ቅዱሳት መጻሕፍት
Open in Telegram
በዚህ ቻናል 👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ:: 👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ:: 👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ። ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ @Holy_scriptures
Show more7 956
Subscribers
+824 hours
+247 days
+4630 days
Loading data
Similar Channels
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
October '26Oct '26
October '26
+138
in 0 channels
September '26
+200
in 3 channels
Get PRO
August '26
+252
in 1 channels
Get PRO
July '26
+179
in 2 channels
Get PRO
June '26
+193
in 2 channels
Get PRO
May '26
+170
in 2 channels
Get PRO
April '26
+150
in 3 channels
Get PRO
March '26
+133
in 1 channels
Get PRO
February '26
+93
in 1 channels
Get PRO
January '26
+130
in 4 channels
Get PRO
December '25
+153
in 1 channels
Get PRO
November '25
+217
in 3 channels
Get PRO
October '25
+146
in 1 channels
Get PRO
September '25
+130
in 3 channels
Get PRO
August '25
+194
in 1 channels
Get PRO
July '25
+222
in 2 channels
Get PRO
June '25
+193
in 3 channels
Get PRO
May '25
+263
in 4 channels
Get PRO
April '25
+242
in 7 channels
Get PRO
March '25
+268
in 5 channels
Get PRO
February '25
+265
in 1 channels
Get PRO
January '25
+318
in 1 channels
Get PRO
December '24
+310
in 0 channels
Get PRO
November '24
+400
in 3 channels
Get PRO
October '24
+266
in 5 channels
Get PRO
September '24
+301
in 3 channels
Get PRO
August '24
+380
in 0 channels
Get PRO
July '24
+218
in 1 channels
Get PRO
June '24
+210
in 1 channels
Get PRO
May '24
+237
in 3 channels
Get PRO
April '24
+345
in 7 channels
Get PRO
March '24
+244
in 5 channels
Get PRO
February '24
+215
in 2 channels
Get PRO
January '24
+243
in 0 channels
Get PRO
December '23
+186
in 1 channels
Get PRO
November '23
+106
in 2 channels
Get PRO
October '23
+95
in 1 channels
Get PRO
September '23
+69
in 0 channels
Get PRO
August '23
+87
in 0 channels
Get PRO
July '23
+93
in 0 channels
Get PRO
June '23
+75
in 0 channels
Get PRO
May '23
+29
in 0 channels
Get PRO
April '23
+23
in 0 channels
Get PRO
March '23
+26
in 0 channels
Get PRO
February '23
+35
in 0 channels
Get PRO
January '23
+58
in 0 channels
Get PRO
December '22
+59
in 0 channels
Get PRO
November '22
+66
in 0 channels
Get PRO
October '22
+50
in 0 channels
Get PRO
September '22
+82
in 0 channels
Get PRO
August '22
+58
in 0 channels
Get PRO
July '22
+67
in 0 channels
Get PRO
June '22
+71
in 0 channels
Get PRO
May '22
+60
in 0 channels
Get PRO
April '22
+57
in 0 channels
Get PRO
March '22
+57
in 0 channels
Get PRO
February '22
+51
in 0 channels
Get PRO
January '22
+54
in 0 channels
Get PRO
December '21
+32
in 0 channels
Get PRO
November '21
+69
in 0 channels
Get PRO
October '21
+85
in 0 channels
Get PRO
September '21
+77
in 0 channels
Get PRO
August '21
+80
in 0 channels
Get PRO
July '21
+106
in 0 channels
Get PRO
June '21
+52
in 0 channels
Get PRO
May '21
+46
in 0 channels
Get PRO
April '21
+106
in 0 channels
Get PRO
March '21
+57
in 0 channels
Get PRO
February '21
+81
in 0 channels
Get PRO
January '21
+172
in 0 channels
Get PRO
December '20
+3 417
in 0 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 29 October | +2 | |||
| 28 October | +9 | |||
| 27 October | +4 | |||
