Peka - ፔካ
Open in Telegram
The Great source of Knowledge. ፔካ ብሩህ የሆነ ነጭ ዕንቁ ነው። እውቀትም ብርሃን ነው። You Tube => ? Channel 2 => t.me/Peka369 Owner - @Lumos1
Show more2 958
Subscribers
No data24 hours
-57 days
-2930 days
Posts Archive
2 958
Repost from FINX Tube - ፊኒክስ ቲዩብ
ሳቅ ከውስጥ ሲሆን ከውጭ ያሳብቃል ፣
ሃዘን እየራቀ ፈገግታው ይደምቃል ፣
ጭንቀት እየወጣ ህልም እውን ይሆናል ።
~~~
•••
✍ ወዳጄ አንተ የእግዚአብሔር ልዩ ፍጡር ስለሆንክ ደስስስ ይበልህ። ከውስጥህ ተደሰት።
√ በምድር ደኻ ነኝ ስትል ከሃብታሞች የተለየ ሞትን የማትሞተው እንዲሁም ከሞትክ በኋላ ፈርሰህ የማትቀረው አምላክህ ቤዛ ስለሆነልህ ነው።
√ አምላክህ በእንጨት መስቀል የተሰቀለው ለአንተ ፍቅር ነው።
√ አምላክ "እነኋት እናትህ" ብሎ አምሣያ የሌላት እናቱን የሰጠህ ስለ ፍቅሩ መግለጫ ነው።
√ አምላክ ሥጋውን እና ደሙን የሰጠህ ስለሚወድህ ነው። እስኪ ንገረኝ ማንም ቢወድህ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ አይሰጥህም።
√ አምላክ "በነቢይ ስም ነቢይን፣ በጻድቅ ስም ጻድቅን የተቀበለ የነቢዩን ወይም የጻድቁን ዋጋ ያገኛል" ብሎ ቅዱሳንን ለአማላጅነት የሰጠህ አንተ የፍጥረቱ ሁሉ በኲር ስለሆንክ ነው።
√ በእቶን እሳት ስትጣል፣ በአንበሳ ጉድጓድ ስትወረወር መላእክትን የላከልህ ስለሚሳሳልህ ነው።
√ ከብዙ ዘመን የምርኮ ቆይታ በኋላ ወደ ርስት ምድርህ ወደ ከነዓን ሊመልስህ ሙሴን የላከልህ ስለሚወድህ ነው። ............
~ ~
በቃ አምላክህ ስለሚወድህ ለአንተ ያላደረገልህ ነገር የለም። ያደረግክለት ግን የለም። ውለታህን ፈልጎ ሳይሆን ከልቡ ስለሚወድህ ነው ሁሉን ያደረገልህ። እናም ወዳጄ እንዲህ የሚሳሳልህ እና የሚወድህ አምላክ ያለህ አንተ ስለምን ትቆዝማለህ? ደስስስ ይበልህ ዝም ብለህ። ፈገግግግግ በል። ፍንድቅድቅ በልልልል። አበባ ሁንንን። እኔ ይህን እያሰብኩ ነው ስስቅ የምታየኝ።
••••
~ እየሳቃችሁ! እየተደሰታችሁ! እየጸለያችሁ! ~
© ዐምደ ብርሃን
2 958
🤗🤗🤗🤗🤗 ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንደምን ቆያችሁ ዛሬም በቃሌ መሰረት በጣም የምትወድትን ሕብረ ከዋክብት ይዤላችሁ መጥቻለሁ ስሟም "ልዕልት አንድሮ ሜዳ "ትባላለች ምርጥ ቆይታ እንደሚኖረን ሙሉ ተስፍ አለኝ። ልዕልት አንድሮ ሜዳ ሑት (Pisces) ሕብረ ከዋክብት ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው ከ3ቱ ሕብረ ከዋክብት አንዷ ነች። ልዕልት አንድሮ ሜዳ በዕብራይስጥ ስሟ "ሲራ" ስትባል" ፍቺውም "ታስራ ወይም የታሰረቺው" ማለት ነው። በግዕዙም "አሲር" ፍቺውም "ማሰር" ማለት ነው። በትልቅነቷም " 19 " ደረጃ ላይ ትገኛለች በህዋው ቴሌስኮፕ በሒፖርከስ የተመዘገቡትም 2112 Constellation በውስጧ ይገኛሉ። ፕላኔት ያላቸው 19 ከዋክብት የተመዘገቡ ሲሆን 24 ኤክሶፕላኔት መኖራቸው ተረጋግጧል። 👆👆👆ከላይ በምስሉ ላይ እንደምታዮት በራሷ ላይ ያለው ብሩሁ ኮከብ "አልፊራትዝ" ፍቺው "የተሰበረው" ሲሆን በሰውነቷ በግራ በኩል ዝቅ ብሎ ያለው ኮከብ "ሚራክ" ፍቺው "የደከመ" ማለት ነው በግራ እግሯ ያለው ኮከብ " አል ሚራክ" ፍቺውም "የሞት ምክንያት" ማለት ነው። ልዕልት አንድሮ ሜዳ በዘመናችን ከተሰሩላት ፊልሞችም " ዘ አንድሮሜዳ እስትሬይን " እና " አንድርሜዳ ራዝ ኦፍ ዘ ቲታንሶ " እናም ሌሎችም አሉ ቤተሰቦች ለዛሬ ይህን ይመስል ነበር ከዛሬውም ትምህርት ብዙ መረጃ እንዳገኛችሁ አልጠራጠርም በሌላ እርዕስ እስክንገናኝ ድረስ
