ በትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ፣በቴክኖሎጂ ፈጠራዎች፣በስራ ዕድል ፈጠራዎች፣ በእንተርፕራይዞች ድጋፍ ጨምሮ ከአዲሱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ተብራርተዋል:: በመስክ ምልከታው ልኡክ ቡድኑን የመሩት ሚንስትር ዴኤታው ከሱፐርቪዥኑ በኃላ በሰጡት አስተያየት በተቋሙ በነበራቸው ምልከታ የተሻለ የሚባል አፈፃፀምና የስራ እንቅስቃሴ መመልከታቸውን ገልፀው በቀጣይም ከአዲሱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤ አንፃር በኮሌጁ የተጀመሩ ተግባራትን ከዳር ለማድረስ በትኩረት መስራት ይጠበቃልም ብለዋል:: በእለቱ በኮሌጁ የተካሄደው ድጋፋዊ ሱፕርቪዥን ምልከታም በሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ለተቋሙ በመስጠት ተጠናቋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

Repost from N/a
photo content
+9

Repost from N/a
photo content
+9

Repost from N/a
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ ልዑክ በዛሬው እለት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ድጋፋዊ የስራ ጉብኝት አካሄደ፡፡ ግንቦት 28/2017 ዓ.ም በሚኒስትር ዴኤታው የተመራው ልዑካን ቡድን በኮሌጁ ሲደርስ በኮሌጁ ዲኖች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ቡድኑ በነበረው ቆይታም በበጀት አመቱ በኮሌጁ የተሰሩ ዋና ዋና ትግባራትን እንዲሁም በተቋሙ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የለውጥ ስራዎችንም ተመልክተዋል:: በበጀት አመቱ በኮሌጁ የተከናወኑ አጠቃላይ ተግባራትን ዝርዝር ሪፖርት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለልዑካን ቡድኑ የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም ኮሌጁ በትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ፣በቴክኖሎጂ ፈጠራዎች፣በስራ ዕድል ፈጠራዎች፣ በእንተርፕራይዞች ድጋፍ ጨምሮ ከአዲሱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ተብራርተዋል:: በመስክ ምልከታው ልኡክ ቡድኑን የመሩት ሚንስትር ዴኤታው ከሱፐርቪዥኑ በኃላ በሰጡት አስተያየት በተቋሙ በነበራቸው ምልከታ የተሻለ የሚባል አፈፃፀምና የስራ እንቅስቃሴ መመልከታቸውን ገልፀው በቀጣይም ከአዲሱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤ አንፃር በኮሌጁ የተጀመሩ ተግባራትን ከዳር ለማድረስ በትኩረት መስራት ይጠበቃልም ብለዋል:: በእለቱ በኮሌጁ የተካሄደው ድጋፋዊ ሱፕርቪዥን ምልከታም በሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ለተቋሙ በመስጠት ተጠናቋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

በቴክኒክና ሙያ  እየተማርክም ትፈለጋለህ…

ወጣቶች በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ ቅጥርን ሳይጠብቁ ስራ ፈጣሪ ዜጋ መሆን እንዲችሉ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል ተባለ:: ግንቦት 25.2017 ዓ.ም ADRA ኢትዮጵያ ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በኮሌጁ በSolar PV Installation Maintenance ሰልጥነው ለተደራጁ ማህበራት ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችላቸውን የማቴሪያል እና የመስሪያ ቦታ ድጋፍ አደረገ:: በSolar Maintenance እቃዎችና የመስሪያ ቦታ ድጋፍ መርሀ-ግብሩ ላይ ለወጣቶች መልዕክት ያስተላለፉት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በንግግራቸውም በዛሬው እለት ከፍተኛ ድጋፍ ከፕሮጀክቱ ያገኙ ወጣቶች የተፈጠራላቸውን ምቹ እጋጣሚ በአግባቡ ተጠቅመው በቀጣይ በዚህ መንገድ ለሚመጡ ወጣቶች አርአያ የመሆን ከፍተኛ ሀላፊነት አብሮ እንደተጣለባቸው የገለፁ ሲሆን አክለውም በተገኘው የማቴርያልና የመስሪያ ቦታ ድጋፍ በአስተዳደሩ የከተማ ወረዳና የገጠር ክላስተሮች በዘርፉ ያልተነካውን የስራ እድል በአግባቡ ተጠቅመው ራሳቸውን ብሎም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ምክራቸውን ለግሰዋል:: በፕሮጀክቱ እንደ ግብ የተቀመጠው 120 ሰልጣኞችን በSolar PV Installation Maintenance አሰልጥኖ ከስራ ጋር ማስተሳሰር መሆኑን ያስታወሱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲጨርሱ እንደትቋም በራሳቸው ስራ ፈጥረውና ተደርጅተው እዲሰሩ አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እየተደረገ እንደሚገኝም ገልፀዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም ኮሌጁከፕሮጀክቱ ጋር በመተባበር የማቴሪያል ድጋፉ በADRA ፕሮጀክት አማካኝነት እንደተደረገ ገልፀው እንደተቋም ለወጣቶቹ ድጋፍ በማድረግ ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመነጋገር ኮሌጁ ለንግድ አገልግሎት የሰራቸውን ቤቶች ወጣቶቹ ተደራጅተው እንዲሰሩበት እድርገናልም ብለዋል:: በእለቱ በሁለት ማህበራት ለተደራጁ 21 ወጣቶች ከ450ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የSolar Maintenance እቃዎች ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን ወጣቶቹም.... በInstallation በMaintenance የSolar እቃዎችን በማቅረብ እንዲሁም ተዛማችነት ያላቸውን ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚሰሩ ማወቅ ተችሏል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