| 26 October | +6 | |||
| 25 October | +9 | |||
| 24 October | +8 | |||
| 23 October | +7 | |||
| 22 October | +2 | |||
| 21 October | +8 | |||
| 20 October | +5 | |||
| 19 October | +7 | |||
| 18 October | +9 | |||
| 17 October | +4 | |||
| 16 October | +4 | |||
| 15 October | +4 | |||
| 14 October | +3 | |||
| 13 October | +3 | |||
| 12 October | +1 | |||
| 11 October | +2 | |||
| 10 October | +2 | |||
| 09 October | +5 | |||
| 08 October | +5 | |||
| 07 October | +2 | |||
| 06 October | +5 | |||
| 05 October | +6 | |||
| 04 October | +6 | |||
| 03 October | +5 | |||
| 02 October | +2 | |||
| 01 October | +3 |
Channel Posts
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ብቻ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ፤ ይህ ከሆነ መጥቼ ባያችሁ ወይም በርቀት ሆኜ ስለ እናንተ ብሰማ፣ ለወንጌል እምነት እንደ አንድ ሰው ሆናችሁ በመጋደል በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ እንደምትቆሙ ዐውቃለሁ።”
ፊልጵስዩስ 1፥27 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
| 2 | ቤተክርስቲያን
ክፍል-3
1. በዚህችም ዓለት ላይ
ጌታ ኢየሱስ ቤተክርስቲያኑን የሚሠራበትን መሠረት ሲገልጥ «በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያንን እሠራለሁ» ብሏል፡፡ ከዚህም ቃል የቤተክርስቲያን መሠረት «ዓለት» እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በማቴ7፡24-27 የተመዘገበውን የጌታችንን ምሳሌ ስናነብ ልባም ሰው ቤቱን በዓለት ላይ እንደሚሠራና ያንንም በዓለት ላይ የተመሠረተ ቤት ዝናብ ቢወርድም ጐርፍ ቢመጣም ነፋስ ቢነፍስም ፈጽሞ ሊወድቅ እንደማይችል ያስረዳል፡፡ በተቃራኒው ግን ሰነፍ ሰው የሚሠራው በአሸዋ ላይ የተመሠረተ ቤት ዝናብ ሲወርድ ጐርፍ ሲመጣ ነፋስም ሲነፍስ ታላቅ አወዳደቅ እንደሚወድቅ ይገልጻል፡፡ ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ኢየሱስ ክርስቶስ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ «ልባም ሰው» ነው፡፡
«በዚህችም ዓለት ላይ...» የሚለውን ይህንን ቃል የሚያነቡ ሁሉ «ይህች ዓለት ምንድር ናት?» ብለው መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡ ጌታችን ከዚህ ንባብ ቀደም ብሎ «አንተ ጴጥሮስ ነህ» ካለ በኋላ «በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ» ብሎ መናገሩን በመመልከት በዚህ ንባብ ውስጥ ዓለት የተባለው «ጴጥሮስ ነው» የሚል የተሳሳተ መረዳት መኖሩ ይታወቃል፡፡ ይህም መረዳት ንባቡ የቀረበበትን ሰዋስው በተለይም የቃሉን ጾታ ካለማስተዋል የመጣ ነው፡፡ ጌታችን «አንተ ጴጥሮስ ነህ» የሚለውን ቃል የተናገረው በተባዕታይ ጾታ እንደሆነ ያስተዋለ አንባቢ «በዚህችም ዓለት» የሚለውን ቃል ሲያነብ ዓለቷ ጴጥሮስ ነው ማለት አይችልም፤ ይህ የተባዕታይንና የእንስታይን ጾታ ማደባለቅ ነው፡፡ በዚህ ፈንታ ግን ጌታችን «በዚህች» በሚለው ጠቋሚ ቃል በእንስታይ ጾታ የጠራት ዓለት ምንድናት? ብሎ በመጠየቅ ምላሹን ከዚሁ ንባብ ውስጥ ያፈላልጋል፡፡ በሰው ሐሳብ ሳይጠላለፍ በመንፈስ ቅዱስ በተቃኘ ኅሊና ሆኖ እሰካነበበ ድረስም ምላሹን በዚሁ አንቀጽ ውስጥ በቅርቡ ያገኛል፡፡ «በዚህች» በሚለው የቅርብ አመልካች ቃል የተጠቆመችው የዚህች ዓለት ምንነት ኢየሱስ ቃሉን በሚናገርበት በዚያው ሰዓት የተገለጠ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም አንባቢው ዓይኖቹን ከፍ አድርጐ ወደ ቊጥር 16 ቢመለከት ጌታችን ስለማንነቱ ለደቀመዛሙርቱ ላቀረበው ጥያቄ ጴጥሮስ የመለሳትን አጭርና ግልጽ መልስ ያገኛል፡፡ እርስዋም «አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ» ብሎ በሥጋና በደም ሳይሆን በሰማያዊ መገለጥ የተናገራት ቃል ናት፡፡
በግሪክ ቋንቋ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ጴጥሮስ የሚለው ቃል «petros/ፔትሮስ/» ተብሎ የተጻፈ ሲሆን ዓለት የሚለው ቃል ግን «petra/ፔትራ/» ተብሎ ተጽፏል፤ ይህም በሁለቱ ቃላት መካከል ግልጽ የሆነ የትርጉም ልዩነት እንዳለ ያሳያል፤ «ፔትሮስ» ማለት ከዓለት የተከፈለ ድንጋይ /ጡብ/ ማለት ሲሆን «ፔትራ» ማለት ራሱ ሙሉው ዓለት ነው፡፡ ጌታችንም ቤተክርስቲያኔን በፔትራ /በንጥፍ ዓለት/ ላይ እመሠርታለሁ አለ እንጂ በፔትሮስ /በጡብ/ ላይ እመሠርታለሁ አላለም፤ ስለሆነም የቤተክርስቲያን መሠረት «አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ» የምትለው የእምነት ቃል ናት እንጂ ጴጥሮስ አለመሆኑን አንባቢው ሊያስተውል ይገባል፡፡ ይህችም የእምነት ቃል ስለክርስቶስ የምትናገር ስለሆነ የቤተክርስቲያን መሠረት ራሱ ክርስቶስ ነው ቢባል ትክክል ነው፡፡ በ1ቆሮ.3፡11 ላይ ‹ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው› ተብሎ ተጽፏልና፡፡
