ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕
Open in Telegram
ይህ የደዕዋ ቲቪ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። ★★★★★ 📡 የ ዳዕዋ ቲቪ ስርጭትን በ ናይል ሳት ለመከታተል:– 👇 ፍሪኩዌንሲ:- 11636 ሲምቦልሬት:- 27500 ፖላራይዜሽን:- vertical ★★★★★ Youtube https://www.youtube.com/@daewatv1 Facebook https://www.facebook.com/daewatv/ Telegram https://t.me/daewa_tv
Show more4 804
Subscribers
-624 hours
+47 days
+14930 days
Posts Archive
4 807
⚠️ ቢያውቁ ኖሮ❗️
ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لَوْ يَعْلَمُ النَّاسُ مَا فِي الْوَحْدَةِ مَا أَعْلَمُ، مَا سَارَ رَاكِبٌ بِلَيْلٍ وَحْدَهُ﴾
“ሰዎች በብቸኝነት (ለብቻቸው ከሌሎች ተለይተው) በጉዞ ላይ የሚደርሰውን አደጋና ጉዳት እኔ የማውቀውን ያህል ቢያውቁ ኖሮ፣ ከእነሱ አንዱም በሌሊት ለብቻው ፈጽሞ አይጓዝም ነበር።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 2998
➖➖➖➖➖➖
4 807
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ የዳዕዋ ቲቪ ተመልካቾቻችን፤
ተወዳጁን ዳዕዋ ቲቪ ይበልጥ ለማሻሻል እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለእናንተ ለማድረስ፣ ባለፉት ወራት ጠንካራ የአሰራር ማሻሻያዎችን (ሪፎርም) ስናደርግ መቆየታችን ይታወቃል።
በዚህ የለውጥ ጉዟችን ውስጥ የናንተ የተመልካቾቻችን አብሮነት እና ጠቃሚ ግብረ-መልስ ለእኛ እጅግ ወሳኝ ነው። ፕሮግራሞቻችንን ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል፣ ክፍተቶቻችንን እንድናርም እና የተሻለ ስራ እንድንሰራ የእናንተ ገንቢ አስተያየቶች ያግዙናል።
ስለዚህም ስለ ቻናላችን እና ስለ ፕሮግራሞቻችን ያላችሁን ማናቸውንም ሀሳብ፣ አስተያየት፣ ጥቆማ እንዲሁም ቅሬታ ከታች ባለው የቴሌግራም ቦት (Bot) አማካኝነት እንድታደርሱን በአክብሮት እንጠይቃለን። ሀሳባችሁን ለመቀበል ዝግጁ ነን!
አስተያየት መስጫ ቦት ፦ @Daewatv1bot
ሁሌም ስለ አብሮነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን!
ዳዕዋ ቲቪ
4 807
በዕለታዊ ህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ውስብስብ ጉዳዮች በእስልምና ሚዛን መፈተሽ እጅግ አስፈላጊ ነው። ፈታዋ (የሃይማኖታዊ ብያኔ) ከጥርጣሬ አውጥቶ ወደ እርግጠኝነት የሚመራን፣ እንዲሁም ተግባራችንን እና አምልኳችንን በአላህ ትክክለኛ መንገድ ላይ እንድናደርግ የሚያግዘን ብርሃን ነው።
ይህንን አንገብጋቢ የኡማውን ፍላጎት በመገንዘብ፣ የፈታዋ ጥያቄና መልስ ዝግጅታችንን ይበልጥ ተደራሽ እና ጥራት ባለው መልኩ በአዲስ ገፅታ ለማቅረብ ዝግጅታችንን አጠናቀን ተመልሰናል።
በቀጥታ ስርጭት ዝግጅታችን ላይ በስቱዲዮ ስልካችን ላይ በመደወል በቀጥታ ጥያቄዎትን ማቅረብ እና ምላሽ ማግኘት ይችላሉ። ይህ ዝግጅት በታላቁ ሸይኻችን ሸይኽ አብደላህ ኢብራህም ጋር በመሆን ወደ እናንተ ይደርሳል።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 807
4 807
🔜 በቅርብ ቀን ይጠብቁ
✨የዕለት ተዕለት የዲን ጥያቄዎቻችሁን የምንመልስበት የፈታዋ ፕሮግራማችን፣ በአዲስ እና በልዩ አቀራረብ ዳግም ጀምሯል።
