en
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Open in Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Channel ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 13 557 subscribers, ranking 1 738 in the Transport category and 2 494 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 13 557 subscribers.

According to the latest data from 06 July, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 300 over the last 30 days and by 10 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 38.10%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 15.63% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 5 164 views. Within the first day, a publication typically gains 2 118 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 11.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 07 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Transport category.

13 557
Subscribers
+1024 hours
+787 days
+30030 days
Posts Archive
በዛሬው ዕለት የመንገድ ልማት ሪፎርም ሰነዶች ማጽደቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ። በውይይቱ መድረክ ላይ ክብርት የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዴኤታዎች ክቡር አቶ ካሳሁን ጎፌ እና ክቡር ኢንጅ. የኋላሸት ጀመረ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅ. ሀብታሙ ተገኘ እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ታድመውበታል። በእለቱም የሚኒስቴር መ/ቤቱ ያፀደቃቸውን ብሔራዊ የትራንስፖርት ፓሊሲ እና 10 ዓመት መሪ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከመንገድ ልማት ሪፎርም አንጻር ወሳኝ የፖሊሲ እና ስትራቴጅያዊ ሰነዶችን ወደ ትግበራ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ሰነዶች እንዲቀርቡ ተደርጓል። ጥናት ተደርጎባቸው ከቀረቡት ችግር ፈቺ ከሚባሉት ሰነዶች መካከል :- የመንገዶች የአገልግሎት ደረጃ ምደባ ጥናት:- ዋና አላማው ወቅታዊ መረጃን መነሻ በሚያደርገው የተከለሰ የትራፊክ አመንጪ አካባቢዎች ላይ በመመርኮዝ ነባር መንገዶችን በዚሁ መሰረት መመደብ ፣የዓዲስ መንገዶችን ደረጃ መመደብ ፣እንዲሁም የመንገድ ንምባለብልትነት ስልጣን እና የዓስተዳደር ሀላፊነትን የሚወስን ሲሆን በጥናት ደረጃ ተጠናቆ ቀርቧል። የክልሎች አቅም ግንባታ :- ዓላማው ሀገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ የተዘጋጀውን የመንገዶች አገልግሎት ደረጃ ለመተግበር የክልሎችን አቅም በመገንባትና አደረጃጀታቸውን ወጥ በማድረግ የስራ ክፍፍል ወይም ክልሎች በተሻለ ብቃት የመንገድ መሰረተ ልማቶችን እንዲዘረጉ አቅም መገንባት። የ10 ዓመት የገጠር መንገድ ዕቅድ:- በቀጣይ 10 ዓመታት የገጠር መንገድ ልማትና ሀብት አስተዳደርን በማሻሻል አብዛኛው የገጠር የህብረተሰብ ክፍል ከዋና ዋና መንገዶች ጋር እንዲገናኙ በማድረግ ትስስርን እና ሁሉን አቀፍ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ያስችላል። የመንገድ አዋጅ :- የመንገድ አገልግሎት ደረጃ ምደባ ጥናትንና ሌሎች ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በመንገድ ዘርፍ ውሳኔ እና አቅጣጫ ለሚሹ ጉዳዮች የሕግ ማእቀፍ በመሆን አሁን ላይ ለሚስተዋሉት አደረጃጀት የስልጠና ሃላፊነት የመንገድ ባለቤትነት ወ ዘ ተ ... ክፍተቶች ምላሽ የሚሰጥ ሰነድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንገዶች ኔትዎርክ መረጃ ስርዓት (ERNIS) ይፋ ተደርጓል። ይህ ስርዓት የተለያዩ የዌብ ቴክኖሎጂ ምንጮችን በመጠቀም የተዘጋጀ የትግበራ ሶፍትዌር ሲሆን አገልግሎቱም ለሀገሪቱ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ስርዓትን በመጠቀም አጠቃላይ የመንገድ መረጃ መረብ ነው። ይህ ሶፍትዌር በአዲስ አበባ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ቡድን አማካሪነት ተጠንቶ በዛሬው ዕለት ጸድቋል። በቀረበው ጥናታዊ ሰነድ ላይ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እንዲሁም በዘርፉ ወሳኝ አካላቶች ውይይት ተደርጓል።