የቤተክርስቲያን መሠረት «አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ» የምትለው የእምነት ቃል ናት እንጂ ጴጥሮስ አለመሆኑን አንባቢው ሊያስተውል ይገባል፡፡ይህንን ቃል የሕይወት መመሪያ ያደረገ ክርስቲያን እኔ የምሰበሰብበት መንፈሳዊ ጉባዔ የተመሠረተው በምን ላይ ነው? ብሎ በማስተዋል ሊመረምር ይገባዋል፡፡ በዘመናችን በየስፍራው የሚቋቋሙት ድርጅታዊ ገጽታ ያላቸው አብያተክርስቲያናት የቆሙበትን መሠረት በጥንቃቄ ልንመረምር ያስፈልጋል፡፡ ለቤተክርስቲያን ህልውና መሠረት የሆነውን «ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው» የሚለውን የእምነት ቃል ወደ ጐን በመተው ወይም ትኩረት በመንፈግ፣ መሠረት ተደርገው ያልተነገሩትን ሌሎች መንፈሳውያን ትምህርቶችና ሥርዓቶች መሠረት ማድረግ አሳዛኙ የክርስቲያኖች ገጽታ እየሆነ መጥቷል፤ ከ4ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሚታየውን የዓለማዊቷን ቤተክርስቲያን መለያየት ስንመለከት ዋነኛ ምክንያቱ ሥልጣንን፣ ጥቅምን፣ ክብርንና ማዕርግን ማስጠበቅ ቢሆንም ሰበብ የሆኑት መንፈሳዊ ምክንያቶች ግን፣ ክርስቶስ አንድ ባሕርይ ወይስ ሁለት ባሕርይ ነው?፣ ጥምቀተ ህፃናት ልክ ነው ወይስ አይደለም? ሥዕል ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? በጌታ እራት ጊዜ ኅብስቱና ወይኑ ወደ ሥጋና ደም ይለወጣል ወይስ አይለወጥም? የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሲገለጡ እንዴት ነው? በልሳን መናገርና አጠቃቀሙን የምንረዳው እንዴት ነው? የቤተክርስቲያን አስተዳደር በሽማግሌዎች ወይስ በካህናት ይሁን? የሚሉትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ «ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው» የሚለውን የቤተክርስቲያን መሠረት የማይተኩ ናቸው፡፡
በእነዚህ አርእስተ ጉዳዮች ያሉት እውነተኛ ትምህርቶችም ቢሆኑ ለቤተክርስቲያን እንደ ዋና መሠረት ታይተው ጉባዔ የሚመሠረትባቸው ቤተክርስቲያን የሚከፈልባቸው አዲስ ስም የሚወጣባቸው ምክንያቶች መሆናቸው አሳዛኝ ነው፡፡ ይሁንና ከዚህ አስተሳሰብ ተለይተው መሠረታቸውን በጥልቀት የተመለከቱ በሁሉም ስፍራ የሚገኙት የእውነተኛ ክርስትና ቅሬታዎች ግን ራሳቸውን «ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው» በሚለው መሠረት ላይ ያገኙታል!!
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.ewnetone.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 257 |
| 3 | በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሞተን ነቢይ ለማነጋገር ወደ መናፍስት ጠሪ ቤት የሄደው የእስራኤል ንጉስ ማን ነው? | 358 |
| 4 | በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሞተን ነቢይ ለማነጋገር ወደ መናፍስት ጠሪ ቤት የሄደው የእስራኤል ንጉስ ማን ነው? | 50 |
| 5 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸው የሕዝቡ ሁሉ ልብ ተቈጥቶ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ።”
1ኛ ሳሙኤል 30፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 548 |
| 6 | ቤተክርስቲያን
ክፍል-2
ቤተክርስቲያን ሕንፃ ወይም ድርጅት ከሆነች ደግሞ ክርስቶስ ለሕንፃ ወይም ለድርጅት ሞቷል ማለት ሊሆን ነው፤ ሆኖም በመጽሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል በሚገኝበት በማናቸውም ጥቅስ ውስጥ በምድር ላይ ሰማያዊ ጠባይን ተላብሳ የምትገኘውን የተመረጠች የእግዚአብሔርን ጉባዔ ከማመልከት በቀር በአንድም ስፍራ ሕንፃን ወይም ድርጅትን አያመለክትም፡፡ እንዲህ ሲባል ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ለማምለክና ቃሉን ለመስማት የሚሰባሰቡበት ቤት እንዲሁም እንደ የአገሩ ሕግ ለመሰብሰብ ሆነ ለሕዝብ መንፈሳዊ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችላቸውን መንፈሳዊ ድርጅት ማቋቋም አይችሉም ማለት አይደለም፤ ይሁን እንጂ ሕንፃውም «ሕንፃ»፣ ድርጅቱም «ድርጅት» ሊባል ይችላል እንጂ «ቤተክርስቲያን» ሊባል አይችልም፡፡ ለምሳሌ በፊልሞና ቤት ውስጥ ትሰበሰብ ስለነበረችው ቤተክርስቲያን በፊልሞና መልእክት መግቢያ ላይ «በቤትህም ላለች ቤተክርስቲያን» የሚል ቃል እናነባለን (ፊል.2)፡፡ በዚህ ንባብ ውስጥ ቤተክርስቲያን በፊልሞና ቤት ስለተሰበሰበች የፊልሞና መኖሪያ ቤት «ቤተክርስቲያን» ተብላ እንዳልተጠራች እናያለን፤ በዚያ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ለቤተክርስቲያን መሰብሰቢያ ተብሎ ሕንፃ መሥራትም አልተጀመረም ነበር፡፡ ቤተክርስቲያን ትሰበሰብ የነበረው ከአማኞች መካከል ቤታቸውን ለዚህ አገልግሎት በሰጡ ወይም በፈቀዱ ሰዎች ቤት ውስጥ ነበር፡፡ ለምሳሌ የማርቆስ እናት ማርያም በኢየሩሳሌም(ሐዋ 12፡5-12)፣ አቂላና ጵርስቅላ በሮሜ (ሮሜ16፡3-5)፣ ፊልሞና በቈላስይስ (ፊልሞ2፣11፤ ቈላ.4፡9)፣ ንምፉን በሎዶቅያ (ቈላ.4፡15) ቤታቸውን ለቤተክርስቲያን መሰብሰቢያ እንዲሆን ከፈቀዱት መካከል የሚጠቀሱ /ቅዱሳን/ ሰዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በቤታቸው የምትሰበሰበው የምእመናን ኅብረት ቤተክርስቲያን ተባለች እንጂ የአንዳቸውም መኖሪያ ቤት «ቤተክርስቲያን» ተብሎ አልተጠራም::
የቤተክርስቲያን መሠረት
ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ትርጉሙ ምን እንደሆነ ከተመለከትን አሁን ደግሞ ቤተክርስቲያን የተመሠረተችበት መሠረት ምን እንደ ሆነ የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እናያለን፡፡ ማንኛውንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ከመሠረቱ ጀምረን ካላወቅን የሚኖረን መረዳት የተሟላ ካለመሆኑም በላይ ጣልቃ በሚገቡ የሰው ሐሳቦች ምክንያት በተሳሳተ መንገድ ልናስብም እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ እውነተኛ አማኝ የቤተክርስቲያን አባል እንደመሆኑ መጠን ትክክለኛ ስፍራውን ያውቅ ዘንድ ይህንን ጽኑ የሆነ የቤተክርስቲያን መሠረት አጥብቆ ሊረዳ ይገባዋል፡፡ የሁላችንንም ትኵረት በእጅጉ የሚስበውን ይህንን የቤተክርስቲያን መሠረት የሚያሳውቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የሚገኘው «ቤተክርስቲያን» የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጽፎ በሚገኝበት በማቴ.16፡13-18 ውስጥ ነው፡፡ ይህም ክፍል እንደሚከተለው ይነበባል:-
«ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሳርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን:- የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ፤ እነርሱም:- አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ኤልያስ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት፡፡ እርሱም:- እናንተስ እኔን ማን እንደሆንኩ ትላላችሁ? አላቸው፡፡ ስምዖን ጴጥሮስም:- መልሶ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ፡፡ ኢየሱስም መልሶ:- የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም» ይላል፡፡
በዚህ ክፍል ውስጥ እንደተገለጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «... በዚህችም አለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም ...» ብሎ ሲናገር እንሰማዋለን/ቊ.18/፡፡ ጌታችን ይህንን ቃል የተናገረው የ3ቱን ዓመት የማስተማር ዘመኑን እያጠናቀቀ ሳለ ወደ ኢየሩሳሌም ለመጨረሻ ጊዜ ከመውጣቱ በፊት በፊልጶስ ቂሣርያ እያለ እንደነበር የዚህን ንባብ ምዕራፍ ስናጠና እንደርስበታለን/ቊ.21/፡፡ በዚያ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ «ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ» ብሎ በትንቢታዊ ቃል መናገሩ በጊዜው ገና ቤተክርስቲያን ተሠርታ እንዳልነበረ ያመለክተናል፡፡ በእርግጥም በደሙ በሚደረግ ቤዛነት ሕዝብን ከነገድ ከቋንቋ ሳይዋጅ ቤተክርስቲያን ልትሠራ እንዴት ትችላላች? ቤተክርስቲያንን በገዛ ደሙ እንደዋጃት የሚያስረዳ ግልጽ ንባብ እናገኛለንና(ሐዋ 20፡28)፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ ሞት የኃጢአት ዕዳ ከመከፈሉ በፊት ቤተክርስቲያን እንዳልተሠራች ልንገነዘብ እንችላለን፡፡
አሁን ደግሞ የቤተክርስቲያንን መሠረት በተመለከተ «...በዚህችም አለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም...» ብሎ ጌታችን በተናገረው ቃል ውስጥ ያሉትን ሁለት ዋና ዋና ኃይለ ቃላትን እንመልከት፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.ewnetone.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 590 |
| 7 | በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ “ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።” በሚለው መልእክቱ የሚታወቀው ነቢይ ማን ነው? | 618 |
| 8 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አሁን ግን፥ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።”
ኢሳይያስ 64፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 690 |
| 9 | ቤተክርስቲያን
ክፍል-1
በክርስትና ስም በሚጠራው ዓለምም ሆነ ክርስቲያን ባልሆነው ዓለም «ቤተክርስቲያንን» በተመለከተ ያለው መረዳት መጽሐፍ ቅዱስ ከሚነግረን እውነት ጋር በሚፋለስበት በዚህ ዘመን ስለ ቤተክርስቲያን ያለውን ትክክለኛ ሐሳብ ማወቅ በብዙዎች ዘንድ የሚናፈቅ ሆኗል፡፡ በብዙ የዶክትሪን አስተሳሰቦች እና ሥርዓተ አምልኮዎች የሚለያዩና በተለያዩ ስያሜዎች የሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት በበዙበት በዚህ በያዝነው ክፍለዘመን የቤተክርስቲያንን ትክክለኛ ማንነት ለማወቅ የተጠማውን የሰዎችን ኅሊና የሚያረካ እውነት መገኘት የሚችለው ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከተጻፈው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ 150 ጊዜ ያህል ተጠቅሶ የሚገኝ በመሆኑ የቤተክርስቲያን ትክክለኛ ገጽታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በስፋት ይገኛል፤ የመንፈስ ቅዱስን ምስክርነት በውስጥ ጆሮአችን እያዳመጥን ብናነበው ስለ ቤተክርስቲያንም ሆነ ስለሌሎች ታላላቅ መንፈሳውያን ርእሶች የተገለጠ እውነትን እናገኝበታለን፡፡
የቤተክርስቲያን ማንነት