💡 ጥያቄዎትን በደስታ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን፤ ከእኛ ጋር ይሁኑ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 807
4 807
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፦
﴿فإن الصلاة عليه (🤎) من أعظم الوسائل التي بها يُستجاب الدعاء، وقد أمر الله بها، والصلاة عليه في الدعاء هو الذي دلّ عليه الكتاب والسنة والإجماع﴾
“በነቢዩ (🤎) ላይ ሰለዋት ማውረድ ዱዓእ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከሚያደርጉ ታላላቅ መዳረሻዎች ውስጥ ትልቁ ነው። አላህም በዚህ ላይ አዟል። በዱዓእ ውስጥ ሰለዋት ማድረግ በቁርዓን በሐዲስና በኡለማዎች ሙሉ ስምምነት የተረጋገጠ ነገር ነው።”
📚 መጅምዑል ፈታዋ፡ 1/347
4 807
4 807
የፈትዋ አደቦች
የፈታዋ ፕሮግራማችንን ከምንጊዜውም በተሻለ እና ማራኪ በሆነ አዲስ ገፅታ ይዘንላችሁ ቀርበናል!
ጥያቄዎቻችሁን ይዛችሁ በቀጥታ መስመራችን በመደወል የዚህ ውብ ዝግጅት አካል እንድትሆኑ በታላቅ ደስታ እንጋብዛለን።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 807
4 807
4 807
ፈትዋ ማለት ምን ማለት ነው
ለእርሶ የተሻለውን ለማቅረብ ሁሌም እንተጋለን! የፈታዋ ዝግጅታችንን አይን በሚስብ አዲስ አቀራረብ አዘምነን፣ እንደተለመደው ጥያቄዎቻችሁን በሸሪዓው ሚዛን ለመመለስ እነሆ ተመልሰናል፤ ይደውሉ ይሳተፉ።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 807
4 807
4 807
4 807
ሳምንታዊውን የጁምዓ ኹጥባ ፕሮግራም በመታደም ጁምዓዎን በብርሃን ያድምቁ!
ሳምንታዊ የጁምዓ ኹጥባ በተከበሩ ዶክተር ሼኽ ሙሐመድ ሓሚዲን በሐጂ ሰዒድ ያሲን መስጂድ
የጁምዓ ኹጥባ ማህበረሰቡን በቁርኣንና በሱና ለመገንባት የሚያግዝ ታላቅ የመመሪያ መድረክ በመሆኑ፣ ኹጥባውን በጥሞና አዳምጦ በተግባር መተርጎም መንፈስን ለማደስና እውነተኛውን ጥቅም ለማግኘት ቁልፍ መንገድ ነው።
በጊዜ መስጂድ በመገኘት የአላህን ቤት በዚክርና በጥሩ ምክር ያድምቁ ፤ አላህ መልካም ሥራችንን ይቀበለን።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 807
በእስልምና ውስጥ የጁሙዓ ቀን ታላቅ ቦታ አለው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ጥሪ የሚያደርገው ሙአዚን አዛን ባደረገ ጊዜ በአካባቢው ባሉ ወንዶች ላይ ወደ ጁሙዓ መውጣትን ግዴታ አድርጎባቸዋል፤ በስብሰባው ላይ እንዲገኙም አበርትቷቸዋል፤ በሷ ላይ ከመዘናጋትም አስጠንቅቋል።
ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) ሱናዎቿንና ሥርዓቶቿን አብራርተዋል።
በዚህ ሀዲስ ውስጥ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከጁሙዓ ሶላት በኋላ መስጊድ ውስጥ ሱና ሶላት መስገድ የሚፈልግ ሰው አራት ረከዓዎችን እንዲሰግድ ይመራሉ::
በሌላ የዐምር አል-ናቂድ ዘገባ ላይ እንደተጨመረው፤ አብደላህ ኢብኑ ኢድሪስ እንደተናገረው "ሱሀይል ኢብኑ አቢ ሳሊህ" እንዲህ ብሎታል፦ «ከጁሙዓ በኋላ ከመስጊድ ለመውጣት የሚያስቸኩልህ ጉዳይ ካጋጠመህ፣ በመስጊድ ውስጥ ሁለት ረከዓዎችን ስገድ፤ ከዚያም ሄደህ የፈለግከውን ጉዳይ ፈጽም። በመቀጠል ወደ ቤትህ ስትመለስ ቀሪውን ሁለት ረከዓዎች ስገድ።» (በአቡ ዳዉድ ዘገባ ላይ ተናጋሪው አቡ ሱሀይል እንደሆነ ቢጠቀስም፣ የሐዲስ ሊቃውንት አባቱ መጀመሪያ አዞት ከዚያም ሱሀይል ለተማሪው ለኢብኑ ኢድሪስ አስተላልፎት ሊሆን እንደሚችል ያስማማሉ)።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 807