የኤዶ-ሴሮፍታ-ወርቃ የአስፋልት ኮንክሪት የመስክ ጉብኝት
+7
የኤዶ-ሴሮፍታ-ወርቃ የአስፋልት ኮንክሪት የመስክ ጉብኝት

የኦሮሚያ ክልልን ከሲዳማ ክልል ጋር በማሰተሳሰር ከማዕከላዊ የሀገራችን ክፍል ጋር የሚያገናኘው የኤዶ - ሶሮፍታ - ወርቃ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ አፈፃፀም በመሰክ ምልከታ ተቃኝቷል :: የመንገድ ፕሮጀክቱ በትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ በኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ እንዲሁም በተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ነው የተቃኘው። የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አሁናዊ አፈጻጸም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ የሰራ እቅድ ላይም ምክክር ተካሄዷል። 73 ኪሜ የሚረዝመው የኤዶ - ሶሮፍታ - ወርቃ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ አጠቃላይ አፈጻጸሙ ጥሩ መሆኑም ተገምግሟል። የአፈር ቆረጣ የመሬት ድልዳሎ የሰብ ቤዝ የድልድዮች ስራን ጨምሮ አስቸጋሪ የሚባሉ የፕሮጀክቱ ክፍሎች ስራ በጥሩ መልኩ መሰራቱ ተመልክቷል ። ፕሮጀክቱ ካለው ሀገራዊ ፋይዳ አኳያ ምርታማነትን በመጨመር በፍጥነት ወደ አስፋልት ማልበስ ስራ እንዲሸጋገር የሰራ ሃላፊዎቹ አሳስበዋል ። መንግስት በመደበው በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ በዓለማየሁ ከተማ ጀነራል ኮንትራክተር እየተገነባ የሚገኘውን ይህን ፕሮጀክት የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ጎንድዋና ኢንጂነሪንግ እያከናወነ ይገኛል። ምንም እንኳን የግንባታው ሂደት ከታቀደው አንፃር መጠነኛ ውስንነት የሚታይበት ቢሆንም ኮንትራክተሩ ስራውን አጥብቆ የያዘበት አግባብ ለሚኖረው ቀጣይ አፈጻጸም መፍትሄ እንደሚሆን እምነት የሚጣልበት መሆኑን የተቋማቱ የሰራ ኃላፊዎች አንሰተዋል። የአፈር ሁኔታ ለመንገድ ግንባታው ምቹ አለመሆን እና የአካባቢው የዓየር ጸባይ ዝናባማ መሆኑ እንዲሁም የወሰን ማሰከበር ተግዳሮቶች ስራውን ቢያከብዱትም፤ ይህ ፕሮጀክት በአግባቡ እየተፈፀሙ ካሉ የመንገድ ግንባታዎች መካከል አንዱ በመሆኑ ተቋራጩ አለማየሁ ከተማ እና አማካሪ ድርጅቱ ይበልጥ እንዲተጉም የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ እና የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ አሳሰበዋል ።