«ቤተክርስቲያን» የሚለው ቃል በግሪክ ቋንቋ «ኤክሌሲያ» ለሚለው ቃል የተሰጠ ትርጉም ሲሆን ኤክሌስያ ማለትም «የተጠራች ጉባዔ» ማለት ነው፡፡ በግእዝም ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል የክርስቲያን ቤት የሚል ፊደላዊ ፍቺ ቢኖረውም ዋነኛ ሐሳቡ «የክርስቲያን ወገን» ማለት ስለሆነ ኤክሌስያ የሚሰጠንን ስሜት በተወሰነ ደረጃ ይዟል፤ በብሉይ ኪዳን ዘመን በምድር ላይ የነበረችው በእግዚአብሔር የተመረጠች ጉባዔ ቤተ እስራኤል ነበረች፡፡ ይህችም ጉባዔ ማለትም እስራኤል፣ ኤክሌሲያ ተብላ የተጠራችበትን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እናገኛለን(ሐዋ 7፡38፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአሕዛብ አገርም በአንድ ምክንያት የሚሰበሰብ ትልቅ ጉባዔ ኤክሌስያ ይባል ነበር (ሐዋ 19፡3)፡፡ እነዚህ በቤተ እስራኤልም ሆነ በቤተ አሕዛብ የነበሩት ጉባዔያት ምድራውያን ሲሆኑ በወንጌል ቃል በኩል ከዚህ ዓለም የተጠሩት ክርስቲያኖች ጉባዔ /ኤክሌስያ/ ግን ሰማያዊ ባሕርይ ያላት ጉባዔ ናት፤ ሐዋርያው ጳውሎስ «... ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ...» (ኤፌ 3፡10) ብሎ ከጻፈው ቃል ውስጥ ይህንን የቤተክርስቲያንን ሰማያዊ ባሕርይ እንረዳለን፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረችው የተጠራች የእግዚአብሔር ጉባዔ በሥጋ ከአብርሃም ዘር የሆኑትን ብቻ ያካተተች ጉባዔ ነበረች፡፡ በአዲስ ኪዳን ያለችው የእግዚአብሔር ጉባዔ (ኤክሌስያ) ግን ከቤተ እስራኤል ብቻ ሳይሆን ከቤተ አሕዛብም የሆኑትን ወገኖች ያቀፈች ጉባዔ ናት፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ «ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል» ብሎ «አብርሃም አባት አለን» እያሉ ለሚመኩት ፈሪሳውያን በተናገረው መሠረት (ማቴ.3፡9) ከቤተ አሕዛብ መካከል በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሁሉ የአብርሃም ልጆች ለመሆን ችለዋል፡፡ ጳውሎስም ክርስቶስ ኢየሱስ በእንጨት ላይ የተሰቀለው አሕዛብን በእርሱ በኩል ወደ አብርሃም በረከት ውስጥ ለማስገባት እንደሆነ ሲናገር «በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፏልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በእምነት ይደርስላቸው ዘንድ» ብሏል (በገላ.3፡14)፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የመሠረተው ከቤተ እስራኤልና ከቤተ አሕዛብ በተጠራ አዲስ ሕዝብ ነው፡፡ በመስቀል ላይ የመሞቱም ዓላማ ይህንኑ አዲስ ሕዝብ ይፈጥር ዘንድ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጥ «እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳ በሥጋው ያፈረሰ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው» ይላል(ኤፌ.2፡11-16)፡፡ ከዚህም እንደምንረዳው በአዲስ ኪዳን ሰዎችን የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ነው እንጂ እስራኤላዊ እና አሕዛባዊ የመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያን አባላት ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መጥለቂያ ድረስ ካሉት ነገዶች ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ያመኑት ሁሉ ናቸው፡፡
በመሆኑም «በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ ለሚጠሩትም ባለጠጋ ነው፤ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና» (ሮሜ.10፡12) የሚለው ቃል የገባቸው አማኞች በምድራቸውም ሆነ በሌሎች የውጭ አገሮች ውስጥ ሰዎች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው መሰብሰባቸውን ይናፍቃሉ፤ እንዲህ ያሉት አማኞች በዓለም ካሉት ነገዶች ሁሉ ሰዎች በክርስቶስ አምነው በስሙ የመሰባሰባቸውን ዜና ሲሰሙ ደስታና መንፈሳዊ ሐሴት ይሞላባቸዋል፡፡ እንደዚሁም በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ እንደተመዘገበው የምስጋና ቃልም «መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሙንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ» እያሉ በጉን /ጌታ ኢየሱስን/ ያመሰግኑታል (ራእ.5፡9)፡፡
«ቤተክርስቲያን» የሚለው ቃል ከሕዝብና ከአሕዛብ መካከል እግዚአብሔር የጠራቸውንና የመረጣቸውን የአዲስ ኪዳን አማኞችን ጉባኤን የሚያመለክት ሆኖ ሳለ ክርስቲያኖች ለመንፈሳዊ ጉዳዮች የምንሰበሰብበትን ቦታ ወይም አዳራሽ እንደዚሁም ራሳችን ስም አውጥተን የፈጠርነውን የእምነት ድርጅት እንዲያመለክት አድርገን መጠቀም ከቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም ውጭ መሆን ነው፡፡ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን የዋጃት በገዛ ደሙ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስረዳ «... በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ ...» ይላል (ሐዋ.20፡28)፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.ewnetone.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 665 |