🥀ጁምዐን ከሱረቱል ከህፍ ጋር🥀
ክፍል አንድ
# ﺳﻮﺭﺓ _ ﺍﻟﻜﻬﻒ
#ሱረቱል_አልከህፍ ( የዋሻው ምእራፍ )
⭕️ አስሀቡል ከህፍ ( የዋሻው ወጣቶች) በጣም አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ በዲናቸው እየሸሹ ሳለ አላህን ምን ነበር የጠየቁት ?
💎 አላህን መመራትንና ቅናቻን ነበር የጠየቁት። በዛ ሁኔታ ላይ ሁነውም እንኳ ማሸነፍን ፣ ድል አድራጊነትን ወይም የበላይ መሆንን አልጠየቁም ነበር ።
🔮 { إِذْ أَوَى ٱلْفِتْيَةُ إِلَى ٱلْكَهْفِ فَقَالُوا۟ رَبَّنَآ ءَاتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةًۭ وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًۭا }
«ጎበዞቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና «ጌታችን ሆይ! ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን፤ ለእኛም ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ »
【 አል ከህፍ 10】
🔮{ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لِى وَلْيُؤْمِنُوا۟ بِى لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ}
« ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና ፡፡ »
【 አል በቀራ 186】
↠ሩሽድ (መመራት ፣ ቅናቻ) ምን ማለት ነው ❓
1️⃣ እውነትን ማግኘት
2️⃣ የነገሮችን ገር መሆን ፣ መስተካከል
3️⃣ በትክክለኛው አቅጣጫ መጓዝ
💎 በእርግጥም አላህ ከመራህ ታላቅ የሆነን መልካም ነገር አግኝተሃል ። እርምጃዎችህም የተባረኩ ይሆናሉ ። ለዚህም አላህ ይህንን በተደጋጋሚ እንድንል አደራ ይለናል።
🔮{ وَقُلْ عَسَىٰٓ أَن يَهْدِيَنِ رَبِّى لِأَقْرَبَ مِنْ هَٰذَا رَشَدًۭا}
«ጌታዬም ከዚህ ይበልጥ ለቀጥታ የቀረበን ሊመራኝ ይከጀላል» በላቸው፡፡»
【 አል ከህፍ 24】
💎 ቅኑን መንገድ ከተመራህ ብዙ ደረጃዎችን ታልፋለህ ። ብዙ ችግሮችንም ታቀላለህ ። አላህም ላንተ ረዳትህና ቅኑን መንገድ የሚመራህ ከሆነ ወጤቱ እጅግ ያማረ ይሆናል።
💎 ሙሳ አለይሁ አሰላም መልካሙን ሰውዬ ሲያገኝ አንድን ነገር ብቻ ነበር የጠየቀው እሱም ፦
🔮 {قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰ هَلْ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰٓ أَن تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمْتَ رُشْدًۭا }
«ሙሳ ለእርሱ «ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን (ዕውቀት) ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህን» አለው፡፡»
【አል ከህፍ 24】
💎 አላህም ቅኑን መንገድ ሲመራን በእርግጥም ለ ዱንያና አኼራ ስኬት ሁኔታዎችን አመቻችቶልናል ማለት ነው ።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩ የሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 807
4 807
