ቅዱሳት መጻሕፍት
Open in Telegram
በዚህ ቻናል 👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ:: 👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ:: 👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ @Holy_scriptures
Show more7 833
Subscribers
+724 hours
+357 days
+15630 days
Posts Archive
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።”
መዝሙር 6፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች
ክፍል-1
መጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ መልዕክቱ ለማንኛውም ሰው ግልፅ ሊሆን በሚችልበት ሁኔታ የተቀመጠ ስለሆነ በሁሉም የዕድሜ ክልሎችና በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሰዎች መናገር የሚችል መጽሐፍ ነው፡፡ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡14-15 ላይ ህጻናት እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና መልዕክት መረዳት እንደሚችሉ ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እኩል በሆነ ሁኔታ ግልፅ ናቸው ወይንም ደግሞ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ክፍሎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው የዘላለምን ሕይወት ማግኘት እንዲችል ማዕከላዊ መልእክቱ ብዙ ጊዜ በመደጋገምና እጅግ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እንድናነበው እንጂ እንደ ምትሃታዊ መጽሐፍ በመቁጠር ተንተርሰነው እንድንተኛ ወይንም ደግሞ ሊነካካ በማይችልበት ስፍራ በጥንቃቄ እንድናስቀምጠው አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ውስጥ ሊሠራ የሚችለው ሲነበብ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደ አድካሚ ኃይማኖታዊ ሕግጋት ስብስብ ሊታሰብ አይገባም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሕይወት ቃል ነው፤ ሕያውና የሚሠራም ነው፡፡ ስናነበው እምነትን በውስጣችን ይፈጥራል፣ ነፍሳችንን ያድሳል፤ ይለውጠናልም፡፡ በውስጡ የተቀመጡትን ሕግጋት በራሳችን ኃይልና ጥረት ልንፈፅማቸው እንደምንችል መቁጠር አይኖርብንም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ሐሳብ ለመኖር መጀመርያ ቃሉ በውስጣችን በሚፈጥረው እምነት በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት በማመን አዲስ ፍጥረት መሆን ያስፈልገናል፤ ከዚያም ኃይል የሚሰጠውን የክርስቶስን መንፈስ መቀበል ያስፈልገናል፡፡
የእግዚአብሔርን ቃል አንብበን የምንረዳው ሰዎች ባወጡት ቀመር መሠረት ባይሆንም ነገር ግን ሊታወቁ የሚገባቸው መርሆች አሉ፡፡ በማስከተል እነዚህን መርሆች እንዳስሳለን፡፡
የልብ ዝግጅት
አንዳድ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚናገሩት የተለመደ ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስን በማንበባቸው ሳብያ ትክክል አለመሆኑን እንደተገነዘቡና በቀደመው ሃይማኖታቸው እንዲፀኑ እንደረዳቸው ነው፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን ያልተገነዘቡት አንድ እውነት ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል ተልዕኮ ሁለት ገጽታ ያለው መሆኑን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ለሚጠሙ ሰዎች የሕይወት ቃል ሲሆን በእውነት ላይ ለሚያምጹ ሰዎች ደግሞ የፍርድ ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሰዎችን ወደ እምነት ያመጣል አለዚያም ደግሞ ልባቸውን በማደንደን ይገፈትራቸዋል፡፡ ሁለቱም ውጤቶች ግን ከሰዎቹ የልብ ዝግጅት አንጻር የሚከወኑ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት አልባ ንግግር ሳይሆን የሚሠራ ነው፡-
“የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል”
(ዕብ. 4፡12)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው በመጨረሻው ቀን በኛ ላይ የሚፈርደው ቃሉ ነው፡-
“ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም። የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።”
(ዮሐ. 12፡47-48)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ መልዕክቱ ላይ የሚከተለውን ይናገራል፡-
“በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?” 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡15-16
ሐዋርያው እያለ ያለው ነገር ቢኖር ወንጌል ዝም ብለን የምንቀበለው ወይንም ደግሞ የምንጥለው ነገር ሳይሆን ብንቀበለው ወይንም ደግሞ ባንቀበለው በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ ማምጣቱ ግድ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲንቁ፣ መዘባበቻ ሲያደርጉና ሲያምጹበት የተሸነፉት እነርሱ እንጂ ቃሉ አይደለም፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ የእግዚአብሔር ቃል አሸናፊ ነው፡፡ ለተቀበሉት የዘላለምን ሕይወት ሲሰጥ ባልተቀበሉት ላይ ግን ይፈርዳል፡፡ የወንጌል መልዕክት እውነትን ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የሕይወት ዜና ነው፤ ለዘባቾች ግን የሞት ዜና ነው፡፡ ውድ አንባቢያን እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል እውነትን በሚፈልግ ልብ ከሚያነቡት ወገን ናችሁ ወይንስ ከቃሉ ውስጥ “ስህተቶችን” ነቅሰው ለማውጣት ከሚያነቡት ሰዎች ወገን ናችሁ? ቀና በሆነ ልብ ቃሉን በማንበብ የዘላለምን ሕይወት ታገኙ ዘንድ ምኞታችንና ጸሎታችን ነው፡፡
ሥነ ፍታቴ (Hermeneutics)
የሥነ ፍታቴ ጥቅም መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ለመጀመርያዎቹ ተቀባዮች የነበረውን ትርጉምና ዛሬም ደግሞ ለኛ ምን ማለት እንደሆነ እንድንረዳ ማገዝ ነው፡፡ በዘመናት መካከል ሰዎች ይህንን ቃል ብዙ ክፉ ሥራዎቻቸውን ለማጽደቅ ጠቅሰውታል፡፡ በዚህ ዘመንም ብዙ ሰዎች በመልካምም ሆነ በእኩይ ፍላጎት በመነሳሳት መጽሐፍ ቅዱስ ያላለውን ነገር ሲያስብሉት እናያለን፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሰባኪያን ትግላቸው በአንድ ጥቅስ ውስጥ ያለን ልዩ ትርጉም ማግኘት ይመስላል፡፡ የስህተት አስተማሪዎችና ከክርስትና ውጪ ያሉ የአንዳንድ ሃይማኖቶች ተከታዮችም ደግሞ የራሳቸውን አስተምህሮ ለመደገፍ ወይንም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት እንዳለበት ለማሳየት በማለም ጥቅሶችን ይጠመዝዛሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ሰዓት ከመሠረታዊ የሥነ ፍታቴ መርሆች ጋራ የሚጣረስ አተረጓጎም የምንጠቀም ከሆነ ወደ ስህተት እንገባለን፡፡ ስለዚህ ማንኛውም መጽሐፍ ቅዱስን ለግል ሕይወቱም ሆነ ሌሎችን ለማስተማር ማጥናት የሚፈልግ ሰው እነዚህን ጠቃሚ መርሆች ማወቅ ይኖርበታል፡፡
ጎርደን ዲ. ፊ. እና ዳግላስ ስቱዋርት የተባሉ ክርስቲያን ጸሐፍት የሥነ ፍታቴን አስፈላጊነት በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል፡-
ሥነ ፍታቴ አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ መርህ በመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ ውስጥ ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕርይ የክርስቶስን ባሕርይ በምትረዳበት ሁኔታ ስትረዳ እንደኖረች ታሪክ ያሳያል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ጊዜ ሰብዓዊም መለኮታዊም ነው፡፡ ፕሮፌሰር ጆርጅ ላድ አንድ ጊዜ እንደተናገሩት፦ “መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ቃላት በታሪክ ውስጥ የተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡” እንግዲህ ይህ ሁለትዮሽያዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ ነው እንድንተረጉመው የሚያስገድደን፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.ewnetlehulu.org
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እኔም እንዳልሞት በሕይወቴ ዘመን የእግዚአብሔርን ቸርነት አድርግልኝ፤”
1ኛ ሳሙኤል 20፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አቤቱ፥ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።”
ኢሳይያስ 26፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
#እራሳችንን_እንመርምር
በአሁን ወቅት አብዛኞቻችን በቅዱሳን ኅብረት ውስጥ የእኛን አስበልጠን በተለያየ ጎራ ተከፋፍለን የምንገኝ ቢሆንስ? ለክርስቶስ ቀንተን ወይስ በምልክት ወይም በጥበብ የተሻለ ነው ያልነው ጎራ ውስጥ ተሰልፈን? ለክርስቶስ ወግነን ቢሆንስ በመከፋፈል እርሱ ይከብራል?
“ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?”
1ኛ ቆሮንቶስ 1፥13
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።”
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥7 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።”
መዝሙር 85፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም
ክፍል-4
(የመጨረሻ ክፍል)
በመጀመሪያ የተከሰተው ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቃል አለመታዘዝ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለውን ሥልጣን ግምት ውስጥ ሳናስገባ አንዳች ማድረግ ወይም እናደርገው ሲገባን ሳናደርገው ብንቀር ኃጢአት ይሆናል፡፡ ኃጢአት በ1ዮሐ.3፡4 "ዓመፅ" ተብሎ ተገልጾአል፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳንጠይቅ እንደፈቃዱ ሳይሆን በገዛ ፈቃዳችን የምንሠራው ሁሉ ኃጢአት ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ መታዘዝን እንዴት እንዳሳየ እስኪ እንመልከት፡፡ በዕብራውያን 10፡7 ላይ ‹‹ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ›› ይላል፡፡ ፈቃድን ለማድረግ ደግሞ መታዘዝን መማር ነበረበት (ዕብ.5፡6) እርሱ ዘላለማዊው አምላክ እንደመሆኑ መጠን መታዘዝ ለእርሱ እንግዳ ነበርና፡፡ በወልድነቱም በምድር በነበረበት ጊዜ ሁልጊዜ አብን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ይሠራ ነበር፡፡ እንዲህም አለ፤ ‹‹የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አድርግ ዘንድ ሥራውንም እፈፅም ዘንድ ነው፡፡›› (ዮሐ.4፡35)
ሰው ሁሉ በየመንገዱ በሚሄድበትና ሁሉም የራሱን ፈቃድ በሚሠራበት በዚህች ምድር ይህ ሰው (ወልድ) ግን ፍጹም ቅዱስ ሆኖ ሳለ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ብቻ ሲፈፅም መታየቱ ለእግዚአብሔር ምንኛ ደስ ያሰኘዋል!
በአሁኑ ጊዜም እግዚአብሔርንና ፈቃዱን አውቀው ለማገልገል ደስተኞች የሆኑና ይህንንም ለመረዳት ቃሉን በትጋት የሚመረምሩ ሰዎች ሲገኙ እግዚአብሔር ምን ያህል ደስ ይሰኝ!
ቃሉን ለማወቅ በመፈለግ ስናጠና የሚሰጠንን ጥቅም ታላቅነት መገመት ይቻላል፡፡ በቃሉ ውስጥ የጌታን ክብርና ጌታ በፍቅሩ ያዘጋጀልንን በረከት ስናይ ልባችን በደስታ ይሞላል፡፡ ቃሉን በማወቅ የእግዚአብሔርን ሐሳብ በበለጠ መረዳት እንችላለን፡፡ ከሰይጣን ጥቃት የምንከላከልበትንና ራሳችንም መልሰን ለሌላው ሰው የነፍሱን ደኅንነት በመንገር ጠላትን የምናጠቃበት የጦር ዕቃችን ቃሉ ነው፡፡
እባክህ ተወኝ ጭንቅላቴ ወንፊት ነው ምንም መያዝ አይችልምና ማጥናቱ ይከበደኛል የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፤ ነገር ግን ወንፊቱም ደጋግሞ ውኃ ሲያልፍበት ማቆር ባይችልም ራሱ ግን ይፀዳል፡፡ ውኃውም የወንፊቱን ቆሻሻነት ያስወግዳል፡፡ የእግዚአብሔር ቃልም ሰውን እንዲሁ ያነፃል፡፡ ማንበብ ብቻ ሳይሆን በቃሉ ላይ ጊዜ ወስዶ ማሰላሰል አስፈላጊ ነው፡፡ ጥሩ የሆኑ ማብራሪያዎችንም መጠቀም መልካም ነው፤ ሆኖም ማብራሪያውን ራሱንም በቃሉ ልንፈትነው የተገባ ነው፡፡ ማብራሪያው ቃሉን እንዲተካ ማድረግ የለብንም፤ ምክንያቱም ቃሉን የሚተካ ሌላ የአማራጭ አስተያየት ሊኖር አይገባምና እንደዚህ ማድረግም በራሱ ስሕተት ነው፡፡
‹‹ልጄ ሆይ ቃሌን ብትቀበል ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፤ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ፤ ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሳ እርስዋንም እንደ ብር ብታፈላልጋት እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፡፡››
(ምሳ.2፡1-5)፡፡
ምንጭ፦ gbv-online.org
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
#አዲስ_ዓመት
የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም
ክፍል-3
የእግዚአብሔር ቃል ያነጻል