| 10 | በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ዲዲሞስ በመባል የሚታወቀው የጌታ ደቀ መዝሙር ማን ነው | 686 |
| 11 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ።”
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 779 |
| 12 | #እራሳችንን_እንመርምር
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።”
ኤርምያስ 6፥16
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 793 |
| 13 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።”
ሐዋርያት 20፥29-30
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 886 |
| 14 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት ለመስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ደስም አያሰኛቸውም።”
ኤርምያስ 6፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 963 |
| 15 | የንስሃ ጥቅም
ዴሪክ ፕሪንስ የተባሉ የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪ በቤተክርስትያን ውስጥ ትልቅ ችግርን የሚፈጥሩ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች ናቸው ይላሉ፡፡
ሰው ህይወቱ የሚለወጠው ንስሃ በገባው መጠን ብቻ ነው ፡፡
አንዳንድ ሰው ንስሃን አስፈላጊነት ስለማይረዳ በንስሃ የሚፈታውን ችግሩን በሌላ ነገር ለመፍታት ሲሞክር ይንከራተታል፡፡ አንዳንድ ሰው ራሱን አዋርዶ ንስሃ ከሚገባ ይልቅ በመልካም ስራ የህይወቱን ችግር ሊያሸንፍ ሲጣጣር ህይወቱን ይገፋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስድስተው ንስሃ የሚገባ ሰው ህይወት ነው፡፡ ንስሃ ያልገባ የማንኛውም ሰው መልካም ስራ እግዚአብሄርን አያስደስተውም፡፡
"እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።"
(ሉቃስ 15፡10)
አንዳንድ ሰው ደግሞ ይቅርታ ነፃ እንደሆነ ስለማይረዳ ንስሃ ከመግባትና መንገዱን ከመቀየር ይልቅ ለክፉ ስራው በመልካም ስራ ለመክፈል ይፈልጋል፡፡ ለክፉ ስራ የሚከፈል ምንም አይነት መልካም ስራ የለም፡፡
"ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።"
(ኢሳ 64፡6)
ሃጢያትን የሰራ ሰው ያሳዘነው እግዚአብሄርን ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ ንስሃን እንጂ መማለጃን አይቀበልም፡፡ ክፉ ስራ ሰርተን እግዚአብሄርን በመልካም ስራ አናታልለውም፡፡ (ዘዳግም 10፡16-17)
ንስሃ ያልገባ ሰው መልካም ስራ በእግዚአብሄር ፊት እንደመርገም ጨርቅ አፀያፊ ነው፡፡
ንስሃ መግባት ማለት ደግሞ ማልቀስ ማለት አይደለም፡፡ ንስሃ መግባት ማለት ደግሞ በሃጢያት ማዘን ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ንስሃ መግባት ማለት እግዚአብሄርን የሚያሳዝን የተሳሳተ መንገድ መሆኑን አውቆ ቀኝ ኋላ ዙር ብሎ ወደኋላ መመለስ ነው፡፡ ንስሃ ሃሳብን መለወጥ ነው፡፡ ንስሃ የህይወት ለውጥ ነው፡፡ (ሮሜ 12፡2)
እግዚአብሄር የሚቀበለው ንስሃ የገባ ሰውን የንስሃን ፍሬ ነው፡፡ ሰው ንስሃ ከገባ በኋላ መመለሱን የሚያሳየው በመልካም ስራ ነው፡፡
ከንስሃ ውጭ ሌላ የተሳሳተን ሰው ህይወት የሚለውጥ ምንም ነገር የለም፡፡ የሰው ህይወት የሚያርፈው በንስሃ ነው፡፡
"የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥"
(ኢሳይያስ 30፡15)
ተመሳሳይ ነገር እያደረግን የሕይወት ለውጥ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ አዲሱን ወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ እንደማያደርጉት ሁሉ ህይወታችን በአዲስ መንገድ እንዲጀመር አሮጌው መተው አለበት። (ማቴ. 9፡17)
ስኬትና ክንውን ያለው ሃጢያትን በመደበቅ ሳይሆን መተው ላይ ነው፡፡ የምንነፃው ስለሃጢያታችንን ንስሃ ስንገባ ብቻ ነው፡፡
"ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።" (ምሳሌ 28፡13)
"በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።" (1ኛ ዮሐንስ 1፡9)
ንስሃ ሃጢያትን ነቅሎ የመጣል ታላቅ ሃይል አለው፡፡ ንስሃ ህይወትን የመለወጥ እና የማደስ ሃይል አለው፡፡
"እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ ደግሞም አስቀድሞ ለእናንተ የተመደበውን ክርስቶስን እርሱም ኢየሱስን ይልክላችኋል።
ሐዋ 3፡19-20 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ምንጭ:- heroaw.wordpress.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 938 |
| 16 | በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጳውሎስ እስከ ምሽት ድረስ እየሰበከ ሳለ ከመስኮት ወድቆ የሞተው ወጣት ማን ነው? | 972 |
| 17 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።”
ሮሜ 10፥11
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 1 097 |
| 18 | በክፉ ቀን..!
'' ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ አንሱ፡፡'' ኤፌ. 6፤10-19
"የክፉው ቀን" የቱ ነው? የክፉው ቀን መቼስ ነው?
ልክ እንደ አሁኑ ጊዜ ማለት ነው ፡፡ ብዙ ፈተና የበዛበት፣ የጸለዩት የማይሰማበት የሚመስልበት ቀን፤ ለጠላት የተፈቀደለት ቀን ይመስላል፡፡ ምናልባትም የዓለም ፍጻሜ ቀን የመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ እንገኛለን፡፡ በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ገጥሞናል፡፡ በዚህ ክፉ ቀን የብዙዎች አቅም የሚፈተሽበት ፣ ጉልበታቸው የሚላላበት፣ እምነታቸውን የሚፈትን ነገር የሚገጥምበት ... ጊዜ ነው፡፡
በሕይወት ያልታሰበ ነገር ሲገጥም ያስደነግጣል፤ ቢሆንም የመጨረሻው ዘመን ባህሪ በመሆኑ ልንታገስ ደግሞ ይገባል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለልጁ ለጢሞቴዎስ እንደጻፈለት '' ነገር ግን በመጨረሻ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና ፣ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክህተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ዕርቅን የማይሰሙ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፤ ችኩሎች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፣ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኀይሉን ግን ክደዋል ከእነዚህ ደግሞ ራቅ፡፡" 2ኛ ጢሞ.3፤1-5
አንዳንዱ ነገር ለምን እንደሆነብን እና እንደሚሆን ላይገባን ይችላል፡፡ አንገታቸውን በሰይፍ የሚቀሉ ሰዎች ብዛት፣ በህክምና ስህተት ያሳደጉዋቸውን ወላጆች የሚያጡ ሰዎች ብዛት፣ ጽኑ ወዳጅነት ወደ ጠላትነት መቀየር፣ ልጆችን በተለያየ አደጋ ማጣት፣ ክፉ ዘዴኛነት ፣ ብልጠት፣ ራስ ወዳድነት፣ ማታለል አስገራሚ ጭካኔዎች ሲሆኑ፤ ለምን ? እንዴት ማለታችን አልቀረም፡፡ ጌታ የት ሄዶ ነው ይህ ሁሉ የሚሆንብን ትሉ ይሆናል፡፡
የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ተፈጥሮበት ነበረ '' የምትመጣው መሲህ አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ ?'' ብሎ ወደ ኢየሱስ መልዕክተኞችን ላከ፡፡ወንጀል ሳይሰራ እስር ቤት መግባቱ ፣ በዚህም ላይ ብዙ የመሰከረለት ብርቱው ኢየሱስ በርሱ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ፣ አልያም አንዳች ተአምራት ሰርቶ እርሱን ከእስር አለማስፈታቱ አደናግሮት ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚህም የከፋ ሆነ፡፡ በእስራቱ ጊዜ ዝም ማለቱ ሲገርመን ጭራሽ በሔሮደስ ልደት ላይ ለዘፈነች አንዲት ወጣት ብላቴና ጥያቄ መሰረት አንገቱ ተቆርጦ በወጪት ቀረበ፡፡ ጌታስ? ዝም! በቃ ዝም!