ስለ ምትከታተሉኝም በደንብ አድርጌ አመሰግናለሁ ቸር ቆዮልኝ። share share 👇👇👇👇👇 @Astronomer21 @Astronomer21
2 958
"Geez Health - ግእዝ ጤና"
አሪፍ ቻናል ነው እየገባችሁ አበረታቱት ተማሩ። - እንማር 😁👍🙌
Video: youtu.be/_q0zxFXp8zw
Channel link: ግእዝ ጤና-Geez Health
2 958
Repost from መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
ታላቅ ተስፋ የሚጠብቃቸውን ሕፃናትን ታዳጊዎችን እናበረታታ ኢትዮጲያዊው የ18 ዓመት ወጣት፣ አቤል አሰፋ ዳኜ፤ የ21 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያስገኘው እና 2400 ተወዳዳሪዎችን ካሳተፈው ዓለም አቀፍ የሳይንስ ውድድር በመሳተፍ ከ30 ምርጥ ሥራዎች ውስጥ በመግባት ለግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ችሏል።
👉 የእርስዎ ሁለት ድምጽ ደግሞ ለመጨረሻው ዙር ከሚገቡ ምርጥ16 ተወዳዳሪዎች መካከል በሕዝብ ድምጽ የሚያልፍ አንድ ብቸኛ ተወዳዳሪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ የሚከተሉትን ሁለት ቪድዮዎች ‘Like’ አድርገው ድምፅዎን በመስጠት ለሌሎች ወጣቶች አርአያ የሚኾን ይህን ኢትዮዽያዊ ወጣት ለፍጻሜ ውድድር እንዲደርስ ያድርጉት።
1. Facebook፡ https://www.facebook.com/watch/?v=595860615362156
2. YouTube፡ https://www.youtube.com/watch?v=PzTAhCHoIMQ&feature=youtu.be
2 958
🔥 New Video: "🔴 ሎርድ ኦፍ ዘ ሪንግስ እና ኢትዮጵያ - LORD of the RINGS and ETHIOPIA | Peka Tube" on YouTube
https://youtu.be/Ui-phlrh918
2 958
ሰላማችሁ ይብዛልኝ ❤️
ዛሬ ከጨረስሁ YouTube ላይ በአስገራሚና አስተማሪ ቪዲዮ የምንገናኝ ይሆናል።
Inboxሰሮች ይቅርታ ታገሱኝ🙏🙌😊
2 958
Watch "Andromeda አንድሮሜዳ | "ገነት በኢትዮጵያ ናትን?" | ቆይታ ከደራሲ ዝጋለ አያሌው ጋር ክፍል 2@Balageru TV" on YouTube
https://youtu.be/5m3gqVcJ_80
2 958
📌 ዓለምን የሚቀይረው የሚናገሩት ቃል አስገራሚ ኃይል
👉🏻 ስለ ቃላት ኃይል ከመናገሬ በፊት ስለ ቃላት ምንነት መረዳትና መገንዘብ አስፈላጊ መስሎ ይታየኛል። ስለዚህ ቃላት ምንድን ናቸው? አንድ ቃል በጆሯችን እናደምጠዋለን ነገር ግን አይያዝም አይጨበጥም ረቂቅ ነገር ነው። ይህም የፊደላት ጥንቅር ሲሆን ይህም ቫይብሬሽን በመሆኑ ምድር ላይ አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖ አለው። ምክንያቱም የቃላት መነሻ ልብ ነው፤ ይህ ሲብራራም የሰው ልጅ ከሰባቱ{7} ባሕርያት የተፈጠረ ነው።
👉🏻 እነዚህም 4ቱ የሥጋ ባሕርያትና 3ቱ የነፍስ ባሕርያት ናቸው። የሰውም የስሙ ምስጢር 7 መሆኑ ስለዚህ ነው። 3ቱ የነፍስ ባሕርያት፦ 1. ሕያዊት ነፍስ(ሕያው የሆነች) 2. ነባቢት ነፍስ(የምትናገር) 3. ለባዊት ነፍስ(የምታውቅ)
👉🏻 በዚህ ሥነ ፍጥረታዊ እሳቤ መሰረትም ነባቢት የምንለው ከላይ እንደተገለጸው መናገር ነው፤ ስለዚህ መናገር የነፍስ ውጤት ነው። ስለዚህም ነው የሞተ ሰው የማይናገረው ምክንያቱም ሞት የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው።
ቃል የልብ ውጤት ነው ካልን፤ ሰው ከልቡ ያለውን ነው አውጥቶ የሚናገረው።
👉🏻 ስለቃላት ይህን ካየን ስለቃላት አይነቶች እንመልከት...