በEASE ፕሮጀክት(ኢትዮጵያ) ዋና ሀላፊ ፕሮፌሰር ሀፍቶም ገ/እግዚአብሔር የተመራ ልዑክ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ጉብኝት አካሄደ፡፡ ግንቦት 22.2017 ዓ.ም ልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ በነበረው የስራ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያለውን የአፈፃፀም ሂደትና እስካሁን የተሰሩ ተግባራትን ጨምሮ በኮሌጁ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የለውጥ ስራዎች በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁም በኮሌጁ ይEASE ፕሮጀክት አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ገልፃ ተደርጎላቸዋል:: የፕሮጀክቱ ዋና ሀላፊ የተመሪው ልዑክም በኮሌጁ ባደረጉት ምልከታና የተደረገላቸውን ገለፃ መነሻ በማድረግ ውይይቶች የተካሄደዱ ሲሆን የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ያሳየው አፈፃፀም ለሌሎችም ፕሮጀክቱ ለሚተገበርባቸው ተቋማት ምሳሌ መሆን የሚያስችል መሆኑንም ዋና ሀላፊው ሀሳባቸውን ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችና ዎርክ ሾፖችን ጨምሮ የተሰሩ የለውጥ ስራዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በመጨረሻም በፕሮጀክቱ ዋና ሀላፊ ፕሮፌሰር ሀፍቶም ገ/እግዚአብሔር አማካኝነት ለኮሌጁ በቀጣይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ላይ የስራ አቅጣጫን በመስጠት ጉብኝቱን አጠናቀዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ አካሄደ:: ግንቦት 22.2017 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት ከፌደራል በመጡ የፕሮጀክቱ ተጠሪዎች አማካኝነት የፕሮጀክቱ ትግበራ ላይ ከኮሌጁ ጋር አብረው ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል:: መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክትም ይህ ስልጠና በዋነኛነት በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ጉልህ ሚና ላላቸው ባለድርሻ አካላት እንደተዘጋጀ ጠቅሰው ኮሌጁ ብቻውን የሚፈልገውን ውጤት ማሳካት እንደማችልና የሁሉንም ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ በተለይም ድሬዳዋ ላይ እንዲሳኩ የምንፈልጋቸውን ተግባራት እውን ለማድረግ እንዲያስችለን ሁላችንም የየድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናልም ብለዋል:: በዕለቱ ስልጠናውን ለተሳታፊዎች የሰጡት የEASE ፕሮጀክት(ኢትዮጵያ) የማህበራዊ ልማት ባለሙያ አቶ መለስ ይመር ሲሆኑ የፕሮጀክቱን ዋና ዋና አላማዎችን በዝርዝር ለመድረኩ ተሳታፊዎች የሚገልፅ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም በፕሮጀክቱ አፈፃፅም ወቅት የኮሌጁ እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን ሚና ምን ምን እንደሆኑ ለይተው በማስቀምጥ ግንዛቤ ሰጥተዋል:: በመቀጠልም በፕሮጀክቱ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ በሆኑት አቶ ሰለሞን አሊ አማካኝነት በEnvironmental Screening ላይ ለተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ መስጠትም ተችሏል:: በቀረበው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድን መነሻ በማድረግም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የመደረኩ ተሳታፊዎች በፕሮጀክቱ አላማና አተገባበር ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ያስቻለ መድረክ ሆኖ ተጠናቋል::

#ጥብቅ ማሳሰቢያ ለ፡-ሁሉም የአስተዳደሩ ተቋማት የሰው ሀብት ኃላፊዎች ቀደም ሲል ግንቦት 20 በካሌንደር ዝግ ሆኖ ይውል የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን እለቱን ካሌንደር የማይዘጋው እና መደበኛ
#ጥብቅ ማሳሰቢያ ለ፡-ሁሉም የአስተዳደሩ ተቋማት የሰው ሀብት ኃላፊዎች ቀደም ሲል ግንቦት 20 በካሌንደር ዝግ ሆኖ ይውል የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን እለቱን ካሌንደር የማይዘጋው እና መደበኛ የስራ ቀን መሆኑን አውቃችሁ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ እንድታደርጉ ያሳስባል።                                          የድሬዳዋ  አስተዳደር

ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ምሩቃን በሙሉ **** በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ "ሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚቢሽን(Job Fair)" የፊታችን ሐሙስ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:
ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ምሩቃን በሙሉ **** በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ "ሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚቢሽን(Job Fair)" የፊታችን ሐሙስ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ሁለገብ ሜዳ የሚካሄድ ይሆናል። በዚህም ስራ ፈላጊ ምሩቃን የተለያዩ ድርጅቶች በቅጥር ሥራ የምታገኙበትን ሁኔታ ሊያመቻቹ እናንተን ስለሚጠብቁ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በመያዝና በአካል በመገኘት  የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።                   የድሬዳዋ አስተዳደር                    ሥራና ክህሎት ቢሮ

የሥራ እድል ፈጠራን ዲጅታላይዝ በማድረግ አሰራራችንን ቀልጣፋ ማድረግ እና ውጤታማ ነትን ማረጋገጥ ያስችለናል። አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