የሮቤ - ጋሴራ - ጊኒር የመንገድ ስራ ፕሮጀክት
+7
የሮቤ - ጋሴራ - ጊኒር የመንገድ ስራ ፕሮጀክት

የሮቤ - ጋሴራ - ጊኒር የመንገድ ስራ ፕሮጀክት በከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በመስክ የስራ ቅኘት ተገመገመ። በዚሁ መርሃ -ግብር የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ።፣የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ፣ የኢመባ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የክልልና የዞኑ አመራሮችም ታድመዋል። የተቋማቱ መሪዎች ከአካባቢውዎቹና ከዞኑ ከተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋርም ምክክር አካሂደዋል። የሮቤ - ጋሴራ - ጊኒር የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አሁናዊ ሁኔታና በእስካሁኑ አፈጻጸም የተሰሩ ስራዎች ያግጠሙ ችግሮችና ቀጣይ የስራ እቅዶችን በተመለከተ ግምገማም ተካሂዶል። በሁለት ምዕራፎች የሚገነባው የሮቤ - ጋሴራ - ጊኒር የመንገድ ስራ ፕሮጄክት ሲጠናቀቅ የ121 ኪ.ሜ ርዝመት ይኖረዋል፡፡ ይህም ከሮቤ ጋሴራ 60 ኪ.ሜ ሲሆን ከጋሴራ ጊኒር ደግሞ 60 ነጥብ 84 ኪ.ሜ ርዝመትን ይሸፍናል። የመጀመሪውን ፕሮጀክት ግንባታ የሚያከሂዱት አፍሮጽዮን ኮንስትራክሽን ከራማ ኮንስትራክሽን ጋር በጋራ ነው። በተደረገው የፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማም መከናወን ከነበረበት አኳያ የዘገየ ሆኗል። የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ የአፈጻጸም ድክመቱን በፍጥነት አስተካክሎ የመንገድ ግንባታውን እንዲከናወን የመጨረሻ ማሳሰቢያ ሰተዋል። በስፍራው የተገኙት የራማ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ፍሬው ተድላ ድርጅታቸው ፕሮጀክቱን ከአፍሮ ጽዮን ተቋራጭ ጋር በጋራ የወሰደው በመሆኑ ችግሮች እንዳሉበት አምነው፣ የህዝብን ቅሬታ ለመፍታት ተቋራጫቸው ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። የግንባታ ፕሮጀክቱ በአፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን ስር ያለው ሁለተኛውን ምዕራፍ ማለትም ከጋሴራ ጊኒር የሚወስደውን መንገድ እጅግ መዘግየቱ ተገምግሟል። በተደጋጋሚ ድጋፍና ክትትል ቢደረግም አፈጻጻሙ ፈቅ ሊል አለመቻሉም የስራ ሀላፊዎቹ በመስክ ምልከታ ጭምር አረጋግጠዋል። በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጉልህ አፈጻጸም ማሳየት ካልቻለ መንግስት አፍጣኘ የመፍትሄ እርምጃ እንደሚወስድም የስራ ሃላፊዎቹ አቅጣጫን አስቀምጠዋል። የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ የመስክ ቅኝቱ መሰረታዊ አላማ ህዝቡ የሚያነሳውን ቅሬታ አዳምጦ ላልተገባ ቅሬታ ምክንያት የሆኑ የስራ ተቋራጮች ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ነው ብለዋል። መንግስት መዋዕለ ነዋይ መድቦ ድጋፍና ክትትል እያደረገም ለዘመናት የቆየ የህዝቦችን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ ፕሮጀክትን በማጓተት ህዝብን ቅሬታ ውስጥ የሚከቱ ድርጅቶችን እንደማይታገስ ገልጸዋል። የስራ ሃላፊዎቹ የጀመሩትን የተጠናከረ የመስክ ቅኘትና ግምገማ አጠናክረው በመቀጠል ችግር ያለባቸውን ፕሮጀክቶች እንዲተረሙ በማድረግ የሀገሪቱ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ እንዲፋጠን እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። በመድረኩ ላይ የአካባቢው ህዝብ ላነሳቸው የመሰረተ ልማት ጥያቄ ፡ መንግስት ከፍተኛ የተፈጥሮ ጸጋ እና አምራች አካባቢ መሆኑን በመረዳትና በመንገድ መሰረተ ልማት እጅግ የተጎዳ መሆኑን በማጥናት በጀት መድቦ የተነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን የስራ ሃላፊዎቹ አረጋግጠዋል። ህዝቡም ሰላሙን በመጠበቅና በማስጠበቅ ለልማት ፕሮጀክቶች ድጋፋን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል ።