የእግዚአብሔር ቃል የምንፀዳበትና የምንቀደስበት ብቸኛ የእግዚአብሔር መንገድ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ያደረገላትን ሲገልጥ ‹‹በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ›› (ኤፌ.5፡25) ይላል፡፡ በዮሐ.17፡17ም እንዲሁ ‹‹በእውነትህ ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው›› የሚል እናገኛለን፡፡
አዘውትረን የእግዚአብሔርን ቃል ለአካሄዳችንና ለመንገዳችን የምንጠቀም ከሆንን ሕይወታችን ነጽቶ ከክፉ ተለይተን መኖር እንችላለን፡፡ በአብ ዘንድ ያለው ጠበቃችን እግሮቻችንን በቃሉ ያጥባቸዋል (1ዮሐ.2፡2)፤ ነገር ግን እግሮቻችን እንዲታጠቡ መፍቀድ የእኛ ኃላፊነት ነው፡፡
መዝሙረኛውም አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ (መዝ.119፡11) ይላል፡፡ በሌላ ስፍራም ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል ይላል(መዝ.19፡11)፡፡
ልምምድ እና ትምህርት ሁሉ በቃሉ ይመዘናል
አሁንም በመዝ.119፡168 ‹‹መንገዶቼ ሁሉ በፊትህ ናቸውና ትእዛዝህንና ምስክርህን ጠበቅሁ›› ሲል ‹‹መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ›› እያለ ደግሞ በራእይ 2 እና 3 የሚያሳስብ ቃል ተጽፎ እናገኛለን፡፡ በአብያተ ክርስቲያናት (በአማኞች ማኅበር) ውስጥ የሚደረጉ ነገሮችን ሁሉ መፈተን አለብን፡፡ የሚሰጠው ትምህርትና የሚደረገው ተግባር ሁሉ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት ከሚለው አንፃር ታይቶ በቃሉ መፈተን አለበት፡፡ በሌላ ስፍራም እንዲህ ይላል ‹‹ነቢያትም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ ሌሎችም ይለዩአቸው›› (1ቆሮ.14፡29) አካሄዳችንንና ሐሳባችንንም በቃሉ መፈተን አለብን፡፡ ሐሳቦቻችን ምንም ጥቅም የላቸውም፡፡ ወሳኙ የእግዚአብሔር ቃል የሚለው ነገር ብቻ ነው፡፡
በሐዋ.17፡11 ስናይ በቤሪያ የነበሩት አይሁዳውያን በተሰሎንቄ ከነበሩት የሚሻሉበት ነበረ፡፡ ምክንያቱም የጳውሎስን ትምህርት ከቃሉ አንፃር እያስተያዩ ይመረምሩት ነበርና፡፡ ጳውሎስም የትምህርቱ መነሻ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሆኑ በግልጥ ያሳየበት ተጽፎ ይገኛል (1ቆሮ.15፡3-4)፡፡
‹‹የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል፡፡››(2ጢሞ.3፡16-17)፡፡
መታዘዝና ለፈቃዱ መገዛት
‹‹ትእዛዛትህን እጅግ እንጠብቅ ዘንድ አንተ አዘዝህ›› (መዝ.119፡4) ‹‹ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል›› (መዝ.19፡11) ‹‹እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ›› (ዮሐ.15፡10)፡፡ ‹‹የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን›› (ዮሐ.14፡23)፡፡ ‹‹ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም›› (1ዮሐ.5፡3)፡፡
ከእነዚህም ንባቦች ሰው ቃሉን አውቆ መታዘዝ እንዳለበት እግዚአብሔር ለመታዘዝ ምን ያህል ዋጋ እንደሰጠ መገመት ይቻላል፡፡ ምን አድርግ ዘንድ ትወዳለህ? ለሚለው ጥያቄ የሚሰጠን መልስ ትእዛዜን ጠብቅ የሚል ይሆናል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ gbv-online.org
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።”
ዘፍጥረት 2፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
#አዲስ_ዓመት
የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ጥቅም
ክፍል-2
የእግዚአብሔር ቃል መሪያችን ነው
መዝሙረኛው በመዝ.119፡9 ‹‹ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው›› ይላል፡፡ ወረድ ብሎም በቊጥር 11 ላይ ‹‹አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ›› ሲል በቁ.105 ላይ ደግሞ ‹‹ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው›› ይላል፡፡
እግዚአብሔር ለኢያሱ እንደዚህ አለው ‹‹ነገር ግን ጽና እጅግ በርታ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፡፡ የዚህ ሕግ መጸሐፍ ከአፍህ አይለይ፡፡ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፡፡ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም›› (ኢያ.1፡7-8)፡፡