ጥሩና መጥፎ ቃላት ተብለው በ2 ይከፈላሉ።
1️⃣ጥሩ ቃላት: መልካም የሆኑና የሰው ልጅን የመፈወስ አቅም ያላቸው ቃላት ናቸው። ስለዚህም ነው የዕብራውያን ንጉሥ ሰሎሞን “ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው” ብሎ የተናገረው፤ ስለዚህ እነዚህ መልካም ቃላት የሰው ልጅን ሊጠግኑ የሚችሉ ናቸው። እኒህ ቃላት መልካም ልብ ካለው ሰው ከልቡ መዝገብ የሚወጡ ናቸው።
2️⃣መጥፎ ቃላት፡ በNegative Energy የተሞሉ ዓለምን፣ የተናገረውን ሰውን፣ እንዲሁም የሚሰማውንም ሰው የሚጎዱ ቃላት ናቸው። እኒህ መጥፎ ቃላት ክፉ ልብ እንዲሁም በማይጠቅሙ ነገሮች የቆሸሸ ልብ ካለው ሰው የሚወጡ ናቸው።
📜 ከቃላት ጋር በተያያዘ መልኩ ወደ ኢትዮጵያውያን መዛግብት ስንመጣ አንድ የፍልስፍና መጽሐፍን ማስታወስ ግድ ይለናል። አንጋረ ፈላስፋ ተብሎ ይጠራል። ስለ ቃላት እንዲህ እያለም ይገልጻል
👉🏻 “አፍና አንደበት የጥበብ መጀመሪያ ናቸው፤ የጥበብ መጀመሪያ አፍና አንደበትን መጠበቅ ነው”
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ሚለውን ወስዶ ስለምን እንዲ አለ? ብንል አፍና አንደበትን መጠበቅ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ወይም እግዚአብሔርን መፍራት የሚገለጸው አፍና አንደበትን በመጠበቅ ነው ማለቱ ነው።
👉🏻 “የሰው ልጅ ጠላቱ አንደበቱ ነው”
ይህስ ምን ማለት ነው? ብትሉኝ ሁሉም ሰው ለተናገራት እያንዳንዷ ንግግር በመጨረሻ ሰዓት መልስ ይሰጥባታል ሲል ነው።
? ለምን ብንል “የጥበብ ቦታ አንደበት ነው” ይለናል፤ “ሞትና ሕይወት በአንደበት እጅ የተያዙ ናቸው” ይህንም ምሳሌ 18፥21 ላይ እናገኘዋለን። ይህ መጽሐፍ ስለአንደበት ብቻ ሳይሆን ስለምንስቀው ሳቅ ሳይቀር ይመክራል፤ ያልታረመ ሰውሲስቅ አፉን ከፍቶ ድምጹን አሰምቶ ነው፤ አዋቂ ብልህ ሰው ሲስቅ ግን አፉን በመጠኑ ከፍቶ ይስቃል፡ ይለናልና ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ ስለቃላትም ስለአሳሳቅም ያስተምረናልና ነገሩ መልካም ስለሆነ ልንማርበት ይገባል።
📜አንጋረ ፈላስፋን እዚጋ አመስግነን ዘጋነው።😁
👉🏻 የምንናገረው ቃላት ከነዚህ በተጨማሪ ያለንበትን ንቃተ-ሕሊና፣ የምናይበትን መነጽር፣ እያንዳንዷን ነገር የምንመለከትበትን “ዐይን” የሚገልጹ ናቸው።
📌 ሌላው ከቃላት ጋር ተያይዞ ጥናቶች ከሰሩ የውጭ ምሁራን መካከል አንዱ Dr Emoto Masaru ናቸው። Dr Emoto Masaru በJapan Yokohama city በ1943 AC የተወለዱ ሲሆን በYokohama University ተምረው። በውሃ ላይ እንዲሁም ስለ ቃል ኃይልም በርካታ ጥናቶችን ሰርተዋል። በመጀመሪያ ያሳተመው መጽሐፍ በ45 በላይ ቋንቋዎች የተተረጎመና ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ኮፒዎች የተሸጠው መጽሓፋቸው “Messages from water” ይሰኛል። ከዚህም በመቀጠል “Hidden messages in water” የሚል መጽሐፍ አሳትሟል።
👉🏻 እነዚህ መጻሕፍት ምንድን ነው የሚናገሩት?
