ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ የደዕዋ ቲቪ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። ★★★★★ 📡 የ ዳዕዋ ቲቪ ስርጭትን በ ናይል ሳት ለመከታተል:– 👇 ፍሪኩዌንሲ:- 11636 ሲምቦልሬት:- 27500 ፖላራይዜሽን:- vertical ★★★★★ Youtube https://www.youtube.com/@daewatv1 Facebook https://www.facebook.com/daewatv/ Telegram https://t.me/daewa_tv
إظهار المزيد4 866
المشتركون
+324 ساعات
+197 أيام
+8230 أيام
أرشيف المشاركات
4 864
4 864
«ሹዩኹና» የተሰኘው ፕሮግራም የእስልምና ታላላቅ ዑለማዎችን እና የቀደምት ኢማሞችን የህይወት ታሪክ ይዳስሳል። በእውቀት ፍለጋ ያደረጉትን ጥረትና በእስልምና ታሪክ ውስጥ ጥለውት ያለፉትን አሻራ አጉልቶ ያሳያል። በተጨማሪም እንደ ትዕግስት፣ ብርታትና ሌሎች የነበሯቸውን ልዩ መገለጫዎች ይቃኛል።
ፕሮግራሙ ዑለማዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ደረጃ እና አስፈላጊነት፣ እንዲሁም ሰዎችን በመምራት፣ እውቀትንና መልካም እሴቶችን በማስፋፋት ረገድ ያላቸውን ጉልህ ሚና ያሳያል። ከዚህም ጋር ከእውቀታቸው መቋደስ፣ ከህይወት ታሪካቸውና ከስነ-ምግባራቸው አርዓያነትን መውሰድ ያለውን ጠቀሜታ ያጎላል።
የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ አዲሱ ትውልድ ዑለማዎቹን እንዲያውቅ ማድረግ፣ ለእውቀት ትኩረት እንዲሰጥ እና መልካም አርዓያ ከሆኑት ሰለፎች ትምህርት እንዲወስድ ማበረታታት ነው።
ስለሆነም ይህንን እጅግ ጠቃሚ ፕሮግራም በዳዕዋ ቲቪ እንድትከታተሉ ስንል በአክብሮት እንጋብዛለን!
ሙሉ ፕሮግራሙን ዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ይመልከቱ!
👇
https://youtu.be/cOcv0kpP2Ck
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
ልጆቻችን ማንን አርአያ አድርገው እያደጉ ነው?
በአሁኑ ጊዜ ልጆቻችን ኳስ ተጫዋቾችን፣ አክተሮችን እና የተለያዩ ዘፋኞችን አርአያ እያደረጉ በሚያድጉበት ዘመን፣ እኛ ስለ ምርጥ የዑማው መሪዎች፣ ሰሃባዎች እና ኡለማዎች ምን ያህል እናውቃለን? ምንስ አስተምረናቸዋል?
ዳዕዋ ቲቪ የዑማውን መሪዎች እና ብርሃን የሆኑትን ታላላቅ ዑለማዎች የህይወት ታሪክ የምንዳስስበት "ሹዩኹና" የተሰኘ ፕሮግራም ይዞላችሁ ቀርቧል!
⏰ዛሬ ምሽት 1:00 ላይ በዩቲዩብ ገፃችን እንዲሁም በዳዕዋ ቲቪ ይጠብቁን!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
"አላውቅም" ማለት ደካማነት ነው ወይስ የትልቅነት መገለጫ? በዲን ጉዳይ ላይ ያለ ዕውቀት ፈትዋ መስጠት (መናገር) የሚያስከትለውን ከባድ አደጋስ ምን ያህል እንረዳለን?
በዚህ ጠቃሚ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርታችን አንድ ሙፍቲ ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን፣ የፈትዋ አሰጣጥ ስነ-ምግባርን እና በሽምግልናና በፈትዋ መካከል ያለውን ልዩነት በሰፊው ዳስሰናል።
⏰ዛሬ ምሽት 2:00 ላይ በዩቲዩብ ገፃችን እንዲሁም በዳዕዋ ቲቪ ይጠብቁን
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
✅ ከውዱዑ በኋላ የሚሰገድ ሁለት ረከዓ ያለው ትልቅ ምንዳ!
ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَن تَوَضَّأَ نَحْوَ وُضُوئِي هذا، ثُمَّ صَلّى رَكْعَتَيْنِ لا يُحَدِّثُ فِيهِما نَفْسَهُ، غُفِرَ له ما تَقَدَّمَ مِن ذَنْبِهِ﴾
“ውዱዑን አሳምሮ ያደረገ፤ ልክ እኔ እደማረገው አይነት ውዱዑ ከዛም በውስጡ ነፍሱን ሳያወራ (ሳይወሰወስ) ሁለት ረከዓ የሰገደ፤ ያለፈው (ጥቃቅን) ወንጀሎቹ ይማርለታል።”
📚 ቡኻሪ (159) ሙስሊም (226) ዘግበውታል
➖➖➖➖➖➖➖
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
MMA፣ ቦክስ እና መሰል ፊትን የሚያስመቱ ስፖርቶች በሸሪዓችን እንዴት ይታያሉ? እራስን ስለመጉዳት እና አሁን ላይ በስፋት እየታየ ስላለው የውርርድ (ቤቲንግ) ወጥመድስ የተሰጠው ከባድ ብይን ምንድነው?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
ሙፍቲ ሚባለው ማነው?
በእስልምና አስተምህሮ 'ሙፍቲ' መባል ስልጣን ወይንም ሹመት ሳይሆን፣ ጥልቅ የሸሪዓ እውቀትን (የቁርዓን፣ የሱና እና የፊቅህ ግንዛቤን) የሚጠይቅ የዕውቀት ማዕረግ እና ከባድ ሀላፊነት ነው። በዚህ ቪዲዮ እውነተኛ ሙፍቲ ለመባል መሟላት ስላሉባቸው መሰረታዊ መስፈርቶች፣ ከሊቃውንት ስለሚሰጥ እውቅና (ኢጃዛ)፣ እንዲሁም ስለ ቀደምት ሰለፎች የፈትዋ አሰጣጥ ታሪክ በአጭሩ ተዳሷል።
እንዲሁም ይህንን ጠቃሚ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሙሉ ትምህርት ረቡዕ ማታ 2 ሰዓት ላይ በዮቲዩብ ገጻችን እንዲሁም በዳዕዋ ቲቪ ይጠብቁን
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
🌱በመልካም ነገር ላይ ሌሎችን አሳትፍ
1.ምናልባት የሰነፈ ሊሆን ስለሚችል አነቃቃው።
2. ወይም የተዘናጋ ሊሆን ስለሚችል አስታውሰው ።
3. ወይም ከችሎታው የፈዘዘ ሊሆን ስለሚችል ተሰጥኦውን አውጣለት።
4. ወይም በበጎ ነገር ላይ የሚጥር ሆኖ አጋዥ የሚፈልግ ሊሆን ስለሚችል አግዘው።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
«ነፍስህ በተወቀሰች ጊዜ የምትሰበር (የምታዝን)፣ በተገሰጽክም ጊዜ ዓይንህ እንባ የምታፈስ እስከሆነች ድረስ፤ በልብህ ውስጥ ገና ህይወት አለ።»
📚 ኢብኑል ጀውዚ (ረሒመሁላህ) | አል-ሙድሂሽ (ገጽ 357)
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
4 864
ተከታታይ ፈትዋ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ዶ/ር
📌 #ፈትዋ_02
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
❓ ጥያቄ፡
የትዳር ሕይወት ሚስጥሮችን አደባባይ ማውጣት እንዴት ይታያል?
✅ መልስ / ማብራሪያ፡
የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የትዳር ውስጥ ሚስጥሮችን ሚዲያ(ለኮንቴንትነት) ማቅረብን ሸይኹ አጥብቀው አውግዘዋል። የቤት ውስጥ ሚስጥር አደራ (አማና) እና ጥብቅ ቃል ኪዳን በመሆኑ ሊደበቅና ሊጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
💡 ያለፈውን #ፈትዋ_01 ካላነበቡ ወደ ኋላ ተመልሰው ማንበብ ይችላሉ።
📲 ሼር በማድረግ ለሌሎችም ወንድም እህቶች እንዲደርስ ያድርጉ!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
አነስ ቢን ማሊክ አላህ መልካም ስራውን ይወደድለትና እንዲህ ብሏል ፦
" ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለአስር አመታት ያህል አገልግያለሁ። አንድም ቀን ኡፍ፣ ለምን ይህን ሰራህ? ለምን ይህን አልሰራህም? ብለውኝ አያቁም ።"
📚 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
🔟 አመታት ያህል አነስ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ከልጅነቱ ጀመሮ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) አገልግሏል። የመበሳጨት/ የማጉረምረም ወይም የወቀሳ ቃል ሰምቶባቸው አያውቅም። ለሰራውም ሆነ ላልሰራው ነገር ወቅሰዉት አያቁም።
ርህራሄ፣ ታጋሽነት ፣ ሰዎች ጋር በመልካም መኗኗርና በዙሪያቸው ላሉ ሰዎች አዛኝ መሆናቸው ከታላላቅ ስነምግባሮቻቸው ነበሩ።
በእጃችን ስር ያሉትን ፣ ልጆቻችንን እንዴት እንደምናሳድግ ፣ እንዲሁም የምንወዳቸው ሰዎች ሲያጎድሉ እንዴት መታገስ እንዳለብን ከነብያችን ሱና መማር ምንኛ አስፈለገን !
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
እስራኤሊያት (الإسرائيليات) ምንድን ናቸው?
«እስራኤሊያት» ማለት ከመጽሐፍ ባለቤቶች (ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች) ታሪክ ወደ ሙስሊሞች የተላለፉና ከፊሎቹም ወደ ተፍሲርና የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ የገቡ ዜናዎችና ትረካዎች (ዘገባዎች) ናቸው።
«እስራኤሊያት» ተብለው የተሰየሙት ወደ በኒ እስራኤል በማስጠጋት ነው። ሆኖም ይህ ማለት በውስጣቸው ያሉ ትረካዎች ሁሉ ውሸት ናቸው ወይም ምንጩ የግድ እስራኤላዊ ነው ማለት አይደለም።
ምሳሌ፦
በአንዳንድ የተፍሲር መጻሕፍት ውስጥ ስለ አስሀቡል ከህፍ ስሞች፣ ስለ ብዛታቸው፣ እንዲሁም ስለ ነቢዩ አደም፣ ሱለይማን፣ ወይም ሙሳ (ዐለይሂሙ-ሰላም) ታሪኮች ዝርዝር የሆኑ ረዣዥም ታሪኮች ይገኛሉ። ቁርኣን ያልጠቀሳቸው ሆነው ሳለ፣ ከእነዚህ ዝርዝር ጉዳዮች ውስጥ ከፊሎቹ ከእስራኤሊያት የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ።
ከእስራኢሊያት ጋር ሊኖር የሚገባ አያያዝ፦
ስለ ቀደምት ታሪኮች የሚወሩት ነገሮች በሦስት ይከፈላሉ፦
① ከእውነት (ከእስልምና አስተምህሮ) ጋር የገጠመው ይቀበላል።
② ውሸት መሆኑ የታወቀው ውድቅ ይደረጋል።
③ እንዲሁም ሸሪዓው ዝም ያለው (እውነትም ውሸትም ያላለው) ነገር ላይጊዜ አይጠፋበትም ይተዋል።
💡ማሳሰቢያ፦ እስራኤሊያትን ለዐቂዳ ወይም ለሸሪዓዊ ብያን ማጽደቂያ ምንጭ አድርጎ መጠቀም፣ እንዲሁም በአንድ የተፍሲር መጽሐፍ ውስጥ ስለተገኙ ብቻ የቁርኣን አካል ናቸው ብሎ ወደ ቁርዓን ማስጠጋት ትክክል አይሆንም።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
የ«ዕውቀት ቅርስ» የምዕራፍ 2 ሙሉ ክፍሎች
በቁርዓን የተፍሲር ዓለም እና በታላላቅ ሊቃውንት ድርሳናት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን የ«ዕውቀት ቅርስ» ምዕራፍ 2 ሙሉ ዝግጅት በአንድ ቦታ ያግኙ!
ከዶ/ር ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን ጋር ያደረግናቸውን ጥልቅ ውይይቶች፣ የታላላቅ ሙፈሲሮችን ታሪክ እና የኪታቦቻቸውን ልዩ ባህሪያት በተከታታይና በምቾት ለመከታተል ይረዳዎ ዘንድ ሁሉንም ክፍሎች በአንድ ፕሌይሊስት አዘጋጅተንልዎታል።
ሁሉንም ክፍሎች በተከታታይ ለማየት ሊንኩን ይጫኑ፦
🔗 https://www.youtube.com/playlist?list=PLrgl7AjWrymEnvxq6T_KCFz3PISqBBufu
ይከታተሉ፤ እውቀትዎን ያዳብሩ፤ ለሌሎችም ሼር በማድረግ የኸይር ምክንያት ይሁኑ!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
4 864
ምነኛ ያማረ ስራ!
ሸሪዓዊ ትምህርት ልዩ ከሚያደርገው ነገር አንዱ ባለቤቱ ስራ ባያገኝበት እንኳ በእርግጥ የአላህን ዲን የተማረ በመሆኑ በእለት ተዕለት ህይወቱ ላይ ይተገብረዋል፣ ለሰዎች ያስተምረዋል፣ እንዲሁም አላህን ይገዛበታል።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
4 864
⚠️⚠️በተናጠል (ለብቻ) የሚደረግ የሌሊትም ሆነ የቀን ጉዞ አደጋ አለው!
ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لَوْ يَعْلَمُ النَّاسُ مَا فِي الْوَحْدَةِ مَا أَعْلَمُ، مَا سَارَ رَاكِبٌ بِلَيْلٍ وَحْدَهُ﴾
“ሰዎች በብቸኝነት (ለብቻቸው ከሌሎች ተለይተው) በጉዞ ላይ የሚደርሰውን አደጋና ጉዳት እኔ የማውቀውን ያህል ቢያውቁ ኖሮ፣ ከእነሱ አንዱም በሌሊት ለብቻው ፈጽሞ አይጓዝም ነበር።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 2998
➖➖➖➖➖➖
4 864
ለእያንዳንዱ አዕምሯዊና ሃይማኖታዊ ጥያቄ መልስ ከመስጠት በፊት ያለው አደራ ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ ያውቃሉ?
ፈትዋ መስጠት የአላህን ድንበር ማሳዋወቅ እና ትልቅ የዲን አደራን መሸከም ነው።"ፈትዋ በአደራ እና በእውነታ መካከል" ልዩ የ አል ፈታዋ አዲስ ምዕራፍ መክፈቻ የሆነውን ፕሮግራማችንን፣ ስለ ፈትዋ አሰጣጥ ጥንቃቄዎች፣ ስለ ሙፍቲ መስፈርቶች እና ወቅታዊ የፈትዋ ችግሮች በሰፊው ከ ታላቁ ሸይኻችን ዶ/ር ሸይኽ ሙሃመድ ሃሚዲን ጋር እንወያያለን።
አዘጋጅ እና አቅራቢ: ዶ/ር ኢብራሂም ሐሰን
⏰ረቡዕ ምሽት 2:00 ላይ በዩቲዩብ ገፃችን እንዲሁም በዳዕዋ ቲቪ ይጠብቁን
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን
📱Facebook 📱Youtube
📱Telegram 📱TikTok
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