አስቸጋሪ ሁኔታ በነበረበት ጊዜ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሽማግሌዎች ‹‹ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ›› (ሐዋ.20፡32) ሲል ለጢሞቴዎስ ደግሞ ‹‹መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል›› (2ጢሞ.3፡15) ይለዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የማናውቅ ከሆነ ኃጢአት ምን መሆኑን እንዴት እናውቃለን? ነገር ግን አለማወቃችን ነፃ ሊያወጣን አይችልም (ዘሌ.5፡17) እግዚአብሔር ስለሁሉም ነገር የተናገረበትን ቃሉን ካላጠናን ማድረግ የሚገባንንና እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የሆነውንስ እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ቃሉን የማናውቅ ከሆንን አንዳንድ አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች እንዴት ልንወሰንና የምንሄድበትንም መንገድ እንዴት ልንመርጥ እንችላለን?
‹‹ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ፡፡ ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ፡፡ ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ፡፡ ... የቃልህ ፍቺ ያበራል ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል፡፡›› (መዝ.119፡98-100፣130)
ቃሉ የጦር ዕቃችን ነው
‹‹የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡›› (ኤፌ.6፡17) ‹‹በቃልህ ታምኛለሁና ለሚሰድቡኝ በነገር እመልስላቸዋለሁ፡፡››(መዝ.119፡42)
ይህን ሰይፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደተጠቀመበት እንመልከት፡፡ ከሰይጣን የሚመጣበትን ጥያቄ ሁሉ ተጽፎአል እያለ ይመክት ነበር (ማቴ.4፡4፣7፣10) ውጤቱም ሰይጣንን እንዲሸሽ አስገድዶታል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቃል መቋቋም የሚችል ኃይል አልነበረውምና ነው፡፡
ጌታችን ቃሉን በቀጥታ ሰይጣንን ለማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የሰዎችንም ሐሳብ ለማክሸፍ ተጠቅሞበታል፤ በሉቃስ 20፡17 ለሚያስተምራቸው ሕዝብ ‹‹... ተብሎ የተጻፈው ይህ ምንድር ነው?›› ብሎ ሲያሳስብ ይታያል፡፡ በዮሐ.10፡34 ደግሞ ‹‹... ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?›› ሲል ይጠይቃል፡፡
‹‹የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና የሚሠራም ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፡፡ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፡፡ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም፡፡›› (ዕብ.4፡12-13)
ሰይጣንና ዓለምን ለመከላከልና ለማጥቃትም ልንጠቀምበት የምንችለው ብቸኛ መሣሪያ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ የሕያው እግዚአብሔር ቃል በመሆኑ በውስጡ ኃይል እንዳለው ልንረሳ አይገባንም፡፡ ስንጠቀምበት ቃሉን የምንሰነዝርበት ሰው ሁሉ የቃሉን ኃይል ያውቃል፡፡ በቃሉ የምናነጋግረው ግለሰብ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ወይም ያልተሰማው በመምሰል የተረጋጋ ለመምሰል ቢሞክር ወይም ተቃውሞው ቢቀጥልም እንኳን ሕሊናውን ግን ይወቅሰዋል፡፡ የተባለው ነገር እውነት እንደሆነም ያውቃል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ gbv-online.org
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7 833
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደገና ለመገንባት ከየትኛው ከተማ በመነሳት ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ?
7 833
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፤ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።”
ዘፍጥረት 49፥22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