አንዳንዱ ጉዳይ ከእኛ አዕምሮ በላይ ነው፡፡ ምናልባት ከጌታ ጋር መግባባት ስለማንችል ይሆን ዝም የሚለን? እስጢፋኖስን በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ሁሉን የሚችለው ጌታ በዙፋኑ ላይ ቆሞ እያየው ነበር፤ ለምን እንዳላስጣለው አይታወቅም፣ የታመነው ምስክሩ አንቲጳስ ሲገደል ጌታ ጣልቃ አልገባም ፣ ሐዋርያቱ በዘይት ተጠብሰው ሲሞቱ፣ ህዝብ በተሰበሰበበት አናብስት ቦጫጭቀው ሲገድሉዋቸው የጠራቸው ጌታ በዙፋኑ ላይ ነበር፡፡ ለአንዳንዱ ጥያቄ መልስ በእጃችን የለም፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ሰው እንዳሉት በፊሊፒንስ የጭቃ ጎርፍ 250 ህጻናትን ለምን ከድኖ እንደገደለ አናውቅም፡፡ በቅርብ ጊዜ አንድ የምታሳሳ ወጣት ከሲያትል ለሚሽን ጉዞ ወደ ህንድ ሄዳ በተመሳሳይ ለአገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ የሄደው መጋቢ አባት ከጥቂት ቀናት በሁዋላ ተጠርቶ የመጣው ፡ ልጅህ ድንገት ሞታለች ተብሎ ተረድቶ ነበር፡፡ በጣም አሳዛኝ ነበረ፡፡ በሌላ ጊዜ አንድ ዘማሪት እህት እናቱዋን በሞት ያጣችው ኦፕራሲዎን ልታስደርጋቸው ወስዳ በወቅቱ ሐኪሞቹ መቀስና ሌሎች ነገሮች ሆዳቸው ውስጥ ረስተው ስለ ሰፉአቸው ነበር፡ ነገሩ ኢንፌክሽን ፈጥሮባቸው ዳግመኛ ሲደረጉ እንደሞቱ ነው ለቅሶ ስደርስ የነገረችኝ፤
ወገኖች ለእኛ የሚበጀን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው ፤ ጥያቄያችን ባይመለስም እናመልከዋለን ፣እንወደዋለን፡፡ እንደዚህ የመሰሉ ቀናትን ልናሸንፍ / ልንቋቋም / እንችላለን ፤የምንችለው ግን የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር በመልበስ / በማንሳት/ ነው፡፡ መሳሪያው ሰው ሰራሽ መሳሪያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ይለዋል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ክፉ ጊዜ እንዲሆነን ያዘጋጀልን መከላከያ እና ማሸነፊያ ዕቃ ጦር ነው፡፡ ቢያንስ ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ቀጥለን እናያቸዋለን፡-
1- የእምነት መታጠቂያ- ወገባችን ላይ
2- የጽድቅ ጥሩር- ደረታችን አካባቢ
3- የሰላም ወንጌል- እግሮቻችን ላይ
4- የእምነት ጋሻ- በአንደኛው እጃችና ላይ
5- የመዳን ራስ ቁር- በጭንቅላታችን ላይ የሚደረግ
6- የመንፈስ ሰይፍ /የእግዚአብሔር ቃል ነው/- በቀኝ እጃችን ይዘን የምናጠቃበት ነው፡፡
ከራስ እስከ እግራችን ድረስ መሸፈን ያስፈለገን ምክንያት ጠላት እኛን ለመጉዳት ወይም ለመግደል ከጭንቅላታችን ጀምሮ ወርውሮ ስለሚሞክረን ነው፡፡ መዳኑ አስተማማኝ የሆነን ክርስቲያን ጭንቅላቱን መትቶ ሊጎዳው አይችልም፡፡ ነገር ግን ደረቱን በጥሩር ካልታጠቀ ማለትም ጽድቅ ላይ ገና የሚያመቻምች ሆኖ ካገኘው ይጎዳዋል፡፡ ነገር ግን እርሱም ከተሸፈነበት ቢያንስ እግሩን ስበሩት ብሎ መልዕክተኛ ይልካል:: ይህን ጊዜ ጠንካራ የወንጌል ከስክስ ያላደረገ ሆኖ ከተገኘ ባይሞትም እንኩዋ ዘመኑን ሁሉ በመንፈስ እያነከሰ ይኖራል ስለዚህ ሙሉውን ትጥቅ መታጠቅና መመላለስ አለብን፡፡ እንደሚታወቀው ሰይጣን ትንሽ ቀዳዳ ፈልጎ ነው የሚያጠቃን ፤ያልተሸፈነ አካላችንን ፈትሸን እንልበስ /እንታጠቅ/፡፡
የእስራኤል ንጉስ አክአብ የሞተው በጥሩርና በጥሩር መጋጠሚያ በኩል ከጠላት ወገን በተወረወረ ቀስት ተወግቶ ነው፡፡ ምናልባት ሁሉን ታጥቆ ነበር፤ ይሁንና መቀነት ግን አላደረገም እንደማለት ነው፡፡ ምንም እንኩዋ በእርሱ ሞት ላይ ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወጣም ቢሆን፡፡ጥቃት የደረሰበትና ለሞት የበቃው ግን በተገኘው ክፍተት በኩል ነበር፡፡
ወገኖች ሙሉ የእግዚአብሔርን ትጥቅ ታጥቀን በዚህ ዘመን እንድንኖር አሳስባችሁዋለሁ! እስቲ የላሉትን ጠበቅ እናድርጋቸው፤ ከትናንሽ ጥያቄዎቻችን እንውጣና ኩርፊያውን ትተን በእግዚአብሔር ፊት በጽድቅ ፣ በእውነት እንመላለስ!! የሚመጣልን መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ወደ ልዩ እረፍት ቦታ ይወስደናል፡፡ ብንጸና እንወርሳለን፡፡ በነገር ሁሉ ጌታ ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡ አሜን!!!
ምንጭ:- lemekeru.com
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 1 066 |
| 19 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ እንነሣና እንሥራ አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።”
ነህምያ 2፥18
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 1 085 |
| 20 | . ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።”
ይሁዳ 1፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures | 1 210 |