ውሃ መረጃን Memorize & Transmit ማድረግ ይችላል የሚል ጥናት ነው። ይህንም በሙዚቃ፣ በጸሎት፣ በፎቶ፣ በቦታ ለውጥ ውሃ እንደሚለዋወጥ፣ መልክ እንደሚለውጡ፣ ጥሩው መጥፎ መጥፎው ጥሩ እንደሚሆን በጥናቱ አረጋግጧል።
ይህ ጥናት ከርሳቸው በኋላ በሌሎችም ሳይንቲስቶችም ተሰርቷል።
👉🏻 ሁለት የውሃ እቃዎችን አስቀምጠው፤ ተመሳሳይ መጠንና አይነት ያለው ውሃ ሞሉባቸው፤ አንደኛው ላይ “እወድሃለሁ አመሰግንሃለሁ” ሌላኛው ላይ “አልወድህም አላመሰግንህም” ብለው ጻፉ። በመቀጠልም ለውጡን ለማየት ወደ በረዶነት ቀይረው ተመለከቱ። “እወድሃለሁ አመሰግንሃለሁ” የተባለው ጠርዙ Transparent ውስጡ ነጭ እንደሆነና ስንጠቃ ብዙም የሌለው በረዶ ሁኖ ሲገኝ ሌላኛው “አልወድህም አላመሰግንህም” የተባለው ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስንጠቃ ያለበት እንዲሁም መሃሉ የጠቆረ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል።
👉🏻 Dr Emoto masaru በዚህ ብቻም አላቆሙም፤ Water & Peace Global Forumን አዘጋጁ(1999)። ለዚህም ጥናት በጃፓን የሚገኘውን ትልቁን ሐይቅና በክረምት ወራት ሽታው ነዋሪዎችን የሚረብሻቸው የነበረውን ቢዋ ሐይቅን(Lake Biwa) መረጡ። በዚህ መርኃግብርም “Thank You, lake biwa” እያሉ ወደዛ ሐይቅ መጮኽ ጀመሩ። በነርሱ አጠራርም ጸሎት ሲሆን በዚህ ጸሎታቸው ውስጥ አርምሞና ተመስጦን ገንዘብ አድርገው ነበር። ከዚህ ዝግጅት በኋላም በሐይቁ ላይ የነበረው ክፉ ጠረን እንደጠፋ ጥናቱ ይገልጻል።
👉🏻 Dr Emoto Masaru የቃላትን ኃይል በቀመር(Formula) አስቀምጧል። ይህ Formula ቀድሞ የሚታወቅ ነው፡ E=MC2 ።
E = Energy of words
M = NuMber of people
C2 = Consciences(ንቃተ-ሕሊና)
እኒህ 3ቱ ለቃላት ኃይል ወሳኝ ናቸው ይላል።
👉🏻 ለዚህም ነው በጸሎት ጊዜ የማይታጠፍ ንቃተ ሕሊና፣ ተመስጦ የሚያስፈልገን፤ በሀገራችን ኢትዮጵያም ምህላና መሰል የሕብረት ጸሎቶች ከዚህ ቀመር ጋር የሚሄዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በየገዳማቱ፣ በየቤተክርስቲያኑ የሚጸለዩት ጸሎቶች ውሃውን ወደ ቅዱስ ውሃ(Holy Water) ቀይረው ከግዙፉና ረቂቁ ነገር ሲፈውሱ አይተናል፤ በዚህም ተጠቅመናል።
📌 ከዚህ የምንረዳው የDr Emoto masaru የቅርብ ጊዜ ግኝት በኢትዮጵያ እንዲሁም በሌሎች የጥንታዊ ስልጣኔ አሻራ ባረፉባቸው ስፍራዎች ቀድሞ ከብዙ ሽህ ዓመታት በፊት ጀምረው ሲጠቀሙበት እንደኖሩ ታሪክ ይዘግባል።
በዚህ መርሃግብር እንድትይዙልኝ የምፈልገው “ ቃላትን ስንናገር ዓለምን ሊለውጥ የሚችል ኃይል ከአንደበታችን እያፈለቅን ነውና ስለምንናገረው ቃል በደንብ ልናስተውል ይገባል። ”
✍🏾 የዛሬው ጽሑፌ ይህን ይመስላል፤ ከወር በፊት በYouTube ቻናሌ(Peka Tube) ከለቀቅሁት ቪዲዮ የተወሰደ ሲሆን Platformን ለማትጠቀሙ በጽሑፍ ጽፌ ለጠፍኩላችሁ፤ ሃሳብ አስተያየት በ @hailemichaeldt እቀበላለሁ።
መልካም አሁን!
@Ethiopetowoderos
@Pekatube