በመስክ ጉብኝት ወቅት
+5
በመስክ ጉብኝት ወቅት

የባሌና የአርሲ ዞንን በማገናኘት ከማዕከላዊ የሀገራችን ክፋል ጋር የሚያስተሳስረው የዋቤ ድልድይ -አጋርፍ -አሊ ከተማ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በመስክ የስራ ቅኘት ተጎበኘ። በአካባቢው በተካሄደው የመስክ የስራ ቅኘት መርሃ-ግብር ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ እንዲሁም የተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የዞኑና የክልል አመራሮችም ታድመዋል ፡፡ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ ያለበትን ሁኔታን የሚዳስስ ገለጻም ለስራ ሀላፊዎቹ ተደርጎላቸዋል። 56ነጥብ6ኪሎሜትር የሚረዝመው ይህ ፕሮጀክት አሁናዊ አፈጻጻሙ 44ከመቶ ላይ ደርሳል። በዚህም ወሳኝና አስቸጋሪ የሚባሉ የፕሮጀክቱ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ። ከፋተኛ የአፍርና የተራራ ቆረጣ የመሬት ድልዳሎ የእስትራክቸርና የአቃፊ ግንብ ስራዎች ተሰርተዋል። በቅርቡም ወደ አስፖልት ንጣፍ ስራ ለመሸጋገር በቂ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል። የፕሮጀክቱ አካል የሆነው እና 180ሜትር የሚረዝመው የዋቤ ወንዝ ዘመናዊ የድልድይ የቅድመ ግንባታ ስራዎችም እየተፋጠኑ ነው። የስራ ሀላፊዎቹ በዛሬው የመስክ ቅኝታቸው ከአካባቢው ነዋሪዎችና የመስተዳድር አካላት ጋርም ውይይት አካሂደዋል። ፕሮጀክቱ ያለውን ከፍተኛ ሚና በመረዳትም የአካባቢው ህዝብ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ሚኒስትር ድኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከህብረተሰቡ የተነሱ ተጨማሪ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን መንግስት ምላሽ ለመስጠት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል። የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ ይህ ፕሮጀክት ከላው ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ አኳያ በልዩ ትኩረት ይበልጥ እንዲፋጠን አሳስበዋል ። የዋቤ ድልድይ- አጋርፋ- አሊ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሀገራዊ ከፍተኛ አምራች አካባቢዎችን የባሌና የአርሲ ዞኖችን ከማእከላዊ የኢትዮጵያ ክፍል ጋር የሚያቆራኘ በመሆኑ ለአምራች ሸማቹ ሚናው የላቀ እንደሆነ የተቋማቱ የስራ ሀላፊዎች ገልጸዋል። በቀጣይ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ፕሮጀክቱ በተያዘለት መርሃ -ግብር እንዲጠናቀቅ አቅጣጫንም አስቀምጠዋል። የዚህ ፕሮጀክት ወጪ 2.1 ቢሊየን ብር ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የሚሸፈነውም በኢትዮጵያ መንግስት ነው። ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው China Communications Construction Company Limited ( CCCC) ሲሆን Hong - IK Engineering እና ልደት አማካሪ ድርጅት ደግሞ የቁጥጥርና የማማከር ስራን እየሰሩ ነው። በተቀመጠው የጊዜ እና የጥራት ደረጃ ፕሮጀክቱን ግንብቶ ለማጠናቀቅ ይበልጥ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።

በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በተለይም በአፋር ክልል እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም እና በቀጣይ የአገሪቱ የመንገድ ልማት ውስጥ የክልል መንገድ ባለስልጣናት የሚኖራቸውን ሚና እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚገባውን አቅም እና አደረጃጀት በተመለከተ የውይይት መድረክ በሰመራ ከተማ ተካሄደ። በውይይት መድረኩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል አርባ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ፣ የኢመባ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የክልል የስራ አመራሮች ታድመዋል። በመድረኩ ላይ አሁን በፌደራል ደረጃ ያለውን የሥራ ጫና እና የቀጣይ የአስር አመታት የሀገራችን የመንገድ መሪ እቅድ ዋና ዋና ይዘትን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀው የክልል መንገድ ባለስልጣናት መነሻ አደረጃጀትና መዋቅር ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። ከዚህ አኳያ በመንገድ ግንባታ ሂደት ውስጥ ክልሎችን በአደረጃጀት፣ በመዋቅር፣ በአቅም ግንባታ ማሳደግ የመሰረተ ልማት አውታሩን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳለጥ የጎላ ሚና እንዳለው ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታና በቀጣይ ከሚኖረው ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ የክልሎችን አቅም ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ የተዘጋጀው ሰነድ ፋይዳው የጎላ መሆኑን እና ክልላቸውም ጥናቱን ወስዶ በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊውን እንደሚፈጽም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል። በትግበራ ወቅት ሊታዩ እና ሊካተቱ ይገባቸዋል ያሏቸውን አንኳር ነጥቦችንም የክልሉ የስራ ሃላፊዎች አንሰተዋል። የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ የአደረጃጀት ሰነዱ እና ተያያዥ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ክልሎች በስፋት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ እና ጥገና እንዲሳተፉ እድል በመፍጠር አንድ ተቋም ላይ ተንጠልጥሎ የቆየውን ከፍተኛ የስራ ጫናን ለክልሎች የሚያጋራ ከመሆኑም ባሻገር በየጊዜው እየጨመረ ለመጣው የህብረተስቡ የመንገድ ጥያቄ አፋጣኝ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል ። ይህም የሀገራችንን የመንገድ አውታር በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት ለመከወን እንደሚያስችል አብራርተዋል። የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ በበኩላቸው ሰነዱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ብልጽግናዎችን ለማጎናጸፍ የመንገድ ዘርፉ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር የሚያስችለው እንደሆነ ገልጸዋል። መንግስት በመስኩ የክልሎችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል መጠነ ሰፊ ስራዎችን እንደሚያከናውንም አረጋግጠዋል ። በተለይም የክልሎችን ሚና እና ሃላፊነት በግልጽ አስቀምጦ ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ለሀገራዊ የመንገድ የመሰረተ ልማት ግንባታ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ እንደሆነም ተናግረዋል። ይህን ተፈጻሚ የሚያደርጉ ዝርዝር የፖሊሲና የህግ ማእቀፍችን መንግስት እያዘጋጀ እንደሆነም የስራ ሀላፊዎቹ ገልጸዋል። በዚሁ በሰመራ ከተማ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ በተለይሞ በክልሉ በግንባታ ላይ ያሉ እና በቅርቡ ግዥያቸው ተጠናቆ ወደ ግንባታ የሚሸጋገሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በዝርዝር ቀርበዋል። በተለይም በግንባታ ላይ የሚገኙ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጻም እና እያጋጠማቸው ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ዝርዝር ምክክር ተካሂዷል። በውይይቱ ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ችግሮችን ይበልጥ ተናቦ ለመፍታት የጋራ አቅጣጫን አስቀምጠዋል። አቶ አወል አርባ በቀጣይ ለሚተገበሩ እቅዶችና ማሻሻያዎች እንዲሁም አሁን በግንባታ ላይ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ ክልሉ እያደረገ የሚገኘውን ክትትልና ድጋፍ የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን ከኤርትራ የአሰብ ወደብ ጋር የሚያስተሳስረው የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ የመንግድ ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ተጀመረ። በዚሁ መርሃ ግብር ግንባታው የተጠናቀቀው የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ _ኤሊዳር _በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። የተጠናቀቀውን መረቀው የሚሰራውን ያስጀመሩት የትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ፣ የትራንስፖርት ሚንስቴር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ እንዲሁም ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች በታደሙበት ነው። የፕሮጀክቱ መገንባት የአሰብ ወደብ መዳረሻ የሆነው የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ መንገድ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለሚኖረው የንግድ ትስስር መጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ። ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽን የሚያበረክት መንገድ ከመሆኑም በላይ ማህበራዊ መስተጋብሩን የሚያዋህድ ነውም ብለዋል ። የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በበኩላቸው መንግስት በክልሉ ብሎም በሀገራችን ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በመመደብ የመንገድ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በተሻለ ጥራትና ብቃት እያካሄደ በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። በተለይም በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያን ከተቀረው አለም ጋር ለሚኖራት የወጩ ገቢ ንግድ ተጨማሪ የአሰብን እና የታጁራ ወደብን ለመጠቀም የሚያስችላትን እድል መፍጠር የተቻለበት ታሪካዊ እለት ነው ሲሉም ገልጸዋል። አቶ አወል የመንገድ ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ በተለይም ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ችግር እንዳያጋጥም ጥብቅ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ በበኩላቸው የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ ፕሮጀክት 71.65 ኪ.ሜትር እርዝመት ያለውና በመንግሥት በተመደበ 2 ነጥብ 08 ቢሊዮን ብር በአስፋልት እና በሲሚንቶ ኮንክሪት ደረጃ የሚገነባ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል። ይህ እውን እንዲሆን የመንገድ ፕሮጀክቱ በውሉ መሰረት በ3 ዓመት ከ6 ወር ውስጥ ለማጠናቀቅ የባለስልጣኑ መ/ቤት አስፈላጊውን ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል ። ዛሬ የተመረቀውን የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ _ኤሊዳር _በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድን የገነባው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ነው። የተቋሙ ሀላፊ ኢንጂነር ደቦ ቱንካ ይህ ለግንባታ እጅግ አስቸጋሪ ሞቃታማ ቦታ ላይ የተገነባው እና በሀገራችን የመንገድ ምህንድስና ሙያ በአይነትም ሆነ በቴክኖሎጂ ትልቅ የእውቀት ሽግግር የተደረገበት እንደ ተቋምም ተጨማሪ አቅም የገነባንበት ነው ብለዋል። የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ ዲዛይና ግንባታ ፕሮጀክት የሚገነባው ሻንዶንግ ሊኪኖ ግሩፕ በተሰኘ የቻይና አለማቀፍ ድርጅት ነው። የመንገዱን ጥራት በመቆጣጠር ረገድ ስሜክ ኢንተርናሽናል እንዲሁም ቫሊዩ ኢንጅነሪንግ በንዑስ ተቋራጭነት ይሳተፋሉ፡፡ መንገዱን በጥራት ገንብቶ በተባለው ጊዜ ለማስረከብም የተቋራጩ የስራ ሀላፊ ተወካይ ቃል ገብተዋል ። #### ስለ ፕሮጀክቶቹ ተጨማሪ መረጃ #### ስራው የተጀመረው መንገድ ካለው 71.65 ኪ.ሜትር ውስጥ ከፕሮጀክቱ መጀመሪያ ከሜሎዶኒ መገንጠያ እስከ 12.5 ኪ .ሜትር ድረስ በሲሚንቶ ኮንክሪት ደረጃ የሚገነባ ነው፡፡ የተቀረው ከኪሜ 12 .5 እስከ ፕሮጀክቱ ማብቂያ ቡሬ ድረስ የሚዘልቀው መንገድ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ይሰራል ። የመንገዱ ስፋት ትከሻን ጨምሮ በከተማ 19 ሜትር እንዲሁም በገጠር 10 ሜትር ስፋተና ደረጃውን ጠብቆ ይግነባል ፡፡ ወደ አሰብ ወደብ የሚዘልቀው የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ መንገድ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የተሻለ የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ መሳለጥ አይነተኛ ሚናውን ይጫወታል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለአመታት ተቋርጦ የነበረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ዳግም በመጀመሩ መስመሩን ለሚጠቀሙ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ 78 ኪ.ሜ የሚረዝመው የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ አዲሱን የታጁራ ወደብ በአማራጭነት ለመጠቀም የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር በነባሩ ጅቡቲ ወደብ ይፈጠር የነበረውን የትራንስፖርት ጫና እና መጨናነቅ እንደሚያቃልለው ይጠበቃል። መንገዱን ለመገንባት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ የጠየቀ ሲሆን የመንግስት ልማት ድርጅት በሆነው በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተገንብቷል። የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድርና ከሲም አማካሪ መሃንዲስ በጥምረት ተሳትፈውበታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም የመንገድ ግንባታውን ለማካሄድ የዋለውን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሸፍኗል፡፡ አካባቢው ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ግንባታው በሲሚንቶ ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ሲሆን ይህም የአየር ጸባዩን የመቋቋም እና የግልጋሎት ዘመኑ ከፍ እንዲል ያደርጋል ።

የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ የመንገድ ገጽታ
+5
የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ የመንገድ ገጽታ

የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ መንገድ

ኢትዮጵያን ከኤርትራ የአሰብ ወደብ ጋር የሚያስተሳስረው የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ የመንግድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊገነባ ነው። በነገው ዕለትም ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ፕሮጀክቱን በይፋ የማስጀመር መርሃ ግብር ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዕለቱ በሚኖረው መርሃ -ግብርም ግንባታው የተጠናቀቀው የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትም ይመረቃል። የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ መንገድ ሲጠናቀቅ ወደ አሰብ ወደብ የሚዘልቅ መንገድ እንደመሆኑ ለኢትዮጵያ የተሻለ የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ መሳለጥ አይነተኛ ሚናውን ይጫወታል፡፡ 71.65 ኪ. ሜ የሚረዝመውን ይህን ፕሮጀክት በብር 2,085,985,162.6 በሆነ ወጪ ጨረታውን አሸንፎ ግንባታውን የሚያከናውነው ሻንዶንግ ሊኪኖ ግሩፕ የተባለ የወጭ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው። የግንባታውን የማማከርና የቁጥጥር ስራ ደግሞ ስሜክ ኢንተርናሽናል እንዲሁም ቫሊዩ ኢንጅነሪንግ በንዑስ ተቋራጭነት ይሳተፋል ። ለፕሮጀክቱ ግንባታ ማስፈጸሚያ ወጪም የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡ በአገልግሎት ሳቢያ የተጎዳ የአስፋልት መንገድና ከ6 ሜትር ያልበለጠ ስፋት የነበረውን በቀጣይ ከተሞች ላይ 19 ሜትር እንዲሁም በገጠር ደግሞ የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 1ዐ ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ የሚገነባ ይሆናል። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለአመታት ተቋርጦ የነበረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ዳግም በመጀመሩ መስመሩን ለሚጠቀሙ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ በተያያዘ ዜናም 78 ኪ.ሜ የሚረዝመው የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን ፕሮጀክት በነገው ዕለትም በይፋ ይመረቃል። መንገዱን ለመገንባት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታ ያካሄደው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተባለ የመንግስት ልማት ድርጅት ነው። የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድርና ከሲም አማካሪ መሃንዲስ በጥምረት ተሳትፈውበታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም የመንገድ ግንባታውን ለማካሄድ የዋለውን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሸፍኖታል፡፡ አካባቢው ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ግንባታው በሲሚንቶ ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ሲሆን ይህም የአየር ጸባዩን የመቋቋም እና የግልጋሎት ዘመኑ እንዲጨምር ያደርጋል ። የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ መንገድ መገንባት አዲሱን የታጁራ ወደብ በአማራጭነት ለመጠቀም የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር በነባሩ ጅቡቲ ወደብ ይፈጠር የነበረውን የትራንስፖርት ጫና እና መጨናነቅ እንደሚያቃልለው ይጠበቃል። ፕሮጀክቱ የአገሪቷ የወጪ ገቢ ንግድ የሚካሄድበት ኮሪደር እንደመሆኑ መስመሩን የሚጠቀሙ ብዙ ቁጥር ያላቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች ክብደት የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ታሳቢ ያደረገ ነው ፡፡

80 ኪሎሜትር የሚረዝመው የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ወደ አሰፓልት ንጥፍ ስራ ተሸጋገረ ። እስካሁን ባለው አፈጻጸም 26 ኪሎሜትሩ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የፕሮጀክቱን ክፍሎች አስፓልት ለማልበስ እየተሰራ ነው። በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣ ና የአፈር ሙሌት ፤ የቤዝ ኮርስ ስራ ፤ የአስፋልት እና ፤ የድልድይ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ ነው። በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት የኦሮሚያ ክልልን ከአጎራባች የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጋር የሚያገናኝ ወሳኝ ፐሮጀክት ነው፡፡ ከቡታጂራ አዲስ አበባ ከሚወስደው አውራ መንገድ ጋርም በአቋራጭ ያስተሳስራል ፡፡ የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት እየተገነባ የሚገኘው ከመንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት ነው፡፡ ግንባታውን የሚያካሂደው ሁናን ሁንዳ ሮድ ኤንድ ብሪጅ የተሰኘ ዓለም ዓቀፍ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ሲሆን የመንገዱን ጥራት በመቆጣጠርና በማማከር አየሰራ ያለው ደግሞ የተባበሩት የምህንድስና አማካሪዎች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው፡፡ 3 ወረዳዎችን አቋርጦ ኬላ ከተማ የሚደርሰው ይህ መንገድ በአካባቢው በሚገኙ በገብስ ፤ ስንዴ ፤ ባቄላና አተር ምርቶቹ የታወቀ በመሆኑ ምርቶቹን በፍጥነት ወደ ማእከላዊ ገበያ እንዲደርስ ስለሚያስችል ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ያጎለብታል፡፡ የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት በቀጣይ አመት ለማጠናቀቅ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ ነው።

የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
+6
የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት