es
Feedback
ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕

ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕

Ir al canal en Telegram

ይህ የደዕዋ ቲቪ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። ★★★★★ 📡 የ ዳዕዋ ቲቪ ስርጭትን በ ናይል ሳት ለመከታተል:– 👇 ፍሪኩዌንሲ:- 11636 ሲምቦልሬት:- 27500 ፖላራይዜሽን:- vertical ★★★★★ Youtube https://www.youtube.com/@daewatv1 Facebook https://www.facebook.com/daewatv/ Telegram https://t.me/daewa_tv

Mostrar más
4 864
Suscriptores
+224 horas
+197 días
+8630 días
Archivo de publicaciones
ተከታታይ ፈትዋ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ዶ/ር ​📌 #ፈትዋ_03 ​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ​❓ ጥያቄ፡ በትክክል ሳይደርሱ "ደርሻለሁ" ማለት ይቻላልን? ​✅ መልስ / ማብራሪያ፡ አንድ ሰው ገና ሩቅ ሆኖ ይ
ተከታታይ ፈትዋ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ዶ/ር ​📌 #ፈትዋ_03 ​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ​❓ ጥያቄ፡ በትክክል ሳይደርሱ "ደርሻለሁ" ማለት ይቻላልን? ​✅ መልስ / ማብራሪያ፡ አንድ ሰው ገና ሩቅ ሆኖ ይህን ማለቱ በውሸት በር ውስጥ ሊያስገባው እንደሚችል ሸይኹ አስጠንቅቀዋል፤ ሆኖም ሰውየው ለመድረስ በጣም ተቃርቦ (ከጫፍ ደርሶ) ቅርበቱን ለመግለጽ ከተናገረው ችግር እንደሌለውና ይቅርታ እንደሚደረግለት ገልጸዋል።.. ​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 💡 ያለፈውን #ፈትዋ ካላነበቡ ወደ ኋላ ተመልሰው ማንበብ ይችላሉ። ​📲 ሼር በማድረግ ለሌሎችም ወንድም እህቶች እንዲደርስ ያድርጉ! °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook 📱Youtube 📱Telegram 📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ስለ ቁርዓን ጠቃሚ ነጥቦች 1. መካ ላይ የወረዱ የቁርዓን አንቀፆችና ምዕራፎች በብዛት የሚያጠነጥኑት ተውሂድ ላይ፣ እሱን ደጋግሞ በማስተማርና ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ነገሮችን ውድቅ በማድረግ ነው ። 2. መዲና ላይ የወረዱ አንቀፆች ደግሞ ድንጋጌዎች፣ ብይኖችና ኢባዳዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው። 3. ኢስም አልጀላላህ (الله) ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው ድንጋጌዎች፣ብይኖች ላይ እንዲሁም ልቅናና ሞገስን በማሳየት ነው ። በሱረቱል ሙጃደላህ ላይ (الله) በእያንዳንዷ አንቀፅ ተጠቅሷል። 4. ከአልሁሩፍ አልሙቀጠዓህ ቡኃላ የሚመጣው ገለፃ ስለ ቁርዓን ነው ። ⇢  ኢብኑከሲር እንዲህ ይላሉ፦ " በእነሱ የሚጀምሩ ሁሉም ምዕራፎች ቁርዓንን ስለ መርዳትና የተወረደውም ያለምንም ጥርጥር በእውነት ከብቸኛው አላህ ስለመሆኑ አመላካች ናቸው "። ⇠  {الم . ذَٰلِكَ الْكِتَابُ لَا رَيْبَ ۛ فِيهِ ۛ هُدًى لِّلْمُتَّقِينَ} « (አሊፍ ላም ሚም ) ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመኾኑ) ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡» {يس . وَالْقُرْآنِ الْحَكِيمِ} «(ያ ሲን) ጥበብ በተሞላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡» {حم .  وَالْكِتَابِ الْمُبِينِ} « ( ሀ ሚም) አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እምላለሁ፡» 5 በሁሩፍ አልሙቀጠዓህ የተጀመሩ ምዕራፎች 29 ሲሆኑ ሁሉም ስለቁርዓን በመግለፅ የተጀመሩ ናቸው ። ከእነዚህ ምዕራፎች በስተቀር ፦ ሱረቱ መርየም ፣ ሩምና አንከቡት። 6. ኢብኑ ኡየይና እንዲህ ይላሉ ፦  ⇠ {وما أدراك} ከተባለ መልሱ ለረሱል ተነግሯል ማለት ነው ⇠{  وما يدريك} ከተባለ ደግሞ መልሱ አልተገለፀም ማለት ነው። 7. ኢብኑ ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ ፦ {ويسئلونك} " የተጠቀሰባቸው አንቀፆች ሁሉ  አላህ ለጥያቄው መልስ እስኪያወርድ ድረስ ነብዩ ምላሽ ከመስጠት የተቆጠቡባቸው ናቸው"። 8. አላህ ቁርዓንን በ {الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ. الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ .مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ} የጀመረው ብይኖችና ግዴታዎችን ከማወቅ በፊት አላህን ቀድሞ ለማወቅና በእሱም ለመታገዝ ነው ። 9. {يا أيها الناس}  የሚመጣው አጠቃላይ ለሰው ልጆች ጥሪ ለማስተላለፍ ነው ። ለምሳሌ፦ {يا أيها الناس اتقوا ربكم} النساء 1 {يا أيها الناس اعبدوا ربكم}  البقرة 21 {يا أيها الناس كلوا مما في الأرض}  البقرة168 10. {يا أيها الذين ءامنوا} የሚከተለው ድግጋጌዎችና ብይኖች ናቸው ። ለምሰሌ ፦  {يا أيها الذين ءامنوا كتب عليكم الصيام } البقرة 183 {يا أيها الذين ءامنوا كتب عليكم القصاص} البقرة 178 11. አላህ ሱብሀነሁ ወተአላህ ነብዩን የሚጠራቸው በነብይነትና በመልዕክተኝነት ማዕረግ ነው ። {يا أيها النبي} {يا أيها الرسول } ስማቸውንም የጠቀሰበት አጋጣሚ በመጣራት( አንት ሙሀመድ! ) እያለ ሳይሆን መልዕክትን እየተናገረ ነው ። {مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا} «ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡» 40 الاحزاب {وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَآمَنُوا بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۙ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ} «እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡» محمد 2 ምንጭ፦ 📚 المجالس القرآنية في تدبر السور والآيات °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ፈትዋ ጠያቂ ማሟላት ያለበት አደብ... °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

«ሹዩኹና» የተሰኘው ፕሮግራም የእስልምና ታላላቅ ዑለማዎችን እና የቀደምት ኢማሞችን የህይወት ታሪክ ይዳስሳል። በእውቀት ፍለጋ ያደረጉትን ጥረትና በእስልምና ታሪክ ውስጥ ጥለውት ያለፉትን አሻራ አጉልቶ ያሳያል። በተጨማሪም እንደ ትዕግስት፣ ብርታትና ሌሎች የነበሯቸውን ልዩ መገለጫዎች ይቃኛል። ፕሮግራሙ ዑለማዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ደረጃ እና አስፈላጊነት፣ እንዲሁም ሰዎችን በመምራት፣ እውቀትንና መልካም እሴቶችን በማስፋፋት ረገድ ያላቸውን ጉልህ ሚና ያሳያል። ከዚህም ጋር ከእውቀታቸው መቋደስ፣ ከህይወት ታሪካቸውና ከስነ-ምግባራቸው አርዓያነትን መውሰድ ያለውን ጠቀሜታ ያጎላል። የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ አዲሱ ትውልድ ዑለማዎቹን እንዲያውቅ ማድረግ፣ ለእውቀት ትኩረት እንዲሰጥ እና መልካም አርዓያ ከሆኑት ሰለፎች ትምህርት እንዲወስድ ማበረታታት ነው። ስለሆነም ይህንን እጅግ ጠቃሚ ፕሮግራም በዳዕዋ ቲቪ እንድትከታተሉ ስንል በአክብሮት እንጋብዛለን! ሙሉ ፕሮግራሙን ዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ይመልከቱ! ​👇 https://youtu.be/cOcv0kpP2Ck °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ልጆቻችን ማንን አርአያ አድርገው እያደጉ ነው? ​በአሁኑ ጊዜ ልጆቻችን ኳስ ተጫዋቾችን፣ አክተሮችን እና የተለያዩ ዘፋኞችን አርአያ እያደረጉ በሚያድጉበት ዘመን፣ እኛ ስለ ምርጥ የዑማው መሪዎች፣ ሰሃ
ልጆቻችን ማንን አርአያ አድርገው እያደጉ ነው? ​በአሁኑ ጊዜ ልጆቻችን ኳስ ተጫዋቾችን፣ አክተሮችን እና የተለያዩ ዘፋኞችን አርአያ እያደረጉ በሚያድጉበት ዘመን፣ እኛ ስለ ምርጥ የዑማው መሪዎች፣ ሰሃባዎች እና ኡለማዎች ምን ያህል እናውቃለን? ምንስ አስተምረናቸዋል? ​ዳዕዋ ቲቪ የዑማውን መሪዎች እና ብርሃን የሆኑትን ታላላቅ ዑለማዎች የህይወት ታሪክ የምንዳስስበት "ሹዩኹና" የተሰኘ ፕሮግራም ይዞላችሁ ቀርቧል! ⏰ዛሬ ምሽት 1:00 ላይ በዩቲዩብ ገፃችን እንዲሁም በዳዕዋ ቲቪ ይጠብቁን! °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

"አላውቅም" ማለት ደካማነት ነው ወይስ የትልቅነት መገለጫ? በዲን ጉዳይ ላይ ያለ ዕውቀት ፈትዋ መስጠት (መናገር) የሚያስከትለውን ከባድ አደጋስ ምን ያህል እንረዳለን? በዚህ ጠቃሚ የግንዛቤ ማስጨበ
"አላውቅም" ማለት ደካማነት ነው ወይስ የትልቅነት መገለጫ? በዲን ጉዳይ ላይ ያለ ዕውቀት ፈትዋ መስጠት (መናገር) የሚያስከትለውን ከባድ አደጋስ ምን ያህል እንረዳለን? በዚህ ጠቃሚ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርታችን አንድ ሙፍቲ ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን፣ የፈትዋ አሰጣጥ ስነ-ምግባርን እና በሽምግልናና በፈትዋ መካከል ያለውን ልዩነት በሰፊው ዳስሰናል። ⏰ዛሬ ምሽት 2:00 ላይ በዩቲዩብ ገፃችን እንዲሁም በዳዕዋ ቲቪ ይጠብቁን °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

✅ ከውዱዑ በኋላ የሚሰገድ ሁለት ረከዓ ያለው ትልቅ ምንዳ! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَن تَوَضَّأَ نَحْوَ وُضُوئِي هذا، ثُمَّ صَلّى رَكْعَتَيْنِ لا يُحَدِّثُ فِيهِما نَفْسَهُ، غُفِرَ له ما تَقَدَّمَ مِن ذَنْبِهِ﴾ “ውዱዑን አሳምሮ ያደረገ፤ ልክ እኔ እደማረገው አይነት ውዱዑ ከዛም በውስጡ ነፍሱን ሳያወራ (ሳይወሰወስ) ሁለት ረከዓ የሰገደ፤ ያለፈው (ጥቃቅን) ወንጀሎቹ ይማርለታል።” 📚 ቡኻሪ (159) ሙስሊም (226) ዘግበውታል ➖➖➖➖➖➖➖ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

MMA፣ ቦክስ እና መሰል ፊትን የሚያስመቱ ስፖርቶች በሸሪዓችን እንዴት ይታያሉ? እራስን ስለመጉዳት እና አሁን ላይ በስፋት እየታየ ስላለው የውርርድ (ቤቲንግ) ወጥመድስ የተሰጠው ከባድ ብይን ምንድነው? °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ሙፍቲ ሚባለው ማነው? በእስልምና አስተምህሮ 'ሙፍቲ' መባል ስልጣን ወይንም ሹመት ሳይሆን፣ ጥልቅ የሸሪዓ እውቀትን (የቁርዓን፣ የሱና እና የፊቅህ ግንዛቤን) የሚጠይቅ የዕውቀት ማዕረግ እና ከባድ ሀላፊነት ነው። በዚህ ቪዲዮ እውነተኛ ሙፍቲ ለመባል መሟላት ስላሉባቸው መሰረታዊ መስፈርቶች፣ ከሊቃውንት ስለሚሰጥ እውቅና (ኢጃዛ)፣ እንዲሁም ስለ ቀደምት ሰለፎች የፈትዋ አሰጣጥ ታሪክ በአጭሩ ተዳሷል። ​እንዲሁም ይህንን ጠቃሚ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሙሉ ትምህርት ረቡዕ ማታ 2 ሰዓት ላይ በዮቲዩብ ገጻችን እንዲሁም በዳዕዋ ቲቪ ይጠብቁን °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

🌱በመልካም ነገር ላይ ሌሎችን አሳትፍ 1.ምናልባት የሰነፈ ሊሆን ስለሚችል አነቃቃው። 2. ወይም የተዘናጋ ሊሆን ስለሚችል አስታውሰው ። 3. ወይም ከችሎታው የፈዘዘ ሊሆን ስለሚችል ተሰጥኦውን አውጣ
🌱በመልካም ነገር ላይ ሌሎችን አሳትፍ 1.ምናልባት የሰነፈ ሊሆን ስለሚችል አነቃቃው። 2. ወይም የተዘናጋ ሊሆን ስለሚችል አስታውሰው ። 3. ወይም ከችሎታው የፈዘዘ ሊሆን ስለሚችል ተሰጥኦውን አውጣለት። 4. ወይም በበጎ ነገር ላይ የሚጥር ሆኖ አጋዥ የሚፈልግ ሊሆን ስለሚችል አግዘው። °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

«ነፍስህ በተወቀሰች ጊዜ የምትሰበር (የምታዝን)፣ በተገሰጽክም ጊዜ ዓይንህ እንባ የምታፈስ እስከሆነች ድረስ፤ በልብህ ውስጥ ገና ህይወት አለ።» 📚 ኢብኑል ጀውዚ (ረሒመሁላህ) | አል-ሙድሂሽ (ገጽ 357) °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ስነ-ፈትዋ ፈትዋ በህይወታችን ውስጥ ያለው ትልቅ ቦታ ምንድነው? ኡለማዎች እና ማህበረሰቡስ በፈትዋ ዙሪያ ምን ሀላፊነት አለባቸው? °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ተከታታይ ፈትዋ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ዶ/ር ​📌 #ፈትዋ_02 ​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ​❓ ጥያቄ፡ የትዳር ሕይወት ሚስጥሮችን አደባባይ ማውጣት እንዴት ይታያል? ​✅ መልስ / ማብራሪያ፡ የገንዘብ ትርፍ
ተከታታይ ፈትዋ በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ዶ/ር ​📌 #ፈትዋ_02 ​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ​❓ ጥያቄ፡ የትዳር ሕይወት ሚስጥሮችን አደባባይ ማውጣት እንዴት ይታያል? ​✅ መልስ / ማብራሪያ፡ የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የትዳር ውስጥ ሚስጥሮችን ሚዲያ(ለኮንቴንትነት) ማቅረብን ሸይኹ አጥብቀው አውግዘዋል። የቤት ውስጥ ሚስጥር አደራ (አማና) እና ጥብቅ ቃል ኪዳን በመሆኑ ሊደበቅና ሊጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል። ​➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 💡 ያለፈውን #ፈትዋ_01 ካላነበቡ ወደ ኋላ ተመልሰው ማንበብ ይችላሉ። ​📲 ሼር በማድረግ ለሌሎችም ወንድም እህቶች እንዲደርስ ያድርጉ! °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

አነስ ቢን ማሊክ አላህ መልካም ስራውን ይወደድለትና እንዲህ ብሏል ፦ " ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለአስር አመታት ያህል አገልግያለሁ። አንድም ቀን  ኡፍ፣ ለምን ይህን ሰራህ?  ለምን ይህን አልሰራህም? ብለውኝ አያቁም ።" 📚 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል 🔟 አመታት ያህል አነስ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ከልጅነቱ ጀመሮ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) አገልግሏል። የመበሳጨት/ የማጉረምረም ወይም የወቀሳ ቃል ሰምቶባቸው አያውቅም። ለሰራውም ሆነ ላልሰራው ነገር ወቅሰዉት አያቁም። ርህራሄ፣ ታጋሽነት ፣ ሰዎች ጋር በመልካም  መኗኗርና በዙሪያቸው ላሉ ሰዎች አዛኝ  መሆናቸው ከታላላቅ ስነምግባሮቻቸው ነበሩ። በእጃችን ስር ያሉትን ፣ ልጆቻችንን እንዴት እንደምናሳድግ ፣ እንዲሁም የምንወዳቸው ሰዎች ሲያጎድሉ  እንዴት መታገስ እንዳለብን ከነብያችን ሱና መማር ምንኛ አስፈለገን ! °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ሙፍቲ ሚባለው ማን ነው.sbv0.03 KB

እስራኤሊያት (الإسرائيليات) ምንድን ናቸው? «እስራኤሊያት» ማለት ከመጽሐፍ ባለቤቶች (ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች) ታሪክ ወደ ሙስሊሞች የተላለፉና ከፊሎቹም ወደ ተፍሲርና የታሪክ መጻሕፍት ው
እስራኤሊያት (الإسرائيليات) ምንድን ናቸው? «እስራኤሊያት» ማለት ከመጽሐፍ ባለቤቶች (ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች) ታሪክ ወደ ሙስሊሞች የተላለፉና ከፊሎቹም ወደ ተፍሲርና የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ የገቡ ዜናዎችና ትረካዎች (ዘገባዎች) ናቸው። «እስራኤሊያት» ተብለው የተሰየሙት ወደ በኒ እስራኤል  በማስጠጋት ነው። ሆኖም ይህ ማለት በውስጣቸው  ያሉ ትረካዎች ሁሉ ውሸት ናቸው ወይም ምንጩ የግድ እስራኤላዊ ነው ማለት አይደለም። ምሳሌ፦ በአንዳንድ የተፍሲር መጻሕፍት ውስጥ ስለ አስሀቡል ከህፍ  ስሞች፣ ስለ ብዛታቸው፣ እንዲሁም ስለ ነቢዩ አደም፣ ሱለይማን፣ ወይም ሙሳ (ዐለይሂሙ-ሰላም) ታሪኮች ዝርዝር የሆኑ ረዣዥም ታሪኮች ይገኛሉ። ቁርኣን ያልጠቀሳቸው ሆነው ሳለ፣ ከእነዚህ ዝርዝር ጉዳዮች ውስጥ ከፊሎቹ ከእስራኤሊያት የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ። ከእስራኢሊያት ጋር ሊኖር የሚገባ አያያዝስለ ቀደምት ታሪኮች የሚወሩት ነገሮች በሦስት ይከፈላሉ፦ ① ከእውነት (ከእስልምና አስተምህሮ) ጋር የገጠመው ይቀበላል። ② ውሸት መሆኑ የታወቀው ውድቅ ይደረጋል። ③ እንዲሁም ሸሪዓው ዝም ያለው (እውነትም ውሸትም ያላለው) ነገር ላይጊዜ አይጠፋበትም ይተዋል። 💡ማሳሰቢያ፦ እስራኤሊያትን ለዐቂዳ ወይም ለሸሪዓዊ ብያን ማጽደቂያ ምንጭ አድርጎ መጠቀም፣ እንዲሁም በአንድ የተፍሲር መጽሐፍ ውስጥ ስለተገኙ ብቻ የቁርኣን አካል ናቸው ብሎ ወደ ቁርዓን ማስጠጋት ትክክል አይሆንም። °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube  📱Telegram °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

የ«ዕውቀት ቅርስ» የምዕራፍ 2 ሙሉ ክፍሎች ​በቁርዓን የተፍሲር ዓለም እና በታላላቅ ሊቃውንት ድርሳናት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን የ«ዕውቀት ቅርስ» ምዕራፍ 2 ሙሉ ዝግጅት በአንድ ቦታ ያግኙ! ​ከዶ/ር
የ«ዕውቀት ቅርስ» የምዕራፍ 2 ሙሉ ክፍሎች ​በቁርዓን የተፍሲር ዓለም እና በታላላቅ ሊቃውንት ድርሳናት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን የ«ዕውቀት ቅርስ» ምዕራፍ 2 ሙሉ ዝግጅት በአንድ ቦታ ያግኙ! ​ከዶ/ር ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን ጋር ያደረግናቸውን ጥልቅ ውይይቶች፣ የታላላቅ ሙፈሲሮችን ታሪክ እና የኪታቦቻቸውን ልዩ ባህሪያት በተከታታይና በምቾት ለመከታተል ይረዳዎ ዘንድ ሁሉንም ክፍሎች በአንድ ፕሌይሊስት አዘጋጅተንልዎታል። ​ሁሉንም ክፍሎች በተከታታይ ለማየት ሊንኩን ይጫኑ፦ 🔗 https://www.youtube.com/playlist?list=PLrgl7AjWrymEnvxq6T_KCFz3PISqBBufu ​ይከታተሉ፤ እውቀትዎን ያዳብሩ፤ ለሌሎችም ሼር በማድረግ የኸይር ምክንያት ይሁኑ! °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook 📱Youtube 📱Telegram °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ከሰዎች ጋራ መጨቃጨቅ አደጋ አለው °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ

ምነኛ ያማረ ስራ! ሸሪዓዊ ትምህርት ልዩ ከሚያደርገው ነገር አንዱ ባለቤቱ ስራ ባያገኝበት እንኳ በእርግጥ የአላህን ዲን የተማረ በመሆኑ በእለት ተዕለት ህይወቱ ላይ ይተገብረዋል፣ ለሰዎች ያስተምረዋል
ምነኛ ያማረ ስራ! ሸሪዓዊ ትምህርት ልዩ ከሚያደርገው ነገር አንዱ ባለቤቱ ስራ ባያገኝበት እንኳ በእርግጥ የአላህን ዲን የተማረ በመሆኑ በእለት ተዕለት ህይወቱ ላይ ይተገብረዋል፣ ለሰዎች ያስተምረዋል፣ እንዲሁም አላህን ይገዛበታል። °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° 📡 Nilesat  Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500] በተለያዩየሶሻል ሚድያ አማርጮች ይከተተሉን 📱Facebook    📱Youtube   📱Telegram    📱TikTok °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ©ዳዕዋ ቲቪ ጉዞ ስንቅን ይዞ